Arada sub-city education office

Arada sub-city education office

Share

ይህ የአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የፌስ ቡክ ገፅ ነዉ!!

Photos from Arada sub-city education office   's post 16/02/2026

በአራዳ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት በ9/6/2018 ዓ.ም በተጋባዥ እንግዳ ሬገን መሀመድ የስርአተ ፆታ አመለካከት(Gender Perspective) በሚል ርዕስ የእውቀት ሽግግር ውይይት ተካሂዷል፡፡

07/02/2026

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 2/2018 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

(ጥር 30/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 2/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

Photos from Addis Ababa Education Bureau's post 03/02/2026
Photos from Arada sub-city education office   's post 27/01/2026

በአራዳ ክ/ከተማ ሲካሄድ የነበረው የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በዛሬው እለት በሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፍጻሜውን አገኘ።

አራዳ ኮሙኒኬሽን ጥር 19/2018 ዓ.ም

ከጥር 12 እስከ ጥር 19/2018 ዓ.ም በአራዳ ክ/ከተማ ውስጥ በሚገኙ ት/ቤቶች መካከል በአራዳ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤትና ት/ት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው ስፖርታዊ ውድድር በዛሬው እለት በምኒሊክ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራንና ተማሪዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ተወካዮች የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፉ ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በበላይ ዘለቀ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትና በቀለመወርቅ ት/ቤት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መካከል በተካሄደ የእግርኳስ የዋንጫ ጨዋታ ተጠናቋል።

ከጥር 12 እስከ ጥር 19/2018 ዓ.ም በተካሔደው የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር እግርኳስ በወንዶችና በሴቶች፣ ቮሊቦል በሴትና በወንድ፣ ቅርጫት ኳስ በሴትና በወንድ፣ ጠረጴዛ ቴነስ በወንድና በሴት፣ አትሌቲክስ በቡድን እንዲሁም ቼዝ በቡድን ውድድር የተካሄደ ሲሆን በመምህራን መካከል በተካሔደው የወንዶች እግርኳስ ወረዳ 4 : 1ኛ፣ ወረዳ 9 : 2ኛ፣ በቮሊቦል ሴት ወረዳ 4 : 1ኛ እንዲሁም በቮሊቦል ወንዶች ወረዳ 9 : 1ኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ በቮሊቦል ወንዶች ወረዳ 4 : 2ኛ ሆኖ አጠናቋል።

የመዝጊያ መርሀግብር የወንዶች የዋንጫ ጨዋታ በበላይ ዘለቀ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትና በ ወ/ሮ ቀለመወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መካከል የተካሄደ ሲሆን ወ/ሮ ቀለመወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመለያምት በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳት የቻለ ሲሆን በሴቶች እግር ኳስ ወ/ሮ ቀለመወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አሸናፊ በመሆን ዋንጫ አግኝቷል።
በአጠቃላይ ውጤት ልደታ ካቶሊክ ኪዳነ ምህረት 5 ዋንጫዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን በ1ኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

የውድድሩን የሽብርቅና የፀባይ ዋንጫ ወረዳ 5 ወስዷል።

በዚህ መርሀ ግብር ላይ ውድድሩን በአንደኝነት ማጠናቀቅ የቻሉ ት/ቤቶች ባሸነፉበት ዘርፍ ክ/ከተማውን ወክለው በከተማ ደረጃ በሚዘጋጀው ውድድር ላይ የሚሳተፉ መሆኑ ተገልጿል።

Photos from Arada sub-city education office   's post 17/01/2026

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል መሰራቱን ገለፀ።

አራዳ ጥር 8/2018 ዓ.ም

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት ያለፉት 6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን ከትምህርቱ ማህበረሰብ ጋር በመገምገም አቅጣጫ አስቀምጧል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ
ባለፉት 6 ወራት ጥሩ አፈፃፀም የነበረ መሆኑን አንስተው የተሻሉትን ማስቀጠልና ጉድለቶችን መሙላት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በበጀት አመቱ 61,371 የተማሪ ቅበላ በማድረግ ፍትሃዊና ተደራሽ እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ተግባራት ወቅቱን ጠብቀው መከናወናቸውን ገልፀዋል።

በአፈፃፀምም የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሳይባክን እና የመፅሀፍት ግምገማ ውስንነት እንዳይኖር እንዲሰራም አሳስበዋል።

የመማር ማስተማር ሂደትን ለማሻሻል ጥናትና ምርምር ማካሄድ የተቻለ ሲሆን የትምህርት ጥራትን አሰመልክቶም የውስጥ ሱፐርቪዥንና ምልከታ በት/ቤቶች ተደርጓል።

ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተለይተውም በአካታች ትምህርት መሰጠቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂ ወደ ስራ ገብቶ ለውጥ የታየበት ዉጤት ለማምጣት እየተሰራበት መሆኑ ተጠቁሟል።

ተሳታፊ የትምህርቱ ማህበረሰብ የተማሪ ውጤት እንዲሻሻል ሁሉም የድርሻውን እየሰራ በመሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች መምጣታቸውን ገልፀው ገች የነበሩና መልካም ጉዳዮችን አንስተው ውይይት በማድረግ በቀጣይ የላቀ አፈፃፀም እንዲኖር በጋራ እንዲሰራ ምላሽ ተሰጥቷል።

የመልቀቂያ ፈተናዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል፣ የማላቅ ስትራቴጂ አተገባበርን ማጠናከር፣ ኦን ላይን ፈተና አሰጣጥን ማጠናከር፣ የመማክርት ጉባኤን ማጠናከርና መሠል ጉዳዮችን ጨምሮ ጥንካሬዎችን በማጎልበት ውስንተቶችን በማስተካከል በትኩረት እንደሚሰራባቸው ተገልጿል።

Photos from Arada sub-city education office   's post 15/01/2026

ከመንግስት 2ኛ ደረጃ ር/መ/ራን ጋር የስራ ግምገማ ተካሄደ

በዉይይቱ የአራዳ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ ለተማሪዎች እየተሰጠ ያለዉ የዉጤትማላቅ "ስትራቴጂው በወረቀት ላይ የሰፈረውን ያህል በተግባር እንዲተረጎም የክትትል ስራው መጠናከር እንዳለበት ፣በተለይ ዝቅተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ፣ የሂሳብና እንግሊዘኛ ስትራቴጂ አተገባበር ሁለቱ የትምህርት አይነቶች ለተማሪዎች ስኬት ወሳኝ በመሆናቸው ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል በመሆኑም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተግባቦት ላይ አሁንም ክፍተቶች እየተስተዋሉ በመሆኑ መምህራን የተማሪዎችን ተሳትፎ የሚጨምሩየማስተማር ዘዴዎችን (Active Learning) በስፋት መጠቀም እንዳለባቸዉ፣ተማሪዎች አካላዊ ብቃት እና ስነ-ልቦና አንጻር የስፖርት ውድድሮች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና የስፖርት ውድድሮች ከተማሪዎች ስነ-ምግባር ጋር ተቀናጅተው መሄድ፣ውድድሩ የፉክክር ብቻ ሳይሆን የወንድማማችነት መገለጫ ሊሆን እንደሚገባ፣ተማሪዎች ያላቸውን አቅም እንዲያወጡ የቁሳቁስ እና የሙያ ድጋፍ ተደርጎላቸዉ ምርጥ የፈጠራ ስራዎችን እንዲሰሩ እውቅና ማግኘት እንዳለባቸዉ እንዲሁም አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራው ያለበት ሁኔታ የመማር ማስተማር ሂደቱ በታቀደው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን በመግለፅ። "አጠቃላይ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በመጨመር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ወላጆች በቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።"

Photos from Arada sub-city education office   's post 15/01/2026

የክላስተር ሱፐርቫይዘር የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑን ተገመገመ
ቀን 07/05/2018 ዓ.ም
ባለፉት ስድስት ወራት በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማቀላጠፍ፣ የመምህራንን አቅም ለመገንባት እና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የታቀዱ ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ።የክፍል ምልከታ (Classroom Observation): መደበኛ በሆነ ሁኔታ በየክፍሉ በመገኘት የመምህራን የክፍል ውስጥ ስነ-ዘዴ እና የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ክትትል ፣የመምህራን ሙያዊ ድጋፍ: ለመምህራን በየደረጃው የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠናዎች እና የልምድ ልውውጥ መድረኮች ፣የትምህርት ግብዓቶች አቅርቦት: መጻሕፍት፣ የቤተ-ሙከራ ዕቃዎች እና ሌሎች የማስተማሪያ ረዳት መሳሪያዎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸው ማረጋገጥ፣የተማሪዎች ስነ-ምግባር እና ክትትል:-የተማሪዎችን ማርፈድ እና መቅረት ለመቀነስ ከወላጆች ጋር በቅርበት የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱ መሆኑን በሪፖርቱ ተገልጻል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ላይ የስራዎች አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ደመቁ ገረመዉ በበጀት አመቱ ግማሽ አመት ውስጥ ውጤታማ ስራ መሰራቱን በመግለጽ በቀጣዩ 6 ወራትም ትኩረት ሰጥቶና ተቀናጅቶ መስራት አለበት በማለት የስራ መመሪያ በመስጠት የእለቱ ዉይይት ተጠናቋል።

Photos from Arada sub-city education office   's post 10/01/2026

11ኛው የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርታዊ ሊግ ውድድር ተጀመረ።

አራዳ ጥር 2/2018 ዓ.ም

11ኛው የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርታዊ ሊግ ውድድር "በአካል ብቁና በአእምሮ ንቁ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ዛሬ መጀመሩን የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ከወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት መርኃ-ግብር የከተማ፣ የክ/ከተማና የወረዳ የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም የ1ኛ፣ መካከለኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን እንዲሁም ተማሪዎች ታድመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አበራ መልእክት ሲያስተላልፉ እንደተናገሩት ትምህርት ቤቶች ሀገር ተረካቢ ዜጎች የሚፈሩበት ስፍራ በመሆናቸው አካላዊና አእምሯዊ እድገት እንዲዳብር ስፖርታዊ ውድድሮች ባህል እንዲሆኑ አስተዳደሩ እየደገፈ መሆኑን ገልፀዋል።

የክ/ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ በትምህርት ቤቶች መካከል የሚደረገው ስፖርታዊ ውድድር በአካል፣ በስነ-አእምሮ እና በእውቀት የበለፀገ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።

የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሁነኝ መሀመድ ጤናማና በዕውቀት የዳበረ ማህበረሰብ ለመገንባት የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

በእለቱ በክፍለ ከተማው የሚገኙ የአንደኛ፣ መካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ልዑካን ቡድኖች ስፖርታዊ ፌስቲቫልና ትርኢት ያሳዩ ሲሆን የወንዶች የእግር ኳስ ውድድርም ተከናውኗል።

11ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርታዊ ሊግ ውድድር እንደ ክፍለ ከተማው ዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 20/2018 ዓ.ም በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚቆይ መሆኑ ተመላክቷል።

Photos from Arada sub-city education office   's post 05/01/2026

በአራዳ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የ2018 ትምህርት ዘመን 11ኛው ክፍለ ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር የማስጀመሪያ መርሐ ግብር አስመልክቶ ከት/ቤት ር/መ/ራን፣ከስፖርት ጽ/ቤት እና የትምህርት ባለሙያዎች ጋር ዉይይት ተካሄደ፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ ስፖርት በአካልና በአእምሮ የዳበረ ትዉልድ ለመገንባት ትልቅ ድርሻ እንዳለዉ ገልፀዋል። በትምህርት ተቋማት የሚካሔዱ የተማሪዎች ስፖርት ሊግና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር ወንድማማችነትንና እህትማማችኘትን ከማጎልበት ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ሚና እንዳለዉ ጨምረዉ በማንሳት የመክፈቻ ፕሮግራማችን በደመቀ ሁኔታ ማስጀመር አለብን በማለት በስተመጨረሻም የስራ መመሪያ በመስጠት የእለቱ ዉይይት ተጠናቋል።

Photos from Arada sub-city education office   's post 31/12/2025

በ12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር ላሸነፉ ተማሪዎች ዕውቅናና ሽልማት ተሰጠ።

አራዳ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአንደኛ መንፈቅ አመት የ12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ መርኃ-ግብር አካሄደ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱጋሳ ፈቃዱ የተማሪዎችን የትምህርት አረዳድና እውቀት ለማመዛዘን የሚረዳ መርኃ-ግብር ነበር ብለዋል።

በውጤትና ስነ-ምግባር የተሻለ ተማሪ ለአገር እድገት የድርሻውን የሚወጣ ዜጋ ይሆናል ብለው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ተማሪዎች ይበልጥ እንዲያውቁ የሚያደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ዱጋሳ አክለውም መርኃ-ግብሩን ያዘጋጁ አካላትን አመስግነው ቀጣይነት እንዲኖረው አሳስበዋል።

ጽ/ቤቱ በከፍተኛ ፉክክር ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለያዙ ተማሪዎች የምስክር ወረቀትና ሽልማት አበርክቷል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የሚገኙ የማህበራዊ ሳይንስና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መካከል ውድድር ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።

Photos from Arada sub-city education office   's post 29/12/2025

የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የአራዳ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የቤቴልሄም ክላስተር ሱፐርቫዘር አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል ባልካቸዉ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአራዳ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ አጠቃላይ በሰነዱ ዙርያ እና በመድረኩ በተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ላይ የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

Photos from Arada sub-city education office   's post 27/12/2025

ዜና አራዳ!!
በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የምስለ ችሎት (moot court) ውድድር ተካሄደ።
(ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም) ውድድሩ ከአስራ አንዱ ክፍለ ከተሞች ፣ ከሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች(ገላን የወንዶች አዳሪ ት/ቤት፣እቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ት/ቤት እና አይነስውራን አዳሪ ት/ቤት በቀረቡ ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ከቀረቡት 14 ትምህርት ቤቶች መካከል ስምንቱ የዛሬውን ውድድር አሸንፈው በቀጣይ በከተማ ደረጃ ለሚካሄደው ተመሳሳይ ውድድር ማለፍ ችለዋል።
በዛሬው ውድድር አራዳን ወክለዉ ለቀጣይ ከተማ አቀፍ ዉድድር ከአቡነ ጎርጎሪዮስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 1ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።መላዉ የትምህርት ማህበረሰብ እንኳን ደስ አለን።
ሁልጊዜም አራዳ!!

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Ethiopia, Ethiopia, 4killo
Addis Ababa
111