አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ page

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ page

Share

ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር ናት ! ETHIOPIA ...FIRST

08/04/2026

✨ በጽዮን ማዕድ ላይ የታየው ጥላ፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ምስጢር
__-_____( #ክፍል፲፰

በዚያች ምሽት፣ የኢየሩሳሌም ሰማይ በከዋክብት ተሞልቶ ነበር፤ በጽዮን አዳራሽ ውስጥ ግን ከከዋክብቱ ብርሃን ይልቅ አንድ የሚቃጠል ምስጢር ሰፍኗል። ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት በማዕድ ተቀምጠዋል—አንዱ ለዘላለም ሊከብር፣ ሌላው ለዘላለም ሊጠፋ። በመካከላቸው ግን ፍጹም ፍቅርና ፍጹም ክፋት ፊት ለፊት ተፋጠዋል። ጌታ ዝቅ ብሎ የከዳተኛውን እግር ሲያጥብ፣ በይሁዳ ኪስ ውስጥ የነበሩት ሰላሳ የብር ሳንቲሞች በፀጥታው መካከል የሞት ዜማ ያሰሙ ነበር። ይህ ታሪክ ስለ ክህደት ብቻ አይደለም፤ እስከ መጨረሻዋ ቃላት ድረስ ታግሶ ለሚያነበው መለኮታዊ ፍቅር እንጂ። ኑ፣ የዚያን አስደንጋጭ ምሽት ምስጢር አብረን እናስታውስና እራሳችንን እንፈትሽበት...

በዚያች ረቂቅና በምስጢር በተሞላች ምሽት፣ በጽዮን አዳራሽ ውስጥ የታየው ትዕይንት ተራ የማዕድ ጨዋታ አልነበረም፤ ይልቁንም የሰማይና የምድር ጌታ የሆነው የብርሃን ምንጭ፣ ከጥልቁ ጨለማ ጋር ፊት ለፊት የተጋጠመበት ታላቅ መድረክ እንጂ።

​በዚያች ሰዓት ዓለም በከባድ እንቅልፍ ተውጣ ነበር፤ በጽዮን ማዕድ ላይ ግን የሰው ልጅ ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት ፍልሚያ እየተካሄደ ነበር። በአንድ በኩል፣ ፍጹም የሆነው መለኮታዊ ፍቅር በሰው ሥጋ ተገልጦ ይታያል፤ በሌላ በኩል ደግሞ፣ በሰው ልብ ውስጥ የሰፈረውና በፍቅረ ንዋይ የጠቆረው ክፋት ይታያል። እስኪ የዚያን ስፍራ አንድ ነጠላ ታሪክ ብቻ ድባብ እንቃኘው፦

⚜️ ስሙና ትውልዱ፦ ይሁዳ "አስቆሮቱ" የተባለው ከይሁዳ አውራጃ በስተደቡብ በኩል ካለችው "ቂርያት ሐጾር" በመጣው ስሙ ነው። ይህም ከገሊላ ሰዎች (ከሌሎቹ ሐዋርያት) በትውልድ የተለየ ነበር (ኢያሱ 15፡25) ጥቁሩ ጥላ ... ይሁዳ አስቆሮታዊ!!

⚜️ ​ድብቁ ማንነት፦ ጌታን ይከተል በነበረበት ወቅት የሐዋርያት የገንዘብ ያዥ ቢሆንም፣ በልቡ ግን (በስውር) ሌባ እንደነበረ ተመዝግቧል። (ዮሐንስ 12፡6)

​ሀ. ዝቅ የሚለው ጌታና ትዕቢተኛው ደቀ መዝሙር፦
​የፍቅሩ ግጥሚያ የጀመረው በውኃ ማጠቢያውና በመጥረጊያው ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚለን፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዕዱን ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት ተነሥቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብ ጀመረ። እስኪ ሕሊናችሁን ሰቅዞ የሚይዘውን ይህን ትዕይንት አስተውሉ፡ ኪሩቤልና ሱራፌል በፊቱ በፍርሃት የሚንቀጠቀጡለት ጌታ፣ ጎንበስ ብሎ የይሁዳን እግር ይይዛል።

​ያ እግር ወደ ክፋት ለመሮጥ የተዘጋጀ፣ በሰላሳ ብር ጥም የቆሸሸ እግር ነበር። ጌታ ግን በዚያች ሰዓት ይሁዳን እንደ ጠላት ሳይሆን፣ ሊያድነው እንደሚገባው በግ የጠፋ ልጅ ተመለከተው። የጌታ እጅ የይሁዳን እግር ሲያጥብ፣ ፍቅር ክፋትን ለማሸነፍና በንስሐ ውኃ የልቡን እድፍ ለማጥራት ያደረገው የመጨረሻው ጥረት ነበር።

​ለ. የይሁዳ "ሐፍረተ ቢስነት" እና የጌታ ዝምታ፦
​ወንጌላዊው ማቴዎስ “ከዐሥራ ሁለቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ” ሲል፣ በዚያ ቅዱስ ስብስብ ውስጥ የተገኘውን የይሁዳን ድፍረት ይገልጻል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን “ሐፍረተ ቢስነት” ይለዋል። ይሁዳ ክፉ አውሬ ሆኖ ሳለ፣ በየዋሃኑ በጎች መካከል ተቀመጠ። የሚገርመው ግን የጌታ ዝምታ ነው። ጌታ ይሁዳን ከመካከላቸው አላባረረውም፤ “አንተ ከዳተኛ፣ እግርህን አላጥብም” አላለውም።

​ይህ ዝምታ የድክመት ሳይሆን የጥበብ ዝምታ ነበር። ጌታ ይሁዳን ለብቻው ጠርቶ “ምስጢርህን አውቄብሃለሁ” ቢለው ኖሮ፣ ይሁዳ በኀፍረት ተቃጥሎ ይበልጥ ሊጨክን ይችል ነበር። ይልቁንም ጌታ በደፈናው “ከእናንተ አንዱ” በማለት ተናገረ። ይህ አገላለጽ ይሁዳ በራሱ ሕሊና ተከሶ፣ ማንም ሳያውቅበት ንስሐ ገብቶ ወደ ፍቅሩ እንዲመለስ የተዘረጋ ድልድይ ነበር።

​ሐ. የወጪቱ ምስጢር፡ የክፋት ጥግ፦
​ግጥሚያው ይበልጥ እየከረረ የመጣው እጃቸውን ወደ ወጪቱ ባጠለቁ ጊዜ ነው። ጌታችን “ከእኔ ጋር እጁን ወደ ወጪቱ ያጠለቀ ርሱ ነው” ሲል፣ ይሁዳ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ እጁን ወደ ማዕዱ ይሰድ ነበር። የፍቅር ጥጉ አብሮ መብላትና መጠጣት ሲሆን፣ የክፋት ጥጉ ደግሞ አብሮ እየበሉ ለሞት አሳልፎ መስጠት ነው።

​በዚህ ትግል ውስጥ ፍቅር መሣሪያው ትሕትና እና ትዕግሥት ሲሆን፣ ክፋት ደግሞ መሣሪያው ግብዝነት እና ጭካኔ ነበር። ጌታ ይሁዳን በትሕትና እየተመለከተው፣ ይሁዳ ግን ጌታውን በሰላሳ ብር ዋጋ ይመዝነው ነበር።

ጌታችን በዚያች ምሽት ለይሁዳ ያሳየው ፍቅር፣ እኛ በበደልን ጊዜ እርሱ ወደ እኛ የሚመጣበትን መንገድ ያሳየናል። ክፋት በልባችን ቢሰፍርም፣ እርሱ ግን አሁንም እግራችንን ሊያጥብና በማዕዱ ሊያቆየን ይፈልጋል። ይሁዳ ግን ያንን የመለኮት እጅ ገፋ፤ የፍቅርን ጥሪ በክፋት ድምፅ አፈነው። ከዚህ በኋላ የሆነው እንዲህ ነበር፦

በጽዮን አዳራሽ ውስጥ የነበረው ድባብ ይበልጥ እየከበደ፣ አየሩም በምስጢር እየታመሰ መጣ። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማዕዱን (ኅብስቱን) ቆርሶ፣ ጽዋውንም አንሥቶ ለወዳጆቹ ሊሰጥ ሲዘጋጅ፣ በአንጻሩ ግን በአንዱ ደቀ መዝሙር ልብ ውስጥ ሌላ ዓይነት "ሒሳብ" ይሰላ ነበር።

⚜️ የመጨረሻው እራት ውጥረት፦ ጌታ "ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል" ሲል ያሳየው መለኮታዊ ኀዘን። (ማቴዎስ 26፡21-25)

⚜️ ​የሰይጣን መግባት፦ ይሁዳ ከጌታ እጅ ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ሰይጣን እንደገባበት የሚገልጸው ጥቅስ። (ዮሐንስ 13፡27)

⚜️ ​በትንቢት መነገሩ፦ "አብሮኝ እንጀራ የሚበላ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ" የሚለው የዳዊት ትንቢት በይሁዳ ላይ መፈጸሙ። (መዝሙር 41፡9)

የሆነው እነሆ እንዲህ ነበር፦
​በዚያች ሌሊት በይሁዳ ኪስ ውስጥ የሚሰማው የብር ሳንቲሞች ድምፅ፣ ከሰማይ መላእክት ዝማሬ ይልቅ በጆሮው ውስጥ ጎልቶ ይሰማው ነበር። ሰላሳው ብር ተራ ገንዘብ አልነበረም፤ የዓለምን መድኃኒት ለማስገደል የተቆረጠ የሞት ዋጋ፣ የይሁዳንም ነፍስ ከብርሃን ዓለም ለይቶ ያሰረ የጨለማ ሰንሰለት እንጂ።

​ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን፣ ይሁዳን እንዲህ ያለ ታላቅ ድፍረትና ጭካኔ ውስጥ የከተተው "ፍቅረ ንዋይ" ነው። ገንዘብን መውደድ ልክ እንደ ከባድ በሽታ የሰውን ሕሊና ያደነዝዛል። ይሁዳ ከጌታው ጋር ለሦስት ዓመታት ተጉዟል፤ ሙታን ሲነሡ፣ ዕውራን ሲበሩ፣ ባሕሩ ፀጥ ሲል አይቷል። ነገር ግን የብር ሳንቲሞች ብልጭታ የእነዚህን ሁሉ ተአምራት ትዝታ ጋረደበት።

​ያደነዘዘው ፍቅረ ንዋይ ምን ያህል ከባድ እንደነበር ተመልከቱ፤ ጌታ "ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል" ሲል፣ ዐሥራ አንዱ ቅዱሳን ሐዋርያት በፍርሃትና በጭንቀት "ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?" እያሉ ሲንቀጠቀጡ፣ ይሁዳ ግን በድፍረት ያንኑ ጥያቄ ደገመው። ራሱ የሚያደርገውን እያወቀ "እኔ እሆንን?" ብሎ መጠየቁ፣ ሰይጣን በልቡ ውስጥ የሠራው የድንዛዜ ግንብ ምን ያህል ጽኑ እንደነበር ያሳያል።

⚜️ እግር ማጠብ፦ ጌታ የይሁዳን እግር ያጠበበት ትዕይንት። (ዮሐንስ 13፡1-11)። እዚህ ጋር "እናንተ ንጹሐን ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም" በማለት ይሁዳን ሳይጠቅስ በረቂቅ ሲገሥጸው እናያለን።

⚜️ ​የብርሃንና የጨለማ መለያየት፦ ይሁዳ ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው ወጣ፤ ወንጌላዊው ዮሐንስ ይህንን ሲገልጽ "ሌሊትም ነበረ" ይላል። ይህ የይሁዳ ነፍስ ወደ ዘላለም ጨለማ መጓዟን የሚያሳይ ምሳሌያዊ አገላለጽ ነው። (ዮሐንስ 13፡30)

​ጌታችን እንዲህ አለ፦ "የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት!" ይህ ቃል በብዙዎቻችን ጆሮ እንደ እርግማን ሊሰማ ይችላል። ነገር ግን ምስጢሩ ሌላ ነው። ጌታ ይህን ያለው ይሁዳን ለመርገም ወይም ለመበቀል ሳይሆን፣ ሊወድቅበት ካለው የጥልቁ ጥልቁ አዘቅት ሊቀሰቅሰው ፈልጎ ነው። "ወዮ" የሚለው ቃል የፈጣሪ የኀዘን ድምፅ ነው። ልክ አንዲት እናት ልጇ ወደ እሳት ውስጥ ሲገባ አይታ በድንጋጤ "ወዮልህ ልጄ!" እንደምትል ዓይነት።

​ይህ "ወዮታ" ይሁዳን ከእንቅልፉ ለመቀስቀስ የተተኮሰ የመጨረሻው የፍቅር ቀስት ነበር። ጌታ የይሁዳን ስም ሳይጠቅስ "ለዚያ ሰው" ማለቱ፣ አሁንም ቢሆን ንስሐ ገብቶ እንዲመለስና በታሪክ ፊት ስሙ በክፋት እንዳይነሣ ዕድል መስጠቱ ነበር።

​ጌታችን ጨምሮ የተናገረው ቃል እጅግ ያስፈራል፦ "ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር።" ይህ አገላለጽ የይሁዳን የጥፋት ጥልቀት ይገልጻል። መወለድና መኖር ጸጋ ነው። ነገር ግን የሕይወትን ምንጭ (ክርስቶስን) ለሞት አሳልፎ ሰጥቶ፣ በገዛ ፈቃድ ከዘላለም ሕይወት መለየት፣ ካለመኖር የከፋ ስቃይ እንደሆነ ያሳያል። ጌታ ይህን ሲል ይሁዳን አሳንሶት ሳይሆን፣ የክህደቱን ውጤት አስቀድሞ በማሳየት ከድንዛዜው እንዲነቃ "በኃይለኛ መድኃኒት" ሕሊናውን መውጋቱ ነበር።

ይሁዳን የገደለው የጌታ "ወዮታ" ሳይሆን የራሱ "ጭካኔ" ነው። ሰላሳው ብር ለጊዜው በኪሱ ውስጥ ሞቅታ ቢሰጡትም፣ በኋላ ግን በነፍሱ ላይ የሚጠነጠኑ የገሃነም ሰንሰለቶች ሆኑ። ጌታችን በዚያች ሰዓት ይሁዳን የሚመለከትበት ዐይን በምሕረት የራሰ ነበር፤ ይሁዳ ግን በፊቱ የቆመውን "አምላክ" ሳይሆን በልቡ የሳለውን "ገንዘብ" ብቻ ይመለከት ነበር።

አየሩ በጥያቄና በጥርጣሬ ደመና ታፍኗል። ዐሥራ አንዱ ቅዱሳን በታላቅ ድንጋጤና በለቅሶ "ጌታ ሆይ! እኔ እሆንን?" እያሉ ነፍሳቸው ስትታወክ፣ በአንዱ ደቀ መዝሙር ዘንድ ግን የሚታየው ድርጊት የሰማይና የምድርን መላእክት የሚያስደንቅ ነበር።

​ይህ በይሁዳ የተስተጋባው የጭንብል "ትህትና" የሰውን ልጅ የሕሊና ድንዛዜና የኃጢአትን አስፈሪ ውጤት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይሁዳ በዚያች ሰዓት በመካከላቸው የነበረው እንደ ደቀ መዝሙር ሳይሆን፣ እንደ አንድ የተራቀቀ ተዋናይ ነበር።

​ሀ. የቃላት ልዩነት፡ "ጌታ" ወይስ "መምህር"?፦
​ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ሲጠይቁት "ጌታ ሆይ!" ነበር ያሉት። ይህም አምላክነቱንና በነፍሳቸው ላይ ያለውን ሥልጣን የሚመሰክር የፍቅር ቃል ነው። ይሁዳ ግን ወደ ጌታችን ቀርቦ ሲጠይቅ የተጠቀመው ቃል "መምህር ሆይ!" የሚል ነበር።

​ለይሁዳ፣ ክርስቶስ አሁን አምላኩና መድኃኒቱ አይደለም፤ እርሱ በሰላሳ ብር የሸጠው ተራ "መምህር" ብቻ ሆኖበታል። በልቡ ውስጥ የነበረው የአምልኮ ክብር በገንዘብ ፍቅር ተተክቷል። ይህ የቃላት አጠቃቀም በይሁዳና በጌታ መካከል ያለውን የርቀት ስፋት በግልጽ ያሳያል።

​ለ. "እኔ እሆንን?" — የድንዛዜው ጥግ፦
​ወዮ! እንደምን ያለ ስንፍና ነው? ይሁዳ ራሱ የሚያደርገውን እያወቀ፣ በኪሱ ውስጥ የክህደቱን ውል ይዞ፣ እጁን ከፈጣሪው ጋር ወደ ወጪቱ እያጠለቀ "እኔ እሆንን?" ብሎ መጠየቁ የድንዛዜው ጥልቀት ምን ያህል እንደሆነ ያሳያል።

​ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚለን፣ ይሁዳ ይህን የጠየቀው ስላላወቀ ሳይሆን፣ ጌታ አሳልፎ እንደሚሰጠው በግልጽ ሲናገር "እንዳላወቀብኝ ሆኜ ልለፍ" በሚል ረቂቅ ግብዝነት ነው። ኃጢአት የሰውን ሕሊና ሲቆጣጠረው፣ ሰውዬው እግዚአብሔርን ቀርቶ ራሱንም መሸወድ ይጀምራል። ይሁዳ በዚያች ሰዓት በራሱ ላይ ጭንብል አጥልቆ ነበር፤ ነገር ግን በፊቱ የቆመው የልብንና የኩላሊትን የሚያውቅ የባሕርይ አምላክ መሆኑን ዘንግቶታል።

​ሐ. የጌታ ምላሽ፡ "አንተ አልህ"፦
​የጌታችን ምላሽ ትሕትናንና ትዕግሥትን የሚሰብክ ታላቅ ምስጢር ነው። ጌታችን "አንተ ርኩስ፣ አንተ ከሐዲ፣ አንተ የሰይጣን ማደሪያ፣ ደግሞ መልሰህ ትጠይቀኛለህን?" ብሎ አልገሠጸውም። ይልቁንም በለሰለሰና ምስጢርን በያዘ ቃል "አንተ አልህ" አለው።

✨ ​ይህ ምላሽ ሁለት ትርጉም ነበረው፦
- ​ለይሁዳ፡ "ምስጢርህን አውቄዋለሁ፤ ነገር ግን በሰው ፊት አላዋርድህም፤ አሁንም ዕድሉ አለህና ተመለስ" የሚል የፍቅር ጥሪ ነበር።

- ​ለእኛ፡ ክፉ ለሚያደርጉብን ሰዎች እንዴት በትዕግሥት መመለስ እንዳለብን፣ ስድብን በስድብ ሳይሆን በዝምታና በእውነት መመለስ እንደሚገባ የሚያስተምር መለኮታዊ ትምህርት ነው።

​መ. የፍቅረ ንዋይ በሽታ፦
​ይሁዳን እንዲህ ያደነዘዘው ፍቅረ ንዋይ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚለው፣ ፍቅረ ንዋይ ሰውን "እንደ በረሃ አውሬ" ያደርገዋል። አውሬ የሚበላውን እንጂ የሚያድነውን አያውቅም። ይሁዳም በገንዘብ ፍቅር ታውሮ፣ የዘላለም ሕይወት የሚሰጠውን አምላክ ለጊዜያዊ ብር አሳልፎ ሰጠ።

​በመጨረሻም፣ በጌታ እጅ ያ ሕብስት ከተሰጠው በኋላ ሰይጣን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረው። ይህ የሚያሳየው፣ የሰው ልጅ የመለኮትን የፍቅር ጥሪ ደጋግሞ ሲገፋ፣ ነፍሱ ለጨለማው ኃይል ክፍት እንደምትሆን ነው።

"እኔ እሆንን?" የሚለው የይሁዳ ጥያቄ ዛሬም በሁላችንም ሕይወት ውስጥ ሊኖር ይችላል። በቤተ መቅደስ ቆመን፣ በእግዚአብሔር እውነት ስም ተሰብስበን ተገኝተን፣ በልባችን ግን ሌላ "ጌታ" (ገንዘብ፣ ጥላቻ ወይም ትዕቢት) የምናመልከው ከሆነ፣ እኛም ያንን የይሁዳን ጭንብል እየደገምን ሊሆን ይችላል። ጌታ ግን አሁንም "አንተ አልህ" እያለን ወደ ንስሐ ይጠራናል።

⚜️ የሰላሳው ብር ዋጋ፦ በነቢዩ ዘካርያስ አስቀድሞ የተነገረው ትንቢት። "ዋጋዬንም ሰላሳ ብር አድርገው መዘኑ።" (ዘካርያስ 11፡12)
⚜️ ​የይሁዳ መጨረሻ፦ በጸጸት ተቃጥሎ ራሱን መስቀሉ። (ማቴዎስ 27፡3-5)

አሁን ወደ ታሪኩ እምብርትና ወደ አእምሮአችን ለሚመላለሱት ጥልቅ ምስጢራት ምላሽ ወደምናገኝበት ምዕራፍ ደርሰናል። በጽዮን አዳራሽ ውስጥ የተከናወነው ድርጊት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ መለኮታዊው ጥበብና የሰው ልጅ ነፃ ፈቃድ ፊት ለፊት የተፋጠጡበት ክስተት ነበር።

​ብዙዎች በታሪክ መጻሕፍትና በሕሊናቸው አደባባይ ይሁዳን በተመለከተ የሚከራከሩባቸው ነጥቦች አሉ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ግን እነዚህን ጭጋጋማ ጥያቄዎች በወንጌል ብርሃን እንዲህ ይፈታቸዋል፦

❓ ​ሀ. ትንቢቱ ስለተነገረ ይሁዳ መክዳቱ ግድ ነበርን?፦
​ይህ ትልቁ የክርክር ነጥብ ነው። "ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ይሁዳ መክዳት ነበረበት፤ ታዲያ ለምን ይጠየቃል?" የሚሉ አሉ። ነገር ግን ምስጢሩ እንዲህ ነው፦ ትንቢት መነገሩ ድርጊቱን አላመጣውም፤ ይሁዳ ክፋትን በፈቃዱ እንደሚመርጥ ቀድሞ ስለታወቀ ትንቢቱ ተጻፈ እንጂ።

​እግዚአብሔር አስቀድሞ ማወቁ የሰው ልጅን ነፃ ፈቃድ አይጋፋውም። ለምሳሌ፡ አንድ ሐኪም አንድ በሽተኛ መድኃኒት መውሰድ ካቆመ እንደሚሞት ቀድሞ ቢናገርና በሽተኛው ቢሞት፣ ሐኪሙ አስቀድሞ ስለተናገረ በሽተኛው ሞተ አይባልም። ይሁዳም ቢሆን እንዲከዳ አልተገደደም፤ ጌታችን ብዙ ጊዜ በምሕረት ቢጠራውም፣ እርሱ ግን በገዛ ፈቃዱ ጨለማውን መረጠ።

❓ ​ለ. ይሁዳ ባይከዳ ኖሮ ሌላ ሰው አሳልፎ ይሰጠው ነበርን?፦
​"ክርስቶስ መሰቀል ካለበት የግድ አሳልፎ የሚሰጥ ሰው ያስፈልጋል" የሚል አመክንዮ ይነሣል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ግን ይህንን ሐሳብ በፍጹም ውድቅ ያደርገዋል። እኛ የዳንነው በይሁዳ "ክህደት" ሳይሆን በእግዚአብሔር "ጥበብ" ነው።

​ጌታችን ያለ ይሁዳም ቢሆን ዓለምን እንዴት እንደሚያድን የሚያውቅ የጥበብ ባለቤት ነው። የእግዚአብሔር ጥበብ ከሰው ልጅ ሐሳብ በላይ ረቂቅ ነው። ስለዚህ "ይሁዳ ለዚህ ግብር ተፈጠረ" ብሎ ማሰብ ስሕተት ነው፤ ይሁዳ ለሐዋርያነት እንጂ ለከዳተኝነት አልተጠራም።

❓ ​ሐ. ክፉ ሰዎች ለምን እንዲወለዱ ይፈቀዳል?፦
​"ጌታ 'ባልተወለደ ይሻለው ነበር' ካለ፣ ለምን እንዲወለድ ፈቀደ?" የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ነው። እዚህ ጋር አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ እግዚአብሔር ሰውን የሚፈጥረው በመልካምነት ነው፤ ክፉ መሆን ግን የሰው ምርጫ ነው። መልካም ሰዎች የሚመሰገኑትና አክሊል የሚቀዳጁት በክፉዎች መካከል ሆነው ራሳቸውን ሲጠብቁና ትዕግሥታቸውን ሲያሳዩ ነው። ክፉዎች ክፉ የሆኑት ወደዚህ ዓለም ስለመጡ ሳይሆን፣ መምህራንና በጎ ምሳሌዎች እያሉላቸው ለመማር ባለመፈለጋቸው ነው። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ትልቁ ስጦታ °ነፃ ፈቃድ° ነው፤ ይህንንም ስጦታ መልሶ አይቀማውም።

❓ ​መ. ሰይጣን መቼና እንዴት ገባበት?፦
​በወንጌላት መካከል ያለው አገላለጽ ልዩነት (አንዱ "አሳልፎ ለመስጠት ከተስማማ በኋላ" ሌላው "ቁራሽ ከተቀበለ በኋላ" ማለቱ) አይጣላም። ምክንያቱም የሰይጣን አገባብ በቀስታና በሒደት ነው።

✨ ​መጀመሪያ በሐሳብ፦ ሰይጣን መጀመሪያ የገንዘብ ፍቅርን በልቡ ዘራ።
✨ ​በመቀጠል በንግግር፦ ይሁዳ ከካህናቱ ጋር ተደራደረ።
✨ ​በመጨረሻ በገቢር፦ ይሁዳ የጌታን የፍቅር ጥሪ ሁሉ ገፍቶ ሲጨርስ፣ ሰይጣን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረው።

⚜️ ​ማጠቃለያ፡ የይሁዳ ትምህርት ለእኛ፦
​የአስቆሮቱ ይሁዳ ታሪክ በጸጸትና በለቅሶ የሚቋጭ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ይሁዳ ምንም እንኳን ፍጹም ጤናማና መልካም ሆኖ ቢፈጠርም፣ በገዛ ፈቃዱ የክፋት አዘቅት ውስጥ ወደቀ። ፍቅረ ንዋይ ልቡን አሳወረው፤ ጌታውን እስከ መግደል አደረሰው። በትውፊት እንደምንረዳው አባቱን የገደለ እናቱን የደ˙ፈረ ጨካኝ ሰው ነበር። ጌታውንም አሳልፎ ሰጠ!!

​"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለስ ዘንድ ብዙ ነገር ቢያደርግለትም ይሁዳ ግን ከክፋቱ ሊመለስ አልቻለም።"

​ይህ ታሪክ ዛሬ ለእኛ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው። እኛም በሕይወታችን የትኛውን መንገድ እየመረጥን ነው? እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት "ጌታ ሆይ!" እያልን በፍቅር እንከተለዋለን ወይስ እንደ ይሁዳ በግብዝነት "መምህር ሆይ!" እያልን በልባችን ዓለምን እናመልካለን?

ታሪኩ በሰላሳ ብርና በአሳዛኝ ሞት ቢደመደምም፣ ትምህርቱ ግን ዛሬም በደጃችን ይቆማል። ይሁዳ የጠፋው ስለከዳ ብቻ ሳይሆን፣ የተዘረጋለትን የምሕረት እጅ ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነበር። በጽዮን ማዕድ ዙሪያ የነበረው ፍቅር በጌቴሴማኒ (በጓሮ) በመሳም ለሞት አሳልፎ በመስጠት ተፈተነ! ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃሙ ሥላሴ ዛሬም በትሕትና ጎንበስ ብሎ እግራችንን ሊያጥብና ከድንዛዜያችን ሊቀሰቅሰን ብዙ ጥሯል ብዙ ደክሟል። ግን ጥያቄው ግን እኛ በየትኛው ወገን ቆመናል? የሚለው ነው። ዓለም በየትኛው ጎን ቆማለች??

❓ አንባቢውን የሚዳስስ የሕይወት ጥያቄ፦
​በሕይወትህ ጉዞ ውስጥ፣ እንደ ይሁዳ 'ገንዘብ ወይም ጥቅም' ዓይነ ልቡናህን ጋርዶት የፍቅርን ጥሪ ቸል ያልህበት አጋጣሚ ምን ያህል እንደሆነ ይታወቅሃል?? ወይስ እንደ ዐሥራ አንዱ ሐዋርያት አጥፍቼ አጉድየ ይሆናል ብለህ በመደንገጥ 'ጌታ ሆይ! የበደልኩህ እኔ እሆንን?' ብለህ ራስህን ለመመርመር ትደፍራለህ??? ከይሁዳ መጨረሻ ይሰውረን!!

​እግዚአብሔር ይመስገን!

01/04/2026

እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ✨

27/03/2026

...ከእግዚአብሔር በሚታዘዘውና በሚመጣው ሀገር ወራሪ በሆነው ጠላት አማካኝነት ሰው ሁሉ ይጨነቃል ይጠበባል፡፡ በተለይ ደግሞ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥትና ቤተክህነት ላይ ወራ ሪው ጠ˙ላት ይበዛል፡፡ ማንም የቤተመንግሥት ጠባቂ ጦ ር ሁሉ የሚከባቸውን ጠላት መቋቋም አይችሉም፡፡ …በጥቅሉ ወራሪው የጠላት ጦር ሀገሩን ሁሉ ያሸ˙ብረዋል፡፡
መላ ኢትዮጵያን ማለት ነው፡፡

በተረፈ ማንም ሆንክ ማን፣ምንም ሆንክ ምን በአምኃ ኢየሱስና በማንኛውም መልእክቴ ላይ በድንቁር˙ናህና በእውር˙ነትህ መንፈስ እየተነሳህ ጣትህን ከመቀሰርህ በፊት፣ አፍህን ከመክ˙ፈትህ በፊት፣ ምላስህን ከማውጣትህ በፊት ቅ ድሚያ አምኃኢየሱስን ሆነህ ለመገኘት ሞክር፡፡

መሆኑ ቀርቶብህ መስለህ ለመገኘት ሞክር፡፡ መምሰሉ ቀርቶብህ ለማለምና ለማሰብ ሞክር፡፡ ለነገሩማ በምንትምህርትህና እውቀትህ? በምን መልካም ስራህና ፀጋህ እያንዳንድህ የሰ˙ይጣን ጭ ፍራ የሆንክ አስመ˙ሳይ ክርስቲያን ነህ፡፡

ሠዓሊውን ማማት ከሠዓሊው በላይ ሆኖ ነው፡፡ መሃንዲሱን ማማት ከመሃንዲሱ በላይ ሆኖ ነው፡፡ ነገር ግን እንኳን በላይ ልትሆን እኩልም አትሆንም፡፡ በላይ የሚሆነው ምንጊዜም ቢሆን ጭንቅላትህና መልካም ሥራህ ሳይሆን አፍ˙ህና ወሬህ ብቻ ነው፡፡

ጥቅምት 5 2013 ዓ.ም ዕለተ ሐሙስ፡-
አባ አምኃ ኢየሱስ ካስተላለፉት ፬ መልእክት የተወሰደ

27/03/2026

"ዛሬ በስተመጨረሻ እግዚአብሔር በእኛ በተናቅን በማንሰማ በሚያዋርዱን በሚሰ˙ድቡን ልጆቹ አማካኝነት ለ17 ዓመታት ሁሉ ፈቃዱን ትእዛዙን ስርዓቱን ለጥፋቱ ሁሉ የሚመጣውን ፍርዱን ቁጣውን ትእግስቱ ጥንፍፍ ብሎ ማለቁን ተናገረ ፤ ሁሌም ተናገረ ፤ አብዝቶ አስጠነቀቀ ፤ ተቆጣ ፤ እኛም ደግመን ደጋግመን የመጣውን ቁጣ እሳት አረ ተዉ አትችሉትም ፈጥናችሁ ተመለሱ አልን ማን ይስማን!? የኖሕ ጩኸት ምን አመጣ ? ጠቅላላ መጥፋትን ፡፡ ዛሬም ከኖሕ ዘመን በሺ እጥፍ ተባዝቶ የመጣውን እሳት ፤ ታይቶ ተሰምቶ የማያውቀውን በታላቁ የቅናቱ ቁ˙ጣ የገነፈለውን እቶን ሊፈስ˙ብህ ተንጠልጥሎልሃል ፡፡ በየደ˙ጅህ እየተንተከተከ ነው ፡፡ የተገደበበትን ጥሶ ለመውጣት እየታገለ ነው ፡፡"

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አስር የተወሰደ - ተጻፈ ጥር 7/2015 ዓ.ም
አዖተ- አስታዋሽ - t.me/Ewnet1Nat

27/03/2026

...ሃገሪቷ በጦ˙ርነት፣ በርሃብ ፣በበሽታ በዚህ ሁሉ ተወጥራ ተይዛለች ። መሪዎች ከዲ′ስኩር ያለፈ ከንግግር ያለፈ በተግባር የሚታይ የሰወችን ችግር ሲፈቱ አላየንም አልሰማንም ። እንደውም የጥፋቱ የህዝቡ መውደቅ መራብ መቸገር ሁሉ መንስኤ ሆነው እግዚአብሔርንም በድለው ህዝብንም በድለው ራሳቸውም ላይ ከባድን ጥፋት ፍርድን አምጥተዋል። እንግዲህ የግድ ነውና ይሸከሙታል ዋጋ˙ውንም ይከፍላሉ። እውነቱ ይሄ ነው ወገኖቼ! ገና ፍርዱ ይቀጥላል ።

እያንዳንዱ የኢትዮጵያም ውስጥ ያለው መሪም ፣ የጥ˙ፋት ሃይልም ሁሉም እጁ˙ን ለእግዚአብሔር ተንበርክኮ እስካልሰጠ ድረስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እስካላከበረ ድረስ ንስሐ ገብቶ አልቅሶ ወድቆ ለምኖ ምህረትን እስካላገኘ ድረስ ቁጣው ከዚህ በብዙ እጥፍ እየጨመረ ይሄዳል ።

እንደተነገረው ቀድመንም እንደነገርናችሁ ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ገና ጉ˙ዳት ይመጣል ። ያ ጉዳት ደግሞ ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት እንጅ ኢትዮጵያን ለማ˙ጥፋት አይደለም። ኢትዮጵያማ የትም አትሄድም ። አጥፊ˙ወቿ በደለኞቿ አገሪቱን ወደ ጥፋ ት የሰደዱ የዲያብሎስ ሰራተኞች ሁሉ ግን ሰዓታቸው እየሞላ ጊዜያቸው እያለቀ ስለመጣ በፍርድ ይካተታሉ ።

ቅድሚያ ግን ከእግዚአብሔር ቤት የሚወ˙ገደው ሁሉ ይወገ˙ዳል ። ቀጥሎም በምድሪቱ ላይ የተንሰራፋው አጥ‛ፊ ሃይል ሁሉ ይወ˙ገዳል። እግዚአብሔር በምድራችን በኢትዮጵያ በርስተ ድንግል ላይ ሥላሴ ይከብሩባታል። ምድሪቱ የሥላሴ ምድር ትሆናለች ፣ ምድሪቱ የድንግል ምድር ትሆናለች፣ ምድሪቱ ብርሃን የሚበራባት ለዓለም ሁሉ ብርሃን የምትሆን ትሆናለች ማን? ኢትዮጵያ ። ዛሬ የሚጠሏት ዛሬ ሊያፈ˙ርሷት የሚታገሉ ይጠፋ˙ሉ ይፈር˙ሳሉ፣ ዛሬ የናቁት ባንዲራ ከፍ ብሎ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሆኖ ልክ በሠማይ ላይ በቀስተደመና እንደሚታየው ምድሪቱን ሁሉ ይሸፍናል። ወደዱ˙ም ጠሉም ይሄ የማይቀር ነው። በእነሱ መጥ’ፋት ኢትዮጵያ እንደገና ታንሰራራለች፣ ትነሳለች።

📌ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የዮሐንስ ወንጌል ትምህርት ክፍል 4(ሀ) ከ01:18:10 - 01:21:10 የተወሰደ።
አዖተ- አስታዋሽ - t.me/Ewnet1Nat

23/03/2026

ከንስሐ ጎን ለጎን ዝግጅትም አንዱ ለእግዚአብሔር የመታዘዝ ግዴታ ነው!!

አንድ የቅርብ ወዳጄ እንዳጫወተኝ አንዳንድ የሰሜን አካባቢዎች (ልዩ ቦታ አልጠቅስም) መብራት ሙሉ በሙሉ የመቆራረጥ ነገር በዝቷል። እና ሰው የሚበላው አጥቶ የእህል ቋጠሮ እየያዘ መብራት በሌለበት ወፍጮ ቤት ተሰልፎ እየዋለ ይመለሳል አለኝ ። እና ቤተሰቦቼ ምን ልላችሁ ነው!? ከነዳጅ መጥፋት ቀጥሎ በተጨማሪም እንደምታውቁትና እንደምትረዱት የፍርድ ሒደቱ ሁሉን አቀፍ ስለሆነ ወደመብራትም ሙሉ በሙሉ መቋረጥ እያመራ ይሆናልና በየትኛውም አካባቢ ያላችሁ መዘናጋት የተስተዋለብን ቤተሰቦቻችን ከንስሐ ሳትጎድሉ በእጅ የሚገፉ የድንጋይ ወፍጮዎችን ማስተካከልና ተፈጭተው የሚያዙ አንዳንድ ነገሮች (በአቅማችሁ) ከወዲሁ እንዳንዘናጋ ወንድማዊ ምክሬን አሳስባለሁ። "ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ!!!"

​"ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፤ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይሄዳሉ፥ ይጎዱማል።"
(መጽሐፈ ምሳሌ 22፥3)

#መዘናጋት

!

አዖተ - አስታዋሽ - t.me/Ewnet1Nat

11/03/2026

« ስለወቅቱ የዓለም ሁኔታ!
ዓለማችን በቀደሙት ተከታታይ አምስት መልእክቶች በመዳኘት ላይ መሆኗን እያስተዋልን ነው ። የአለማቱ ገዢዎች መልእክቶቹ ዓለማትን ሁሉ መዳኘታቸውን እያወቁ ፤ የመጥፋታቸውን ፍርድ በመገለፁ ምክንያት በአንድም ቀዳዳ እንዳይነገር የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። በግል ብዙዎች እንዳገኙት ይታመናል። ከመልእክቱ መውጣት በኋላ ዓለማችን በየደረጃው በእሳቱ ወንፊት በመበጠር ላይ ነች ። እንደትእቢቷ መጠንም እሳቱና የእሳት ወንፊት በሰባት እጥፍ እየተባዙ ማድቀቃቸውንና ማክሰማቸውን ይቀጥሉበታል። ዓለም ሁሉ አሜን ብሎ እስከሚንበረከክ ድረስ! ሸሸጉትም አልሸሸጉትም መልእክቶቹ ውስጥ የተጠቀሱት ፍርድና ቅጣቶች በታዘዙት ጊዜና ሰዓት ስራቸውን ያከናውናሉ እንጂ ከፍርድና ቅጣቱ አንዳች የሚቀር ነገር የለም። »

⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን አዋጅ ነጋሪ መልእክት 6 ገፅ 9-10* ተፃፈ 19/4/2007ዓ.ም!

ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር።
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም።
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን።
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዥ።
አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
💚 t.me/Ewnet1Nat
💛 t.me/christian930
❤ t.me/Amharic_Messages
______

Photos from Joseph Ethiopia Page's post 04/09/2024
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa