Alie Assefa

Alie Assefa

Share

“መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ።”

TikTok · Geisinger Unfiltered 08/03/2026

Get out of all of them and give Glory to Jesus Christ Our Lord! He has been giving us His Resurected Life! Life and death are in front of us all; Let's choose Life Eternal!

TikTok · Geisinger Unfiltered 8757 likes, 614 comments. “This young woman is speaking hard truths. We need more outrage. They're literally eating children.”

TikTok · WordSword 08/03/2026

Get ready for the Revelation of Jesus Christ the King and His Eternal Kingdom. ከ ዓመተ-ምኅረት ወደ ሰዐተ-ፍርድ ከዛም ወደ ሺሁ ዓመት የክርስቶስ መንግስት ከዛም ወደ ነጩ ዙፋን ቅጽበተ ፍርድ በመጨረሻም ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም=የአዲሱ ሰማይና የአዲሷ ምድር ዋና ከተማ። ሁሉም በየተራው እንዲሁ ነው። አዎ! ሰማይና ምድር ያልፋል፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።

TikTok · WordSword 23.1K likes, 3858 comments. “The Moment John Survived Boiling Oil, Rome Realized Who Was Really in Control.”

06/03/2026

እንዲህ ሊሆን ነውና እንኳን ደስ ይበለን ብዬ እኮ ነው።

መልካም ቀን።

11/09/2024

የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት በተስፋ እና በናፍቆት ነቅተን እየተጠባበቅን የምንኖርበት አዲስ ዓመት ይሁንልን። አዲሱን ዓመት የመንፈስ ቅባት ዘይታችን ሳያልቅብን፣ ብርሐናችን በዓለም ሁሉ እየበራ፣ በማስተዋል፣ በእውቀት፣ በጥበብና በእውነት ጀምረን የምንዘልቀው ያድርግልን።

09/06/2024

በሥጋ መሠረት አንታለልምና
************************
የመጨረሻው መጨረሻ ተፈጽሞ ነቅተውና ተዘጋጅተው ለሚጠባበቁት መልካሙን የኢየሱስን ዳግም መምጣት የምናይበት ዘመን በደጅ ነው። ከማይረባውና ከምናምንቴው ዓለማዊ ወሥጋዊ ሕይወት ዘወር ብለን ጌታን በንቃትና በትጋት ተዘጋጅተን እንጠብቅ። ስለ ዓለማዊ ምናምንቴ ሥርዓቶችና ጉዳዮች መጨነቅ ጣኦትን ከማምለክ ክፋት አይተናነስም፤ ስለ ሥጋ ማሰብም ሞት ነው። በሥጋ መሠረት ልንታለል አይገባንም።

1ኛ ተሰሎንቄ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።
⁶ ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤
⁷ ስለዚህም በመቄዶንያና በአካይያ ላሉት ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው።
⁸ ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፥ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል።
⁹-¹⁰ እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ።

29/05/2024

በጌታ አምነው ያንቀላፉ ወገኖች ያሏችሁ አማኞች ሆይ፦ የትንሣኤው ተስፋ ይኸውና! ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች አትዘኑ። እኛ በሕይወት ባለንበት በዚህ ሰዐት ክርስቶስ ይመጣል። ሁለት ሰማያዊ መለከቶች ይነፋሉ። በመጀመሪያ አምነው በሞት ያንቀላፉት ወገኖቻችን ሁላ ከያዛቸው ሞት ይነቃሉ። በሕይወት ያለነውን ይቀላቀላሉ። ከዛም የሚሞተው ሥጋችን የማይሞት ሆኖ ጌታ በሚሰጠን ክብር ሥጋችን ይለወጣል። በመጨረሻም ለዘላለም ከጌታ ጋር ለመኖር በአየር ላይ እንነጠቃለን። ይህ ሁኔታ በዘመናችን ይፈጸማል። ድምጹን ለመስማት ነቅታችሁ ኑሩ። ስንሰራም፣ ስንዝናናም፣ ስንተኛም፣...ዘወትር ሳንታክት እየጸለይን የጌታን ሀሳብ ብቻ ቀዳሚ አስተንትኗችን እናድርግ። ሀሳቦቻችንን በሞላ ለጌታና ለቃሉ እናስገዛ። ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች አንዘን። የጌታ መምጣት ለእኛ ታላቅ ደስታ ነውና። ማራናታ!ጌታ ሆይ፦ ቶሎና። አሜን።

1ኛ ተሰሎንቄ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።
¹⁴ ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።
¹⁵ በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤
¹⁶ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
¹⁸ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።

28/05/2024

ሁለቱ ታላላቅ ተስፋዎች እነዚህ ናቸው፦

፩ኛ. የመለከቱን ድምጽ የሚሰሙቱ ታማኝ አማኞች ስብስብ/የእውነተኛይቱ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ወደ በጉ ሰርግ በአየር ላይ መነጠቅ፣

፪ኛ. የክርስቶስና ቅዱሳኑ በምድር ላይ ለመንገሥ ሁሉም ነዋሪዎች እያዩ ወደ ምድር ዳግም መመለስ( ዳግም ምጽአት)

የክርስቶስ ከድንግል መወለድ እውን ሆኖ እንዳለፈ ሁሉ የክርስቶስ ዳግም ምጽአትም እርግጥ ሊሆን በደጅ ነው።

እያንዳንዷን ዕለት ዛሬ የመጨረሻ እንደሆነ እያሰብን በንጽሕና፣ በቅድስና፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ኃያል ስም መልካሙን ተጋድሎ እንኑር።

ቃሉንም ዕለት በዕለት በመንፈሳዊነት እንመገበው።

ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤

“የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤”
— ማቴዎስ 24፥30

ራእይ 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።
¹² ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤
¹³ በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።
¹⁴ በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።
¹⁵ አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።
¹⁶ በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።
¹⁷-¹⁸ አንድም መልአክ በፀሐይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፥ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፦ መጥታችሁ የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር እራት ተከማቹ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
¹⁹ በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ጭፍራዎቻቸውም ተከማችተው አየሁ።
²⁰ አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
²¹ የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።

27/05/2024

ጌታ በደጅ ነው። ነቅተን የመለከቱን ድምጽ ለመስማት የተዘጋጀን እንሁን። በሥጋዊ መሠረት አንታለል። ሕይወት መንፈሣዊ እንጂ ሥጋዊ አይደለችም። ሥጋዊነት የሞት ባላባት ነው። መንፈሣዊነት ግን ከጌታ ጋር ለዘላለም የንጉሥ ክህነትን ተቀብሎ መኖር ነው። የዘላለም ሕይወትን አንጣል። የዘላለም ሕይወትን እንምረጥ።

1ኛ ተሰሎንቄ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።
¹⁴ ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።
¹⁵ በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤
¹⁶ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
¹⁸ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።

26/05/2024

መዳን ሁለመናዊ ነው፦ መንፈሳችን፣ ነፍሳችንና ሥጋችን ማለትም ሁለመናችን ሲድን እንዲህ ነው፦

፩. “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥17....መንፈሳችን ሲድን/ዳግም መወለድ፣

፪. “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
— ሮሜ 12፥2. በልብ/በአእምሮ/በነፍስ ዕለት በዕለት በእግዚአብሔር ቃል መታደስ/ መለወጥ...የነፍሳችን መዳን፣

፫. “እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።”
— ፊልጵስዩስ 3፥21. ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ ደግሞ ሥጋችን ይከብራል።

በዚህም ሁለመናዊ መዳናችን እርግጥ ይሆናል።

24/05/2024

በአንዱና በብቸኛው መንገድ፣ በአንዱና በብቸኛው እውነት፣ በአንዱና ብቸኛው ሕይወት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እንመላለስ። ሁለተኛውንና የመጨረሻውን መለከት ለመስማት ጆሯችንን አንቅተን በእሱ ብቻ እንኑር። መለከቱን ለመስማትና ለመነጠቅ የሚጠባበቁትን ለተወሰነው ጊዜ በአባቱ ቤት የደስታ መኖሪያን ቤት አዘጋጅቷልናል። ኖህንና አብረውት የነበሩትን፣ ሎጥንና ቤተሰቡን ያስመለጠው እሱ እኛንም በምድር ሊሆን ካለው እጅግ ከባድ መከራና ጥፋት አስመልጦ በአባቱ ቤት ባዘጋጀልን የበጉ ሰርግ ድግስ ሊወስደን ቀኑ እጅግ ቀርቧል፤ ጥሪው በደጅ ነውና ነቅተን እንጠባበቅ።

ማራናታ። ጌታ ሆይ ቶሎና።

ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
² በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
³ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
⁴ ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ።
⁵ ቶማስም፦ ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው።
⁶ ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።

“ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።”
— ራእይ 4፥1

22/05/2024

ጌታ ለእኛ ያለው ህይወት አሜን ይሁን።
*************************
“ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት።”
— ሮሜ 9፥12
ማቴዎስ 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና።
² ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።
³ በሦስት ሰዓትም ወጥቶ ሥራ የፈቱ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው አየ፥
⁴ እነዚያንም፦ እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ሄዱ።
⁵ ደግሞም በስድስትና በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ።
⁶ በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና፦ ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ? አላቸው።
⁷ የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው አሉት። እርሱም፦ እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ አላቸው።
⁸ በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን፦ ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው አለው።
⁹ በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።
¹⁰ ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።
¹¹-¹² ተቀብለውም፦ እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፥ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው ብለው በባለቤቱ ላይ አንጐራጐሩ።
¹³ እርሱ ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው፦ ወዳጄ ሆይ፥ አልበደልሁህም በአንድ ዲናር አልተስማማኸኝምን?
¹⁴ ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን?
¹⁵ ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን?
¹⁶ እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Addis Ababa
251