23/09/2020
ልጆች ጨዋታ በመጫወታቸዉ የሚያገኟቸዉ 5 ጠቀሜታዎች
በልጆች ህይወት ዉስጥ ጨዋታ ትልቅ ትረጉም አለዉ፡፡ ጨዋታ የልጆች መዝናኛ፤ ከሌሎች ጋር መተዋወቂያና የመግባቢያ መንገድ ነዉ፡፡ የጨዋታዉ አይነትና አጨዋወት ይላያይ እንጅ በየትኛዉም ቦታ የሚኖሩ ፤በየትኛዉም የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ልጆች ይጫወታሉ፡፡ ጨዋታ የልጆች ሥራ ነዉ፡፡ የዕዉኑን አለም አኗኗርና አስተሳሰብ፤ ህግጋትና ሥርዓታት መለማመጃ መድረክ ነዉ፡፡ ለወደፊት ህይወት ወሳኝ የሆኑ ክህሎቶችን የመማሪያ ተግባር ነዉ፡፡
ጨዋታ የመዝናኛ መንገድ ብቻ አይደለም፡፡ ልጆች ከጨዋታ በርካታ ጥቅሞችን ያገኛሉ፡፡ ጨዋታ ለልጆች አዕምሯዊ፤ አካላዊ፤ ማህበራዊና ስሜታዊ እድገት ትልቅ አስተዋፅዖ አለዉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ጨዋታ የልጆች የቋንቋ ችሎታቸዉ እንዲያድግ፤ የማህበራዊ ክህሎታቸዉ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ጨዋታ ልጆች የሌሎችን ስሜት እንዲረዱ፤ የማስብ አድማሳቸዉ እንዲሰፋ፤ የፈጠራ ችሎታቸዉ እንዲድግና ችግር ፈች አንዲሆኑ ያግዛቸዋል፡፡ ጨዋታ ለልጆች እድገት የሚኖረዉን ፋይዳ ይበልጥ ለመረዳት እንዲያመች በሚከተለዉ መልኩ ከፋፍለን እንመከተዉ፡፡
1. . ለአካላዊ እድገት መዳበር
ልጆች የሚጫዎቷቸዉ አብዘሀኛወቹ ጨዋታዎች የተለያዩ የአካል እንቅስቃሴ የተካተቱባቸዉ ናቸዉ፡፡ ልጆች እነዚህን እንቅስቃሴ ማድረጋቸዉ የአካል ጥንካሬያቸዉ እንዲጨምርና ጤናማና የተስተካከለ የሰዉነት አቋም እንዲኖራቸዉ ያደርጋል፡፡
2. ለአዕምሯዊ እድገት መዳበር
ጨዋታ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ቀደም ብሎ ተጠቅሷል፡፡ ልጆች በጨዋታ አማካኝነት እዉቀትን ይቃስማሉ፡፡ ማሰብን፤ ማስታወስንና ችግር ፈችነትን ይማራሉ ፡፡ ጨዋታ ልጆች አስተሳሰባቸዉን የሚፈትሹበት አለምን የሚመረምሩበት መንገድ ነዉ፡፡
3. ለማህበራዊ ክህሎት መዳበር
ልጆች በተናጠል የሚጫወቷቸዉ ጨዋታዎች እንዳሉ ሆኖ አብዘሃኛዉን ጨዋታዎች ከሌሎች ልጆች ጋር በጋራ ይጫወታሉ፡፡
4. የፈጠራ ችሎታ እንዲዳብር ያደርጋል
በርካታ የልጆች ጨዋታዎች የተለያዩ ንዑሳን ተግባራት፤ የአጨወዋዎት ቴክኒኮችንና ህግጋትን ፤ በዉስጣቸዉ አካተዉ ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ተግባራት ደግሞ ልጆች የተለያዩ የአዕምሮ ክፍላቸዉን አንዲጠቀሙ ያደርጋል፤ ይህም የልጆች የምርምርና የፈጠራ ችሎታ እየዳበረ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡
5. ለስሜትዊ እድገት መጎልበት
ጨዋታ ልጆዎን ከእርስዎ ጋር የሚያቆራኝ አንዱ ገመድ ነዉ፡፡ እርስዎ የልጅዎ የመጀመሪያዉ መምህር ነዎት፡፡ አብዘሃኛዉ ትምህርት ደግሞ የሚተላለፈዉ በጨዋታ ነዉ፡፡ ለምሳሌ እርስዎ ከልጅዎ እየተጫወቱ ነዉ እንበል፡፡ በጨዋታዉ ህግ መስረት እርስዎ ተሰሸነፉ፤ ሽንፈትዎን በፀጋ ተቀብለዉ ወደ ቀጣዩ ጨዋታ አለፉ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጅዎ የጨዋታዉ አሸናፊ በመሆኑ ትልቅ ደስታ እንደሚሰማዉ አያጠራጥርም፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን እርስዎ ለጫዎታዉ ህግ ያሳዩትን ተገዥነት በመመልከት ልጅዎ ህግና መመሪያ አክባሪነትን ይማራል፡፡ ይህም ልጅዎ የቤተሰቡን ህግጋት አክባሪና መብትና ግዴታዉን የሚያዉቅና የሚረዳ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡ ከፍ እያለ ስሄድ ደግሞ በማህበረሰቡ ዉስጥ ያሉትን አጠቃላይ ህግጋት እየተረዳና እየተገበረ እንዲሄድ ያደርገዋል፡፡
23/06/2020
19/05/2020
17/04/2020
09/12/2019
09/12/2019
21/11/2019
21/11/2019
11/10/2019