06/08/2026
በአረንጓዴው የጎጃም ምድር ነጭ የለበሱ ልጃገረዶች እና ታዳጊዎች ድንቅ ዝማሬ እያሰሙ የሚታደሙበት የእንግጫ ነቀላ በዓል እየደረሰ ነው‼️
የአዲስ ዓመት መምጣት ብስራት ከሆኑ የድንቅ ምድር ድንቅ ክብረ በዓላት አንዱ የሆነው እንግጫ ነቀላ በጎጃም በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች በልጃገረዶችና ታዳጊዎች በናፍቆት እየተጠበቀ የሚከበር ተወዳጅ በዓል ነው፡፡
የእንግጫ ነቀላ በዓል መከበር የሚጀምረው ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት በአንዳንድ የጎጃም ወረዳዎች በዓሉ ከአሸንድዬ እና ከከሴ አጨዳ በዓላት ጋር በጥምረት ሲከበር ይቆያል፡፡ ነሐሴ አልፎ ጳጉሜን እና መስከረም ሲደርሱ ደግሞ የእንግጫ ነቀላ በዓል ድባብ እና ድምቀት ምልዑ ሆኖ በምድሪቱ ላይ ይታያል፡፡
የእንግጫ ነቀላ በዓል መነሻ ምክንያት እንደሆኑ ከሚታመኑ መላምቶች አንዱ ሀይማኖት ነው፡፡ መላምቱ የበዓሉን ጅማሮ ወደ ኖህ ዘመን የሚወስደው ሲሆን በዘመኑ የነበረው የጥፋት ውሃ መጉደሉን ለማብሰር የተላከችው እርግብ በአፏ ለምለም ቅጠል(ቄጠማ) ይዛ ከመምጣቷ ጋር ያገናኘዋል፡፡ ምሳሌነቱንም ለጨዋታው የሚወጡ ልጃገረዶች ነጭ መልበሰቸውን ከእርግቧ ነጭ መልክ፣ እንግጫ የሚባለውን የሳር ዘር ነቅለው በእጃቸው መያዛቸውን ከእርግቧ ለጥፋት ውሃ መጉደል ምልክት ይሆን ዘንድ አረንጓዴ ቄጤማ በአፏ ይዛ ከመምጣቷ ጋር፣ የክረምቱን ማለፍ እና የአዲስ ዘመን መምጣትን ማብሰራቸው ከኖህ የጥፋት ውሃ በኋላ ከነበረውን የምስራች እና ተስፋ ጋር ያዛምዱታል፡፡
በዚህ ምክንያት እንግጫ ነቀላ የአዲስ ዘመን መምጣትን አብሳሪ በዓል ሆኖ እስከ ዛሬ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ ልጃገረዶች ልክ እንደ እርግቧ ነጭ ለብሰው የውኃውን መጉደል፣ የክረምቱ ጨለማ ማለፍን እና የጋራ ሸንተረሩ መለምለምና ማበብን ለማየት ወደ መስክ በመውጣት እንግጫ ነቅለው እና በአደይ አበባ አስጊጠው ወደ ዘመድ አዝማድ እና አብያተ ክርስቲያናት እየሄዱ “አዲስ ዓመት ገብቷል፤ ክረምቱ አልፏል፤ እንኳን አደረሳችሁ” እያሉ የምስራች ስጦታ ያበረክታሉ፡፡
እንግጫችን ደነፋ፣
ጋሻዉን ደፋ . . . .
እንግጫችን የወሩ፣
የቦረቦሩ . . . .
የቅዱስ ዮሐንስ፣ የዓመቱ የዓመቱ
ስደድልኝ ድሪ፣ ከነቀለበቱ . . .
እንግጫ ጎንጉኜ፣ በአደይ በሶሪት
እንቁጣጣሽ ብዬ፣ ቤቱ ላክሁለት . . .
!!
አደይ የጣይቱ እልፍኝ ሸማ Debre Markos city communication David Bezuneh ጎጃም Times Yalemwerk Birhanu Tiruye Atinafu Zinabu Endalfer Bahirdar City Communications Blue nile press Ante'Neh Ze'Ghion ሰለሞን ዘባህርዳር መንቆረር 𝐓𝐢𝐦𝐞𝐬 ሀዩቲ መተከል ማርዳ መልቲሚዲያና ኘሮሞሽን /Marda Multimedia And Promotion/ Girmaw Ashebir