Brightmind

Brightmind ይህ ፔጅ ለህይወት ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን የሚያስተላልፍ ሲሆን

23/10/2025
✍️✍️✍️✍️✍️✍️ፍቅርና ህይዎትዛሬን ኖረናል ነገን እንደምንኖር ወይንም እንደማንኖር እርግጠኛ ሆነን መናገር አንችልም። ምክንያቱ ደሞ ህይወት በተስፋ ስለት የተሳለች እና በአጋጣሚዎች ስብስ...
07/10/2024

✍️✍️✍️✍️✍️✍️ፍቅርና ህይዎት

ዛሬን ኖረናል ነገን እንደምንኖር ወይንም እንደማንኖር እርግጠኛ ሆነን መናገር አንችልም። ምክንያቱ ደሞ ህይወት በተስፋ ስለት የተሳለች እና በአጋጣሚዎች ስብስብ የቆመች የእስትንፋስ ጓዳ ናት። ስለ ህይወት ሳወራ ቀድመዉ የሚመጡብኝ ለወደፊት ይሆኑልኛል ያልኳቸዉን ነዉ። ሞትን የምፈራዉም እንድሆኑልኝ የተመኘኋቸዉን እንዳያቸዉ ስለምጓጓ እንጅ የማየዉ እና እንድሆንልኝ የምመኘዉ ባይኖረኝ ኖሮ ህይወት ለራሷ ምን ትርጉም ይኖራት ነበር። ፍቅር የህይወትን ጣዕም የሚያጣፍጥ የመኖርንን ጉጉት የሚያሰፋ የደስታ ንጉስ የሆነ የተፈጥሮ ግሩም ስጦታ ነዉ። ለኔ መኖሬም መመኘቴም ለፍቅሬ ስል ብቻ ነዉ። ፍቅርን ተርጉሜ አስሸ እና መርምሬ ያልጠገብኩ ነኝ። ፍቅሬን ሳስብ ነገን እናፍቃለሁ ሞትን እፈራለሁ ፍቅሬን ስመኝ ትናንትን ነገ እንድሆን ዛሬን ሌቱ እንድጎድል የማልመኘዉ ነገር የለም። ግን ስለሁሉም ነገር ስለፍቅር አሳብቤ ልንገራችሁ እንጅ ፍቅር እኮ ከኔጋ የለም። ዛሬማ ተለይቶኛል ዉደታ የሚባል የለም ናፍቆት በራሱ ሳይረሳኝ አልቀረም። ለመወደድ ምኑ ነበር የቀረኝ ህይወት ትኑር ከምንየዉም በላይ ታስደስተኛለች ለኔ ፍቅሬ ህይወቴ ናት፤ እወዳታለሁ አፈቅራታለሁ እሳሳላታለሁ ሁሌም ፍቅሬ ናት ከህይወት በላይ ምን ፍቅር አለ። ፍቅር በብዙ ቦታ ሊኖር ይችላል የገንዘብ ፍቅር የሰዉ ፍቅር የስራ ፍቅር የእናት ፍቅር ብሎ ቢዘረዘር ወደር የሌለዉ ነዉ....... ፍቅር የሌለበት የለም። ፍቅር የሌለበት አለ ካላችሁ እራሱ እንደለለ እኔ እመሰክራለሁ።
ከምነየዉም በላይ ግን ለኔ ትዝታየም ፍቅሬም ናፍቆቴም ሀሳቤም ህይወቴ ብቻ ናት። ሁሉን ነገር ልታሳየኝ የምትበቃዉ ህይወቴ ስትኖር እና በፍቅሯ ጣዕም ስጎነጭ ብቻ ነዉ።

ቀጣይ የምትሉ ....በኮሜንት ግለፁልኝ

The effect of war
05/10/2024

The effect of war

 ?????የሰዉ ልጅ ስንት ችግሮችን እየፈታ የአለም ስልጣኔን ጫፍ ያደረሰ አእምሮ እያለዉ። የሰዉን ልጅ ችግር የሚፈቱ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በሚሰራበት ሰዓት ለሰዉ ልጅ ምቾት ስንት እና ስ...
02/09/2024

?????

የሰዉ ልጅ ስንት ችግሮችን እየፈታ የአለም ስልጣኔን ጫፍ ያደረሰ አእምሮ እያለዉ። የሰዉን ልጅ ችግር የሚፈቱ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በሚሰራበት ሰዓት ለሰዉ ልጅ ምቾት ስንት እና ስንት የሰዉ ስሪቶች በሞሉበት በዚች ሁሉነገር በሚታይበት አለም...እኛ ኢትዮጱያኖች ግን እርሃብን የሚያጠፋ😭 መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በሽታን,,, የሚያጠፋ መድሃኒት ከመፍጠር ይልቅ ''' የህዝቡን ሰላም ከማስፈን በላይ! የተሻለ ስራ ከመፍጠር ይልቅ .... #ጦርነት ቀለብ ይመስል #ጦርነት ስራ ይመስል #ጦርነት ሰላም ይመስል #ጦርነት ምቾት ይመስል ---በመሳሪያ ድምፅ እና በጥይት ተኩስ በፈንጅ ፍንዳታ ሰዉን ከማስደንገጥ ከማሸበር በላይ መግደል ማሳደድ ማቁሰል መረበሽ እንደመፍትሄ ይዘነዋል። እና መቸ ነዉ የምንነቃዉ ስንት መፍጠር የሚችል አእምሮ ይዘን በመነጋገር በቀላል አማረኛ መግባባት ካቃተን በቀላል ቋንቋ አለመግባባቶችን መፍታት ካልቻልን በጦርነት እስከመቸ መፍትሄ የሚፈለገዉ። አቦ ጦርነት ያስጠላል።😭😭😭😭😭

ጦርነትን ከሩቅ ሆኖ ስለጦርነት ማዉራት በጣም ቀላል ነዉ። ጦርነትን ከሩቅ ሆኖ መደገፍ ማበረታት ቀላል ነዉ። ግን ጦርነትን የሚያዉቀዉ በጦርነት ዉስጥ ያለ ብቻ ነዉ። የሚተኮሰዉ የመሳሪያ ብዛት ምድርን ሲያናዉጣት የተተኮሰ ጥይት መታኝ አልመታኝ ሰዉነትህ ሲረበሽ እዚህም እዛም የፈራረሱ የጋዩ ቤቶች ስታይ የሰዉ ልጅ በየቦታዉ ሰዉነቱ ተገነጣጥሎ ስታይ እንስሳት አራዊት ያለስራቸዉ በየምንገዱ ላይ በየጥሻዉ ሞተዉ ተሰንቅረዉ ሲታዩ። የሚጨሱ የቤት ፍርስራሾች የተረበሸ መንገድ የተቆራረሰ አስፓልት ስታይ ወድህም ወዳም የሚያለቅሱ እናቶች ህፃናቶች ብቻቸዉን የቀሩ ልጅ እናት አባት ስታይ። በዚህም በዛም የተኩስ መዓት ስትሰማ የጭንቀት መዓት ስታስተናግድ የሰላም አየር የሰላምን ትልቅነት አስፈላጊነት የዛኔ ይገባሃል። ጦርነት ያስጠላል....አሁንም ......ወደፊትም.....

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Brightmind posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Brightmind:

Shortcuts

Share

Category