17/11/2025
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ
Federal TVET Agency established by regulation number 199/2011 in March 2011 with a duties and respon
17/11/2025
04/11/2025
💡ተሰጥዎንና ፍላጎትዎን ወደማይነጥፍ ሀብት መቀየር ይፈልጋሉ?
🛠️ሙያ የማይነጥፍ ሀብት ነው፡፡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ደግሞ ፍላጎትና ተሰጥዎን ወደ ወደማይነጥፍ💰ሀብትነት ቀይረው ወደ ስኬት የሚወስድዎ አውራ ጎዳና ነው፡፡
በቴክኒክና ሙያ ተቋሞቻችን👇
💻በአይ ሲቲ፣
🚗በአውቶሞቲቭ፣
⚙️በኢንደስትሪያል ኤሌክትሪካል ኮንትሮል፣
📏በሰርቨይንግ፣
🏨በሆስፒቴልና ሆስፒታሊቲ፣
🏗️በኮንስትራክሽን፣
👗በፋሽንና ዲዛየን እና መሰል ዘመኑን የዋጁ ስልጠናዎች አሉ፡፡
የእርስዎ ምርጫ የቱ ነው?
✅የትኛውንም ቢመርጡ፤ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋሞቻችን እርስዎን ለማስተናገድ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል፡፡
🏃 ጊዜው አሁን ነው!
📍አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የቴክኒክና ሙያ በመሄድ አሁኑኑ ይመዝገቡ!
ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
30/10/2025
የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ አዲስ ምዕራፍ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ስልጠና ጥራትና አግባብነት፤ ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ለማሻሻል መሰረተ ሰፊ የሪፎርም አጀንዳዎችን ቀርፆ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የዘርፉ የሪፎርም አዳዲስ እሳቤዎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኩን ሳቢ ለማድረግ እና ሀገራዊ የሥራ ገበያውንና የልማት ፍላጎቱን መመለስ እንዲያስችል ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ሪፎርሙን ተከትሎ በዘርፉ ወደ ሥራ ከገቡ ስርዓቶችና አሰራሮች መካከል ዲጂታላይዝድ በሆነ መልኩ የሚተገበረው የሳይኮሜትሪክ ምዘና አንዱና ዋነኛው ነው፡፡
ምዘናው በዋናነት ዘርፉን በአዲስ መልክ ለሚቀላቀሉ አዲስ ሰልጣኞች የሚሰጥ ሲሆን ይህም ለሰልጣኞች፣ ለስልጠና ተቋማቱ እና ለሀገር ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ታሳቢ ተደርጎ የተቀረፀ ስርዓት ነው፡፡
ምዘናው የሰልጣኞቹን ፍላጎቶት ብቻ ሳይሆን ተሰጥኦና ዝንባሌን መሰረት በማድረግ ውጤታማ ሊሆኑባቸው የሚችሉ የሙያ መስኮች እንዲመርጡ ያግዛቸዋል። ይህም ውድ ጊዜያቸውን ውጤታማ በማይሆኑበት የትምህርትና ስልጠና ዓለም ውስጥ እየማሰኑ እንዳያባክኑ ያደርጋል፡፡
ከዚህ ባሻገር የማሰልጠኛ ተቋማት የሰልጣኞች ምደባ ሥራቸውን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመምራት፣ በኮሌጁ የአቋራጭ ምጣኔን ለመቀነስ እና መረጃ ላይ የተመሰረተ ውጤታማ የካውንስሊግ ሥራ እንዲሰሩ የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡
ከሁሉም በላይና ባሻገር ደግሞ የሥልጠና ጥራትና አግባብነት እንዲሁም ውጤታማነትን ከሥራ ገበያ ፍላጎቱ ጋር በማጣጣም ብቁ፣ በቂና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን በማፍራት እንደ ሀገር ለሥራ ገበያው ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ የቴክኒክና ሙያ ስርዓት ባለቤት እንድንሆን ያደርገናል፡፡
ይህም ምርትና ምርታማነትን በማሻሻልና ቅልጥፍና በመጨመር ሀገራዊ ተወዳዳሪነታችንን በሁሉም መስክ በማሳደግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ ያስችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር የሥራ አጥነት ምጣኔን ትርጉም ባለው መልኩ ከመቀነስ አኳያም ሚናው የላቀ ነው፡፡
በዚህ አዲስ የሪፎርም እሳቤ መሰረት በፓይለት ደረጃ የተመረጡ የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የ2018 የስልጠና ዘመን አዲስ የሰልጣኞች ቅበላቸውን በተቀመጠው አግባብ ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛል፡፡
የሳይኮሜትሪክ ምዘናውን መስጠት ከጀመሩ መካከልም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኘው አንጋፋው የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አንዱ ነው፡፡ ኮሌጁ እንዳስታወቀው ከጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዘናውን እየሰጠ ይገኛል፡፡
የሞጣ ፓሊክኒክ ኮሌጅም እንደ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሁሉ ከጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዘናውን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ክህሎት ለሁለንተናዊ እድገትና ውጤታማነት ነው!
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
26/10/2025
ከሞተር ሳይክል ማጠብ እስከ ተሽከርካሪ አስመጪነት ...
የምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ ተወላጅ የሆነው ወጣት ሳዳም አብዳ ከ12 ዓመታት በፊት በ10 ብር ክፍያ ነበር የሞተር እጥበት ስራውን የጀመረው።
በወቅቱ በጥቃቅንና አነስተኛ ማሕበር በመደራጀት ባገኘው 5 ሺህ ብር ስራውን የጀመረው ወጣቱ፣ በትጋት በመስራት ወደ ተሽከርካሪና ሞተር ሳይክል አስመጪነት መሸጋገሩን ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሯል።
በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በመግባት በአውቶሞቲቭ ስልጠና በከፍተኛ ውጤት መመረቁን የሚገልጸው ወጣት ሳዳም፣ ትልቅ ዓላማ ሰንቆ በመነሳት ከምርቃቱ በኋላ በጊኒር ከተማ የሞተር ሳይክል እጥበት ስራውን እንደጀመረ አስታውሷል።
ቀስ በቀስም ስራውን ሞተር ሳይክል ወደ መጠገን በማሳደግ ከዓመታት በኋላ የሞተር መለዋወጫና አሮጌ ሞተር ሽያጭ ስራ ላይ በመሰማራትና በትጋት በመስራት ወደ ተሽከርካሪ መለዋወጫ መሸጫ ማሸጋገሩን ገልጿል።
በዚህም በጥቂት ዓመታት ወስጥ የተለያዩ ዘመናዊ ሞተር ሳይክሎችን በማምጣት ሽያጭ እንደጀመረ በመግለጽ፣ በሂደትም ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ መለዋወጫና ሞተር ሳይክሎችን ከውጭ ሀገር በስፋት እያመጣ መሸጥ መጀመሩን ጠቁሟል።
ከ5 ዓመታት በፊት ጀምሮ ከሞተር ሳይክል አስመጭነት በተጨማሪ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን በማስመጣት የንግድ ሥራውን እንዳሳደገና በጊኒር ከተማ የጀመረውን ስራ በተለያዩ ሰባት ከተሞች ላይ ቅርንጫፎችን በመክፈት እየሰራ እንደሚገኝ ነው የገለጸው።
አሁን ላይ ከራሱ አልፎ ከ230 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል እንዲሁም በጊዜያዊነት ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ችሏል።
በቀጣይም ስራውን በማሳደግ ወደ ተሽከርካሪ ማምረቻነት ለመሻገር ወጥኖ እየሰራ መሆኑን ይናገራል።
ማንም ሰው ዓላማውን ማሳካት ከፈለገ የስራ ባህሉን ማሳደግ፣ ስራን ማክበር፣ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀምና የተግባር ሰው ሊሆን እንደሚገባም ሐሳቡን አጋርቷል።
ወጣቱ ድጋፍ ላደረገለት ማሕበረሰብ የምስጋና መርሐ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን÷ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሙሀመድ አብዱልቃድር አቶ ሳዳም ለወጣቱ ምሳሌ የሚሆንና ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግለት አረጋግጠዋል።
ከዚህ ቀደም ለተሽከርካሪ መገጣጠሚያ መክፈት የሚያስችል 5 ሺህ 300 ካሬ ሜትር ቦታ ከከተማ አስተዳደሩ በማግኘት ስራውን ለመጀመር የግንባታ ስራው እየተከናወነ እንደሚገኝም ተመላክቷል።
አቶ ሳዳም በታማኝ ግብር ከፋይነት 900 ሚሊየን ብር በመክፈል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተከታታይ ሦስት ዓመታት እውቅና ማግኘቱን ጠቅሶ የዘገበው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው፡፡
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
26/10/2025
የተገልጋዮችን እርካታ 95 ከመቶ በላይ ማድረስ ያስቻለው ማዕከል
ቴክኖሎጂ የሥራ ቅልጥፍናን፣ ምርታማነትንና ውጤታማነት ያሳድጋል፡፡ ፈጠራና ፍጥነትን ማዕከል ባደረገው አቅጣጫ መንግስት ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለዜጎች ለማቅረብ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ፣ ምቹ እና ቀልጣፋ ለማድረግ አገልግሎቶቹን በቴክኖሎጂ አስተሳስሮ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡
በፌዴራል ደረጃ ባለው ማዕክል 23 ተቋማት አገልግሎታቸውን በማዕከሉ አስገብተዋል፡፡ ከእነዚ ተቋማት መካከል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚገኝ ሲሆን የውጭ ሀገር ባለሙያዎች የሥራ ፈቃድ እና የዲጂታል ኢንተርፕራይዝ ምስረታ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች በማዕከሉ እየተሰጡ ይገኛል፡፡
የ100 ቀናት የሥራ አፈፃፀም ላይ እንደተመላከተው በማዕከሉ 180 አገልግሎቶች ባሳለፍነው መቶ ቀናቶች ብቻ ተሰጥተዋል፡፡ ከ79 ሺህ በላይ ተገልጋዮችም በማዕከሉ አገልግሎት እንዳገኙና በማዕከሉ አገልግሎት ካገኙ ዜጎች በተወሰደ መረጃም የእርካታ ደረጃቸው 95 በመቶ በላይ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ የተሰጡ አቅጣጫዎችን አስመልክቶ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ በሰጡት ማብራሪያ የመንግስት ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት በቴክኖሎጂ አግዞ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ መንግስት በልዩ ትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡
በፌዴራል ደረጃ ወደ ሥራ ከገባው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በተጨማሪ ወደ ክልሎች እንዲሰፋ አቅጣጫ ተቀምጦ በዚህም በተለያዩ የክልል ከተሞች ማዕከሉን ወደ ሥራ ማስገባት እንደተቻለም አብራርተዋል፡፡
መሶብ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን በዘላቂነት ከመፍታት፣ ብልሹ አሰራርን ከማስቀረት እና የተገልጋይ እርካታን ከማሳደግ አኳያ ፋይዳው ትልቅ መሆኑን ያብራሩት ክቡር አቶ አደም ፋራህ እስከ ሰኔ 2018 ድረስ ማዕከላቱን 100 ለማድረስ በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
24/10/2025
በሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራዊ የተደረገው ሪፎርም በዘርፉ ያለው አቅም እንዲያድግ ማስቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
ክብርት ሚኒስትር እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ተግባራዊ የተደረጉ ሪፎርሞች ሀገራዊ የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅም እንዲያድግ አስችለዋል።
በዘርፉ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቁመው፤ አዳዲስ እሳቤዎችና አሰራሮች መዘርጋታቸው በስራ ዕድል ፈጠራ መስክ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ማስቻሉን ጠቅሰዋል።
በ2017 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ፣ በውጭ ሀገርና በርቀት የሥራ ዘርፎች ለ4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅደን 96 በመቶ ያህሉን አሳክተናል ብለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም በሀገር ውስጥ፣ በውጭ ሀገርና በርቀት የሥራ ዘርፎች ከአምስት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን አብራርተዋል።
ዕቅዱን በተሟላ መልኩ ለመፈጸም የባለድርሻ አካላትን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተያዘውን ዕቅድ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ሥራ ላይ ለማዋል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
ዜጎች ወደ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት በቂ ክህሎትና እውቀት እንዲጨብጡ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አሰራር በመዘርጋት በርካታ ዜጎች ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ለስራ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ዜጎች የሚገጥሟቸውን ችግሮች መፍታት ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ዜጎች ለስራ ወደ ውጭ ከመጓዛቸው በፊት ተገቢውን ክህሎት እንዲጨብጡ እየተደረገ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ሚኒስቴሩ በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ የሥራ ሀሳብ ባንክ ሟቋቋሙን ገልጸው በዚህም በርካታ የሥራ ሀሳቦች ተሰብስበው በዲጂታል ፎርማት መቀመጣቸውን አስረድተዋል።
ባንኩ ምን ልስራ ብሎ ለሚነሳ ሰው በየዘርፉ መነሻ የሚሆኑ የሥራ ሀሳቦችን የያዘ መሆኑንም ገልጸዋል።
በሥራ ዕድል ፈጠራ ያለውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከባንኮች ጋር ሰፊ ምክክር መደረጉን ጠቁመው ባንኮች በተለያዩ አማራጮች ፋይናንስ እንዲያቀርቡ እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት በሀገር ውስጥ፣ በውጭ ሀገርና በርቀት የሥራ ዘርፎች ከ671 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተገልጿል። ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡
21/10/2025
ህጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት: ለሁለንተናዊ ደህንነትና ተጠቃሚነት!
✈️ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ ይፈልጋል።
⚠️ ህጋዊ ያልሆኑ አማራጮች ሁሉ ህይወትዎን ለከፋ አደጋ፣ ገንዘብዎን ለቀማኛ ይዳርጋልና በእጅጉ ይጠንቀቁ።
🚨 #ያስታውሱ
✅ለደህንነትዎ ቅድሚያ ይስጡ!
✅በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ ይመዝገቡ!
✅ስልጠና ይውሰዱ!
✅ስምሪቱ አማራጭም ሆነ አቋራጭ መንገድ የለውም!🚫
ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Website
Address
Yeka
Addis Ababa
251
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |