18/01/2025
በቅርብ እንመለሳለን!
ከብዙ መቋረጥ በኋላ!
በሚከተሉት ጉዳዮች!
"Practical Challenges"
"How to overcome them?"
👉 what are the major challenges in obtaining finance with interest free scheme in Ethiopia?
👉what are the major challenges for the smooth operation of interest free banking in Ethiopia?
Coming Back Soon!
Challenges of Interest Free Banking and Finance
15/04/2023
ስለ (Online Financial Dealings) የኢስላሚክ ባንኪንግ ሸሪዓ ስታንዳረድ ብይኖች፡፡
(የኢስላሚክ ባንኪንግ ሸሪዓ ስታንዳረድ (38) )
⭐⭐⭐
በአለም አቀፉ የኢስላሚክ ፋይናንስ የአካዉነቲነግ እና ኦዲት ድርጅት (AAOIFI ) ያዘጋጀውን የኢስላሚክ ባንኪንግ ሸሪዓ ስታንዳረድ ቁጥር 38 ስለ የመስመር ላይ የፋይናንሺያል ስምምነቶች ይመለከታል፡፡
በመስመር ላይ የፋይናንሺያል ግብይቶች ላይ ያለው የሸሪዓ ውሳኔዎች በ AAOIFI በተዘጋጁት እስላማዊ የፋይናንስ ተቋማት በሸሪዓ መስፈርት ላይ በዝርዝር ተቀምጧል። ይህ ስታንዳርድ የመስመር ላይ የፋይናንስ ኮንትራቶችን ማለትም የንግድ ድረ-ገጾችን በመክፈትእና የመስመር ላይ አገልግሎት አቅርቦትን በተመለከተ የሸሪዓ የተላለፉትን የሸሪዓ ውሳኔዎችን እና ተያያዥ ጉዳዮች ማለትም ውል የሚጀመርበትን ጊዜ መወሰን፣ ውሉ ከተፈራረሙ በኋላ የሚኖረው የንብረቱ የባለቤትነት ሁኔታ እና የመስመር ላይ የፋይናንሻል ግብይቶች ስምምነት ጥበቃ ያካትታል/ይሸፍናል።
በመሆኑም በሸሪዓው ስታንዳረድ መሰረት የሚከተሉት የመስመር ላይ ፋይናንሺያል ስምምነቶች #የተፈቀዱ ናቸው፡-
1) ለኮንትራት ስምምነቶች መክፈት እና እና የመስመር ላይ ኮንትራቶችን ማከናወን፣
2) ለተጠቃሚዎች በማቅረብ የደንበኝነት ምዝገባ፥ ውል ወይም ሌላ ማንኛውንም ተመሳሳይ ተግባራትን ክፍያ መሰረት በማድረግ ማቅረብ::
እነዚህ ለንግድ ተብለው የተከፈቱ የንግድ ድረ-ገጾችን በሸሪዓው ያልተፈቀዱ ተግባራት ማከናወን ግን የለባቸውም፡፡ ለምሳሌ የማይፈቀዱ እቃዎች እና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ ወይም የተፈቀደ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ የማይፈቀዱ መንገዶችን መጠቀምን የመሳሰሉ ማንኛውንም የማይፈቀድ ድርጊት መፈጠም የለባቸውም።
በተጨማሪም በተቋሙ እና በደንበኞቹ መካከል የሚደረጉ የኦንላይን ኮንትራቶች በሸሪዓ የተደነገጉትን የፋይናንስ ግብይቶች አጠቃላይ ህጎችን ማክበር አለባቸው ፣ ለምሳሌ የሂሳብ መክፈት ፣ ገንዘብ ማስተላለፍ እና የንግድ ውሎችን መፈረም ።
ከዚህ ባለፈም የመስመር ላይ አገልግሎትን የሚሰጠው ተቋም ደንበኞች ኢንተርኔትን ያለአግባብ መጠቀምን ለመከላከል አስፈላጊውን የጥንቃቄና እርምጃ ሊወስድ ይገባል።
🌠🌠🌠
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
https://moonlight-ibf.blogspot.com/
05/02/2022
በኢስላሚክ ፋይናንስ እና ባንኪንግ ውስጥ የገንዘብ💵የጊዜ 🕑ዋጋ ጽንሰ-ሀሳብ
🌠🌠🌠
በኢስላማክ ፋይናንስ ውስጥ ስለ ገንዘብ የጊዜ ዋጋ ጽንሰ-ሀሳብ የለም:: እናም በኢስላክ ፋይናንስ በማንኛውም አይነት ሪስኬጁል የተደረገ ብድር የገንዘብ የግዜ ዋጋ እውቅና አይሰጥም፡፡
አንድ ጊዜ የሽያጩ ሂደት በተዋዋይ ወገኖች መካከል ስምምነት ላይ ከተደረሰ በመዘግየቱ ምክንያት በዚህ ዋጋ ላይ ተጨማሪ ገንዘብ መጨመር የተከለከለ እና ሀራም ነው።
ይህ የሆነበት ምክንያት፣ እቃው አንዴ ከተሸጠ (በዱቤ እንኳን ቢሆንም)፣ እቃው ንብረትነቱ የገዢው ነው፣
እናም ሻጩ የዕቃውን ዋጋ እንደገና የመወሰን መብት የለውም። በዋጋው ላይ ያለ ማንኛውም ጭማሪ እንደ ሪባ ወይም ወለድ ይቆጠራል።
ሆኖም፣ ይህ ጽንሰ-ሀሳብ ከአንዳንድ ትክክለኛ የእስላሚክ ፋይናንስ ዘዴዎች ጋር መቀላቀል የለበትም። ለምሳሌ:
፡- ውል ላይ እንደሚታየው እቃ ገዝቶ በሚሸጥበት ግዜ ከመጀመሪያው ግብይት ዋጋው ላይ ትርፍ ተጨምሮበት ለገዢው ወደ ፊት በተላለፈ ክፍያ እንዲከፍል ይሸጥለታል፡፡
፡- ወደፊት ለሚረከቡት እቃ በቅድሚ ክፍያን የሚፈፀምበት ሂደት ነው፡፡
07/11/2021
Shari’ah Standard (3): Procrastinating Debtor (Revised)
The purpose of this standard is to explain the Shariah rulings applicable to the transactions of Islamic financial Institutions relating to solvent ..
06/10/2021
የሸሪዓህ_ስታነዳርደ_ቁጥር_5 - #ዋስትናዎች
ክፍል 2
/ #ምስክርነት
ስምምነቶች በጽሑፍ ሰነዶች ማስደገፍ በሸሪዓ ይመከራል። ይህ የአብዛኛው የፉቃሃ/ Fuqaha አስተያየት ነው:: አብዛኛዎቹ ፉቃሃዎች እንዲሁ በመተማመን ላይ የተመሰረተ ስምምነቶች ግን የፅሁፍ ሰነድ/ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ እንዳልሆነ ያምናሉ፡፡
የጽሑፍ ሰነዶች ቅፅ እና ማስረጃ አስፈላጊነት ለመወሰን በተለምዶ የምናደርጋቸው ኩነቶች መሠረት መሆኑን እንዳለበት ልብ ሊባል ይገባል ፣ ምክንያቱም ሸሪዓ ተቀባነት ያለው ወጥ የጽሁፍ ማስረጃዎችን የሚቀርቡበት ዘዴ እንዲኖር አልገለጸም።
በባህላዊው ፉቃሃ መሠረት የማረጋገጫ/የምስክርነት ማስረጃ ከጽሑፍ ሰነዶች የበለጠ ጠንካራ ነው። ነገር ግን በዘመናችን አንዳንድ ሕጎች በጣም ውስን በሆኑ ጉዳዮች ላይ በምስክሮች ላይ ብቻ ሲመሰረቱ ባብዛኛው ህጎች ግን ከፍተኛውን ተቀሜታ ለጽሑፍ ሰነድ ማስረጃዎች ተሰጥቷል።
4.1. የፅሁፍ ሰነዶች (ገላዊም ወይም ኦፊሴላዊ) በሸሪዓ ይመከራል። ሆኖም እንደዚህ ያሉ ሰነዶችን በመቅረጽ እና እንደ ማስረጃ መጠቀም ሂደቱ ግን ያካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡
4.2. በፋይናነስ ሰነዶች ላይ የምስክርነት ማረጋገጫ እንዲኖር ማድረግ በሸሪዓ ይመከራል። እንዲሁም የሚያስመሰግን ነው ፣ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ምስክርነት መስጠት ግዴታ ነው። በሌላ በኩል በሐሰት መመስከር የተከለከለ ሲሆን ከዋና ዋና ኃጢአቶች አንዱ ነው።
4.3. በሸሪዓ የተከለከሉ ድርጊቶችን ላይ ምስክርነት መስጠት የተከለከለ ነው፡፡ ለምሳሌ በወለድ ላይ የተመሰረተ ብድር ላይ ምስክር መሆን ወይንም ማረጋገጥ በሸሪአህ የተከለከለ ነው፡፡
🌠🌠🌠
For more, please visit: https://moonlight-ibf.blogspot.com/2021/10/shariah-standard-5-guarantee-revised.html
30/09/2021
አለም አቀፍ ኢስላሚክ ባንክ
- #ዋስትናዎች 🏠🚙
🌠🌠🌠
ይህ ሰታነዳርድ ሰፊ በመሆኑ በተለያዩ ክፍሎች እናቀርበዋለን፡፡
ክፍል ❶
►►◄◄
A) በዋስትናዎች ላይ የተሰጡ አጠቃላይ
1. የተፈቀዱ ዋስትናዎች እና ለኮንትራክቶች ያላቸው ጠቀሜታ
➖➖➖
1.1. የኮንትራት ዋስትናዎች እንደ የግብይት ውሎች (ለምሳሌ የሽያጭ ውሎች) ወይንም የመብቶች ውል (ለምሳሌ የአዕምሯዊ ንብረት መብት ዉሎች) የተፈቀዱ ናቸው። ምክንያቱም አንደዚህ ያሉ የኮነትራት/ውል ዋስትናዎች የኦርጅናል/ የመጀመሪያው ዉሎች ተፈቃጅነት/ permissibility አይለዉጡትም፡፡ በተጨማሪም ዋስትና በኦሪጅናል ኮንትራት አካል አድርጎ ማካተትም ቢሆን ይፈቀዳል ምክንያቱም ዋስትና በኮትራቶች ማካተት አስፈላጊና ትክክል ነው፡፡
1.2. በአንድ ውል ውስጥ በርካታ ዋስትናዎችን ማካተት በሸሪዓ የተከለከለ አይደለም፣ ለምሳሌ በአንድ ውል ውስጥ የግል ዋስትና ከብድር መያዣ ጋር አብሮ ማካተት።
2. ዋስትናዎች አደራን (እምነትን) መሰረት ላደረጉ ኮንትራቶች/ዉሎች
➖➖➖
2.1. አደራን (ታማኝነትን) መሰረት አድርገው የሚከወኑ ኮንትራቶች የንብረት ወይንም የሰው ዋስትና መጠየቅ በሸሪዓ #የተከለከለ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ዋስትናዎች የታማኝነት ተፈጥሮአዊ ሁኔታ የሚቃረኑ ናቸው (ቸልተኝነትን ፣ በስነ ምግባር ጉድለት፣ ደንቦችን እና ድንጋጌዎች በመጣስ ለሚከሰቱ ችግሮች ታስቦ የሚደረግ ካልሆነ በስተቀር)።
መተማመን መሰረት ተደረጎ በሚከወኑ ኮንትራቶች ላይ ዋስትና መጠየቅ ክልከላው የበለጠ ጥብቅ የሚሆነው በበሙዳራባህ እና በሙሻራካህ ውሎች ላይ ነው። ምክንያቱም ከአንድ የበሙዳራባህ ወይም በሙሻራካህ ማናጀር ወይንም የኢንቨስትመንት ተወካይ ወይንም አጋር ከሆነ አካል የካፒታል ዋስትና ወይንም ዋስትና ያለው ትርፍ መጠየቅ የተከለከለ ነው፡፡
2.2. የኤጀንሲ እና የግል ዋስትናዎች በተመሳሳይ ግዜ በአንድ ኮነትራት/ዉል ጥምረት አይፈቀድም፡፡ (ማለትም አንድ አካል በአንድ በኩል እንደ ተዎካይ በሌላ በኩል እንደ ዋስትና ሰጭ መሆን የተከለከለ ነው)፤ ምክንያቱም እንደህ አይነት ጥምረት ከውክልናዎች ተፈጥሮ ጋር ይጋጫል፡፡
በተጨማሪም፡ የኢንቨስትመንት ወኪል በሆነ አካል የተሰጠ ዋስትና ግብይቱን ወደ ወለድ ላይ የተመሰረተ ግብይትነት ይለወጣል፡፡ ምክንያቱም ከኢንቨስትመንት ካፒታሉ በተጨማሪ ከኢንቨስትመንቱ የሚገኘው ገቢ ዋስትና ተገብቶለታል፡፡ ማለትም የየኢንቨስትመንት ወኪሉ ብድር እንደወሰደና ከወሰደው ተጨማሪ እንደከፈለ እናም ይሄ ወለድ/ሪባ ጋር እኩል እንደሆነ)
ነገር ግን ዋስትናው በኤጀንሲው ውል ውስጥ ካልተገለጸ እና ወኪሉ ከውክልና ውል ውጭ በሆነ ሁኔታ ለደንበኛው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ዋስትና ከሰጠ ፣ በዚህ ግዜ ከወኪሉ ከተወካይነቱ ማንነት በተለየ ሁኔታ ዋስትና ሰጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ግዜ ምንም እንኳን የተወካይነቱ ዉል ቢቋረጥም ዋስትና በሰጠበት ጉዳይ ላይ ግን ተጠያቂ ሆኖ ይቆያል፡፡
3. ነባር የተከራዩ ንብረቶችን ዋስትና መስጠት
➖➖➖
አከራዩ ከተከራየው ንብረት ጋር ተያይዞ ያለውን ሪስክ ሃላፊነት ሲወስድ ተከራዩ ደግሞ የተከራየውን ንብረት በአደራ ይይዛል። ስለሆነም አከራዩ ባከራየው ንብረት ላይ ለሚደርሰውን ብልሽት ወጭ ለማካከስ በማሰብ በኪራይ ውሉ ውስጥ ዋስትና ውል ወይም የሞርጌጅ ዋስትና ወዘተ ማካተት ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ድንጋጌ ሥነ ምግባር ጉድለት ፣ ቸልተኝነት ወይም የውል መጣስ ጉዳዮች ላይ ካልተገደበ በስተቀር።
ስለዚህ አከራዩ በተከራዩ ሥነ ምግባር ጉድለት ፣ ቸልተኝነት ወይም የውል መጣስ ከሚከሰቱ ጉዳቶች ውጭ ባከራየው ንብረት ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳቶች እና ማንኛውም ተያያዥ የኢንሹራንስ ክፍያዎች ሃላፊነት ይወስዳል፡፡ በተጨማሪም አከራዩ ያከራየዉን ንብረት ለተከራዩ በኪራይ ውሉ መሠረት በቂ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችለው ሁኔታ ውስጥ ለማቆየት የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ወሳኝ ጥገና ሥራ ለማድረግ የሚያስፈልገው ወጪ ይሸፍናል።
➖➖➖
ክፍል 2 ይቀጥላል ...
04/05/2021
(ቁጥር 3) ፡ የመክፈል አቅም እያለው እዳውን የማይከፍል/የሚያዘገይ ተበዳሪ/ Procrastinating Debtor/
ተበዳሪ ዕዳውን መክፈል እየቻለ እዳው በሚከፈልበት ቀን ወይንም ከዚያ በኋላ ዕዳውን ለመክፈል ፈቃደኛ ያልሆነ፡፡ አበዳሪው የብድር መከፈያውን ግዜ ለተበዳሪው ካሳወቀ በኋላ ተበዳሪው ያለምንም በቂ ምክንያት ክፍያውን ለሌላ ጊዜ የሚያስተላልፍ ማለት ነው፡፡ በሸሪዓው መሠረት ተበዳሪዎች ዕዳቸውን በተቀመተው ቀንነ ገደብ ውስጥ መክፈል አለባቸው፡፡ ዕዳውን መክፈል እየቻለ አለመክፈል ወይንም ማዘግየት በሸሪዓ መሰረት ክልክል/ሀራም ነው፡፡ አበዳሪው የዘገየ ዕዳ ዕዳውን ለማስመለስ ለሚከፈለው የሕግ ወጪዎች ካለ ተበዳሪው ተጠያቂ ነው።
የዚህ ስታንዳረድ/መመዘኛ ዓላማው የኢስላሚክ የገንዘብ ተቋማት መክፈል እየቻሉ ለማይከፍሉት ወይንም ለሚያዘገዩት ተበዳሪዎች እና ወይንም ዋስትና አቅራቢዎች ጋር ብድራቸውን ለማስመለስ ለሚያከናውኑት ሂደቶች እና በህም ሳቢያ በስምምነቶች ውስጥ ያሉ የቅጣት ክፍያዎች በተመለከት የተሰጡ የሸሪአህ ብይኖች ገለጻ ለማድረግ ነው፡፡
1. የመክፈል አቅም እያላቸው ዕዳን በማይከፍሉ/በሚያራዝሙ ላይ የተሰጠ የሸሪዓ ውሳኔ
1.1. /
1.1.1. ዕዳውን መክፈል እየቻለ አለመክፈል/ማራዘም የተከለከለ/ራም ነው።
1.1.2. አበዳሪው ብድሩን በማይከፍል ወይንም በሚያራዝም ተበዳሪ ላይ የፋይናነስ ማካካሻ (በገንዘብ ወይንም በሌላ ነገር ሊሆን ይችላል) የቅጣት አንቀጽ (ቀድሞ የተወሰነ የገንዘብ መጠን ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል) ማስቀመጥ የተከለከለ ነው፡፡ ማካካሻው በእዳ ክፍያ መዘግየት ምክንያት የሚከሰት የገቢ ኪሳራ ወይንም በገንዘብ ምንዛሪ ለውጥ ምክንያት የሚመጣ ኪሳራንም ያካትታል ፡፡
1.1.3. ብድሩን ባዘገየ ተበዳሪ ላይ የገንዘብ/ፋይናንሻል ካሳ (በጥሬ ገንዘብ ወይንም በሌላ) እንዲከፍል ጉዳዩ ወደ ህግ ስዶ ክስ መመስረት የተከለከለ ነው፡፡
1.1.4. የዘገየ ዕዳውን ለማስመለስ አበዳሪው ለሚፈጽማቸው ሕጋዊ እና ሌሎች ወጪዎች ተበዳሪው ተጠያቂ ነው።
1.1.5. አበዳሪው ለእዳ ማስያዣነት የዋለው ማንኛውንም ንብረት መሸጥና ዕዳውን ለእዳው ክፍያነት የማዋል ሙሉ መብት አለው፡፡ ባለዕዳውም በብድር ማስያዣነት የሰጠው ንብረት ለአበዳሪው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመሸጥ መብት መስጠት አለበት ፡፡
1.1.6. ከአቅም በላይ የሆነ ችግር አጋጥሞት ካልሆነ በስተቀር፣ ተበዳሪው ኢነስቶልመንቱን ካልከፈለ በቀሪ እዳው በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ የተፈቀደ ነው፡፡ ይህ አንቀጽ ተግባራዊ መሆን ያለበት ተበዳሪው እንዲያውቅ ከተደረገና በቂ ግዜ ገደብ ከተሰጠው በኋላ ብቻ ቢሆን ተመራጭ ነው፡፡ [የሸሪአህ ስታንዳርድ ቁጥር (5)፡ ስለ ዋስትናዎች (ቁጥር 5/1) ይመልከቱ]
1.1.7. የሙራባሀ ሽያጭ በተመለከተ የተሸጠው ንብረት በተሸጠበት ሁኔታ ካለ እና ገዢው ክፍያው ካቋረጠ እናም ኪሳራ ውስጥ ከገባ፣ ሻጩ (ተቋሙ) መመሪያን ተከትሎ የኪሳራ አተገባበር ሂደት ከመጀመር ይልቅ ንብረቱን መልሶ የማግኘት መብት አለው፡፡
1.1.8. ዕዳን በሚመለከቱ ውሎች (ለምሳሌ ሙራባሀህ) ተበዳሪው ብድሩን መክፈል እየቻለ ብድር ክፍያውን በሚያዘገይበት ግዜ የተወሰነ የገንዘብ መጠን ወይንም የእዳውን መጠን በመቶኛ ተሰልቶ በተቃሙ በኩል ለበጎ አድራጎት ማህበራት እንዲሰጥ ውል ማስገባት የተፈቀደ ነው
1.2. #ዋስትና
ሀ) ዋስትና ሰጪው ዕዳውን ማስምለስ ሂደት በመጀመሪያ ከባለዕዳው እንዲሆን ካልተደነነገ በስተቀር አበዳሪው እዳውን በተበዳሪው ወይንም በዋስትና ሰጪው በኩል እንዲከፈለው መጠየቅ ይችላል፡፡
ለ) ሁሉንም በተበዳሪዎች ላይ ተፈፃሚ የሆኑት የሸሪዓህ ውሳኔዎች በሙሉ በዋስትና ሰጪዎች ላይም ተፈጻሚ ይሆናሉ ፡፡
1.3.
ለግንባታ ፣ ለኢስቲሳና እና ለአቅርቦት ኮንትራቶች ውል ውስጥ የቅጣት አንቀጾችን ማካተት ይፈቀዳል ፡፡ በቅጣት አንቀፅ መሠረት የሚከፈለውን መጠን ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆን፣ በተበዳሪው የሚመለከቱት የቅጣት ውሳኔዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ ፡፡ ቅጣቱም ከተቋራጩ ቀሪ ሂሳብ ላይ ለመቁረጥ ይፈቀዳል ፡፡
1.4.
ተቋሙ በችግር ባለባቸው ደንበኞች ስም ዝርዝር (በጥቁር መዝገብ) ውስጥ የባለ እዳው ስም የማካተት እና ለሌሎች የፋይናንስ ተቋማትም እንዲሁም ለሌሎች ኩባንያዎች (ጥያቄ በሚቀርብበት ጊዜ ሊሆን ይችላል) የማሳወቅና የማስጠንቀቂያ ምክር የመላክ መብት አለው ፡፡
1.5.
1.5.1. ተቋሙ እዳውን መክፈል እየቻለ በማይከፈለ ወይንም ባዘገየ ተበዳሪ ላይ የተበዳሪው የሂሳብ ሁኔታ እና እንቅስቃሴ በተፈቀደና ሕጋዊ በሆነ መንገዶች ሁሉ የመቆጣጠር እና የመመርመር መብት አለው።
1.5.2. በጽሑፍም ሆነ በቃል ፣ ወይም ከዚህ ተጨማሪ መጠን ጋር የሚገናኝ የጋራ ስምምነት ከሌለ ፣ ተቋሙ በእዳ ካለበት መጠን በላይ የሆነ ክፍያ ከተበዳሪው ሊቀበል ይችላል።
1.6. አንድ ተበዳሪ ብድሩ የማይመልስ/የሚያዘገይ ነው ብሎ ማለት
አንድ ተበዳሪ ብድሩን መመለስ አቁሟል ወይንም አዘግይተቷሊ ሊባል የሚችለው መደበኛ የክፍያ ጥያቄን ተከትሎ ፣ ተበዳሪው መክፈል ባለበት ቀን መክፈል አለመቻሉን በተጨባጭ መረጃ ማረጋገጥ ሲያቅተው ነው ፡፡
ለበለጠ እና አዳዲስ የኢስላሚክ ባንክ የተመለከቱ መረጃዎች እንዲደርስዎ የሚከተለውን በኢሜል አድራሻዎ አባል ሆነው ይከታተሉ፡፡
https://moonlight-ibf.blogspot.com/
እንደዚሁም ይህንን ላይክና ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡