ወንጌልን ለፍጥረት በሙሉ

ወንጌልን ለፍጥረት በሙሉ

Share

yes

09/06/2021

ወደድክም ጠላህም እግዚአብሔር እንደ ቃሉ ነው።።።

Photos 16/10/2020

እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፥ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፥ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።
- ትንቢተ ሶፎንያስ 2:3 https:///bible/f544448ff1326ad7-01/ZEP.2?passageId=ZEP.2.3

18/10/2019

ወዳጄ ሆይ
ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ ኀዘን የልብ መሰበርን ያመጣል፣ የልብ መሰበርም እግዚአብሔርን ያያል። መገፍተር ሲያቅትህ ያቀፍከው የወደድከው አይደለም። አገርን የትኛውም ጠላት ማፍረስ አይችልም፣ አገርን የሚያፈርሱት የአገሬው ሰዎች ናቸው። እንኳን ጠላት ያለበት ወዳጅ ያለውም የሚጠቃው በመጠጥ ነው። መልካም ባልንጀራ መፈለግ ያደክማል፣ መሆን ግን ያሳርፋል። ለምኖ አነሰ ማለትና መሳደብ ታላቅ ውርደት ነው። እጅህ የሚሠራልህን የሰው እጅ አይሠራልህምና ሌሎች ይሥሩልኝ ብለህ አትቀመጥ። እንደ ደረስህ በር አትግፋ፣ አንኳኳ። እንደ ሰማህም ቱግ አትበል ፣ አጣራ። ተበደልሁ እንጂ በደልሁ የሚል እየጠፋ ነው። ሰላም ራሳቸውን ባጸደቁ ሳይሆን ንስሐ በሚገቡ ትሑታን ጋ ትኖራለች። ሙትን ሲያወግዙ መኖር ተናጋሪ ሙት መሆን ነው። ዘረኝነት በቃል የተወገዘ በተግባር የሚኖሩት አስመሳይነት ነው። የጋራ ጠላት ከሌለው የጋራ ፍቅር የሚያጣ ሕዝብ ምስኪን ነው።

ወዳጄ ሆይ
ሁሉን ነገር ለእኔ የሚሉ ሕፃናት፣ ያልሰለጠኑ፣ ወፈፌና አውቆ አበዶች ናቸው። አስበው የማይናገሩ ፣ ተናግረው ያስባሉ። በሰማበት ሁሉ ጣዱኝ የሚሉ የሰፈር ምጣድ ናቸው፣ ባለቤት የላቸውም። ካህን ፖለቲካ ፖለቲካ ከሸተተ፣ ፖለቲከኛ ዕጣን፣ ዕጣን ከሸተተ ነገር ተበላሸ! ብዙ የሚያሳይ ዕድሜ፣ ልጅና እጦት ነው። በርግጥ የታመምከው እህል እምቢ ያለህ ቀን ነው፣ በርግጥ የተፈተንከው ቃለ እግዚአብሔር ያስጠላህ ቀን ነው።

ወዳጄ ሆይ
ከአዲስ ንጉሥ የቆየ ወታደር፣ ከአዲስ ባለትዳር የቆየች ሠራተኛ፣ ከአዲስ ሐኪም የቆየ በሽተኛ፣ ከአዲስ ባለጠጋ የቆየ ደላላ፣ ከአዲስ ሰባኪ የቆየ የደብር ዘበኛ፣ ከአዲስ መካሪ የቆየ ጥፋተኛ፣ ከአዲስ ቄስ የቆየች አቃቢት ይበልጣሉ። የከረመ ወይን ዋጋው ትልቅ ነው፣ የበሰለም ሰው ተፈላጊ ነው። አገር የምታብደው እውነተኛ አዋቂዎቿን የናቀች ቀን ነው።

25/07/2019

ከኀዘን የተነሣ

“ከጸሎትም ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣና ከኀዘን የተነሣ ተኝተው ሲያገኛቸው፡- ስለ ምን ትተኛላችሁ ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው ።” ሉቃ. 22፡45 ።

ጌታችን ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ ሰጥቶናል ፤ እንዲሁም ኑሮውን አብነት አድርጎልናል ። በመከራ ሰዓት ፣ ፈተና ሲቃረብ ፣ የጭንቅ ዋዜማ ሲመጣ ፣ ወዳጅ ሲለወጥ ፣ የታመነም ሲከዳ ፣ ቤተ ክህነትና ቤተ መንግሥት እውነትን ተባብሮ ለመስቀል ሲወዳጅ … መፍትሔው ጸሎት ብቻ መሆኑን ጌታችን ሊያስተምረን በብርቱ ጸለየ ። ጸሎቱ የሚያስፈልገው ለደቀ መዛሙርቱ ነበር ፣ ደቀ መዛሙርቱ ተኝተው ግን ጌታችን ጸለየ ። መጸለይ የሚገባቸው ለጸሎት አልተጉም ። ሰይፍ ለመምዘዝ የተጋው ጴጥሮስም ለጸሎት መትጋት አልቻለም ። ጌታችን ከታላቅ የጸሎት ትጋት በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸው ።

የፈተና ሰዓት ሲቃረብ ለመጸለይ አቅም የሚነሣ አዚም ይመጣል ። ሽብርና ወሬ ይነግሣል ። አእምሮም ፋታ አጥቶ ይበጠበጣል ። ግምትና መረጃዎች አየሩን ይቆጣጠሩታል ። እግዚአብሔርን ከማሰብ ወቅቱን ማግነን ይበረክታል ። በዚህ ግፋ በል በሚባልበት ፣ በለው በበዛበት ሰዓት የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሰው ሐሞት የሚያፈስስ ተደርጎ ይገመታል ። ጸሎት መግደል ባይሆንም መግደል ጸሎት ነው ተብሎ ይታመናል ። እገሌ ከዳ ፣ እገሌ ካደ የሚለው ወሬ ይበዛል ። ነፋሱን ለመስማት የሰላው ጆሮ ቃሉን ለመስማት ይፈዝዛል ። ለመጸለይ አቅም ያጣ ሰይፍ ለመምዘዝ አቅም ያገኛል ። በሊቀ ካህናቱ የተናደደ የባሪያውን ጆሮ ይቆርጣል ፤ በመስፍኑ የተበሳጨ ሎሌውን ካልገደልሁ ይላል ። “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” መደብደብ ይበዛል ። እየተጓዘ የሚጓዝና ተቀምጦ በአሳብ የሚጓዝ ብዙ ይሆናል ። ሁሉም ከውስጡ የሚያወጣው የተቃጠለ አየር ይሆንና ሕይወት የሚሰጥ ትንፋሽ የሚገኝበት ሰው ይታጣል ። አንዱ አንድ ሰው ሞተ ሲል ሌላኛው የበለጠ መርዶ ይዟልና አሥር ሰው ደግሞ እዚያ ጋ ሞተ ይላል ። ልውውጡ የበለጠ ክፋት እንጂ የደግነት ድምፅ አይደለም ። እግር ሳይያዝ አሳብ ይያዛል ። ጠላት ሳይመጣ በወሬ አገር ይፈታል ። የሩቅ ሲጠበቅ የቅርቡ ቀድሞ ይከዳል ። በዚህ ሰው ሳይጠጣ በሚሰክርበት ጊዜ እንደ ምንም ብሎ መጸለይ መቻል መታደል ነው ። ከሚነፍሰው ጋር ላለመንፈስ ፣ አየር እየጎሰሙ ከንቱ ውድድር ላለማድረግ ጸሎት ወሳኝ ነው ። ጸሎት ለሁሉ ነውና ስንጸልይ ጠላትን ሳይቀር የመውደድ አቅም እናገኛለን ። ያለፉትን ብቻ ሳይሆን እየመጡ ያሉትን ጠላቶችም ይቅር ብለን ለመጠበቅ ኃይል እናገኛለን ። ጸሎት ሁኔታን ሳይሆን እግዚአብሔርን ያያል ፤ ጸሎት ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን ያጸናል ። ስለዚህ ጌታችን ተግተው እንዲጸልዩ ቢነግራቸው ደቀ መዛሙርቱ ግን አብዝተው ተኙ ። አብዝቶ ሲነግራቸው አብዝተው ደነዘዙ ።

“ባለጌ የተመከረ ዕለት ፣ ቁንጫ የተጠረገ ዕለት ይብስበታል” ይላሉ ። ጸልዩ በተባለው ልክ ስድብ ከበረከተ ፣ ቃሉን መስማት በሚገባ ሰዓት ራስን መስማት ካየለ አስቸጋሪ ነው ። ደቀ መዛሙርቱ መከራው የጌታ ሲሆን እነርሱን ግን ጣላቸው ። ፍሙ ሳይሆን ወላፈኑ ፈጃቸው ። “የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ” እንዲሉ እነርሱ በሚያበረቱበት ሰዓት መከረኛው ጌታ እያበረታቸው ነበር ። መጸለይ የሚገባቸው መከራ እንዳይመጣባቸው አይደለም ፣ መከራውማ የጌታ ነው ። የሚጸልዩት በስፍራቸው መገኘት እንዲችሉ ፣ በሚያቀል ቀን እንዳይቀሉ ፣ በዝምታ ዘመን እንዳይለፈልፉ ፣ ለታላቅ ሰራዊት ትንሽ ቢላዋ እንዳይስሉ ፣ ለመንፈሳዊ ውጊያ በሥጋ እንዳይጋጠሙ ነው ። የፈተና ሰዓት ጥቂት ነው ፣ ነገር ግን ለዘመናት የገነባነው የሚናድበት ፣ አለሁ ብለን በፎከርንበት ነገር የምንታጣበት ነው ። “ሊያልፍ ውኃ አደረገኝ ድሀ” እንዳለው ሊያልፍ ቀን ክፉ የሚያናግር ፣ ፍቅር አልባ የሚያደርግ ነው ። ልብ ከጸሎት ውጭ አጥር የለውም ። ክፉ ቀን ከጸሎት ውጭ መሻገሪያ ድልድይ የለውም ።

ጌታችን መለስ ብሎ ያያቸው ነበር ። እርሱ ለብዙዎች መከራ ቀድሞ የተገኘ ፣ ሲከሰሱ ጠበቃ ሁኖ የተናገረ ፣ ሲታመሙ ሐኪም ሁኖ የፈወሰ ነው ። በእርሱ የፈተና ሰዓት ግን ደቀ መዛሙርቱ ለአንዲት ሰዓት እንኳ መትጋት አቃታቸው ። ዛሬ በከንቱ የሚወገሩ ወዳጆች አሉን ፣ ነገር ግን እውነቱ ይህ ነው ብለን አንደበት ካልሆናቸው ፣ ዛሬ በከንቱ ለሚገፉት ጥግ ካልሰጠናቸው ፈተናው ከፈተነኞቹ ይልቅ እኛን እያበጠረን ነው ። በሰፌድ ላይ ያለ ስንዴ ቀሎ እንዲበጠር እንዲሁም ክፉ ቀን ያበጥራል ። “ክፉ ቀን አይምጣ ወዳጅ እንዳላጣ” የሚባለው ለዚህ ነው ።
“ከጸሎትም ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣና ከኀዘን የተነሣ ተኝተው ሲያገኛቸው፡- ስለ ምን ትተኛላችሁ ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው ።” ሉቃ. 22፡45 ።

በጸሎት እየተጋ ያለው ጌታችን ያልተጉት ወገኖቹ አሳሰቡት ። ከጸሎት ተነሥቶ ወደ እነርሱ መጣ ። እንኳን መኝታ ከንቱ ንቃት እንኳን በማያድንበት ሰዓት እነርሱ ተኝተው አገኛቸው ። የሆሳዕና እንጂ የዓርብ ወዳጅ መሆን ያልቻሉት ለዚህ ነው ። በሚያስፈልጉበት ቀን የሸሹት ፣ በደቀ መዝሙር ወግ ያልተገኙት ለዚህ ነው ። ወታደር በክፉ ቀን ለንጉሡ ይገኛል ። እናትም ከልጇ በፊት ለመሞት ትደራደራለች ። ደቀ መዝሙር ግን ለአንዲት ሰዓት በጸሎት መትጋት ካልቻለ የሚገርም ነው ። ስንቱ ወገን በፈተና ሰዓት መረጃ ያሯሩጣል እንጂ ልጸልይ አይልም ። ካልጸለይን መከራውን ዕድሜ እየሰጠነው ነው ።

ከኀዘን የተነሣ ተኝተው አገኛቸው ይላል ። ኀዘኑ የተወለደው ጌታ እንደሚሞት ስለሰሙና አጠገባቸውም ብዙዎች መንጠባጠብ ስለጀመሩ ነው ።ኀዘን ልቅሶ ስላለው ያስተኛል ። ሕፃን ልጅ አቅልሶ ፣ አልቅሶ እዚያው ፍንግል ብሎ ይተኛል ። ኀዘን በእንባ ጎርፍ ወደ እንቅልፍ ሸለቆ ይወስደናል ። ኀዘን ችግሩና ጉዳቱ ላይ መቆየት ስለሆነ ያደክማልና ያስተኛል ። ለሰሙት ችግር መፍትሔውን መፈለግ እንጂ ማዘን ብቻውን ጥቅም የለውም ። ኀዘን ፣ ኀዘን ወልዳል ። ኀዘን ካልራቁት ተጣብቆ ይኖራል ። ኀዘን በቃኝ ካላሉት ገና ለቀጣይ ዓመታት ይሻገራል ። ምን ማድረግ ይገባኛል ማለት ግን የኀዘን መድኃኒት ነው ። የኀዘን መፍትሔው ጸሎት ነው ።

ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ አለ ። መከራው የጌታ ነው ፣ ፈተናው ግን የደቀ መዛሙርቱ ነው ። ፈተና በመከረኞች ላይ የሚኖረን አስተሳሰብ ፣ የቀለለ ሚዛን ነው ። ፈተና ከመከረኞች ጋር አብረን ለመቆም ድፍረት ማጣት ነው ። የጊዜ ሆያሆዬ የሚጫወቱ ለተጠቁት ለመቆም አቅም ያንሳቸዋል ። ከቀኑ ጋር ለመክፋትም ፣ ለክፋት አወዳሽ ለመሆንም ተላልፈው ይሰጣሉ ። ተግቶ መጸለይ ግን ሚዛናዊ ኅሊና ፣ የጸና አቋም ይሰጣል ።

እያዘንን ብቻ ከሆነ እንደክማለን ። መጸለይ ግን ላለፈው ስርየት ፣ ለሚመጣው ንጹሕ ልብ ይፈጥርልናል ።

24/05/2019

🗣ወንጌልን ላልዳኑት መስበክ ያለበት ማን ነው?🗣

❤️ወንጌልን ለፍጥረቱ እንዲሰበክ እግዚአብ አዝዞአል።ወንጌል ስለ ልጁ ስለጌታችን ስለኢየሱስ ነው።ማንኛውም ሰው ወንጌል የመስማት እድል ባላገኘበት ጌታን ኢየሱስን በማመን ሊድን አይችልም ምክንያቱም፦ ።።ሮሜ.10:17

✝ታዲያ እምነት ከመስማት ከሆነና ያለሰባኪም የመስማት እድል ከሌለ ወንጌልን ማን ይስበክ?

❤️ብዙዎች መጋቢዎችና አገልጋዮች ናቸው መስበክ ያለባቸው የሚሉ አሉ።ሆኖም ስህተት ነው።ሁሉም አማኝ ወንጌልን ላላመኑት የመናገርና የመስበክ ግዴታ አለበት።

👉ምንም የመፅሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እንኳን ባይኖረን በሕይወት የመኖራችን ምክንያት ጌታን ላላመኑት እንድንመሰክር ካልሆነ በዚህ ዓለም መኖር ለአማኝ ትርፉ ስቃይ፥መንገላታትና መከራ ነው።ወደ ጌታ መሄድና ከእርሱ ጋር መኖርን የመሰለው እድል በዚህ ዓለም ከመኖር ጋር አይነፃፀርምና።ፊልጵ.1:23-24

❤️በማቴዎስ 28:19-20 ባለው ለሐዋርያት የታዘዘውን ትእዛዝ አማኞች እንዲጠብቁ መማር እንዳለባቸው ተፅፎአል።ብዙዎች ለሐዋርያት ብቻ የተነገረ ይመስላቸዋል።ሆኖም ኢየሱስ፦ ነው ያለው።

❤️በሐዋርያት 1:8 ላይ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበለና የተሞላ አማኝ ሁሉ የኢየሱስን አዳኝነት መመስከር አለባቸው።

❤️በሐዋርያት ሥራ 8:1-4 እንደተፃፈው በእስጢፋኖስ ሞት ምክንያት የተበተኑት ክርስቲያኖች ሁሉ ወንጌል እየሰበኩ ይዞሩ ነበር።ስለዚህ ወንጌል የአገልጋዮች ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም አማኝ ኃላፊነት እንደሆነ እንረዳለን።

❤️በሐዋርያት ሥራ 11:19-21 ላይ በእስጢፋኖስ ሞት ምክንያት የተበተኑት ለአይሁዳውያን ብቻ ወንጌል ይናገሩ ነበር እንጂ ለአሕዛብ አልሰበኩም።ቤተክርስቲያን ያልሾመቻቸውና በስም እንኳን የማይታወቁ አንዳንድ አማኞች ግን ለግሪክ ሰዎች ወንጌልን ሰበኩላቸው።ብዙዎችንም ወደጌታ አመጡ።ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሰራ ነበር።ስለዚህ ወንጌልን ለመስበክ ማንንም ሳንጠብቅ ሁላችንም መስበክ አለብን።

❤️❤️በመጨረሻም 1ኛ ጴጥሮስ 2:9 ላይ እንደተፃፈው እኛ የጌታን በጎነት ልንናገር የተመረጥን ትውልድና የንጉሡ ኢየሱስ ካህናት ነንና ወንጌልን ሁላችንም ወንጌልን እንመስክር።

✝✝ለመስበክ እውቀትና ችሎታ የለንም እንኳን ብለን ብናስብ እንደ ሳምራዊቷ ሴትና እውር ሆኖ ተወልዶ በኢየሱስ ዓይኑ እንደበራለት ሰው ስለ ኢየሱስ ልናወራና ልንመሰክር ይገባል።በዚህ ጊዜ የጌታ አብሮነትና ፀጋ ከእኛ ጋር ይሆናል።

ስለዚህ ወንጌልን ለፍጥረቱ በመስበክ ጌታ ታማኝ አድርጎ ቆጥሮ የሰጠንን ኃላፊነት እንድንወጣና የመኖራችን ትልቁን ምክንያት እንድናገኝ በጌታ ፍቅር መልእክቴን አስተላልፋለሁ።ተከናወኑ።

" ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤"
(የማቴዎስ ወንጌል 10:32)

11/05/2019

እማማም_አባባም
**********
በሰንበት ለት ፕሮግራም ለመካፈል ከኛ ቤት ለጥቆ የሚኖሩት እማማና አባባ ወደ ቤተ ክርስቲያን አመሩ፡፡መርሀ ግብሩ ቅደም ተከተሉን ይዞ እየተከናወነ የስብከት ሰአት ደረሰ፡፡ሰባኪው ወጥቶ Hallelujah!!Holy spirit በመካከላችን አለ የክብር እንግዳችን Jesus!!Jesus!!Jesus!! በማለት ደጋገመና give thanks to God አለ፡፡ጉባኤው እልልታና ጭብጨባውን አቀለጠው፡፡እማማ ወደ አባባ ዘወር ብለው እነዚህ ሰዎች ምን ነክቷቸዋል አጨብጭቡ ሳይባሉ የሚያጨበጭቡት አሉ፡፡አባባ መለሱ እኔም አልገባኝም ምናልባት በመሀላችን አለ ያለውን ፈረንጁን እንግዳ ወደ መድረክ እየጋበዘ ይሆናል አሉ፡፡ሰባኪው ቀጠለ ዛሬ የምንማረው Christ ለኛ ስላለው ፍቅር ነው፡፡Christ ለኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጠው cross ላይ ሆኖ ነው፡፡Brothers Christ ስለኛ ያልሆነው የለም፡፡he cursed ስለኛ he crucified ስለኛ he was wounded ስለኛ he died ስለኛ.Peter deny አረገው God እንኳን ፊቱን አዞረበት፡፡እማማ በጣም የሰለቻቸው ይመስላሉ ወደ አባባ ዞር አሉና ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ አንማርም መሰል ፈረንጅ እያወደሰ ሊሞት እኮ ነው አሉ፡፡አባባ መለሱ ምን እያለ እንደሆነ እንጃ ስለኛ ያልሆነው የለም ብሏል ፈረንጁ ብዙ ነገር ያደረገ በጎ ምግባረ ሰናይ ሰው ሳይሆን አይቀርም፡፡ወይ አንዴ መድረክ ላይ ወጥቶ ፊቱን ቢያሳየን እንኳን እንዴት መልካም ነበር፡፡ይሄን ያህል የሚጨበጨብለት ማን ሆኖ ነው አሉ፡፡እማማ መለሱ እህ ሌሎቹ ሰዎች የሚያጨበጭቡት ሰውየውን የት አውቀውት ነው ለመወደድ ብለው ይሆናል እንጂ፡፡ደሞ እስታሁን ድረስ አንድም ነጭ ሰው እዚህ ቤተ ክርስቲያን ዝር ብሎ አያውቅም አሉ፡፡ሰባኪው ስብከቱን ወደ ማጠቃለሉ መጣ፡፡ok now አንዳንድ pointochin እናነሳና እንጨርሳለን አለ፡፡ይህኔ እማማ ወደ አባባ ዞር ብለው ጠርጥሬ ነበር ድግስ ነው መሰል ብፌ ሳይኖር አይቀርም አንዳንድ እናነሳለን ብሏል፡፡ባይሆን በዚህ ይካሰን እንጂ አሉ፡፡አባባ መለሱ አይ እኔ እንኳን አላነሳም ለፈረንጅ የተዘጋጀ ምግብ ነው የሚሆነው እንጀራዬ ይሻለኛል ባይሆን ባይሆን እንዳያዝኑብኝ እቀማምሳለሁ አሉ፡፡ፕሮግራሙ አልቆ እማማም አባባም የድግስ ምግብ እየጠበቁ ሰው ወጥቶ አለቀ፡፡ስለሚያውቁት ክርስቶስ ለመማር ሄደው ስለማያውቁት Christ ሳይማሩ ተመለሱ፡፡ስለሚያውቁት እግዚአብሔር ሊሰሙ ሄደው ስለማያውቁት God ሳይሰሙ ተመለሱ፡፡ስለሚወዱት ኢየሱስ በቋንቋ ምክንያት ሳይረዱ ተመለሱ፡፡በማያውቁት ቋንቋ ሆኖባቸው ስለ ህይወታቸው ጌታ የተሰበከው ስብከት ስለ አንድ የማያውቁት ነጭ የተወራ መሰላቸው፡፡እማማም አባባም እንዴት ስለ መድሀኒዓለም በሚወራበት መድረክ ስለ ሰው ይወራል እያሉ አዝነው ተመለሱ፡፡ይህ ታሪክ ያንድ መድረክ ብቻ አይደለም የሁላችንንም መድረክ ይፈትሻል፡፡say Amen እያሉ አሜን አላላችሁም የምንል ሰባኪዎች ብዙ ነን፡፡የምንሰብከው ምሁሐራንን ብቻ ሰብስበን አይደለምና ኢየሱስ በሚገባን ቋንቋ እንደመጣ የምንሰብካቸውን ሰዎች በሚገባቸው ቋንቋ እንስበካቸው፡፡ያኔ እማማም አባባም ይረዱናል፡፡

03/05/2019

አቤቱ ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ!!!!

03/05/2019

ችንካሩማ እኔው ነኝ!
***
"ልደቱ ጨለማውን አስደንግጧል። ሕይወቱ አጠያይቋል፤ ትምህርቱ አወዛግቧል። በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ በኀጢአት ላይ የተመሠረተው የሰው አገዛዝ በዚህ ብርሃን መጋለጡ የሚጠበቅ ነበር። የመንግሥተ እግዚአብሔር መገለጥ በክርስቶስ ማንነትና ትምህርት በኩል ወደ ዓለም ሲገባ የጨለማው ሥልጣን መንኰታኰቱ አልቀረለትም። ፍትሕና ጽድቅ በተጓደለበት የአዳም ሥርዐት ላይ ብርክ የሚያዘንብ የታሪክ ባለቤትና ጌታ በተሠገዎ ብርሃን ሲገለጥ ክፉው እንዴት አይደናገጥ?

እንጂማ፥ እርሱ የማንንም ሕይወት አልጐዳም ነበር፤ በዘረፋና ምርኮ አልተሳተፈም፤ ሥዒረ-መንግሥት አላካኼደም፤ ለድኾች ወዳጅ፥ ማኅበራዊ ስብራት ወደ ጠርዝ ለገፋቸው ምንዱባን ጓደኛቸው ነበር። እረኛ እንደሌለው መንጋ ለተበተኑት ሕዝብ በርኅራኄ ያዝናል። የተራቡትን መግቧል። የተጠቁትን ነጻ አውጥቷል። የታሰሩትን ፈትቶ፥ የተበተኑትን ሰብስቧል (ሉቃ. 4፥17-19)። “ኹሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል” (ማር 7፥37)።

ሰው ግን ውለታውን የከፈለው በተገላቢጦሽ ኾነ። ኹሉን የያዘና የሰውን ሕይወት እርቃን በጸጋው የሚሸፍን የሕይወት ራስ ሰውን ፍለጋ በመጣ ጊዜ ዓለም ለእርሱ ቦታ አልነበራትም። ሕይወታችንን በሚመስል ምጸት ዓለም ለኢየሱስ ያቀረበችለት ቦታ በረትና ግርግም ብቻ ነበር (ሉቃ. 2፥7፡ 12፡ 16)፤ ያውም የተውሶ ግርግም። ለማስተማር ታንኳ ተውሶ ነበር (ሉቃ. 5፥3)፤ ንጉሣዊ አገባቡን የሚያረጋግጠው የኢየሩሳሌም ጕዞው በተውሶ አህያ ጀርባ ላይ በመቀመጥ ኾነ (ማቴ 22፥ 1-16)። የመጨረሻውን የፋሲካ ራት በተውሶ ቤት አበላ (ሉቃ. 22፥7-12)። በመጨረሻም የሰው ልጅ ለመሲሑ ያዘጋጀው “ከፍታ” የመስቀል እንጨት ኾነ፤ በዘረጋው የፍቅር እጁ ላይም ችንካር አኖረበት። ንፉጉ ዓለም፥ ክፉውም የሰው ልብ የእግዚአብሔርን መሲሕ በጭካኔ ሰቀለ። ሊቤዠው የወረደለትና የተዋረደለትን መሲሕ በክፋት ገደለ፤ ቀበረም። የተቀበረውም በተውሶ መቃብር ነበረ (ማቴ. 27፥60)።" ("የተቈረሱ ነፍሶች"፥ 236-7) አያችሁ፤ የዚያ ዘመን ሕዝብ ንቅል ብሎ ወጥቶ መድኅኑን በመንጋ ገደለ፤ ሰቀለ።

ያንን መሲሕ ገዳይ መንጋ የትውልድ ተራ ተርታችንን ጠብቀን በታሪክም በትምህርትም ስንወቅሰው፥ በምሳሌና በፈሊጥም ስንቀጠቅጠው ኖረናል። በርግጥ ሲወቀስና ሲነቀፍ መኖሩ ገና ይቀጥላል። ነገር ግን፥ እኔ በመካከላቸው ኖሬ ብኾን ምን አደርግ ነበር? ከሰቃዮቹ ወይም ከአሠቃዮቹ ላለመኾኔ ማረጋገጫ የሚኾነኝ ቅንጣት ምስክር አላገኝም። የተጣራና የተረጋገጠ ማስረጃ ግን አለኝ። መሲሑ ኢየሱስን የሰቀለው የኔ ኀጢአት ነው። "እርሱ ስለመተላለፋችን ተወጋ፤ ስለበደላችንም ደቀቀ" (ኢሳ. 53፥5ዐመት) አልተባለምን? አያችሁ፤ ችንካሩ እኔው ነበርሁ። በደሌ ነበር ያደቀቀው። ጌታዬ ከላይ መጥቶ በመስቀል ላይ የተሰበረው ለእኔ ኀጢአት ሲኾን፥ የሰበርሁት እኔው ነበርሁ። አንተና አንቺ ናችሁ ብዬም እገምታለሁ። የእኔ ግን ርግጥ ነው፤ ችንካሩ እኔው ነኝ:::

03/05/2019

ችንካሩማ እኔው ነኝ!
***
"ልደቱ ጨለማውን አስደንግጧል። ሕይወቱ አጠያይቋል፤ ትምህርቱ አወዛግቧል። በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ በኀጢአት ላይ የተመሠረተው የሰው አገዛዝ በዚህ ብርሃን መጋለጡ የሚጠበቅ ነበር። የመንግሥተ እግዚአብሔር መገለጥ በክርስቶስ ማንነትና ትምህርት በኩል ወደ ዓለም ሲገባ የጨለማው ሥልጣን መንኰታኰቱ አልቀረለትም። ፍትሕና ጽድቅ በተጓደለበት የአዳም ሥርዐት ላይ ብርክ የሚያዘንብ የታሪክ ባለቤትና ጌታ በተሠገዎ ብርሃን ሲገለጥ ክፉው እንዴት አይደናገጥ?

እንጂማ፥ እርሱ የማንንም ሕይወት አልጐዳም ነበር፤ በዘረፋና ምርኮ አልተሳተፈም፤ ሥዒረ-መንግሥት አላካኼደም፤ ለድኾች ወዳጅ፥ ማኅበራዊ ስብራት ወደ ጠርዝ ለገፋቸው ምንዱባን ጓደኛቸው ነበር። እረኛ እንደሌለው መንጋ ለተበተኑት ሕዝብ በርኅራኄ ያዝናል። የተራቡትን መግቧል። የተጠቁትን ነጻ አውጥቷል። የታሰሩትን ፈትቶ፥ የተበተኑትን ሰብስቧል (ሉቃ. 4፥17-19)። “ኹሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል” (ማር 7፥37)።

ሰው ግን ውለታውን የከፈለው በተገላቢጦሽ ኾነ። ኹሉን የያዘና የሰውን ሕይወት እርቃን በጸጋው የሚሸፍን የሕይወት ራስ ሰውን ፍለጋ በመጣ ጊዜ ዓለም ለእርሱ ቦታ አልነበራትም። ሕይወታችንን በሚመስል ምጸት ዓለም ለኢየሱስ ያቀረበችለት ቦታ በረትና ግርግም ብቻ ነበር (ሉቃ. 2፥7፡ 12፡ 16)፤ ያውም የተውሶ ግርግም። ለማስተማር ታንኳ ተውሶ ነበር (ሉቃ. 5፥3)፤ ንጉሣዊ አገባቡን የሚያረጋግጠው የኢየሩሳሌም ጕዞው በተውሶ አህያ ጀርባ ላይ በመቀመጥ ኾነ (ማቴ 22፥ 1-16)። የመጨረሻውን የፋሲካ ራት በተውሶ ቤት አበላ (ሉቃ. 22፥7-12)። በመጨረሻም የሰው ልጅ ለመሲሑ ያዘጋጀው “ከፍታ” የመስቀል እንጨት ኾነ፤ በዘረጋው የፍቅር እጁ ላይም ችንካር አኖረበት። ንፉጉ ዓለም፥ ክፉውም የሰው ልብ የእግዚአብሔርን መሲሕ በጭካኔ ሰቀለ። ሊቤዠው የወረደለትና የተዋረደለትን መሲሕ በክፋት ገደለ፤ ቀበረም። የተቀበረውም በተውሶ መቃብር ነበረ (ማቴ. 27፥60)።" ("የተቈረሱ ነፍሶች"፥ 236-7) አያችሁ፤ የዚያ ዘመን ሕዝብ ንቅል ብሎ ወጥቶ መድኅኑን በመንጋ ገደለ፤ ሰቀለ።

ያንን መሲሕ ገዳይ መንጋ የትውልድ ተራ ተርታችንን ጠብቀን በታሪክም በትምህርትም ስንወቅሰው፥ በምሳሌና በፈሊጥም ስንቀጠቅጠው ኖረናል። በርግጥ ሲወቀስና ሲነቀፍ መኖሩ ገና ይቀጥላል። ነገር ግን፥ እኔ በመካከላቸው ኖሬ ብኾን ምን አደርግ ነበር? ከሰቃዮቹ ወይም ከአሠቃዮቹ ላለመኾኔ ማረጋገጫ የሚኾነኝ ቅንጣት ምስክር አላገኝም። የተጣራና የተረጋገጠ ማስረጃ ግን አለኝ። መሲሑ ኢየሱስን የሰቀለው የኔ ኀጢአት ነው። "እርሱ ስለመተላለፋችን ተወጋ፤ ስለበደላችንም ደቀቀ" (ኢሳ. 53፥5ዐመት) አልተባለምን? አያችሁ፤ ችንካሩ እኔው ነበርሁ። በደሌ ነበር ያደቀቀው። ጌታዬ ከላይ መጥቶ በመስቀል ላይ የተሰበረው ለእኔ ኀጢአት ሲኾን፥ የሰበርሁት እኔው ነበርሁ። አንተና አንቺ ናችሁ ብዬም እገምታለሁ። የእኔ ግን ርግጥ ነው፤ ችንካሩ እኔው ነኝ።

07/04/2019

ከላይ የቀጠለ.......

በዕብራውያን 11:1-3 ውስጥ የሚገኙ ሦስት ቃላት እውነተኛ የመፅሐፍ ቅዱስ እምነት ምን እንደሆነ ጠቅለል ያለ አሳብ ይሰጡናል። እነዚህም ማስረገጥ (Substance)ማስረዳት (Evidence)እና መመስከር(Witness) ናቸው። በዚህ ክፍል" ማስረገጥ" ተብሎ የተተረጎመው ቃል በቁሙ "ምርኩዝ መሆን መደገፍ "ማለት ነው። እምነት ለክርስቲያን እንደ ቤት መሰረት ነው። በመሆኑም የሚቆምበትን መተማመኛና እርግጠኝነት ይሰጠዋል። ስለሆነም "እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ .....ነው"ማለት ይቻላል። እምነት እግዚአብሔር የገባውን ተስፋ እውን እንደሚያደርግ የምናስረግጥበት መንገድ ነው።

ማስረዳት ማለት ግንዛቤንና መረዳትን ያመለክታል። ይህም አንድ ሰው እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠውን ነገር እንደሚያገኝ ውስጣዊ መረዳትን የሚያገኝበት መንገድ ነው። በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ከእግዚአብሔር የተሰጠ እምነት መኖሩ እግዚአብሔር ቃሉን እንደሚጠብቅ ለማስገንዘብ በቂ ነው።

ምስክር (ኬጂቪ በተባለው የእንግሊዘኛ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ "መልካም ሪፖርት ያገኙት" በዚህ ምእራፍ ውስጥ አስፈላጊ ቃል ነው። ይህ ቃል ቁጥር 2 ብቻ ሳይሆን ቁጥር 4ትም ሁለትጊዜ ተገልጦዋል። በዕብራውያን12:1 የሚገኛው ማጠቃለያ ይህንኑየእምነት ስዎች ዝርዝር" እነዚህንም የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙርያችን ካሉልን" ሲል ገልጾአል። እግዚአብሔር ለእለሱ ሰለመሰከረ እነርሱ ለእኛ ምስክሮች ናቸው። እግዚአብሔር ለተጠቀሱት ሰዎች ሁሉ መስክሮላቸዋል። ይህም ምስክርነት ሕይወታቸውና አገልግሎታቸው መለኮታዊ ተቀባይነት እንዳገኘ ዋስትና የሚሰጣቸው ነው።

በማያምኑ ሰዎች ስለ እምነት ምንም ዓይነት ነገር ይናገሩ እምነት ተግባራዊ ነገር መሆኑን የዕብራውያን ፅሐፊ በግልፅ ጽፎታል(ቁ3)። እምነት እግዚአብሔር የሚሰራውን ለመረዳትና የማያምኑትን ሊያዩ የማይችሉትን ማየት እንድንችል ያደርገናል። ከዚህ የተነሳ እምነት የማያምኑ ሰዎች ሊያደርጓቸው የማይችሉዋቸውን ነገሮች እንድናደርግ ያስችለናል። እነዚህ የእምነት ሰዎች በእምነት ተግባራዊ እርምጃዎችን በወሰዱባቸው ጊዚያት ሰዎች ተሳልቀውባቸዋል። እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ ጋር ስለነበረ ለክብሩ ታላላቅ ድሎች እንዲቀዳጁ እረድቷቸዋል። እምነት የምታምን ነፍስ የወደፊቱን እንደ አሁን ጊዜ የማይታየውን እንደሚታይ አድርጋ እንድትወስድ ያደርጋታል።

ተባረኩ ወንድሞች እሕቶች..

ይቀጥላል.........

07/04/2019

እምነት ምንድን ነው? ዕብ 11:1-3

ይህ እምነት ምን እንደሆነ ለማብራራት የተሰጠ ትርጉም እምነት ምንን እንደሚያደርግና እንዴት እንደሚሰራ የሚያመለክት ገለፃ ነው። እውነተኛ መፅሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ጭፍን የሆነ ተምኔት ወይም እራሳችን የምንፈጥረው "ተስፋ አደርጋለሁ" አይነት ስሜት አይደለም። በተጨማሪም እምነት አስተምሮን በአእምሮ የመቀበል እሽታ አይደለም። ደግሞም እምነት ከማስረጃ ውጭ ማመን አይደለም! ይህ እምነት ሳይሆን አጉል አምልኮ ነው።

እውነተኛ መፅሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ከሁኔታዋችና ከውጤቶቻቸው ባሻገር ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ የሚገኛው ሀሳብ እንደገና በማንበብ በአእምሮአችሁና በልባችሁ ውስጥ እንዲሰርፅ አድርጉ።

ይህ እምነት የሚመሰረተው በቀላሉና ባልተወሰነ መንገድ ነው። እግዚአብሔር ሲናገር ድምፁን እንሰማዋለን። ሁኔታዎቻቸውና ውጤታቸው ምንም አይነት ይዞታ ይኑራቸው ይኑራቸው ቃሉን አምነን ተግባራዊ እናደርጋለን። ሁኔታዎች የማይሞክሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ተግባራችን የሚያስከትሉት መዘዞች እጅግ አስፈሪዋች ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል በማመን እርሱ ትክክለኛውና ከሁሉም የሚሻለውን እንደሚያደርግ እንተማመናለን።

ምን አልባትም ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙም እምነት ተግባራዊ ሲሆን ባለመመልከቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ያልዳነው አለም እውነተኛውን የመፅሐፍ ቅዱሳዊ እምነት አይገነዘቡም። በእግዚአብሔር ሕልውና የማያምነው ተጠራጣሪው ኤዲተር ወይም አርታኢ ኤች.ኤል.ሜንኪን እምነት "ሊሆን የማይችል ነገር ይሆናል ብሎ በጭፍኑ ማመን" እንደሆነ አድርጎ ገሎጾል። አለማመን የእምነት ዋጋ የሚለካው እምነቱ ባረፈበት አካል እንደሆነና የእምነታችንም ማረፌያ እግዚአብሔር እራሱ እንደሆነ መገንዘብ ይሳናቸዋል። እምነት እኛ እንዳሻን የመረጥነው የሆነ ስሜት ሳይሆን እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ለገለፀው ሐሳብ የምንሰጠው አጠቃላይ ምላሻችን ነው።

ይቀጥላል.........

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Addis Ababa