18/05/2026
ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩት ውጤት ያስመዘገበው የአካቶ ትምሕርት - ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Reliable News Source In Ethiopia
ኦቲዝም ያለባቸውም ሆኑ ሌሎች አካል ጉዳተኛ ልጆች መማርና ማደግ ይችላሉ፡፡ ለቤተሰባቸው፣ ለማኅበረሰባቸውና ለአገራቸው አስተዋጽኦ ማበርከትም የሚችሉ ናቸው፡፡ ሆኖም እንዲህ ያለው ....
29/04/2026
Fana Entertainment
7 likes. "ኦቲዝም የሚለፋበትን ያህል አስቸጋሪ አይደለም |የእሳት ዳር ጨዋታ| ኦቲዝም"
25/04/2026
ሻምፒየንስ አካዳሚ # Champions Academy
19ኛው የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ
ኦቲዝም እና ሰብአዊነት – እያንዳንዱ ሕይወት ዋጋ አለው!!!
ኦቲዝምና የሻምፒየንስ አካዳሚ የአካቶ ጉዞ
ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናይ ጉዟችን ቀላል አልነበረም፤ ነገር ግን እጅግ አስፈላጊ፣ ትርጉም ያለው እና ውጤቱ የሚታይ ታላቅ ጉዞ ነበር።
እንደ ትምህርት ቤት እና እንደ ማህበረሰብ ረጅም መንገድ ተጉዘናል። ከዓመታት በፊት ስለ አካል ጉዳተኝነት እና ስለ ኦቲዝም ማውራት ስንጀምር፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ያለው ግንዛቤ እጅግ አነስተኛ ነበር። "አካታች ትምህርት" (Inclusive Education) የሚለው ቃል በወቅቱ እንግዳ ከመሆኑም በላይ፣ እንደ አማራጭ እንኳ የማይታሰብበት ጊዜ ነበር። በዙሪያችን የእርግጠኛነት ማነስ፣ ተቃውሞ እና አንዳንዴም ዝምታ የሰፈነበት ነበር።
እኛ ግን ዝምታን አልመረጥንም!
በመምህራን፣ በወላጆች እና በሰፊው ማህበረሰብ ውስጥ ግንዛቤ ለመፍጠር አቅደን እርምጃዎችን መውሰድ ጀመርን። ስልጠናዎችን ሰጠን፤ የፓናል ውይይቶችን አዘጋጀን፤ ቀደም ሲል ተዘግተው የነበሩ የውይይት በሮችን ከፈትን። ከግንዛቤም ባለፈ ወደ ተግባር ተሸጋገርን።
አካታችነትን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ወሰንን።
ይህ ውሳኔ ግን የራሱ ዋጋ ነበረው። ኦቲዝም ካለባቸው ልጆች ጋር ልጆቻችንን አብረን አናስተምርም ያሉ ወላጆች ትምህርት ቤቱን ጥለው የሄዱበት፣ ጥያቄዎችና ጥርጣሬዎች የበዙበት አስቸጋሪ ወቅት ነበር። ነገር ግን እኛ በአላማችን ጸናን። እውነተኛ ለውጥ ሁልጊዜም ምቹ እንዳልሆነ እንረዳ ነበር፤ ለውጥ ጽናትን፣ ትዕግስትን እና ግልጽ ራዕይን ይጠይቃል የሚለውን የሁልጊዜ አስተሳሰባችንን እንደሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገን አውለበለብን።
ከዚህም የተነሳ ዛሬ ላይ ሆነን ጽናት ውጤት እንደሚያመጣ ህያው ምስክሮች ሆነን ቆመናል!
ከዓመታት ትግል በኋላ፣ ዛሬ ትምህርት ቤታችን ለአካታች ትምህርት እንደ ተምሳሌት (Model) ይጠቀሳል። ይህ ውጤት በአንድ ጀምበር የመጣ አይደለም፤ የጽናት፣ የቡድን ስራ እና የማይናወጥ እምነት ውጤት ነው።
ኦቲዝም ያለባቸውም ሆነ ሌሎች አካል ጉዳት ያለባቸው ልጆች መማር፣ ማደግ እና ለቤተሰባቸው፣ ለማህበረሰባቸው እንዲሁም ለሀገራቸው ትልቅ አስተዋፅዖ ማድረግ እንደሚችሉ ያለ ምንም ጥርጥር እናምናለን። ይህ እምነታችን ደግሞ በንድፈ-ሐሳብ ብቻ የቀረ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጠ ነው።
በዚህም ተጨባጭ ውጤቶችን አይተናል!
• ተማሪዎቻችን የሚኒስትሪ ፈተና ሲወስዱ ከመንግስት ጋር ተደጋጋሚ ፅናትን የሚፈትን ውይይት አድርገን የግል ፈታኞች እንዲመደብላቸው አድርገናል፡፡
• ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎቻችን የሚኒስትሪ ፈተናዎችን ወስደው በቂ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ቀጣዩ ክፍል አልፈዋል። ይህን ድል አንዴ ብቻ ሳይሆን ደጋግመን አሳይተናል። ገናም እናሳያለን፡፡
• ከእኛ አልፈው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መግባት የቻሉ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች አብቅተናል ። እነዚህ ትናንሽ ስኬቶች አይደሉም፤ እነዚህ ውጤቶች አቅምን፣ ብቃትን እና ታላቅነትን የሚያረጋግጡ ትልልቅ ስኬቶች ናቸው።
የዚህ ጉዞ አስደናቂው ክፍል ደግሞ በመላው የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ ላይ የፈጠረው ተጽዕኖ ነው።
በእኛ ትምህርት ቤት አካታችነት በወረቀት ላይ የሰፈረ መመሪያ ብቻ አይደለም፤ በየቀኑ የምንኖረው ባህላችን እንጂ፡፡ ከጽዳት ሰራተኞች እስከ ጥበቃ አባላት፣ ከመምህራን እስከ ከፍተኛ አመራሩ ድረስ እያንዳንዱ የማህበረሰባችን አባል የራሱ ድርሻ አለው። እዚህ አካታችነት የቡድን ስራ ነው፤ የጋራ ኃላፊነት ነው፤ በንቃት የሚተገበር እሴት ነው።
ምናልባትም ከሁሉም በላይ ትልቁ ስኬታችን መደበኛ ተማሪዎቻችን (Typical students) ላይ ያመጣነው ተፅዕኖ ነው። ይህውም የመደበኛ ተማሪዎች(Typical students) ልዩ ክትትል የማያስፈልጋቸው ተማሪዎቻችን ስለአካታችነት የማይረሱት ታላቅ ትምህርት ተምረዋል፡፡ እነዚህ መደበኛ ተማሪዎቻችን (Typical students) ስለ አካታችነት የተማሩት በንድፈ ሀሳብ ሳይሆን አብረው በመኖር ነው። ሌሎችን የመቀበል፣ የመደገፍ እና አብሮ የመቆም ባህልን አዳብረዋል። ይህ ደግሞ ጊዜያዊ ትምህርት ሳይሆን የህይወት ዘመን እሴት ነው። እነዚህ ልጆች በህይወት አካታችነትን የሚያስፋፉ እና ማንም ወደ ኋላ የማይቀርበትን ዓለም የሚገነቡ ዜጎች እንዲሆኑ አድርገን ሰርተናቸዋል።
ይህ ሁሉ ውጤት በትምህርት ቤቱ እና በወላጆች መካከል ባለው ጠንካራ ጥምረት የተገኘ ነው። የእናንተ እምነት፣ ትብብር እና ቁርጠኝነት ለዚህ ሁሉ መሰረት ሆኖናል። ይህ የሁላችንም የጋራ ድል ነው።
እዚህ ላይ ግን አንቆምም!
በትልቅ ራዕይ እና በቁርጠኝነት ወደ ፊት እንመለከታለን። አላማችን ተደራሽነታችንን ማስፋት ነው፤ አካታች የሆነ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ቀጥሎም አካታች የሆነ ኮሌጅ የመመስረት ህልም አለን። ምክንያቱም አካታችነት በአንድ የትምህርት እርከን ብቻ መገደብ የለበትም፤ ማደግና መጥለቅ ይኖርበታል።
ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች የተሟላ ዕድል ይገባቸዋል። ኃላፊነትን መውሰድ እንደሚችሉ እናምናለን፤ አስተዋፅዖ ማድረግ እንደሚችሉ እናምናለን
20/04/2026
የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ 2018 ዓ.ም
Autism Awareness Day 2026
09/04/2026
የትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ፣ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ልጆች ለሚያሳድጉ ወላጆች አልባሳት እና ምግብ ልገሳ እንዲደረግ አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ ሻምፒየንስ አካዳሚ ፣ የሻምፒየንስ ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ እናመሰግናለን ።
02/04/2026
ሻምፒየንስ አካዳሚ.....በቀዳሚነት በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ልጆችን በማካተት ለከፍተኛ ስኬት በማብቃት ፤ ለወላጆች ተስፋ በመስጠት፤ በማገዝ እና ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ይቀጥላል ... ይቀጥላል ... ይቀጥላል ....
0930303235/0946417368
06/01/2026
The Champions❤️❤️❤️28/04/2018 E.C