Blatenaldp

Blatenaldp

Share

My page is mainly created to preach Gospel and leach Christians to know God and their identity in Je

06/11/2021
17/02/2021

ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ለሰጠኝ ውድ ልጆቼ የምትመች ምድር እንድትሆን የሁልግዜ ፀሎቴ ንው።

11/02/2020

Strategic Planning, Staffing, Leading, and Evaluating the total performance of the Project.

18/10/2018

መልክፀዲቅ የኢትዮጵ አባት የኢትዮጵያውያን አባት ከፕሮፌስር ፍቅሬ ቶሎሳ

ስለ የሳሌም (ኢየሩሳሌም) ንጉሥ መልከፀዲቅ ስናወሳ የእሱን ማንነት አስመልክቶ ውዥንብር አለ;; መልክጸዲቅ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ በኦሪት ዘፍጥረት (11. 18-21)፣ በቅዱስ ዳዊት መዝሙር (109-110. 4) እና የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ እብራውያን (ምእራፍ 7) ተጠቅሶአል;; —
በኦሪት ዘፍጥረት (14. 18-21) ስለ አብርሃም እና መልከፀዲቅ እንዲህ ይላል;–
››አብርሃም ኮሎዶጎምርንና ከእሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰም በሁዋላ የሶዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ በሆነው የሌዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ;; የሳሌም ንጉሥ መልከፀዲቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ;; እርሱም የልኡል እግዚአብሄር ካህን ነበረ;; ባረከውም (አብርሃምን)– አብርሃም ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ ለልኡል እግዚአብህር የተባረከ ነው;; ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ ልኡል እግዚአብሄርም የተባረክ ነው፣ አለውም;; አብርሃምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው;;››
በዳዊት መዝሙር ደግሞ (109—110‹ 4) አግዚአብሄር አብ፣ በዳዊት አፍ ውስጥ ስለ እየሱስ ክርስቶትስ ዘላለማዊ ካህንነት ምሎአል–
››እንደ መልከፀዲቅ ሥርዐት አንተ የዘላለም ካህን ነህ ብሎ፣ እግዚአብሄር ማለ፣ አይፀፀትም;;; ..
ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ (እብራይስጥ 7) በመጀመሪያ ስለ መልከፀዲቅ፣ ቀጥሎም መልከፀዲቅ ምሳሌው ስለ ሆነው ስለ እየሱስ ክርቶስ ይናገራል;; እንዲህ ሲል–
.የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሄር ካህን የሆነው ይህ መልከፀዲቅ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤ ለእርሱም ደግሞ አብርሃም ከሁሉ አስራትን አካፈለው;; የስሙም ትርጉዋሜ በመጀመሪያ የፅድቅ ንጉሥ ነው;; ሁዋላ ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነወ;;›› (ስለ እየሱስ ከርስቶስ ማንነት ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ አያይዞ ሲናገር) አባትና እናት፣ የትውልድም ቁጥር የሉትም፣ ለዘመኑም ጥንት፣ ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፣ ዳሩ ግን በእግዚአብሄር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል;;››
ስለ እየሱስ ክርቶስ ቅዱስ ጳውሎሰ ሲናገር ››አባትና እናት፣ የትውልድም ቁጥር የሉትም›› ያለውን ቆንጽሎ በማውጣት አያሌ መጽሃፍ ቅዱስን እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ይህን አባባል ለኢየሩሳሌም ንጉሥ ለ መልከፀዲቅ በመስጠት ››መልከፀዲቅ አባትና እናት ስሌለውና ዘመኑ ጥንት፣ ትውልዱ ቁጥር፣ ህይወቱም ፍጻሜ ስለሌለው መልከፀዲቅ ከእናትና አባት የተወለደ አጥንትና ሰጋ የነበረው ሰው አይደለም;; እሱ ራሱም ልጆች ሊወልድ አይችልም፤›› ይላሉ;; ነገር ግን ቅዱሰ ጳውሎስ ››አባትና እናት፣ የትውልድም ቁጥር የሉትም፣ ለዘመኑም ጥንት፣ ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፣ ዳሩ ግን በእገዚአብሄር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል;;›› የአለው ስለ እየሱሰ ክርስቶስ አንጂ ስለ ሳሌም ንጉስ እነዳልሆነ አይገነዘቡም;; የእየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ የሆነው ንጉሥ መልከፀዲቅ የተባለው ትልቅ ሰው ግን የዛሬ 4000 ዐመት በክህነት እና ንጉሥነት ኖሮ ሞቶአል;; በመሞቱም ህይወቱም፣ መንግሥቱም ክህነቱም አልፈዋል;; ሞቶአል የምለውም ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ ሰው ነበር፣ ስለሚል ነው;; የት ነው ይህን የሚለው? በዛው በእብራውያን ምእራፍ 7 ቁጥር 4. እንዲህ ይላል–
››የአባቶች አለቃ አብርሃም ከዘረፋው የሚሻለውን አስራት የሰጠው ይህ ሰው (ይህ ሰው የሚለውን በአፅንኦት አንየው፤) አንዴት ትልቅ እንደነበረ አሰኪ ተመልከቱ;;›› አዎን ሰው ስለነበር ሞቶአል;; መንገሥትና ክህነቱም አልፈዋል;; እሱ ምሳሌ የሆነለት የእየሱሰ ከርቶስ መንግሥት፣ ህይወት አና ከህነት ግን ዘላለማዊ ናቸው;; እሱ የማይሞት ዘላለማዊ ነወና;; አባታችንን፣ ማለትም የኢትዮጵን አባት መልከፀዲቅን፣ ቅዱሰ ጳውሎስ ››ይህ ሰው ትልቅ እንደነበረ እሰቲ ተመልከቱ፣›› ባለው ደስ እያለኝ ክእሱ አባባል እስማማለሁ›; አዎን በአባታችን ትልቅነት ሁላችንም የኢትዮጵ ልጆች ኢትየጵያውያን ልንደሰት እና ልንኮራ ይገባል;; ቅዱሰ ጳውሎስ፣ አባታችንን መልከፀዲቅን ትልቅ ሰው ካለባቸው ምክንያቶች ዋነኛው የእየሱስ ክርቶስ ስርዐተ-ክህነት አነስተኛው የዕብራዊው የሌዊ ስርዐተ-ክህነት ሳይሆን የአባታችን የኢትዮጵ አባት፣ ስለዚህም የኛ አባት የሆነው ትልቁ የመልከፀዲቅ ስርዐተ-ክህነት መሆኑ ነው;; እሱ አባታችን ስለሆነ ከእብራውያኑ ከነ ሙሴና አና ከነ ቅዱስ ጳውሎስ የበለጠ ስለ እሱ ማንነት መረጃ አለን;; በመጀመሪያ ነገር፣ ከቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ ስለ መልከፀዲቅ በጥቂቱም ቢሆን የጻፈው ሙሴ ነው;; ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ሙሴ በጻፈው ላይ ተመርኩዞ ከተበ;; ሙሴ ራሱ መረጃውን ያገኘው ከኛው ከኢትዮጵያውያን ነው;;
እንዴት ቢባል፣ አንደ መልከፀዲቅ ካህን ከነበረው ከመልከፀዲቅ ዝርያ፣ ከኢትዮጵዊው አማቱ ከየቶርአብ ጋር 40 ዐመት ሙሉ በኢትዮጵያ ሲኖር አኛ የአባታችንን የመልከፀዲቅን ትውልድ ታሪክ በዝርዝር የዘገብንበትን መጽሃፈ ዣንሽዋ ን አግኝቶ ስለ አነበበ;; ሙሴ አስቀድሞ የኛን መጽሃፍ ማንበቡን ራሱ አምኖአል፣ መሰክሮአልም;; ይህንንም የመሰከረው በ መጽሃፈ ሆልቆ (21‹ 14) ነው;; ይህን እውነት አንባቢው በቀና ልቦና ሊመረምረወ ይችላል;;
በዛው በ እብራውያን 7 እና 8 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠ የዘላለም ሊቀ-ካህን አለን የሚለውም ፈጣሪን እየሱስ ክርስቶስን ብቻ እንጂ ሰው የሆነውን አባታችንን መልከፀዲቅን ሊሆን አይችልም;; ለአብርሃም ህብስትና ወይንጠጅ ያበረከተለት (ከማንም አሰቀድሞ ያቆረበው ማለት ነው፣) ሊቀ-ካህኑ አባታችን መልከፀዲቅ አንጂ እየሱስ ክርስቶስ ራሱ ስጋ ለብሶ፣ ገዝፎና ታይቶ አልነበረም;; እየሱስ ክርስቶስ ክ ቅድስት ማርያም ስጋ ነስቶ የዛሬ 2000 ዐመት ከመወለዱ በፊት ስጋ ሆኖ ገዝፎ ለሰው ተከስቶ ነበር፣ ማለት የስህተት ስህተት ነው;; ከሴት ሳይወለድ ስጋ ለመሆን ቢፈቀድ ኖሮ ለምን ከቅድስት ማሪያም ተወልዶ የሰውን ልጅ ከሃጥያቱ ለማዳን አቀደ?
በእርግጥ መልከፀዲቅ አባታችን ስጋ ለባሽ ሰው ነበር;; ሰው ስለነበረ ነው ከእናትና አባት የተወለደውና ራሱም ልጆች የወለደው;; ከመጽሃፍ ቅዱሰ በፊት በተጻፈው፣ ሙሴ እኛ ዘንድ ሳለ ባነበበው ዣንሸዋ በተባለው መጽሃፋችን ውስጥ የአባታችን ትውልድና ልጆች የዘር ሃረግ ተመዝግቦአል;; በዚህ መጽሃፋችን ውሰጥም መልከፀዲቅ ከናምሩድ፣ ማለትም የባቢሎንን ግንብ ከገነባው ታላቅ ንጉሥ ዘር ይጠቅሳል;; እንዲህም ይላል — ››ናምሩድ አዳማን ወለደ፣ አዳማ ራፌልብን፣ ራፌልብ ቄናን፣ ቄና ደግሞ ጌራን;; ጌራ በክህነት ስሙ መልከፀዲቅ የተባለው ነው;; ጌራ (መልከፀዲቅ) በበኩሉ እናታችንን ሳሌምን (የነገሠባትን ከተማ በእስዋ ስም ነው ሳሌም ወይም ኢየሩሳሌም ያለው፣) አግብቶ ከእስዋ ዐራት ሴቶችና ሶሰት ወንደች ልጆች ወልዶአል;; የወንዶቹ ስሞች ኢትኤል (አባይን ተከትሎ ሄዶ ጣና ላይ ሰፍሮ በሁዋላ .›ኢትዮጵ.. የተባለው አባታችን) ሃሙኤል (ሃሙራቢ ተብሎ ወደ ባቢሎን ተጉዞ የሃሙራቢን ህጎች Hamurabi’s Code of Lawን የሰጠው) አና አቡመሊክን (የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ የሆነውን) ወልዶኣል;; ከእሱ አብራክ እኛን ኢትዮጵያውያንን ያስገኘን እገዚአብሄር ይከበር ይመስገን;; ታዲያ ይሄ ሁሉ ለምን መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ አልሰፈረም? ሙሴ መጽሃፍ ቅዱስን ከመጻፉ ወይም ከማጻፉ በፊት ይህን ታሪካችንን ጠንቅቆ ያውቃል;; አንቦታልና;; ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ ለምን በኦሪት ዘ ፍጥረት ውስጥ እንዳላካተተው ትክክለኛውን መልስ ሊሰጠን የሚችለው ነቢዩ ሙሴ ብቻ ነው;; እሱ ስላልከተበው ግን የኛ እውነተኛ ታሪክ የለም ማለት አይደለም;; መጽሃፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት የእኛን ጉዳይ እኛው ከትበነዋል;; ስለዚህ፣ እሱ ስላልከተበው ብዙ አይጨንቀንም;; ይህ ለሁሉም ሰው ግልጽ ሊሆን ይገባል;;

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa