Space science and geo-spatial institute

Space science and geo-spatial institute

Share

Space Science and Geospatial Institute(SSGI)

Photos from International Space Station's post 22/05/2026
19/05/2026

በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትንተና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አባስ መሐመድ፣ ስለ ኢትዮጵያ የመረጃ ሉዓላዊነት ጉዞ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሕጋዊ ዕውቅና ያላቸው፣ በሳይንሳዊ ስልት የተዘጋጁ እና ለሕዝብ ክፍት የሆኑ ይፋዊ ስታቲስቲክስ እንዴት ጥሬ መረጃዎችን ወደ ተጨባጭ ማስረጃ፣ ማስረጃዎችን ደግሞ ወደ መልካም አስተዳደር እንደሚቀይሩ አብራርተዋል። ያለ መረጃ የሚታቀድ ትልም ምኞት ብቻ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፤ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ እምነት የሚጣልባቸውና የኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የተረጋገጠባቸውን መረጃዎች (ቁጥሮች) እንደሚሹ አሳስበዋል።

‎በተጨማሪም በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም ሥር የተመዘገቡ ታላላቅ ስኬቶችን አጉልተው ያሳዩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሙሉ በሙሉ ይፋ የተደረገውን የሥነ-ህዝብ እና ጤና ጥናት፣ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን የመንግሥት ሠራተኛ ባለሙያዎች የተከናወነውንና ከተለመደው ያደገውን የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት፣ እንዲሁም በግብርና ቆጠራ እና በኢኮኖሚ ተቋማት ቆጠራ ላይ የተመዘገቡ ዋና ዋና እመርታዎችን ጠቅሰዋል።

Photos from Ethiopian Broadcasting Corporation's post 19/05/2026
Photos from Abiy Ahmed Ali's post 18/05/2026
Photos from AMECO Addis Ababa 
አሚኮ አዲስአበባ 's post 17/05/2026
Photos from Ethiopian News Agency's post 16/05/2026
Photos from Space science and geo-spatial institute's post 16/05/2026

"የአድራሻ ሥርዓት ሳይኖር የዲጂታል ኢኮኖሚንም፤ ስማርት ሲቲንም መገንባት አይታሰብም" ክቡር አብዱላዚዝ ዳውድ (ዶ/ር)
======= SSGI =======
(ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም SSGI)
የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት ያለማው የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማገዝ እና ዘመናዊ ከተማን ለመገንባት የመሪነት ሚና የሚኖረው የአዳማ ከተማ የዲጂታል አድራሻ ስርዓት (eDAS) የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

የዲጂታል አድራሻ ስርዓቱን መርቀው ለአዳማ ከተማ አስተዳደር ያስረከቡት የኦሮምያ ቤ/ክ/መንግስት ፕሬዚዳንት ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ሀላፊ አብዱላዚዝ ዳውድ (ዶ/ር) የኦሮሚያ መንግስት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት ስትራቴጂ ነድፎ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው የዲጂታል መታወቂያ፣ የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶች (e-service) እንዲሁም የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ዝርጋታ ማሳያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአድራሻ ሥርዓት ሳይኖር ዲጂታል ኢኮኖሚም፤ ሰማርት ሲቲም መገንባት አይታሰብም ያሉት አብዱላዚዝ ዳውድ (ዶ/ር) በአዳማ ከተማ ተግባራዊ የተደረገው አድራሻ ስርዓቱ (eDAS) አስተዳደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን እና የከተሞችን ምቾትና ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ዘላቂ የልማት ግቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ዓይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በዝግጅቱ ላይ የስፔስ ሳይንስና ጂእስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ በአዳማ ከተማ አስተዳደር የተተገበረው የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ዝርጋታ በቀጣይ በ73 የኢትዮጵያ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ ኢንስቲትዩት እየሰራ እንዳለ አንስተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ የከተሞች አድራሻ ስርዓት ከፍተኛ ጥረት እና ቁርጠኝነትን የሚፈልግ በመሆኑ በአዳማ የተገኘውን ልምምድ በመጠቀም ፕሮጀክቱን በተለያዩ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሮች አስፈላጊውን ዝግጅትን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሀይሉ ጀልዴ ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ዝርጋታን በአዳማ ከተማ መተግበሩን አመስግነው በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ በማድረግ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከተማ አስተዳደሩ የሚያደረገውን ጥረት በእጅጉ የሚያቀል ነው ብለዋል።

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት ከአዳማ ከተማ በተጨማሪ የ9 ከተሞችን የዲጂታል አድራሻ ስርዓት በማጠናቀ ላይ ሲሆን የአዳማ ከተማ የዲጅታል አድራሻ ስርዓቱን የፌደራል እና የክልል ተቋማት አመራሮች ፣የአዳማ ከተማ አመራሮችና አባገዳዎች፣ አዳሲንቄች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተመረቀ ሲሆን ፕሮጀክቱ በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት እና በአዳማ ከተማ አስተዳደር ትብብር መዘርጋቱ ተገልጿል።

Photos from Space science and geo-spatial institute's post 14/05/2026

The 3rd Space and Geospatial Annual Research Conference Concluded Successfully.
======= SSGI =======
(May 14, 2026 – SSGI)
The 3rd Space and Geospatial Annual Research Conference 2026 (S-ARC2026), held under the theme “Space Science and Geospatial Innovation for Sustainable Development and Digital Transformation,” has successfully concluded after two consecutive days of scientific sessions and discussions.

Organized by the Ethiopian Space Science and Geospatial Institute, the annual conference brought together leading scholars, researchers, senior sector officials, professionals, and students working in the fields of space science and geospatial technologies.

During the conference, participants presented a wide range of research findings and innovative studies aimed at strengthening Ethiopia’s competitiveness in the global space science and geospatial sector.

The event also served as an important platform for knowledge sharing, academic collaboration, and professional networking among experts and institutions engaged in the field.

Participants emphasized that the annual conference created a valuable opportunity for researchers and academicians in Ethiopia to exchange experiences, ideas, and scientific knowledge.

They further noted that the conference would play a significant role in laying a strong foundation for advancing the country’s capacity in space science and geospatial research and innovation.

The successful completion of S-ARC2026 reaffirmed the growing importance of space science and geospatial technologies in supporting sustainable development and accelerating digital transformation efforts in Ethiopia.

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa
33679

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:00
Tuesday 08:30 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 08:30 - 00:00