Armauer Hansen Research Institute

Armauer Hansen Research Institute

Share

The Armauer Hansen Research Institute (AHRI) was founded in 1970.

Photos from AMN-Addis Media Network's post 21/05/2026
Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 21/05/2026

ሦሰት ወጣት ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች የ23ኛውን ዙር የቶሬ ጎዳል (Tore Godal) ሽልማት አሸነፉ

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) የቶሬ ጎዳል ሽልማት ኮሚቴ፤ በኢትዮጵያ የሕክምና ምርምር ዘርፍ ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ያበረከቱ 3 ወጣትና ተስፈኛ ሳይንቲስቶችን የ23ኛው ዙር የቶሬ ጎዳል ተሸላሚ አድርጓል።

በዶ/ር ቶሬ ጎዳል ራዕይ መነሻነት በየዓመቱ የሚሰጠው ይህ ታዋቂ ሽልማት፤ በሀገራችን የሚካሄደውን የጤና የምርምር ጥራት እና ስፋት ለማሻሻል እና ወጣት ተመራማሪዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የዘንድሮው የ23ኛው ዙር የቶሬ ጎዳል ሽልማት በወባ መከላከልና ቁጥጥር ላይ ያተኮሩ አስደናቂ የምርምር ሥራዎችን ያካሄዱትን ሄርመላ ብርሃኑ፣ ቤዛ ጋረደው እና ናትናኤል ለሜሳ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ለተሸላሚዎች ባስተላለፉት መልዕክት 23ኛው የቶሬ ጎዳል ሽልማት ተሸላሚዎች ላስመዘገቡት አስደናቂ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ወጣት ሳይንቲስቶቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ለሚሄደው የእውቀት ዘርፍ ውድ አስተዋፅዖ ያበረከቱ ሲሆን፣ በተለይም ወባን ለመዋጋት በምናደርገው ሀገራዊ ጥረት ውስጥ በማስረጃ ላይ ለተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ መንገድ የጠረጉ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም የቀረቡትን ማመልከቻዎች አርአያ በሆነ መልኩ በመገምገም፣ ከምርጦች ምርጡን ለሽልማት በመምረጣቸው ልባዊ ምስጋናቸውንና ታላቅ አድናቆታቸውን ለቶሬ ጎዳል ሽልማት ኮሚቴው ያቀረቡ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ1970 እስከ 1973 ዓ.ም. ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት የመሩትንና በኢትዮጵያ በጤናና በባዮሜዲካል ሳይንስ ምርምርና ልማት ዘርፍ የወጣት ምሁራንን የላቀ ብቃት ዕውቅና ለመስጠት ያለመውን ይህንን ታላቅ ሽልማት ለመሰረቱት እና የገንዘብ ድጋፍ ለሚያደርጉት ለዶ/ር ቶሬ ጎዳል ያላቸውን ጥልቅ አክብሮትና ምስጋና በድጋሚ ገልጸዋል።
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/

Website:
https://ahri.gov.et/

Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #

Youtube: https://www.youtube.com/

Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 21/05/2026

የአርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት ከፌደራል የጤና ተቋማት ጋር በጤና ምርምር ዘርፍ በጋራ ለመስራት ስትራቴጂካዊ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

የአርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ከቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል እና ከኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ጋር በሕክምና ምርምር፣ በክሊኒካል ልህቀት እና በባዮሜዲካል ፈጠራ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በይፋ ተፈራርመዋል።

ይህ ስምምነት ተቋማቱ ያላቸውን የላቀ አቅምና ጠንካራ ጎኖች በማስተባበር፣ በሀገሪቱ ጤና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መሠረት ያደረጉ የምርምርና የሕክምና ሥራዎችን በጋራ ለማከናወን ያለመ ነው፡፡

የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማ በሆስፒታሎቹና በተቋማቱ ያለውን ሰፊ የክሊኒካል አገልግሎትና የታካሚዎች ፍሰት ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የምርምርና የቴክኒክ ልምድ ጋር ማቀናጀት ፤ በምርምርና ሥልጠናዎች ላይ ትብብርን ማጠናከር፣ እንዲሁም የጋራ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን መቅረጽና መተግበር፤ በጋራ የሚመነጩ የምርምር ውጤቶችን በመተንተን ለውሳኔ ሰጪ አካላት የሚጠቅሙ የፖሊሲና የቴክኒክ ማጠቃለያዎችን ማዘጋጀት እንዲሁም ለተቋማቱ የምርምርና ልማት ፍላጎቶች ጠቃሚ የሆኑ ሳይንሳዊ መረጃዎችን በጋራ ማመንጨትና መጋራት በሚሉ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

የተቋማቱ አመራሮች ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ የጤና ምርምርና የሕዝብ ጤና አገልግሎት ላይ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍትና ከፍተኛ አገራዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል።
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/

Website:
https://ahri.gov.et/

Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #

Youtube: https://www.youtube.com/

Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 20/05/2026

አብሮነት ለተሻለ የህክምና ሙከራ ምርምር

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) እና የአለርት (ALERT) አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎችና ሰራተኞች “አብሮነት ለተሻለ የህክምና ሙከራ ምርምር” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የክሊኒካል ህክምና ሙከራ ቀንን (International Clinical Trials Day) በጋራ በድምቀት አክብረዋል።

ይህ ዕለት በህክምናው ዘርፍ አዳዲስና ፍቱን መድሃኒቶችን፣ ክትባቶችንና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ለታካሚዎች ለማድረስ በምርምር ሂደት ውስጥ ውድ ህይወታቸውንና እውቀታቸውን የሚዬዋጡ የህክምና ባለሙያዎችን ተመራማሪዎችን እና በፈቃደኝነት በሙከራው ላይ የሚሳተፉ ወገኖችን እውቅና ለመስጠት ታስቦ የሚከበር ነው።

በበዓሉ አከባበር ላይ በሁለቱም ተቋማት በኩል ጠንካራ አጋርነትንና የወደፊት የጋራ ራዕይን የሚያንጸባርቁ በርካታ ነጥቦች የተነሱ ሲሆን “አብሮነት ለተሻለ የህክምና ሙከራ ምርምር” የሚለው መሪ ቃል የሳይንስ ሊቃውንት፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ተቆጣጣሪ አካላት እና ማህበረሰቡ እጅ ለእጅ ተያይዘው ካልሰሩ በስተቀር በጤናው ዘርፍ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል አስገንዝቧል።

ዓለም አቀፍ የህክምና ሙከራ ቀን (Clinical Trials Day) በየዓመቱ ግንቦት 12 (ሜይ 20) የሚከበር ሲሆን፣ ታሪካዊ መነሻው እ.ኤ.አ በ1747 ስኮትላንዳዊው ሀኪም ጄምስ ሊንድ (James Lind) በባህር ተጓዦች ላይ ይከሰት የነበረውን የቫይታሚን ሲ እጥረት በሽታ (Scurvy) ለመከላከል የመጀመሪያውን ዘመናዊ የክሊኒካል ሙከራ (Controlled Clinical Trial) አሰራርን በይፋ የጀመረበትን ቀን ለማስታወስ ነው።

ይህ ዝግጅት የአህሪ እና የአለርት ሰራተኞች ከኢትዮጵያ የህክምና ሙከራ ህብረት (ኔትወርክ) ጋር በመተባበር የተደረገ ክብረ በዓል ሲሆን ሁለቱ ተቋማት በህክምና ምርምር እስከአሁን ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በማውሳት ለወደፊት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ በማጉላት ነበር።

በዚሁ ዝግጅት በአለርት ሆስፒታል የቆዳ ስፔሻሊሰሰት ሀኪም ለሆኑት ዶ/ር ሽመልስ ንጉሴ እሰሰከሁን በህክምና ምርምር ዘርፍ ለአበረከቱት አስተዋፆኦ እውቅና ተሰጥቷል።

የዛሬው ኩነት በኔትወርኩ ከግንቦት 12-20 "የህክምና ሙከራ ሳምንት በኢትዮጵያ " በሚል ከሚደረጉ ዝግጅቶች የመጀመሪያው ነው።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/

Website:
https://ahri.gov.et/

Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #

Youtube: https://www.youtube.com/

Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 19/05/2026

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የሳይንስ አማካሪ ቦርድ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) በሕክምና በባዮሜዲካልና በጤና ዘርፍ ያከናወናቸውን የምርምር ተግባራት ለመገምገም እና የወደፊት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን ለመቀየስ የሚያስችለውን ዓመታዊ የሳይንስ አማካሪ ቦርድ (Scientific Advisory Board - SAB) ጉባኤ በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህ ከፍተኛ የሳይንሳዊ ምክክር መድረክ ላይ የቦርዱ አባላት፣ ዓለም አቀፍና አገር በቀል ከፍተኛ ተመራማሪዎች፣ የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች እና የኢንስቲትዩቱ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሳይንሳዊ አማካሪ ቦርድ አባላት በተገኙበት በሚካሄደው በእዚህ ከፍተኛ የውይይት መድረክ ላይ፣ የሀብት እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች የተቅማጥ በሽታዎችን (Diarrheal Diseases) ለመከላከል የሚያስችሉ የምርመራና የክትባት አማራጮች፣ በድንገተኛ ወረርሽኞችና ከዚያም ባሻገር የክሊኒካል ሙከራዎችን አስቀድሞ ለማዘጋጀት ከማርበርግ ቫይረስ ክሊኒካዊ የክትባት ሙከራ የተገኙ ልምዶች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ሁኔታ የማጅራት ገትር (Meningitis) በሽታን አስቀድሞ የመለየትና የክትትል ሥርዓቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፋ ያሉ ማብራሪያዎች ቀርበው ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ባለፉት ዓመታት ሳይንሳዊ ግኝቶቻችን በታዋቂ ዓለም አቀፍ የሳይንስ መጽሔቶች ላይ ቢታተሙም፤ ሳይንቲስቶቻችን በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ምርጥ ተሳትፎ ቢያደርጉም፤ በሀገር ውስጥ ግን ተቋማችን በሰፊው አይታወቅም ነበር። አሁን ግን በክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተደረገው የላቦራቶሪ ኮምፕሌክስ ምርቃት የ AHRIን ሀገራዊ ታይነት በእጅጉ ለመጨመር ረድቶናል ሲሉ የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ገልፀዋል።

የሳይንስ አማካሪ ቦርዱ በቆይታው የኢንስቲትዩቱን የምርምር ጥራትና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ሳይንሳዊ ግብረ-መልሶችንና ምክረ-ሀሳቦችን የሚያቀርብ ሲሆን፥ የምርምር ውጤቶች ወደ ጤና ፖሊሲና የጤና ክብካቤ አገልአገልግሎት መለወጥ በሚችሉበት አግባብ ላይም አቅጣጫ ያስቀምጣል።

የሳይንስ አማካሪ ቦርዱ ሰብሳቢ ፕ/ር ፅጌ ገ/ማርያም ወረርሽኞች፣ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ (Antimicrobial Resistance)፣ አዳዲስ ኢንፌክሽኖች፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ በሽታዎች እና የጤና ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት እኩል አለመሆን ማኅበረሰባችንን በሥጋት ላይ በጣሉበት በዛሬው ዓለም ውስጥ፥ እንደ አህሪ ያሉ ተቋማት የቅንጦት መገለጫዎች አይደሉም፤ ይልቁንም ለሀገር ህልውና አስፈላጊ የሆኑ መሠረታዊ ፍላጎቶች ናቸው ብለዋል።

ይህ ዓመታዊ ጉባኤ ኢንስቲትዩቱ በምስራቅ አፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የምርምር መሪነት ሚና ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። መድረኩ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 16/05/2026

የድህረ-ማርበርግ ወረርሽኝ የምርምር ጥናትን የተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ : አርባ ምንጭ :ወላይታ ሶዶ እና በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ላይ ተካሄደ።

በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የድህረ-ማርበርግ ወረርሽኝ የምርምር ተግባራትን የተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በተለያዩ ከተሞች ተካሂዷል።

ይህ መድረክ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በሀገር ደረጃ ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝን የመከላከል ሂደት እንዴት እንደተመራ ለመገምገም እና በቀጣይ የዚህ መሰል የጤና ስጋቶች በሚከሰቱበት ወቅት በጥናትና ምርምር የታገዘ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ጥናት ለማድረግ ነው።

በውይይት መድረኮች ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሆስፒታል ሀላፊዎች የዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

መድረኮቹ በሃይማኖት አባቶች የምርቃት ፀሎት የተከፈቱ ሲሆን ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ማህበረሰቡና የጤና ባለሙያዎች እጅግ አስደንጋጭና ፈታኝ ጊዜ ማሳለፋቸውን በማንሳት ያንን አስቸጋሪ ወቅት በድል ለመሻገር አብረው ለነበሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የጤና ፅ/ቤት ሀላፊዎችና ለአህሪ ተመራማሪዎች ምስጋና ቀርቧል። በቀጣይም መሰል አደጋዎች ሲገጥሙ በቅድመ ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ ዝግጁነት መፍጠር እንደሚገባ በመድረኮቹ ተገልጿል።

በሁሉም መድረኮች የኢንስቲትዩቱን ዋና ዋና የምርምር ውጤቶችና በቀጣይ ሊከናወኑ ስለታሰቡ የትብብር ስራዎች ዝርዝር ማብራሪያ ቀርቧል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በምርምርና በስልጠና ረገድ የተከናወኑ ተግባራትን እንዲሁም በማርበርግ ወረርሽኝ ወቅት የተሰሩ ስራዎችም በዝርዝር ቀርበዋል።

በተያያዘም በአህሪ ተመራማሪዎች በወረርሽኙ ዙሪያ በሚከናወኑ ጥናቶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ጥናቱ በወረርሽኙ መከላከልና ቁጥጥር ሂደት ውስጥ የታዩ ሳይንሳዊ እና ተግባራዊ ተሞክሮዎችን በሰነድ በመቀመር ለቀጣይ ዝግጁነት በግብዓትነት ለመጠቀም ያለመ ነው።

በማንኛውም የጤና ምርምር ሂደት ውስጥ የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎና ግንዛቤ ለውጤታማነቱ ወሳኝ መሆኑን የሚያስገነዝብ ገለፃም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኮቹ ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ተሠጥቷል።

የውይይት መድረኮቹ የጥናትና ምርምርን ወሳኝነት ከማሳየታቸውም በላይ በአህሪ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በጤና መዋቅሮች መካከል ያለውን ቅንጅት ይበልጥ ያጠናከሩ መሆናቸው ተነግሯል።

በመጨረሻም የጥናቱ ውጤት ለታለመለት ግብ እንዲበቃ ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ በማቅረብ ውይይቶቹ ተጠናቀዋል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopi

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 15/05/2026

የኢትዮጵያ ጤና ግብዓት አምራቾች እና የፋርማሲ ሙያ ዘርፍ ማህበራት የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

የኢትዮጵያ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማህበር: የኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር አመራሮች: በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባሕል ሕክምና አዋቂዎች ማህበር እና ሌሎች የጤና ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ጉብኝት አደርገዋል።

ጎብኚዎቹ የኢንስቲትዩቱን አዲስና ዘመናዊ የምርምር ላቦራቶሪዎች ኮምፖሌክስ፣ ለምርምር ተግባር የሚውሉ የላብራቶሪ እንስሳት እርባታና የምርምር ቤተ-ሙከራ: የተቋሙን መሰረተ ልማቶች ተመልክተዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ በተደረገው ውይይት፣ እንግዶቹ በሀገራችን በዚህ የላቀ ደረጃ የተደራጀ የምርምር እና የባዮ ኢኩቫለንስ (Bio-equivalence) ማዕከል በመኖሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። በውይይቱ ወቅት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተነስተዋል፦
የሰው ኃይል ልማት፦ ቤተ-ሙከራዎቹንና ማሽኖቹን በብቃት ለመምራትና አገልግሎታቸውን ለማስቀጠል የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊነት።
ገቢ ማስገኛ፦ የተቋሙን መሰረተ ልማቶች ለገበያ በማቅረብ ገቢ እንዲያስገኙ ማድረግ።
የትብብር ስራ፦ ከኢንዱስትሪዎች: ከዩኒቨርስቲዎችና ከሌሎች መሠል የምርምር ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችሉ መንገዶችን ማመቻቸት።

በዚሁ መድረክ ላይ ኢንስቲትዩቱ ከብሉም ፐብሊክ ሄልዝ (Bloom Public Health)፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባሕል መድኃኒት አዋቂዎች ማህበር እና ከባህል መድኃኒት አዋቂው አቶ ጋሻው አለሙ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ እና የውል ስምምነት ተፈራርሟል። የአህሪ ዋና ዳሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ጎብኚዎቹ ስለሰጡት ምክረ ሀሳብ አመስግነው፤ በዛሬው ለት የተደረገው የስምምነት ፊርማ የቅንጅት ማሳያ ነው ብለዋል፤ እንዲሁ ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማትም በቅንጅት ለመስራት የድርሻቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር መሳይ ወልደማርያም እንደገለጹት፣ ከባህል መድኃኒት አዋቂዎች ጋር የተደረገው ስምምነት የሀገር በቀል መድኃኒቶች በሳይንሳዊ ምርምር አልፈውና የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲመዘገቡ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ፋይዳ አለው። አክለውም በኢንስቲትዩቱ የምርምር ውጤት የሆኑ መድኃኒቶች በስፋት ለምርት እንዲበቁ የመድኃኒት አምራች ኢንዱስትሪዎች ከተቋሙ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የአህሪ ም/ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር አለምሰገድ አብዲሳም ብዙ ማነቆዎች ቢኖሩብንም፤ ብሩህ ተስፋ እና የተነቃቃ የሰው ሀይል አለን። እነዚህን አስተባብረን እየሰራን ነው ብለዋል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Ethiopian News Agency's post 14/05/2026
Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 13/05/2026

የኢትዮጵያና ቻይና የጤና ትብብር አዲስ ምዕራፍ፦ የአርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩትን አቅም የሚያሳድግ መርሃ ግብር ተጀመረ

በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ግምት የሚሰጠው የቻይና ከፍተኛ የሕክምና ባለሙያዎች የምክር ልዑክ (Senior Expert Advisory Mission) በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) በይፋ ሥራውን ጀምሯል።

ከግንቦት 2 እስከ ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከሜይ 10 እስከ ጁን 15 ቀን 2026) የሚቆየው ይህ ተልዕኮ፣ ዘላቂ የአቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረጉ ልዩ ጠቀሜታ እንዲኖረው ያደርገዋል። መርሃ ግብሩ በተለይም የቤተ ሙከራ አመራር እና አስተዳደር ፣የባዮ ሴፍቲ እና ባዮ ሴኩሪቲ (Biosafety and Biosecurity) ፣የጄኔቲክ ኢንጂነሪንግ (Genetic Engineering) ፣የክሊኒካዊ ሙከራዎች እና የባዮኤኩይቫለንስ (Clinical Trials and Bioequivalence) እንዲሁም የባዮአናሊቲካል (Bioanalytical) አገልግሎቶች የቴክኒክ ዘርፎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፣ ይህ ትብብር ከቴክኒካዊ ድጋፍ ባለፈ በሰው ሀብት ልማት ላይ የተደረገ ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው። ሚኒስትሯ አክለውም “ይህ ዘመናዊ መሠረተ ልማት ሙሉ አቅሙን እውን ለማድረግ ከሚያስፈልገው የሰው ኃይል ክህሎት፣ የሥራ ክንውን ጥራት እና የሳይንሳዊ አመራር ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ ዛሬ ቀጣዩን ወሳኝ እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ በበኩላቸው፣ አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን የጤና ነፃነት (Health Independence) ለማረጋገጥ ቁልፍ ተቋም መሆኑን ገልጸው፣ ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፣ ተቋሙ ባለፉት 56 ዓመታት ውስጥ በሥጋ ደዌ (Leprosy) ምርምር ተጀምሮ ዛሬ ለአህጉሪቱ የሚተርፍ የፈጠራ ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል። ከቻይና የምርምርና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

ይህ የምክር ልዑክ በቆይታው የቤተ ሙከራ አመራር ሥርዓትን ከማዘመን ባለፈ፣ በመድኃኒትና ክትባት ምርምር እንዲሁም በጂኖም ቴክኖሎጂ ዙሪያ ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ታውቋል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Photos from Armauer Hansen Research Institute's post 10/05/2026

የድህረ-ማርበርግ ወረርሽኝ የምርምር ጥናትን የተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሄደ::

በአርባ ምንጭ ከተማ በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የድህረ-ማርበርግ ወረርሽኝ የምርምር ተግባራትን የተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ይህ መድረክ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በሀገር ደረጃ ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝን የመከላከል ሂደት እንዴት እንደተመራ ለመገምገም እና በቀጣይ የዚህ መሰል የጤና ስጋቶች በሚከሰቱበት ወቅት በጥናትና ምርምር የታገዘ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ጥናት ለማድረግ ነው።

በመድረኩ ላይ የአርባ ምንጭ ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ፣ የአርባ ምንጭ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራሮች ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

መድረኩ የአርባ ምንጭ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አንተነህ ካሳዬ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ማህበረሰቡና የጤና ባለሙያዎች እጅግ አስደንጋጭና ፈታኝ ጊዜ ማሳለፋቸውን አስታውሰው ያንን አስቸጋሪ ወቅት በድል ለመሻገር አብረው ለነበሩ የሃይማኖት አባቶች፣ ለአህሪ ተመራማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል። አያይዘውም በቀጣይ መሰል አደጋዎች ሲገጥሙ በቅድመ ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ ዝግጁነት መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአህሪ የእውቀት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አክሊሉ አለሙ የኢንስቲትዩቱን ዋና ዋና የምርምር ውጤቶችና በቀጣይ ሊከናወኑ ስለታሰቡ የትብብር ስራዎች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አክለውም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በምርምርና በስልጠና ረገድ የተከናወኑ ተግባራትን እንዲሁም በማርበርግ ወረርሽኝ ወቅት የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

በተያያዘም ዶ/ር አቸንፍ ኪዳኔ እና ዶ/ር ተስፋዬ ገላነው በወረርሽኙ ዙሪያ በሚከናወኑ ጥናቶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ጥናቱ በወረርሽኙ መከላከልና ቁጥጥር ሂደት ውስጥ የታዩ ሳይንሳዊ እና ተግባራዊ ተሞክሮዎችን በሰነድ በመቀመር ለቀጣይ ዝግጁነት በግብዓትነት ለመጠቀም ያለመ ነው።

ወ/ሮ ብዙነሽ ስንታየሁ በገለፃቸው በማንኛውም የጤና ምርምር ሂደት ውስጥ የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎና ግንዛቤ ለውጤታማነቱ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ዶ/ር ተክሉ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ፕሬዝዳንት በድህረ ማርበርግ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ይህ መድረክ በጤና ጥበቃ ረገድ የጥናትና ምርምርን ወሳኝነት ከማሳየቱም በላይ አህሪ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በጤና መዋቅሮች መካከል ያለውን ቅንጅት ይበልጥ ያጠናከረ መሆኑ ተነግሯል። በመጨረሻም የጥናቱ ውጤት ለታለመለት ግብ እንዲበቃ ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ በማቅረብ መድረኩ ተጠናቋል።

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00