Tricks & Tech Hacks

Tricks & Tech Hacks

Share

Just having fun posting!

Photos from Tricks & Tech Hacks's post 10/09/2021

ኢንተርኔት መጠቀም ከጀመርክባት ጊዜ አንስቶ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ምን ስታደርግ እንደነበር ይታወቃል!

አንድ ነገር ላስታዉስህ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልክ ገዝተህም ይሁን ተዉሰህ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንተርኔት ዉስጥ የገባኸዉ መቼ ነዉ? አዎን ከዛ google.com ብለህ ፅፈህ ሰርች ያረከዉ? ከዛ ደምበኛ ተጠቃሚ ሆነህ ያለ ፌስቡክ እንቅልፍ አልወስድ ያለህ? ከዛ በኃላ እስካሁን ምን ያህል ድህረ ገፆች አየህ?
መልሱን አንተ ታዉቀዋለህ!

***
ኢንተርኔት የጊዜዉ ምርጥ ፈጠራ እንደሆነ ግልፅ ነዉ፡፡ መረጃ ህይወት የሆነበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ንግድ፣ መዝናኛ፣ ትምህርት፣ ፖለቲካና ወዘተ ሁሉም በኢንተርኔት ወደ መከወን ሽግግር ላይ ናቸዉ፡፡ አንተም በየዕለቱ ኢንተርኔት ላይ የተለያዩ ነገሮች ታደርጋለህ፡፡ ሶሻል ሚድያ ላይ ስትፅፍ ሌሎች ድህረገፆች ስትጎበኝ ትዉላለህ፡፡
ግን እንቅስቃሴህ እንዴት ይካሄዳል? ምስጢራዊነቱስ? ለምሳሌ አንድ ሰዉ ፌስቡክ ላይ ማንነቱን ደብቆ ሲፅፍ፣ በቃ ማንም አያዉቀዉም ማለት ነዉ? የፖርን ቪድዮ ሲያወርድና ሂስትሪ ሲያጠፋ ሁሉም እንቅስቃሴዉ ጠፋ ማለት ነዉ?

መልሱ፡ በፍፁም አይደለም ነዉ!

ትንሽ ላብራራዉ፡፡ ኢንተርኔት ለመጠቀም መጀመሪያ ISP(Internet Service Provider) የሚባል ተቋም ያስፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያ ብቸኛዉ ISP ኢትዮ ቴሌኮም ነዉ፡፡ ይህ ተቋም የኢንተርኔት አገልግሎት መጠቀም ለሚፈልግ ስልክ ወይም ኮምፒዉተር የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣል፡፡ ይህ ቁጥር IP Address(public) ተብሎ ይጠራል፡፡ ማንኛዉም ተጠቃሚ በዚህ ቁጥር ከግዙፉ ኢንተርኔት ጋር ይገናኛል፡፡

ኢንተርኔት ላይ የምትከፍተዉ እያንዳንዱ ድህረገፅም የራሱ መታወቂያ ቁጥር አለዉ፡፡ IP Address ይባላል፡፡ ይሄን IP ከቀድሞዉ የሚለየዉ ሰጭዉ አካል ISP ሳይሆን ሁሉንም ዌብሳይቶች የሚቆጣጠር DNS(Domain Name Server) የተባለ አካል ነዉ፡፡ ለምሳሌ ፌስቡክ ለመክፈት Domain Name (ለምሳሌ ' facebook.com ') ስትፅፍ ብሮዉዘርህ ወደ DNS መልዕክት ልኮ በዚህ ስም የተመዘገበ IP Address ይፈልግና ይከፍተዋል፡፡ ለምሳሌ ' 31.13.67.35 ' ብለህ ብራዉዘር ላይ ብታዝ ፌስቡክ ይከፍትልሀል፡፡ ይህ IP Adress ነዉ፡፡

እንግዲህ የኢንተርኔት ማንነትህ IP Address ነዉ እንደማለት ነዉ፡፡

ከላይ እንደተባለዉ ISP ወይም ቴሌ የቁጥሩ ሰጪ ስለሆነ የትኛዉ IP ምን ድህረገፅ ላይ ነበር የሚለዉ በሙሉ ተከማችቶ ይቀመጣል፡፡ ስለዚህ ኢንተርኔት መጠቀም ከጀመርክባት ጊዜ አንስቶ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ምን ስታደርግ እንደነበር ተከማችቶ ቁጭ ብሏል(ጉድ ፈላ)፡፡

ሌላዉ ደግሞ ማንኛዉም ሰዉ ያንተ IP Adress ካለዉ በቀላሉ መገኛህን ማወቅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የራስህን IP Adress ' https://www.iplocation.net/ ' ላይ መየት ይቻላል፡፡

ግን አትጨነቅ፡፡ መፍትሔ አለ - VPN አፕ፡፡ ብዙዎች VPN ኢንተርኔት ማፍጠኛ አፕ ይመስላቸዋል፡፡ VPN በፍፁም ኢንተርኔት አያፈጥንም፡፡ VPN(Virtual Private Network) ከISP የተሰጠዉን IP በሌላ IP በመተካት ከኢንተርኔት ጋር ያለን ግንኙነት secure ያደርጋል፡፡

VPN የኢንተርኔት እንቅስቃሴዎችህን ከISP የተደበቀ ያደርጋል፡፡ VPN ስትጠቀም የምታያቸዉ ድህረገፆች encrypt በመሆን ወደ ISP ይላካሉ፡፡ ያ ማለት በISP በኩል decrypt ካልተደረገ ምን እንደተደረገ ማወቅ አይቻልም፡፡

ለማንኛዉም ኢንተርኔቱን እያወቅነዉ እንጠቀመዉ ለማለት ያህል ነዉ፡፡

13/06/2021

ሰላም ቤተሰቦች
ጠቃሚ የቴሌግራም ቦቶች እነሆ

bot መስራት ከፈለጋቹ

ከቻናሉ ውስጥ ban ብትደረጉ በተዘዋዋሪ የሚለቁትን ነገር የምታገኙበት

የናንተን ፅሁፍ ወደ ሚገራርሙ ፁፎፍ የሚቀይር

vote የምታስደርጉበት

ይህ ደግሞ markdown እና button ለመስራት ከፈለጋቹ

ይህ ደግሞ ፅሁፍን ወደ ድምፅ የሚቀይር

ግሩፕ ውስጥ ሳይታወቅባቹ ለማውራት

የተለያዩ ጌሞች የያዘ

ከዘጠኝ እስከ 12 ላላቹ teacher and student book

ከተለያዩ በአልም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ጋር ለማውራት ማለትም ማንነታቹ ሳይታወቅ

ግሩፓችውን ለመቆጣጠር ::

sticker መስራት ከፈለጋቹ

ግሩፓቹ ውስጥ እውነት ወይም ድፍረት የምታጫውት

ይህ ቦት ፍይሎችን ማልዌር ሌሎችንም ቫይረስ ነፃ መሆንን እና አለመሆንን ያረጋግጣል አሪፍ ቦት ነው ተጠቀሙበት።

የፈለግነውን app ምናወርድበት ቦት

ሰለ corona Top 20 በ virusu የተያዙ ሀገራትን ምናይበት እና እንደ አለም

ለግሩፕ ሰው join ሲል ወዲያው እንዲያጠፋው

ይሄ በgmail የሚላክልንን text በዚ ባት መቀበል እንችላለን official ነው

ይሄ ቦት ደሞ ቻናላችንን ወደ ፈለግነው ለመቀየር ስንፈልግ መጀመሪያ ፖስት ያረግነውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት የሚረዳን bot ነው ለቦቱ admin ትሰጡታላችሁ ከዛ /delall ብላቹ ከጻፋቹህ ቡሀላ post ስታረጉ ወዲያው ያጠፋዋል።አንዴ ካጠፋቹ መመለስ አይቻልም

- ላይ ቪድዮ ማውርድ ከፈለጋቹ ይህን ቦት ተጠቀሙ። ከናንተ ሚጠበቀው የቪዲዮውን ሊንክ ለቦቱ መላክ ብቻ ነው።

- ለቻናል ከሁለት በላይ አድሚኖች ለመቆጣጠር በቦቱ ብቻ የፈለጉትን ነገር ለምሳሌ ጹሁፍ ወይም እስቲከር ሊንክ እንዳይልኩ ያደርጋል።

- ይህ ቡት ደሞ Telegram ላይ የምናገኛቸውን Audio ብዙ mb ቢሆን እንኮን ወደ kb ይቀይረዋል። ማሳሰቢያ ይህ ቡት በቀን ውስጥ ከ 4 or 5 በላይ Audio convert አያረግም ሰለዚህ 4 ብቻ ነው በየቀኑ convert የሚደረገው።

- የቦት Calculator

and

Photos 01/08/2019

3.1 ቢሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ቪኤልሲ ፕሌየር
ለጥቃት ተጋልጧል
በዓለም አቀፍ
ደረጃ ከ3.1 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች እንዳሉት
የሚታመነው የቪኤልሲ ማጫወቻ 'VLC player'
አደገኛ የሚባል የደህንነት ክፍተት እንዳለበት
የጀርመን የብሄራዊ የሳይበር አደጋ ምላሽ መስጫ
ማእከል(ሰርት) ይፋ አደርጓል፡፡
ማንኛውም አካል በነጻ ከኢንተርኔት ላይ አውርዶ
መጠቀም የሚችለው ሶፍትዌር እስካሁን
የክፍተት መሙያ እንዳልተለቀቀለት ተጠቁሟል፡፡
በቪኤልሲ ላይ የተፈጠረው የሶፍትዌር ክፍተት
አደገኝነት ደረጃው በከፍተኛ የሚመደብ መሆኑ
ተጠቁሟል፡፡
ህገ-ወጦች ክፍተቱን በመጠቀም በርቀት
ሶፍትዌሩን መቆጣር የሚያስችላቸው ሲሆን
ክፍተቱ የአገልግሎት መስተጓጎል denial-of-servi
ce፣ ያለፍቃድ መረጃዎችን መውሰድ እንዲሁም
ያለተጠቃሚው ፍቃድ ፋይሎችን እንዲቆጣጠሩ
ያደርጋል ሲል የጀርመን ሰርት ጠቁሟል፡፡
ለተጋላጭነት የተዳረጉት የቪኤልሲ ምርቶች እስከ
ቅርብ ጊዜው 'VLC media playe'r እትሙን
ጨምሮ በሁሉም ምርቶች ላይ የተከሰተ መሆኑም
ታውቋል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ የቪኤልሲ ማጫወቻው
ላይ በተከሰተው ክፍተት ሳቢያ የደረሰ ጥቃት ይፋ
አልሆነም ሲል ዊ ሊቭ ሴኪዩሪቲ አስነብቧል፡፡

Photos from Tricks & Tech Hacks's post 07/06/2019

ከግንቦት 29 - ሰኔ 3 የሚቆይ ኢኖቬት ኢትዮጵያ Tech-Expo በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነዉ፡፡ በርካታ ሀገር በቀል የሆኑና የዉጭ በቴክሎጂ ላይ የሚሰሩ ኩባንያዎች ይገኛሉ፡፡ መጎብኘት እንዲሁም የፈጠራ ሀሳቦች ማቅረብ ይቻላል፡፡

Photos from Tricks & Tech Hacks's post 17/05/2019

የBitCoin Mining ማጭበርበር



ሰላም የፔጃችን ተከታዮች ዛሬ ስለ BitCoin Mining የማጭበርበሪያ ስልቶችና በሃገራችንም እየተፈፀሙ ስለሚገኙ የማታለል ስራዎች እንዲሁም ራሳችንን ከዚህ ተጋላጭነት እንዴት እንደምንጠብቅ እናወራለን፡፡

ወደፊት ዘርዘር ያለ ፅሁፍ በCryptocurrency ዙርያ አቀርባለሁ፡፡

እንደሚታወቀዉ BitCoin Cryptocurrency ዲጅታል የመገበያያ ገንዘብ አንዱ ሲሆን BlockChain በሚባል ቴክኖሎጂ ይተዳደራል፡፡

አሰራሩም ምንም አይነት ባንክ ወይም የፋይናንስ ተቋም ሳያስፈልግ ማንኛዉንም አይነት ግብይትም ሆነ የገንዘብ(Bitcoin) ዝዉዉር መፈፀም ያስችላል፡፡

እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ መጠየቅ ግድ ነዉ፡፡ ምንም አይነት የፋይናንስና ተቋም ወይም ባንክ ከሌለ ማን ይቆጣጠረዋል ግብይቱ መፈፀሙንስ ማን ያረጋግጣል?
ጥሩ ከላይ እንደገለፅኩት Blockchain የተባለዉን ቴክኖሎጂ ይህን ይፈፅማል፡፡
ታድያ በዚህ መሀል ግብይቱ በትክክል መፈፀሙን የሚያረጋግጡ ማይነርስ(Minors) የሚባሉ አካላት አሉ፡፡

ማይኒንግ(Mining) ማለት ዲጅታል ገንዘቡ(BitCoin) መተላለፉን በማረጋገጥ ብቻ ጉርሻ የሚገኝበት ቢዝነስ ነዉ፡፡
ታድያ ለዚህ እጅግ ከፍተኛ የኮምፒውተር ፕሮሰሲንግ አቅምና ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ያስፈልጋል፡፡
እዚህ ቢዝነስ ዉስጥ ያሉ እጅግ ትርፋማ የሆኑ ብዙ ኩባንያዎች በቻይና ሃገር ይገኛሉ፡፡ ምክንያቱ ደግም ቻይና የኤሌክትሪክ ዎጋ ርካሽ ስለሆነ ነዉ፡፡

ይህንን ካልን የBitCoin Mining ማጭበርበር ስንል ምን ማለት ማለታችን ነዉ?

ሁለት አይነት ዋናዋና የማጭበርበሪያ ስልቶች አሉ፡
1. Ponzi scheme(ፖንዚ ስኪም)
2. Pyramid scheme(ፒራሚድ ስኪም)

Ponzi scheme(ፖንዚ ስኪም):-

- ይህ የማጭበርበሪያ ስልት በሌሉ የማይኒንግ(Mining) ድርጅቶች ስም፡ እኛ የማይነር ቢዝነስ ሰዎች ነን በሚል ገንዘብ አምጡ ኢንቨስት አድርጉ በማለት ገንዘብ መሰብሰብ የማጭበርበር ስልት ነዉ፡፡


2. Pyramid scheme(ፒራሚድ ስኪም)

- ይህ የማጭበርበሪያ ስልት ነዉ እንግዲህ በሀገራችንና ሌሎችም ሀገሮች እየተስፋፋ የሚገኘዉ፡፡ የዚህ ስልት ዋናዉ መገለጫ ገንዘብ አምጡ በዚህ ጊዜ ዉስጥ ይህን ያህል ፐርሰንት በየጊዜዉ ታተርፋላችሁ፡ ሌላ ሰዉ ባመጣችሁ ቁጥር የትርፍ ፐርሰንታችሁ ይጨምራም በማለት ሰዉን በማነሳሳት የሚደረግ ማጭበርበር ነዉ፡፡
አብዛኛዎቹ በሆቴሎች ስብሰባና ኮንፈረንስ በመጥራት በመስበክ ገንዘባችሁን እንድትሰጡ የማግባባት ስራ ይሰራሉ፡፡ እናንተም ያንን የተጋነነ ትርፍ እዉነት ነዉ ብላችዉ ስትሰጡና ገንዘብ አየሰራችሁ ሲመስላችሁ ነገር ግን እነሱ ጥቂት ተመላሽ እየሰጧችሁ ገንዘባችሁን በሙሉ ለግላቸዉ ያደርጉታል ማለት ነዉ፡፡

ተጠንቀቁ ስለ Cryptocurrency በቂ ዕዉቀት ሳይኖራችሁ ስለ ማይኒንግ አሰራር ሳታዉቁ ገንዘባችሁን እንዳትበሉ !

ከዚህም ሌላ ኢንተርኔት ላይ በመፈለግ ተጨማሪ መረጃዎችን ማንበብ ትችላላችሁ፡፡

ማንኛዉንም ጥያቄና አስተያየት

16/05/2019

ስፔስ ኤክስ ከህዋ ላይ ኢንተርኔት የሚያቀርቡ ሳተላይቶችን ዛሬ ምሽት ወደ ህዋ ሊልክ ነው

*************************************
አዲስ አበባ ግንቦት 8/2011: "ስፔስስኤክስ" SpaceX ኩባንያ ዛሬ ምሽት እንደሚያመጥቀው የሚጠበቀው ሳተላይት ከህዋ ላይ የኢንተርኔት አቅርቦት ተደራሽነት ባልሆነባቸው የአለም ክፍሎች ተደረሽ የሚያደርግ ነው፡፡

የኩባንው እቅድ ከተሳካ በታሪክ ፋና ወጊ በዘርፉም እመርታዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል፡፡

የኤለን መስክ ንብረት የሆነው የአሜሪካው የህዋ ተቋም ስፔስኤክስ በዛሬ ምሽት 60 ሳተላይቶችን ወደ ህዋ እንደሚልክ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

ሳተላይቶቹ በምድር ዝቅተኛው ምህዋር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን "ሰታርሊንክ" በሚል መጠሪያ ህብረ ሳተላይቶች ሰይሟቸዋል፡፡

ስፔስኤክስ ለኢንተርኔት ተደረሽነት በሚል ወደ ህዋ ዛሬ የሚልካቸው ሳተላይቶች ተቋሙ ከያዘው ግዙፉ እቅድ ጥቂቱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ወደፊትም ኩባንያው በሽዎች የሚቆጠሩ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ በመላክ በአለም አቀፍ ደረጃ የበይነ-መረብ "የኢንተርኔት" አቅርቦት ለሌላቸው አካባቢዎች በዝቅተኛ ዋጋ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢንተርኔት ተደራሽነት በአብዛኛው ግዙፍ ማማዎችን በመትከል ገመድ አልባ አገልግሎቶች አልያም በኢንተርኔት ገመዶች አማካኝነት በየቢሮቻችን እና በቤታችን ነው፡፡

ይህ የኢንተርኔት ማሰራጫ አማራጭ በገጠራማ አካባቢዎች የሚገኙ አካላትን ተደራሽ ያላደረገ እና በተመጣጣን ዋጋ ማግኘት ከባድ ሁኔታን መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡

ከሳተላይት የሚለቀቅ የኢንተርኔት አቅርቦት ግን የተሸለ አማራጮችን እንደሚያመጣ ታምኖበታል፡፡
ወደፊትም ኩባንያው እስከ 12ሽህ የሚደርሱ ሳተላይቶችን በዝቅተኛው የመሬት ምህዋር ለኢንተርኔት አቅርቦት እንደሚልክ ይጠበቃል ሲል ሲኤንኤን አስነብቧል፡፡

22/02/2019

ማይክሮሶፍት የበይነ-መረብ መረጃ ፍለጋ ሂደት መስተጓጎልን የሚቀርፍ የደህንነት ማሻሻያ ለቋል **********************************

ማይክሮሶፍት ያቀረበው የደህንነት ማስጠንቀቂያ የኮምፒውተሮቻችን ማእከላዊ መከወኛ ክፍል (CPU) 100 በመቶ ተግባሩን እንዳይከውን የሚያግዱትን የኢንተርኔት የመረጃ አገልግሎት (Internet Information Services) ክፍተት የሚጠቁም ነው፡፡ ማሻሻያው የኢንተርኔት መረጃ አገልግሎትን የሃይፐር ቴክስት ትራንስፈር ፕሮቶኮል "HTTP/2" ትዛዞችን በድንገት እንዲቋረጥ እና እንዲዘገይ የሚያደርጉ ክፍተቶችን የሚሞላ ነው፡፡ የኩባንያው የደህንነት ስጋት ምላሽ መስጫ ማእከል የኢንተርኔት አገልግሎቶች ማስተጓጎል (DOS) በበይነ-መረብ የመረጃ አገልግሎት ላይ የሚፈጥረው ችግር ላይ ጠቃሚ የሆኑ ምክሮችን ይፋ ማድረጉም ተጠቁሟል፡፡ የHTTP/2 መጠይቆች በሚከውኑበት ጊዜ የመዘገየት እና አገልግሎቱ በድንገት ከሚቋረጥባቸው የማይክሮሶፍት ምርቶች የዊንዶው 10 እና የዊንዶው ሰርቨር 2016 ናቸው፡፡ HTTP/2 የቅርብ ጊዜው የሃይፐርቴክስት ትራንስፈር ፕሮቶኮል "HTTP" እትም "version" ሲሆን ለወርልድ ዋይድ ዌብ "www" ድጋፍ የሚያደርግ ነው፡፡

©INSA

12/11/2018

ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት ሳተላይት ታመጥቃለች
==============================
ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሚሆነውን
የምድር አሰሳ ተልእኮ ያላትን ሳተላይት በሚቀጥለው መስከረም ታመጥቃለች፡፡
ሳተላይቷም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ካሉ ሳተላይት ካመጠቁ ጥቂት ሃገራት
መካከል አንዷ በመሆን እንደምትካተት ይጠበቃል፡፡
ሳተላይቷ በፈረንጆቹ 2019 መስከረም ወር ላይ በቻይና አማካኝነት ወደ ህዋ
ለማምጠቅ እቅድ ተይዟል፡፡
ሆኖም የቁጥጥር እና ማዘዣ ጣቢያው በኢትዮጵያ እንደሆነ የኢትዮጵያ የህዋ
ሳይንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ መናገራቸውን
ዘኢስትአፍሪካን ኒውስፔፐር ዘግቧል፡፡
በጣም ወሳኝ የሚባሉ የዲዛይን ምእራፎች በኢትዮጵያዊያን መከናወኑን
የገለጹት ዋና ዳሬክተሩ በፕሮጀክቱ 20 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊ የስነ-ፈለክ
ተመራማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸው ጠቁመዋል፡፡
የቻይና መንግስት ስልጠናዎችንእና ለዲዛይን 6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር
መስጠቱን ዶ/ር ሰለሞን መናገራቸው ተናገረዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ሳተላይት በህዋ ላይ ካላቸው ሌሎቹ 7 የአፍሪካ ሃገራት
ተርታ የሚያስመድባት ሲሆን እስካሁን ደቡብ አፍሪካ፣ግብጽ፣ጋና፣አልጄ
ሪያ፣ሞሮኮእና ጎረቤት ኬኒያ ባለቤት የሆኑ ሃገራት ናቸው፡፡

ምንጭዘኢስትአፍሪካን ኒውስፔፐር

18/09/2018



ሰላም ቤተሰቦች ቤኪ ነኝ ጎግል በቅርብ ጊዜ አዲሱን የአንድሮይድ ስሪት(Version) አስተዋዉቋል፡፡

አንድሮይድ ፓይ 9.0 (Android Pie 9.0 ) ይሰኛል፡፡
ይህ የአንድሮይድ ስሪት አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተለያዩ አዳዲስ ፊቸሮችንም ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

* New user interface for the quick settings menu. [12]

* The clock has moved to the left of the notification bar . [13]

* Battery saver no longer shows an orange overlay on the
notification and status bars. [12]

* A " Screenshot" button has been added to the power options. [13]

* Rounded corners across the graphical user interface .

* New transitions for switching between apps, or activities within
apps.

* Richer messaging notifications, where a full conversation can be
had within a notification, full scale images, and smart replies akin
to Google's new app, Reply.
Support for display cutouts.

* Redesigned volume slider, which is now located next to the device's
physical volume button.

* Battery percentage now shown in Always-On Display.

* A new gesture-based system interface, similar to the one found on
the iPhone X and other devices. [14]

* Redesigned, horizontal multitask app switcher with Google search
bar and app drawer built in.

* A "Digital Wellbeing" feature which discourages excessive usage of
your phone which will launch officially on Pixel phones this
fall.

* An adaptive battery feature that maximizes battery power by
prioritizing the apps you're most likely to use next.

* New back button icon in navigation bar if gesture navigation is
enabled.

* Manual theme selection.

እና ሊሎችንም አዳዲስ ፊቸሮች ይዞ ቀርቧል፡

መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዲደርሷችሁ Like / Share

beckypac-com.over-blog.com 14/09/2018

ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን መጎብኘት ትችላላችሁ

beckypac-com.over-blog.com ቤኪ pac ነኝ የ Facebook ፕሮፋይሌን ከስር ማግኘት ትችላላችሁ ፡ ፡ በመጀመርያ ግን ላይክ ማድረግ እንዳትረሱ ይኸዉላችሁ በጣም ቀላል ነው , , , , ,, , እነዚህን...

Photos 13/07/2018


ሰላም ቤተሰቦች
!
1. ለስልኩ በተዘጋጀ ቻርጀር ብቻ መጠቀም፦ ሁል ጊዜም ቢሆን ለስልኩ
በተዘጋጀ እና በራሱ ቻርጀር ብቻ ቻርጅ ማድረግ የመጀመሪያው ጥንቃቄ ሊሆን
ይገባል።
ይህን አለማድረጉ በባትሪው እድሜ ላይ አወንታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል፤ ባትሪው
በጊዜ የመጎዳትና የመሞት ባህሪም ይኖረዋል።
ከዚህ ባለፈ ግን መንገድ ላይ በአጋጣሚ የሚያገኟቸውንና ከታወቀ አምራች
ያልተመረቱ ቻርጀሮችን መጠቀም ቢያቆሙም ይመከራል።
2. ለስልኩ መከላከያ የገጠሟቸውን ነገሮች ማስወገድ፦ ስልክ ቻርጅ
ሲደረግ ቀስ እያለ መሞቁ የተለመደ ጉዳይ ነው።
ይሁን እንጅ ስልኩን ከአደጋ ለመከላከል በሚል የለጠፏቸው መከላከያዎችን
ቻርጅ በሚያደርጉ ጊዜ አለመንቀል ባትሪው ከመጠን በላይ እንዲግልና በጊዜ
አገልግሎት መስጠት እንዲያቆም ሊያደርገው ይችላል።
ስለዚህም በተቻለ መጠን ቻርጅ ሲያደርጉ እነዚህን መከላከያ ነገሮች
ማስወገድ ይመከራል።
3. ፈጣን ቻርጀሮችን አይጠቀሙ፦ ምናልባት አንዳንድ ጊዜ ከመቸኮል የተነሳ
ቶሎ ሃይል የሚሞሉ ፈጣን ቻርጀሮችን መጠቀምና እነሱኑ አማራጭ ማድረጉ
አይመከርም።
4. ሌሊቱን ሙሉ ስልክዎን ቻርጅ አያድርጉ፦ ምናልባት ከቀን ውሎዎ ወደ
ቤት ሲያመሩ ስልክዎ ቻርጅ ከሌለው እንዲሞላ በሚል ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ
ሰክተው ማሳደር የለብዎትም።
5. የባትሪ መተግበሪያዎችን ማጥፋት፦ ከኢንተርኔት አውርደው
የሚጠቀሙባቸውን አንዳንድ “የባትሪ እድሜ ማራዘሚያ” መተግበሪያዎችን
በዚህ ጊዜ መዝጋት ይመከራል።
6. 100 ፐርሰንት እስከሚሆን ቻርጅ አለማድረግ፦ በተቻለ መጠን ስልክ ሙሉ
በሙሉ ሙሉ እስከሚሞላ ድረስ ቻርጅ ማድረጉም አይመከርም።
7. በየጊዜው ቻርጅ አለማድረግ፦ በጣም በአጭር ጊዜ ልዩነት ቶሎ ቶሎ
ቻርጅ ማድረጉ አይመከርም።
ቻርጅ ሲያደርጉ 80 በመቶ ከደረሰ በኋላም መንቀልና መጠቀም ይቻላል፥ ይህን
ሲያደርጉ ባትሪው ቶሎ ቶሎ እንዳይጨርስ ይረዳዋል።
8. ቻርጅ እያደረጉ አለመጠቀም፦ በተቻለ መጠን ስልኩን ቻርጅ እያደረጉ
መጠቀም የለብዎትም።
ይህን ሲያደርጉ ስልኩ ከልክ በላይ እንዲግልና እንዲሞቅ ስለሚያደርገው
መጥፎ አጋጣሚም ሊፈጠር ይችላልና ከመጠቀም ይቆጠቡ

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa