የመመቻቻል ተምሳሌት ኮልፌ ትንሿ ኢትዮጵያ

የመመቻቻል ተምሳሌት ኮልፌ ትንሿ ኢትዮጵያ ኮልፌ ስታሳድገን ዘረኝነትን እንድንጠየፍ. በጋራ መቆምን በደስታም በሀዘን በችግር ጊዜ እርስ በርስ እንድንደጋገፍ ቤት ጎረቤት ሰፈር ቤተሰብ ታላቅ ታናሽ እንድንከባበር አድርጋ በጨዋነት ነው ያሳደገችን!

🎂 እንኳን ተወለድክ አመለ ሸጋው! ❤️እንኳን ተወለድክ ውድ ወንድሜ፣ ልበ ወርቁ የኮልፌ ልጅ! 🎂❤️የባዩሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት መስራች፣ የብዙ እናቶችን እንባ ያበሰ፣ የጠፉ ልጆችን ከቤተሰቦ...
23/08/2026

🎂 እንኳን ተወለድክ አመለ ሸጋው! ❤️

እንኳን ተወለድክ ውድ ወንድሜ፣ ልበ ወርቁ የኮልፌ ልጅ! 🎂❤️

የባዩሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት መስራች፣ የብዙ እናቶችን እንባ ያበሰ፣ የጠፉ ልጆችን ከቤተሰቦቻቸው ያገናኘ፣ በጎነትን በተግባር የምታሳይ ውድ ወንድማችን። 🙏❤️

ለሌሎች ብርሃን ለመሆን ራስን መስጠት ትልቅ ልብን ይጠይቃል። የምታደርገው በጎ ሥራ በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም፤ በተመለሰ ፈገግታ፣ በተገኘ ልጅ፣ በተመለሰ ተስፋ እና በተበሰ የእናት እንባ የሚታይ ነው። ❤️

ዛሬ የልደትህን ቀን ስናከብር፣ “እንኳን ተወለድክ” ብቻ ሳይሆን፣ ለብዙዎች ተስፋና ብርሃን የምትሆን ሰው ሆነህ ስለተፈጠርክም እናመሰግናለን። 🙏

አምላክ የልብህን መልካም ምኞት ያሳካልህ፣ በጎ ሥራህን ይባርክልህ፣ የምትዘራውንም መልካምነት በብዙ ፍሬ ይመልስልህ።

ቀሪ ዘመንህ በጤና፣ በሰላም፣ በደስታና በበረከት ይሁን! 🙏❤️

እንኳን ተወለድክ አመለ ሸጋው! 🎂🎉❤️
ልበ ወርቁ የኮልፌ ልጅ! 👑❤️

አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የት ተማራችሁ? በዛው የተጠፋፋው ተማሪ ይገኛኝ!
15/08/2026

አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የት ተማራችሁ? በዛው የተጠፋፋው ተማሪ ይገኛኝ!

11/08/2026

🥊🔥 ቢኒ ሳሎን ይለይልን እያለ ነው! 😂
ቢኒ 👉 “ሳሎን ይለይልን!” እያለ ሲጠይቅ፣

ዘቤ በበኩሉ 👉 “ዛቻ ምንም አያስበረግገኝም!” እያለ ቆርጦ ቆሟል። 😤🥊

እንግዲህ ኮልፌዎች… ምን ትላላችሁ? 👀

😂 አርፈው ይቀመጡ?

🔥 ወይስ ቀጣቅጠው ይጨርሱ?

የኮልፌ ልጆች ውሳኔ ምንድነው? 🥊🔥

 ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የኮልፌ ልጅ ወንድማችን ማሙሽ ግሮሰሪ (ፍቃዱ ብርሀኑ)ይባላል።  በጣም ጎበዝና ታታሪ ሰራተኛ ነው። ማሙሽ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ባለቤቱንና ሶሰት ልጆቹን  ለ...
08/08/2026



ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የኮልፌ ልጅ ወንድማችን ማሙሽ ግሮሰሪ (ፍቃዱ ብርሀኑ)ይባላል። በጣም ጎበዝና ታታሪ ሰራተኛ ነው።
ማሙሽ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ባለቤቱንና ሶሰት ልጆቹን ለማኖር ሌት ተቀን የሚተጋ ስራውን የሚያከብር፣ለትንሽ ለትልቁ እሺ የሚል ታዛዥ፣አቅመ ደካማን የሚደግፍ ወንድማችን ነበር።

ማሙሽ ባደረበት ህመም ያለውን ጥሪት በመጨረስ በተለያዩ የህክምና ተቋማት ቢታከምም በመጨረሻም በዘውዲቱ ሆስፒታል በህክምና ሲታገዝ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ማለትም ነሀሴ 2-12-2018 ይቺን አለም ተሰናብቶ አርፏል።

የቀብሩ ስርአትም በነገው ዕለት 3-12-2018 ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ኮልፌ በሚገኘው ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን ከረፋዱ 5:00 ላይ ይፈፀማል።
ለቅሶውን መድረስ የምትፈልጉ አድራሻው ኮልፌ ኖክ 18 ማዛርያ ወረድ እንዳሉ 06 መዝናኛ ክበቡ ጀርባ ትንሽ ገባ እንዳሉ ያገኙታል።

ቤተሰቦቹም የእኛን እገዛ ይሻሉና እነሱን ማገዝ የምትፈልጉ ልበ ቀና የኮልፌ ልጆች እና ኢትዮጵያዊያን ከስር ባለው የባለቤቱ አካውንት መጠቀም ትችላላቹ።

1000457317585
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ወርቅነሽ ጌቱ ወርቁ

06/08/2026

ሰላም ቤተሰቦች በመላው አለም ለምትገኙ በጠቅላ ለወንድማችን ድጋፌ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል በዚህ ርብርብ ያልተሳተፋቹ በፈጣሪ ስም እንድትረባረቡ እንጠይቃለን::

ወንድማችን መደገፍ ለምትፈልጉ በባንክ አማራጭ ንግድ ባንክ CBE 1000222703477 ማንደፍሮ ንጉሴ በዚህ የሒሳብ ቁጥር ተጠቀሙ 🙏

"ዛሬ የምታደርገው ጥረት፣ ነገ የምትኮራበት ታሪክ ይሆናል።""ዛሬ የምታደርገው ጥረት፣ ነገ የምትኮራበት ታሪክ ይሆናል።"
04/08/2026

"ዛሬ የምታደርገው ጥረት፣ ነገ የምትኮራበት ታሪክ ይሆናል።"

"ዛሬ የምታደርገው ጥረት፣ ነገ የምትኮራበት ታሪክ ይሆናል።"

21/07/2026

"ለጌቱ ጉርሻ የተዘጋጀው የመታሰቢያ ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ"

አገኘውና ጓደኞቹ ከ አዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የመታሰቢያ ውድድር በአስደሳች ሁኔታ ተካሄደ::

በቅርቡ በሞት ያጣነው ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ውድድሮች በፓራላምፒክ በክብደት ማንሳት መወከል የቻለው ስፖርተኛ ጌቱ ጉርሻ የመታሰቢያ ቦክስ ውድድር ባማረ መልኩ ተጠናቀቀ::

ቤተሰቦቹን ጨምሮ በርካታ የጌቱ ጉርሻ ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት መታሰቢያ ውድድሩ ተካሂዷል::

በዕለቱ ስፖርተኛውን ጌቱ ጉርሻን ለማሰብ የ 1ደቂቃ የህሊና ፀሎት የተደረገ ሲሆን ውድድሩ ባማረና በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል::

ውድድሩን በማስተባበር ግቡን እንዲመታ ያረጉት አገኘውና ጓደኞቹ በስተመጨረሻ ለጌቱ ጉርሻ ባለቤቱና ለልጁ በጋራ የመኪና ቁልፍ አበርክተውላቸዋል::

በስተመጨረሻም ውድድሩን ያዘጋጁት ከቶ አገኘው ጥላሁን ይህ ፕሮግራም እንዲሳካ ለተረባረበ በሙሉ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ በሙል ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

16/07/2026

Teddy ወንድማችን ከአሜሪካ ዲሲና ቨርጂኒያ ካሉት ጓደኞቹ በማስተባበር52,200 ለወንድማችን ድጋፌ የመታከሚያ ድጋፍ አድርጎልናለ እናመሰግናለን🙏

በመላው አለም የምትገኙ ወንድሞቻችን የኮልፌ ልጆች ትብብራቹ አይለየን🙏

ወንድማችን የኮልፌው ወጣት ድጋፌ ሁለቱ ኩላሊቶች ፌል አርገው ለህክምና ከፍተኛ ገንዘብ ያስፈልገዋል ያን ለማድረግ በቤተሰብ አቅም ብቻ የሚሆን አይደለም ያ ስለሆነ እናንት ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ ወጣት ወንድማችን የተቻላቹን ድጋፍ እንድታረገለት ስንል በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን::

ወንድማችንን አለሁልህ ለማለት የቻላቹትን ደገፍ ማድረግ ትችላላቹ የኮልፌ ወጣቶች ከ ሶስት መቶ ብር ጀምሮ ቻሌንጅ አስጀምረዋል ያን ቻሌንጅ በመቀላቀል የወንድማችንን ድጋፌን ህይወት እንታደግ::

ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ CBE 1000222703477 ማንደፍሮ ንጉሴ በዚህ የሒሳብ ቁጥር ተጠቀማቹ የቻላቹት ድጋፍ ማድረግ ትችላላቸለ::

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የመመቻቻል ተምሳሌት ኮልፌ ትንሿ ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category