Orthodox tewahdo

Orthodox tewahdo orthodox tewahdo religious

27/09/2020

በአምላኩ ደም የተቀደሰ ፣ ከፈጣሪው ጎን በወጣ ውኃም የተጠመቀ ዕፅ እንዴት ያለ ነው?

ለገነት ዛፎች አክሊል ፣ ለገዳም ዛፎችም ክብር የሆናቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው?

ለአሸናፊ የእግዚአብሔር በግ መሠዊያ የሆነው ዕፅ እንዴት ያለ ነው?

ከእርሱ ምዕመናንን ለማተም የሚሆን የሕግና የሥርዓት ደምን ያንጠባጠበ ዕፅ ምን ዓይነት ነው?

የተከሉትን የበተናቸው ፣ ያመኑትንም የሰበሰባቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው?

ምድርን የቀደሳት፣ ሰማይንም ያማተበበት፣ ዓለምንም ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በረከት የባረከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው?

06/09/2020

ርኢክዋ አእመርክዋ አፍቀርክዋ ለቤተክርስቲያን ።
(አየኋት አቅኳት ወደድኳት ቤተክርስቲያንን )

ደብረ_ታቦር (ነሐሴ 13)ደብረ ታቦር ከዘጠኙ የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በምዕመናን ዘንድ ቡሄ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ብርሃን፤ የደመቀ...
18/08/2020

ደብረ_ታቦር (ነሐሴ 13)

ደብረ ታቦር ከዘጠኙ የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ በምዕመናን ዘንድ ቡሄ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት ብርሃን፤ የደመቀ የጎላ ማለት ነው፡፡ ይህም ስያሜ በደብረ ታቦር የጌታችንን ብርሀነ መለኮት መገለጥ ጋር የተያያዘ ስያሜ ነው፡፡ የችቦ ማብራት ቱፊትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ደብረ ታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ ተራራው ከገሊላ ባህር በስተ ምስራቃዊ ደቡብ በኩል ይገኛል፤ መሳ.4 ÷6-14 ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል፤ ጌታችን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን በጠየቃቸው ጊዜ አንዳንዶች መጥምቁ ዮሀንስ ሌሎች ኤልያስ ነው፤ ሌሎችም ኤርምያስ ነው ወይም ከነብያት አንዱ ነው ይላሉ ብለውት ነበር፤ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ’’ ብሎ መልሶለታል ይህ በሆነ በስደስተኛው ቀን ከሐዋርያት መካከል ሦሥቱን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወጣ በኋላ ብርሀነ መለኮቱን ገለጠላቸው ከዚያም ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን ጠርቶ ያመጣቸው ሙሴ ክብርሀን አሳየኝ ብሎት ነበር (ዘጸ. 33÷17-23) ጌታችን ግን በሕይወተ ሥጋ እያለ እኔን ሊያይ የሚቻለው ማንም የለም ቢለውም ከመቃብር አስነስቶ ልመናውን ፈጽሞለታል ፡፡

ስለ እርሱም ማንነት ግራ ለተጋቡ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት እንደተናገረው የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንጂ ከነብያት አንዱ አለመሆኑንና ለዘለአለምም ሰዎች በዚህ እንዳይሰናከሉ በተግባር አስተምሯቸዋል፡፡ ከዚያም ደመና ጋረዳቸውና አብ ከሰማይ "የምወደው ልጄ ይህ ነው አርሱን ስሙት" ሲል መሰከረ፡፡ ማቴ 17÷ 2 ሉቃ 9÷29፡፡

እግዚአብሔር ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን

12/08/2020

ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አርእየኒ እመከ አሐተ ሰዓተ
(ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንዲት ሰዓት እናትኽን አሳየኝ)

24/06/2020

እግዚአብሔር ድካምህን እንደሚያውቅና እስካሁን ድረስም እንደሚወድህ እርግጠኛ ሁን ! በኃጢአት ውስጥ ብትሆንም እግዚአብሔር ሊያድንህ ወደ እርሱ ሊያቀርብህና ወደ ቀደመ ደረጃህ ሊመልስህ እንደሚሰራ እመን ። አዳም የዳነው ንሥሐ ለመግባት ባደረገው ሙከራ ሳይሆን አዳምን በተመለከተው የእግዚአብሔር ቸርነት ነው ።

25/05/2020

"እግዚአብሔርን እንደ ባልንጀራችሁ ቁጠሩት"
እግዚአብሔርን ለመውደድ ከፈለጋችሁ እንደ ባልንጀራችሁ ኣድርጋችሁ ቁጠሩት።

ይልቁንም እርሱ የመጀመሪያ ባልንጀራችሁ ይሁን፤

ወደ ማንም ከመጣደፋችሁ በፊትም ወደ እርሱ ተጣደፉ።

ምስጢራችሁን ለእርሱ ግለጡለት፤
ሁሉንም ነገር ንገሩት፣
ከእርሱ ጋር መሆናችሁ የሚሰማችሁ የመደላደል ስሜት ጥልቀትም ይታወቃችሁ።

ኣሳቦቻችሁንም በሙሉ ንገሩት፣
የውስጣችሁንም ውስጥ ግለጡለት፤
ይህንንም በግልፅነት፣በምሉ እውነት፣በመተማመን እና ክፍት በሆነ ልብ ኣሳዩት።
ከእርሱ ጋር በመነጋገራችሁም ስልቹ ኣትሁኑ።

ይልቁንም""ጌታዬ ሆይ፦የምነግርህ ብዙ ነገር ኣለኝ""በሉት።

ለእኔ ያለህን ፍቅር ኣምናለሁ፣ኣንተ ለእኔ መልካም የሆነውን ነገር እንደምታደርግልኝም እርግጠኛ ነኝ።ኣንተ ይህን ለማድረግ በቂ ኃይል ኣለህ።ኣንተ ይህ ኃይል ካለህ እኔ ለምወዳቸው ሰዎች የምነግራቸውን ነገር ለኣንተ የማልነግርህ ለምንድር ነው"?።
"እግዚአብሔር በማንኛውም ስራችሁ ውስጥ ከእናንተ ጋር የስራ ባልደረባችሁ እንዲሆን ሞክሩ"።

እርሱ ከምናምናቸው ሰዎች በላይ ለቃሉ ታማኝና ሁሉን የሚችል ኤልሻዳይ ስለሆነ።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251973830785

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Orthodox tewahdo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category