የትም ብትሆን አላህን ፊራ

የትም ብትሆን አላህን ፊራ

Share

People

13/06/2025

Leedâ party Qikibbossah,tasgalle party.💡💚

Leedâ yaanam inkih tan Ityoppiyah Xayloh Leeda kinnim kee Ityoppiyah Leeda Kaadu edde nummattam xiqtam inkih tan Ityoppiyah Xayloh gabah assagolla kinniimih sabbatah "Leeda kulli marah Kulli marah Leedah '' inta radmol inkih Leedah macallay.

30/10/2024

አንድን ጤናማና ሰላማዊ ማህበረሰብ ለመፍጠር፦

በውስጡ ያሉትን ግለ ሰቦች በመልካም ስነ-ምግባር ያሸበረቁ እና የተለያዩ የመልካም ስነ-ምግባር መገለጫ የሆኑ ባህሪያት ሊላበሱ ይገባል።

የኛ የግለ ሰቦች መልካም ስነ ምግባር መስተካከል መህበረ ሰቡ ላይ ትለቅ ውጤት አለው ።

ሀዲሱን አብደላህ ቢን ዓምር ሲነግረን፦

ያአላህ መልክተኛ ሰ.ዐ.ወ ከኔ ዘንድ ይብልጥ ተወዳጅና በእለተ ቂያማ ለኔ ይበልጥ የቀረበ ማረፊያ የሚኖረው ሰው ማነ እንደሆነ ልንገራችሁን?በማለት ሁለት ወይም ሶስተ ጊዜ ደጋግሞ ጠየቁ።አዎ አሏቸው።

ስነ ምግባሩ ይበልጥ ያማረው ሰው ነው ሲሉ መለሱ።

በሁሉም ቦታ የኢስላምን አኽላቅ መላበስ አለብን

ስነ ምግባራቸው ካማረው ያድርገን

08/09/2024

1, ረሱል ﷺ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች እየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ ﷺ አቡበክርንረ.ዐ "ያ አቡበከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።
አቡበክርም ረ.ዐ "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ከአንቱን ጋር መቀመጥ፣
2.አንቱን ማየት፣
3.አንቱ ባዘዙዋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።
°
ዑመርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ
1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣
2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣
3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።
°
ዑስማንን ረ.ዐ ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሰዎችን ማብላት፣
2.ሰላምታን ማብዛት፣
3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣
°
አልይን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"
"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.እንግዳን ማክበር፣
2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣
3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣
°
አባ ዘርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-
1.እርሃብን እወዳለሁ፣
2.በሽታን እወዳለሁ፣
3.ሞትን እወዳለሁ፣
ነብዩም ﷺ "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"
አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣
በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣
ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።
°
ነብዩ ﷺ " እኔም በዱኒያ ላይ
3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሽቶን እወዳለሁ፣
2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣
3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣
በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል አ.ሰ.ወ ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ
"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ
ነብዩም ﷺ "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።
1.መልዕክትን ማድረስ፣
2. አማናን አደራን መጠበቅ፣
3.ሚስኪኖችን መውደድ፣
ጅብሪል አ.ሰ.ወ ተመልሶ ወደ ከሄደ በኋላ ረሱልና ﷺ ሱሃቦቻቸው ረዲየሏሁ አጅመኢን ከመቀመጫቸው ሳይነሱ
ተመልሶ መጣና አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-
"አላህም ሱ.ወ. ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:-
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣
2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣
3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።
አላህ ሱ.ወ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ﷺ ሱሃቦች ረ.ዐ.አ የወደዱትን ያስወድደን!
°
ይህን ጣፋጭ ሐዲስ በማንበባችሁ ከፍ ያለ አጅር ታገኛላችሁ -ኢንሻ አሏህ።
ሼር በማድረግ ለሌሎች ብታካፍሉ ግን እነሱ ባነበቡት ልክ ለናንተም ሀሰናት ይፃፍላችኋል!
ኢንሻ አሏህ!!
አላህ አንብበው ከመጠቀሙት ያድርገን!!!

02/08/2024

ለአዲሶቹ ተከታዮቼ ምስጋና! በመቀላቀልዎ ደስ ብሎኛል! መሀመዘይኑ ረመቶ, Abdrmn Ades Es

10/03/2024

ያመልካሉን??

ከኢስላም ውጭ ያሉ አካላቶች ሙስሊሞችን ጨረቃን ያመልካሉ ለዚህም ጨረቃ አይተው ይፆማሉ ጨረቃ አይተው ፆም ይፈታሉና መሰል ነገሮችን ያነሳሉ።
ለዚህ የመጀመሪያው ምላሽ ሎጅክ ሚዛን ይደፋላቸዋልና ሎጅካዊይ ሲሆን እሱም፦ “ኢስላም ማንኛውንም ፍጥር አታምልኩ እያለ ተመልሶ እንደት ጨረቃን አምልኩ ይላል?? ጨረቃ ፍጡር እና የጊዜ መቁጠሪያ እንጅ ፈጣሪ አይደለም።” የሚል ሲሆን
ቀጣዩ ማስረጃ ታላቁ ቁዱሳዊይና መንፈሳዊይ ማስረጃ ሲሆን የላቀው አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፦

{{ለፀሀይና ለጨረቃ አትስገዱ ለዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ስገዱ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደሆናችሁ ለሌላ አትሰገዱ}} ሱረቱል ፉሲለት 37

በሌላ የቁርአን አንቀጽ ጠቅላላ ፍጡሮች ለፈጠራቸው ሀያል አምላክ ለርሱ ለአላህ የሚሰግዱ መሆናቸውን እንዲህ ሲል ተናግሯል።

{{አላህ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ፣ ፀሐይና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም ከሰዎች ብዙዎችም፣ ለርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን?}}

“ከአላህ ውጭ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም።”

Follow me

17/12/2023

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa