02/06/2026
#ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ጌታ ሆይ አንተን የሚያውቅ ይሰደዳል!
ሮሜ 8:36
#በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ የ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።
#የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።
#እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ማቅ የለበሱ እናቶች፣ እንባቸው ያላለቀ ሕፃናትና ማደሪያ ያጡ አረጋውያን ጩኸት ሰሚ አጥቷል።
#ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠላታ ጨፋ ቀበሌና ካራ ኩፍቴና በሚባሉ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።
#እጅግ አሳዛኝና አረመኔያዊ በነበረው ጭፍጨፋ በአሰኮ ወረዳ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ ብቻ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት ከ10 በላይ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል።
#የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚፈተትበት መቅደስ ላይ ኢላማ ባደረገ ጥቃትም በአካባቢው የሚገኘውና 101 ዓመታት ያስቆጠረው፣ የዕድሜ ባለጸጋው የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።
#በተመሳሳይ ጥቃት በካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆኑ ቤቶች በመቃጠላቸው ምእመናን የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ጽላት ይዘው በእግራቸው ወደሌላ አካባቢ መሸሻቸው ታውቋል።
#ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል።
#ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ ሲሉ ነበር በሃዘን ተውጠው የነገሩን።
#በተያያዘ ዜና በዚሁ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ተሰምቷል።
#በሚታና ዋጂ ቀበሌ የተፈጸመው ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ወጣቶቹ መኖሪያ ቤት የገቡት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ካዋሏቸው በኋላ ወደሚታና ጋዶ ቀበሌ በመውሰድ፣ አንደኛውን በስለት አርደው፣ ሁለተኛውን ደግሞ በጥይት በመምታት በጭካኔ ገድለዋቸዋል።
#የወጣቶቹ ሥርዓተ ቀብር ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በጋዶ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናንና በቤተሰብ በተገኘበት በአንድ መቃብር ተፈጽሟል።
#በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ በተደጋጋሚ ለሚፈጸመው የክርስቲያኖች ጥቃትና ግድያ ከየትኛውም አካል መፍትሔ አልተሰጠውም።
EOTC MK TV
#የአባቶቻችን ዝምታ እስከ መቼ? በቤተክህነቱ ከፍታ ላይ የተቀመጣችሁ መሪዎች ጳጳሳትና አባቶች ሆይ! መቼ ነው የምትናገሩት? መቼ ነው የምትተነፍሱት?
መሪነታችሁና አባትነታችሁ ለበጎች ጥበቃ ካልሆነ...
የምዕመናን እምባና ሞት ካላሳዘናችሁ...
ወጥታችሁ ለግፉአን ድምፅ ካልሆናችሁና "በቃ!" ካላላችሁ... የአባትነታችሁ ትርጉም ምንድነው?
ሁላችንም ልናውቀው የሚገባ እውነት፦ ዛሬ በሩቅ የምንሰማውና የለመድነው የሞት ዜና ነገ እያንዳንዳችን ቤት ማንኳኳቱ የማይቀር እውነታ ነው!
ማንም በተራው ሳይታ,ረድ የሚያመልጥበት ምድር ላይ አይደለንም።
አሁኑኑ እንነጋገር በአንድነት እንቁም!
ከእንግዲህ ዝምታ ፈራጅ ነው!
ሁላችንም ተቀራርበን ስለ መፍትሔው ልንወያይ በቁጭት ልንነሳና ኦርቶዶክሳውያን በአንድነት ልንቆም ይገባል።
የአባቶቻችን እምነትና የንፁሃን ደም በታሪካችን ፊት ይፋረደናል!
ዝምታችን ይብቃ!
"የሞታችን ዜና የዕለት ተዕለት ወሬአችን ሊሆን አይገባም!"