Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions' Association

Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions' Association

Share

Ethiopian Private Higher education and TVETs' Institution Association is established on 16th Octo. 2

09/12/2023

የማህበሩ አባል ተቋማት ሁሉ በሰዓቱ እንድትገኙ በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

08/11/2023
03/11/2023

የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል!

| የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 255 ያመጡ

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 -234 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600- 218 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 200 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 224 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 - 192 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 - 180 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።

Photos from Ethiopian Private Higher Education & TVET Institutions' Association's post 09/10/2023

ተማሪዎች ውጤታቸውን እንዴት ማየት ይችላሉ?

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ሲል ትምህርት ሚ/ር ገልጿል።
በመሆኑም:-

በዌብ ሳይት 👉 https://eaes.edu.et
በአጭር የጽሑፍ መልዕክት 👉 6284
በቴሌግራም 👉 https://t.me/eaesbot

በመጠቀም ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ።

09/10/2023

የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

👉 የማለፊያ ውጤት ያመጡት 3 ነጥብ 2 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው፣
👉 ተፈታኞች ውጤታቸውን ማየት የሚችሉት ከነገ ጀምሮ ነው፣

| የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በፈተናው የማለፊያ ነጥብ ያመጡት 27 ሺህ 267 ተማሪዎች ወይም 3 ነጥብ 2 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከፍተኛ ውጤት ከተፈጥሮ ሳይንስ 649 በአዲስ አበባ ከተማ ሲመዘገብ÷ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 በደብረ ማርቆስ ከተማ ተመዝግቧል፡፡

አምስት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎችን በሙሉ ማሳለፋቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የፈተና መመሪያ እና ደንብ በመጣስ በግል 483 ተማሪዎች እንዲሁም በቡድን ደግሞ 376 ተማሪዎች መቀጣታቸውን አንስተዋል፡፡

ተፈታኞች ውጤታቸውን ማየት የሚችሉት ከነገ መስከረም 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ነው ተብሏል።

***
" ፈተናው ካለፈው በተሻለ ከኩረጃ እና ሌብነት የፀዳ ነበር። "

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ግንቦት ወር ይሠጣል፡፡"

"በሚቀጥለው ዓመት የሚሰጠው ፈተና ድብልቅ ፈተና ይሆናል፡፡ ግማሹን በኦንላይን፣ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ በአካል ይሰጣል፡፡"

የትምህርት ሚኒስትሩ የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክተው መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

09/10/2023

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክተው መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

"የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ግንቦት ወር ይሠጣል፡፡"

"ከሰኔ ጀምሮ ለሦሥት ወራት ዩኒቨርሲቲዎች የክረምት ትምህርት ይሰጣሉ፡፡"

"በሚቀጥለው ዓመት የሚሰጠው ፈተና ድብልቅ ፈተና ይሆናል፡፡ ግማሹን በኦንላይን፣ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ በአካል ይሰጣል፡፡"



በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል፡፡

በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡ በድምሩ 845,677 ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 31, 224 ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

በዚህም 160 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በሬሜዲያል ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚቀበሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ትህርት ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

"አምስት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ አሳልፈዋል፡፡"

"ሌሎች አምስት ትምህርት ቤቶች ድግሞ ካስፈተኗቸው ውስጥ 95 ከመቶ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል፡፡"

ከፍተኛ አፈጻጻም ያሳዩ አስር ትምህርት ቤቶች (በደረጃ)፦

1. አዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት
2. ደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ባህርዳር ስቴም ትምህርት ት
4. ሀይራንዚ አዳሪ ትምህርት ቤት (ስልጤ ዞን)
5. ሊች ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት (ሀድያ)
6. ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት (አዳማ)
7. ኮተቤ ሼርድ ካምፓስ
8. የኔታ አካዳሚ
9. ወላይታሊቃ አዳሪ ትምህርት ቤት
10. ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት

በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ 200 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አምጥተዋል፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ መስክ 15 ተማሪዎች ብቻ ከ500 በላይ ውጤት አምጥተዋል፡፡

በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛው ውጤት 649 ሲሆን በአዲስ አበባ የልደታ ክሩዝ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ ከፍተኛው ውጤት 533 ሲሆን የደብረ ማርቆስ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው፡፡

በከተማ ደረጃ አዲስ አበባ፣ ሀረሪ እና ድሬዳዋ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ ከተሞች ናቸው፡፡

05/10/2023

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴ/ሙ/ት/ስ/ተቋማት ማህበር ፕረዚደንት የሆኑት የ ዶ/ር አረጋ ይርዳው 3ኛ መጽሐፍ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይመረቃል።
ዶ/ር አረጋ ይርዳው በኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴ/ሙ/ት/ስ/ተቋማት ማህበር አባላት ስም እንኳን ደስ አለዎት ማለት እንወዳለን።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Bole Subcity Woreda 14 Gerji Unity University
Addis Ababa
2618