15/09/2025
ካሊድ_በሽር👏
የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ካሊድ በሽር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 591 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ተማሪ ካሊድ በሽር ፦
- እንግሊዘኛ 96፣
- ሒሳብ 100፣
- ፊዚክስ 100
- ኬሚስትሪ 98፣
- ባዮሎጂ 99፣
- አፕቲትዩድ 98 አምጥቷል፡፡
የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ደቱ ዲቦ " ተማሪ ካሊድ በሽር በትምህርቱ በጣም ጎበዝ፣ ጥሩ ሥነ ምግባር ያለው እና አርአያ የሆነ ተማሪ ነው " ሲሉ ለኤፍ ኤም ሲ ተናግረዋል።
15/09/2025
አዲስ አበባ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ሴት ተማሪዎች 👏👏
በ2017 ዓ.ም በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች፦
⭐️ ኃይማኖት ዮሐንስ ውብሸት
579 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ከብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት
⭐️ ሲምቦ ደረጄ አያና
548 የማኅ ሳይንስ ተማሪ ከሴይንት ጆን ካቶሊክ ትምህርት ቤት
15/09/2025
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡
በዚህም የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም ምዝገባ መስከረም 21 እና 22/2018 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ትምህርት መስከረም 23/2018 ዓ.ም ይጀምራል የተባለ ሲሆን፤ በቅጣት የመመዝገቢያ ጊዜ መስከረም 23-24/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡
(የተቋሙ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል
15/09/2025
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት መመልከቻ አማራጮች ይፋ ሆነዋል።
የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሚከተሉት አማራጮች ከዛሬ መስከረም 05/2018 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡
ውጤት የመመልከቻ አማራጮች፦
➫ በድረ-ገጽ፦ https://result.eaes.et
➫ በቴሌግራም ቦት፦ https://t.me/EAESbot
➫ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት፦ 6284
13/08/2025
መምህራን
“ እየተራብን አንሰለጥንም፡፡ ወደ 4000 የሚሆኑ ሰልጣኝ መምህራን ስልጠናውን አቋርጠው ዶርም ተቀምጠዋል ” - የክረምት ሰልጣኝ መምህራን
➡️ “ ክልሉ ገንዘቡን ወደ ትምህር ቢሮ አካውንት አስገብቷል፤ የግለሰቦቹን ሒሳብና አካውንት እያጣራ ነው፡፡ አጣርተው ወደ አካውንታቸው ያስገባሉ ” - ወላይታ ዩኒቨርሲቲ
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የክረምት የስልጠና ከሳምንት በፊት የጀመሩ "4000 ነን" ያሉ ሰልጣኝ መምህራን “የዩኒቨርሲቲው ምግብ ጥራት የሌለው በመሆኑና በቂ ስላልሆነ፤ አበልም ስላልተከፈለ” ስልጠናውን ለማቋረጥ መገደዳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
ከሰልኞች መካከል አንዱ በሰጡት የቅሬታ ቃል፣ “ ስልጠና እንደመሆኑ መጠን በመጀመሪያ ተዘጋጅተው ደወመዛችንንም አስገብተው ሊልኩን ሲገባ ምንም ነገር በሌለበት ሐምሌ 27/2017 ዓ/ም ትገባላችሁ ተብለን ወደ ዩኒቨርሲቲ ገባን፡፡ ስንገባ ዶሩሙም የንጽህና ጉድለት አለው፤ ካፌውም ቁርስ፣ ምሳና እራት የተመቻቻ አይደለም ” ብለዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው በቂ መድኃኒት እንደሌለና ለህመም ሁኔታ እንዳለ ገልጸው፣ ቅሬታውን ቢያቀርቡም መፍትሄ ባለመሰጠቱ “ ያለፈው ሰኞ ስልጠናውን መቀጠል አንችልም በሚል ወደ 4000 የሚጠጉ ሰልጠኞች ስልጠናውን አቋርጠው ነበር ” ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የአበሉም ደመወዙም፣ የዩኒቨርሲቲውም ያለው ጉዳይ "እናሻሽላለን" እንዳሏቸውና ስልጠናውን ቀጥለው እንደነበር፣ ሆኖም በተባለው ቀንም ቅሬታቸው ባለመፈታቱ ዛሬ ጠዋት በድጋሚ ስልጠናውን ማቆማቸውን ገልጸዋል።
“ ካፍቴሪያ ላይ የሚመች ቁርስ አይደለም ያለው፡፡ ደህና ሩዝ፣ ቅንጬ አንዳንዴ ይስጣል ግን ቢሆንም ምንም የሚመች አይደለም፤ ዘይት አይጨመርበትም፤ ውሃ ብቻ አስገብተው ያወጡት ፍርፍር ነው የሚሰጠን። የሚቀርበው ሻይም የቀዘቀዘ ነው፤ አንዳንዱ ምግብ ደግሞ የሚያቃጥል ነው፤ በዛ ላይ በቂ አይደለም፡፡ ለህመም የሚዳረግ ነው ” ብለዋል፡፡
ሌላኛው ስልጣኝ መምህር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ስልጠናው ባልተመቻቸ ሁኔታ ነው የጠሩን፡፡ ወደ ዶርም ስንስገባ ትኋን ነበረው አልተፀዳም፤ ምግብም አለ ብዬ አልልም፤ ምንም መመብላት የማይሆን ምግብ ነው፤ አበል ደግሞ ምንም የለም ” ነው ያሉት፡፡
“ ስለዚህ አንሰለጥንም ብለን ዛሬ ጠዋትም አቋርጠን ወጣን፤ ወደ ቤታችንም አልሄድንም ዶርም ቁጭ ብለናል፤ መጥቶ የሚያነጋግረን አካል ራሱ የለም” ብለው፣ “ ሲሳይ የሚባል ጓደኛዬ ሦስተኛ ቀኑ ሆስፒታል ተኝቷል በምግብ ምክንያት ታሞ፡፡ ከምግቡ በተጨማሪ ትኋን ያለበት ክፍል ስለሆነ ትኋን ደሙን ሲመጥ ታይፎይድ ተያዘ፡፡ ግቢው ሙሉ ትኋን በትኋን ነው፡፡ በዚያ ምክንያት የታመሙ ብዙ ሰዎች አሉ፤ እንድን ሰው በምለሳሌ ነው የጠቀስኩት ” ብለዋል፡፡
ቅሬታ አቅራቢ መምህራኑ፣ “ ሰርተን የምንበላ ሰዎች ነን ግን የስልጠና መስፈርቱ ተሟልቶ ቢያንስ የሰው ልጅ የሚመገበው ምግብ ይዘጋጅልን፣ የተወሰነም ቢሆንም ከዚህ ቀደም ለሰልጣኞች እንደተሰጠው ይሰጠን ፣ አበል ይከፈለን፣ ደመወዝ ይከፈለን ” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ቅሬታው ይዞ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የጠየቃቸው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር)፤ “ በኛ በኩል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ እነርሱ አበል አልተከፈለም ነው ጉዳያቸው እኛ ጋ ሌላ ጥያቄ አላቀረቡም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ሰልጣኞቹ ከምግብ ጥራት ጋር በተያያዘ ጥያቄ እንዳቀረቡ ስንገልጽላቸውም፣ “ እሱ ችግር እንደሌለ ራሳቸውን ብትጠይቁ ጥሩ ነው፡፡ ከእነርሱ ጋር ተስማተን የምግብ የመኝታ ቤት፣ የትምህርት ኮሚቴ አዋቅረን በጋር እየተሰራ ነው ያለነው” ሲሉም ተናግረ
08/10/2024
የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችለው የመቁረጫ ነጥብ ስንት ነው ?
በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን የመቁረጫ ነጥብ ፦
➡️ በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ የወንድ ተማሪዎች የሬሜዲያል የመግቢያ ውጤት ከ600ው 204 ነው።
➡️ በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ የሴት ተማሪዎች የሬሜዲያል የመግቢያ ውጤት ከ600ው 192 ሆኖ ተቆርጧል።
(ተጨማሪ የመቁረጫ ነጥብ ከላይ ተያይዟል)
ከዚህ ባለፈ ግን እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግልና በመንግስት ተቋማት) በራሳቸው ክፍያ የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ።
ይህ ማለት ፦
➡️ ከ600ው የትምህርት ብዛት ፈተናቸውን ተፈትነው 31% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ (186 እና በላይ) ፤
➡ ከ500 የትምህርት ብዛት የተፈተኑ (ዓይነስውራን ተማሪዎች) 31% እና በላይ ውጤት ያመጡ (155 እና በላይ) ፤
➡ ከ700ው የትምህርት ብዛት የተፈተኑ 31% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ (217 እና በላይ) ... በፈለጉት አማራጭ ማለትም በግል ሆነ በመንግሥት ተቋማት ከፍለው የሬሜዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ።
በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና #በቀጥታ የሚያሳልፈው ውጤት 50% እና በላይ መሆኑ ይታወቃል።
የሬሜዲያል ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ (በመንግሥት ስፖንሰርሺፕ / ተመድቦ ለመማር) ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።
በግል ከፍለው በመንግሥትም ይሁን በግል ተቋም ለመማር የሚፈልጉ ከተፈተኑት ፈተና ውጤት 31% እና በላይ ውጤት ማምጣት አለባቸው።
07/10/2024
#
for all mizan tepi university students
18/09/2024
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች በውድድር ነጻ የትምህርት እድል (ሶኮላርሺፕ) ሊሰጥ እንደሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን የመጀመርያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ተወስኖ ተማሪዎችን በራሱ የቅበላ ስርዓት ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እያከናወነ ነው።
ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያዘጋጀውን የተማሪዎች መግቢያ ፈተና ይሰጣል። በዚህም ብቃትን፣ ብዝሃነትንና ፍትሐዊነትን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎችን በውድድር ነፃ የትምህርት እድል ከዶርሚታሪና የካፌ አገልግሎት ጋር እንደሚሰጥ አሳውቋል።
አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ " ብቃትና ተሰጥዖ ያላቸው ተማሪዎች መዳረሻ ለመሆን ያለኝን ቁርጠኝነት እገልጻለሁ " ብሏል።
10/09/2024
ዮናስንጉሰ #ሔለንበርኸ👏
በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሀገሪቱ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው የትግራይ ፣ የቓላሚኖ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪው ዮናስ ንጉሰ ነው።
በትግራይ ሀገር አቀፉ ፈተና ከ700 መሰጠቱ ይታወሳል።
ተማሪ ዮናስ ንጉሰ ከ700ው 675 በማምጣት በሀገር ደረጃ ታሪካዊ ነው የተባለውን ውጤት አስመዝግቧል።
ከዚህ ቀደም ከ700 በተሰጠ ፈተና ይሄን ያህል ከፍተኛ ውጤት (675) በሀገር ደረጃ ሲመዘገብ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።
ሌላኛዋ የቓላሚኖ ተማሪ ሔለን በርኸ 662 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።
ሌሎችም የቓላሚኖ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸው ተሰምቷል።
የትግራይ ልማት ማህበር በተመዘገው ውጤት መደሰቱን ገልጿል።
ትምህርት ቤቱ እጅግ ጎበዝ የሚባሉ ተማሪዎች የሚማሩበት ነው።
10/09/2024
የአዲስ አበባዋ ተማሪ ሲፈን ተክሉ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600ው 575 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።
ሲፈን የኦግዝሌየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት።
ተማሪዋ " ጌዜን ትምህርት ላይ ማሳለፌ ፣በቡድን ማጥናቴ ፣ የቤተሰብና የመምህራኖቼ ድጋፍ ለዚህ ስኬት አብቅቶኛል " ብላለች።
ለቤተሰቦቿ 2ኛ ልጅ የሆነችው ሲፈን የስርዓተ ምግብ ባለሙያ የመሆኑ ዝንባሌ እንዳላትም ተናግራለች።
10/09/2024
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 06 እና 07/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡