26/08/2025
The Livestock Development Institute (LDI) held a productive discussion today with representatives from SNV, a Dutch development organization. The meeting's primary focus was to establish a clear path forward for a new partnership. The two parties are collaborating on an initiative that will focus on capacity building within the livestock sector. This partnership aims to leverage SNV's extensive experience in sustainable development to strengthen the LDI's programs and expertise. The discussion concluded with a mutual agreement on the next steps to officially begin the partnership.
02/08/2025
https://www.ena.et/web/amh/w/amh_7067475
ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የስጋ እና የእርድ ተረፈ ምርቶች 120 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26/2017 (ኢዜአ) :-በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የስጋ እና የእርድ ተረፈ ምርቶች 120 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢፌዲሪ እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ገ...
26/06/2025
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ማኔጀመንት ከሥራ ዘርፎች፣ ከመሪ ሥራ አስፈጻሚዎች እና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር በመሆን የ2017 የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በተጨማሪም በ2018 ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ ተወያይቶ የ2018 ዕቅድን በማስቀመጥ ለትግበራው አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
04/01/2025
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ድጋፍ ለሚሹ 40 የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ
ኢንስቲትዩቱ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በተቋሙ ዙሪያ ለሚገኙና ድጋፍ ለሚሹ 40 ነዋሪዎች በ50 ሺ ብር ወጪ 4 ኩንታል ዱቄት ዛሬ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ለወረዳው አፈጉባኤ መንግሥቱ መዳልቾ
ያስረከቡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አሥራት ጤራ (ዶ/ር) እንደገሉፁት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አነሳሽነት የተጀመረውን ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት እየሰራ ነው ብለዋል።
ማህበራዊ ድጋፍ ኃላፊነቱን በክረምትና በጋ በጎ አድራጎት አጠናክሮ ከመቀጠል ባሻገር ከወረዳውና በከተማ አስተዳደሩ አርሶአደርና ግብርና ልማት ኮሚሽን ጋር በቅንጅት የሌማት ትሩፋቱን በሙያ እና በግብዓት ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ካሁን በፊት ለሁለት ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ከተሟላ የቤት ቁሳቁስ ጋር ከማስረከብ ጀምሮ በየዓመቱ በተለያዩ አውደ በዓላት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ዶ/ር አስራት አስታውሰዋል።
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ ለክርስትና እምነት ተከታዮች የገና በዓል የሰለም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
31/12/2024
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ለ56ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የአዳቃይ ቴክኒሽያኖች አስመረቀ!
==========================================
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ከምግብ ሥራዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለ56ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 141 (ወ 126፣ ሴ 15) ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የእንስሳት አዳቃይ ቴክኒሽያኖችን ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የተከበሩ እንግዶች፣ ለሥልጠናው ልዩ አስተዋጽዎና ድጋፍ ያደረጉ እና የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት እና ሠራተኞች በተገኙበት በይፋ አስመርቋል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ዘርፍ ሚኒስተር ዴኤታ የሆኑት ክቡር ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ(ፒኤችዲ) እና የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አስራት ጤራ(ፒኤችዲ) ተመራቂዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ለተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ክቡር ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ(ፒኤችዲ) በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በተነደፈው የሌማት ትሩፋት ስኬት የእንስሳትን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በግንባር ቀደምትነት ዝርያ ማሻሻል ወሳኝ ሥራ መሆኑን በመጥቀስ ይህን የእንስሳት ዝርያና ለማሻሻል ደግሞ የአዳቃይ ቴክኒሽያኖች ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ መሆኑን በመጥቀስ መንግስት ከፍተኛ ኃላፊን የጣለባቸው መሆኑን በመጥቀስ ተመራቂ ሠልጣኞች ወደመጡበት ተመልሰው ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት እና ጥራት እንዲወጡ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋቸዋል፡፡
በመቀጠልም የክብር እንግዳው ክቡር ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ (ፒኤችዲ) አጭር የሥራ ጉብኝት አድርገው የዕለቱ ፕሮግራም ተጠቃሏል፡፡
እልኢ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
12/12/2024
‹‹እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት በንብ እርባታ ቴክኖሎጂ ሞዴል የስልጠና ማዕከል እንዲሆን እንሰራለን›› አዉራሪስ ጌታቸዉ(ዶ/ር)
ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም እ/ል/ኢ አዲስ አበባ
እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ከ CRS (Catholic Relief Service) ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጊ ድርጅት ዝርያን ለማሻሻል የእናት ንብ እርባታ እና የማር ምርት ጥራት(Queen rearing and Honey quality) በሚል ርዕስ ዙሪያ በዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሮበርት ኦውን (Dr. Robert Owen) ተሰጥቷል፡፡ ሰልጣኞች ከእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ሁለቱንም ማዕከላት ጨምሮ፤ ከግብርና ሚኒስቴር፤ ከኢትዮጵያ ንብ ሀብት ማህበር፤ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፤ አናቢዎች (ከአዲስ አበባ፤ ቢሾፍቱ፤ ሰበታ) እና ማር አቀነባባሪዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡
CRS ዓለም አቀፍ ድርጅት (Farmers to Farmers Program) በእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በዘርፉ የሚያጋጥማቸውን የእዉቀትና ክህሎት ክፍተት በስልጠና በመሙላት እንዲሁም ችግር ፈቺ ምርምር እንዲሰራ፤ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና እንዲሰጥ እና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርግ አስፈላጊዉን ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ (memorandum of understanding) ተፈራርመዋል፡፡
የተቋሙ የእንስሳት ምርትና መኖ ማቀነባበርና ጥራት ምርምር ዶ/ር አዉራሪስ ጌታቸዉ እንደገለፁት ተቋሙ ለሙከራ ያህል 10 የንብ መንጋ በዘመናዊ ቀፎ ጅማሮ መኖሩን ገልጸው በቀጣይ እስከ 30 የንብ ቀፎ ለማድረስ እና በሆለታ ማዕከልም ተጨማሪ የንብ እርባታ ጣቢያ እንደሚቋቋም ተናግረዋል፡፡
አክለውም ኢትዮጵያ ሀገራችን 7 ሚሊዮን የንብ ቀፎ ቢኖራት ከ90 በመቶ በላይ በባህላዊ ቀፎ የሚመረት በመሆኑ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ባለመሆኑ አጥጋቢ ምርት እያገኘች አይደለም ብለዋል፡፡ ዘርፉን የማዘመን ሥራ በሚፈለገው ደረጃ ባለመስራታችን ሀገሪቱ በዓመት 500,000 ቶን ማር የማምረት አቅም ቢኖራትም እያመረትን ያለነው ከ147,000 ቶን ማር ያልበለጠ ነው፡፡
11/12/2024
የእንስሳት ልማት እንስቲትዩት፤ሆለታ ማዕከል(ሆ/እ/ል/ማ) ከ 40.000-45.000 የድርቆሽ ሳር ቦንዳ ለማገኘት እየሰራ ይገኛል
በ2017 ዓ.ም ማዕከሉ ከ40-45 ሺህ የድርቆሽ ሳር ቦንዳ ለማገኘት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ሙሉጌታ ተስፋዬ ገልጸዋል።
ለሳሩ ማከማቻ የሚሆን ሃያ(20) ሃያ(20) ሽህ የሚይዙ ሁለት መጋዝኖች ተዘጋጅቷል።
ስራዉ በአጠቃላይ ከ 80 በላይ ዜጎች ግዜያዊ የስራ እድል መፍጠር እንደተቻለም አክለዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም 58,409 የድርቆሽ ሳር ቦንዳ ተሰብስቦ እንደ ነበርም ጠቅሰው የዘንድሮ ምርት ግን የከብቶች ብዛት መጨመርን ተከትሎ ይመረት ከነበረዉ ምርት እንደቀነሰ ጠቅሷል።
የሳር አጨዳ እና መሰብሰቡ ስራ በአጠቃላይ ከ 80 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ግዜያዊ የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡
ማዕከሉ በተጨማሪም የድርቆሽ ሳር ከማምረት ባሻገር የተቀነባበረ የእንስሳት መኖ እንደ አስፈላጊነቱ ለጥጃ፤ ለኮርማ እና ለወተት ላሞች በ ራሱ መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እያመረተ ለዋና መስሪያ ቤት ኮርማዎች ፤ ለቢሾፍቱ እንስሳት ልማት ማዕከል የወተት ላሞች እና ክልሎች እንደሚያከፋፍል እና ፋብሪካዉ በቀን እስከ 150 ኩንታል የማምረት አቅም አለው።
10/12/2024
ኢትዮ-ቻይና የኢኮኖሚ ንግድ ወደ ላቀ እድገት የሚያሸጋግር ልምድ ልውውጥ ተደረገ
በእንስሳት ልማት እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አሥራት ጤራ(ፒኤችዲ)ና አመራሮች እንድሁም የመካከለኛ አፍሪካ ቀጠና ስራ ሀላፊ ው ሊያዓንቢን(Ms Wu Lianbin) እና ሊዩ ያጅናን(Mr Liu Yajnan) ጋር የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ(import-export) ያሉት እድሎችና እንቅፋቶች በተለይ በተቋማችን እየተሰራ ባለው የቄራዎች ጥራት እና ደረጃ የማሳደግ ፡እንዲሁም ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች ብዛታቸውና ጥራታቸውን ጠብቆ በተለይ የስጋ ምርት ወደ ቻይና ተልኮ ለሀገሪቱ የዉጭ ምንዛሬውን ማሳደግ በሚቻልበት ዙሪያ ተዋያይቷል።
በዚህ አመት ብቻ ኢትዮጵያ ከቻይና ወደ 435.95ሚ ዶላር በላይ ስጋን ጨምሮ ከተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች አግኝታለች። የሀገሪቱ የስጋ መላክ ሙሉ አቅሟ 200,000 ስጋ ቶን ብሆንም በአሁኑ ወቅት ግን 22,000ስጋ ቶን ስጋ ብቻ መላክ እንደተቻለ ስሆን የመላክ አቅሟን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።
25/11/2022
ትምህርታቸውን በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ላሻሻሉ ሠራተኞች እውቅና ተሰጠ
=====================================
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ማኔጅመንት እና ሠራተኞች በጋራ 2 በሁለተኛ ዲግሪ እና 1 በሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ላሻሻሉ የኢንስቲትዩቱ ሠረተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ ፕሮግራም በማዘጋጀት ዛሬ ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም አከበረ፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር አስራት ጤራ ዶ/ር ዳንኤል ደምሴ በሁለተኛ ዲግሪ(MVSC)፣ አቶ ዳኜ ሙሉነህ (MSC) በሁለተኛ ዲግሪ እና ዶ/ር ከፈለኝ ስዩም (PHD) በሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ላሻሻሉ ሠረተኞች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት አድናቆታቸውን በመግለጽ ሌሎች ሠራተኞችም ይህንኑ አርዓያ እንዲከተሉ አደራ ብለዋል፡፡