05/08/2026
በፃድቃኔ ማርያም ገዳም በሞት የተለየችዉ
በአሰቃቂ እና ድንገተኛ አደጋ በተከሰተው በመሬት መናድ ምክንያት በፃድቃኔ ማርያም ገዳም ከነበሩት አህቶችና ወንድሞች መካከል ተስፋነሽ (እሚቲ) አንዷ ስትሆን አድሮባት በነበረው ህመም ምክንያት "ካልዳንኩኝ ከዚህ ቅዱስ ስፍራ አልወጣም" በሚል የፀና መንፈሳዊ እምነትና ፅናት፣ ገዳሙ ውስጥ ቆይታ በማድረግ ላይ ነበረች።
በዚሁ ፅኑ እምነቷ ሳለች በስጋና ደሙ ተወስና ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች።
ቀብሯ ዛሬ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት በዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር የወዳጅ ዘመዶቿ፣ የቤተሰቦቿ እንዲሁም የእምነት ወንድሞችና እህቶች በተገኙበት ስርዓተ ቀብሯ ተፈፅሟል።
ነፍሷን በአፀደ ገነት ያኑርልን!