13/12/2023
🌷አንተ ሰው !🌷
👉ቃለ እግዚአብሔርን ተማር !
===================
☦ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር !
ኹልጊዜ ተማር !
ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር!
ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ።
☦ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም፡፡
ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን
እየወቀስክ ትሠራለህ፡፡
ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች !!!
"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ☦🌷
09/12/2023
ስለዚህ ምንም አይነት ፈተና ችግር ቢያጋጥማችሁ ለበጎ ነው እግዚአብሔር ለኔ ቀን አለው በሉ በእርግጥ አወ እግዚአብሔር ቀን አለው ካላንዳች ነገርም አልፈጠረንም ሁሉንም ነገር ለመልካም ውብ አድርጎ የሰራው አምላክ ነው ያ አምላክ ደሞ ልዑል እግዚአብሔር ለእኛ ስለኛ ከኛ የበለጠ ያዉቅልናል አንተ ታውቃለህ እንበለው ምክንያቱም ፍጠረን ሳንለዉ ወዶ ፈጥሮናልና ሰርቶናልና በማንኛውም ችግሮቻችን እግዚአብሔር መልስ አለው ማለትን እንልመድ🌷🥰
እግዚአብሔር መልስ አለው follow
08/12/2023
ዕለተ ዐርብ የፍቅር ቀን ጌታችን ስለ ሰው ልጆች ያለውን ፍቅሩን አስከ መስቀል ድረስ የገለጸባት ቀን፡፡
"ቸርነቱ አይለየን🙏❤
04/12/2023
ብቻህን ምንም አቅም እንደሌለህ እና በአንተ ውስጥ በሚሰራው በእግዚአብሔር ግን ጠንካራ እና ኃይለኛ እንደሆንክ ይሰማህ። ስለዚህ ይህን ጠንካራና መለኮታዊ ኃይል ሁልጊዜ ትሁት በመሆን በውስጥህ ጠብቀው።
የልብህን መሻት ለእግዚአብሔር በጸሎትህ ውስጥ ንገረው፤ ገና ከመውለዳችን አስቀድሞ ሁላችንንም ለሚያውቀን ለእርሱ። ሁሉም ነገር እንደኔ ፈቃድ ይሁን ብለህ አትጠይቅ፤ ምክንያቱም ሰው ለእርሱ የሚጠቅመውን ምን እንደሆነ ላያውቅ ይችላልና። ስለዚህ ለእግዚአብሔር እንዲህ በለው እንደ ፈቃድህ ይሁን! እርሱ ሁሉን ለጥቅማችን ያደርገዋልና።
ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
01/12/2023
ታቦተ ጽዮን እና ቅድስት ድንግል ማርያም
▬[በቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶች]▬
🔅🔅🔅
🙏እንኳን ለኅዳር ጽዮን ዓመታዊ የእመቤታችን ክብረ በዓል አደረሰን!
▬▬▬▬▬▬▬
"ጽዮን" ማለት "አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው፡፡
አባታችን አዳም ድኅነቱ የሚፈጸመው በሚስቱ እንደ ኾነ አውቆ ለሚስቱ "ሔዋን" የሚል ስም እንደ ሰጣት ሁሉ ንጉሥ ዳዊትም በቅድስት ድንግል ማርያም አማካይነት እንደሚድን በመረዳቱ እመቤታችንን፣ "ጽዮን፣ አምባዬ መጠጊያዬ" እያለ በመዝሙሩ ይጠራታል፡፡ ብዙዎች ነቢያትም ስለድንግል ማርያም ሲናገሩ ጽዮን የሚለውን ስም ተጠቅመዋል፡፡
▬▬▬▬▬▬▬
ከእመቤታችንና ከጽዮን ጋር በተያያዘ ቀደምት አባቶቻችን ያስተማሩትን ቀጥለን እንመልከት
🔅ስለቃል ኪዳኗ ታቦት
"ከአዳም ጎን በተገኘችው አንዲት ዐጥንት ምክንያት ሰይጣን ከአዳም ማስተዋልን አራቀ፡፡ ነገር ግን ከእርሱ አብራክ በተገኘችው በቅድስት ድንግል ማርያም ምክንያት በእርሱ ላይ ሠልጥኖ የነበረው ሰይጣን እንደ ዳጎን ተንኮታኩቶ ወደቀ፡፡ በታቦቱ በተመሰለችው በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ ባደረው በጌታችን በመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድል ዐዋጅ ታወጀ፡፡ በቃል ኪዳኗ ታቦት ሥር ዳጎን ተሰባብሮ እንደተገኘ እንደዚሁ ክፉው ሰይጣን በታመኑበት ፊት ድል ተነሣ፡፡ ለነገር ጥላ አለውና እግዚአብሔር የማደሪያው ምሳሌ በኾነችው በቃል ኪዳኗ ታቦት ኃይሉን በዳጎን ጣዖት ላይ እንዳሳየ እንደዚሁ አጥፊያችንን በማጥፋት እግዚአብሔር ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ተወልዶ በኃጢአት ምክንያት በእኛ ላይ ሠልጥኖ የነበረውን ሰይጣንን ድል ነሳው፡፡ የእግዚአብሔር በግ በኾነው በክርስቶስ እኛን ያዳነን እግዚአብሔር አብ ስሙ የተመሰገነ ይኹን"
▬▬▬ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
🔅ስለንጽሕናዋ
"ቅድስት ድንግል ማርያም ለጌታዋ በእርግጥ እውነተኛ አገልጋዩ ነበረች፡፡ እርሷ እንደ ቃል ኪዳኗ ታቦት በሕሊናዋ ከእግዚአብሔር ሕግጋት ውጪ ሌላ ምንም ሐሳብ አልነበራትም፡፡ በውስጥም በውጪም ነውር የሌለባት ንጽሕት ናት፡፡ እንደ ቃል ኪዳኗ ታቦት በውጪም በውስጥም በቅድስና የተጌጠችና ሕጉንም ጠብቃ የተገኘች የክርስቶስ ሙሽራ ናት፡፡ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ከሕጉ ጽላት ውጪ ሌላ ምንም ነገር እንደሌለ እንዲሁ አንቺም ቅድስት ሆይ በሕሊናሽ ምንም ነውር የሌለብሽ ንጽሕት ነሽ››
▬▬▬▬▬ቅዱስ ጀሮም
🔅ስለመመረጧ
"ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካህን ይኾን ዘንድ በሰው እንዳልተመረጠ እንደዚሁ የቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን የእርሱ ማደሪያ ይኾን ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ ማደሪያ የቅድስት ድንግል ማርያምን ቅድስናና ንጽሕና ያውጅ ዘንድ ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ታትሞአል፤ ታትሞም ለዘለዓለም ይኖራል"
እስክንድርያዊው ዲዮናስዮስ
🔅የታቦተ ጽዮን ምሳሌ ስለመኾኗ
"ነቢዩ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት በደስታ እየዘለለ ለአምላኩ ዘመረ፡፡ የቃል ኪዳኗ ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌና ጥላ ካልኾነች የማን ምሳሌና ጥላ ልትኾን ትችላለች? ይህቺ ታቦት በውስጧ የሕጉን ጽላት እንደ ያዘች እንደዚሁ ቅድስት ድንግል ማርያምም የሕጉ ባለቤት የኾነውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማኅፀኗ ተሸክማዋለች፡፡ የቃል ኪዳኗ ታቦት የኦሪትን ሕግ በውስጧ እንደያዘች አማናዊቷ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም ወንጌል የተባለው ክርስቶስን ይዛዋለች፡፡ የመጀመሪያይቱ ታቦት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የያዘች ስትኾን ሁለተኛይቱና አማናዊቷ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ግን እግዚአብሔር ቃልን በውስጧ ተሸክማዋለች፡፡ የቃል ኪዳን ታቦቱ በእርግጥ በውስጥም በውጪም በወርቅ የተለበጠ ነበር፡፡ አማናዊቷ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ግን በውስጥም በውጪም በድንግልና የተጌጠች ናት፡፡ የቃል ኪዳኗ ታቦት የተጌጠችው ምድራዊ በኾነ ወርቅ ሲኾን አማናዊቷ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ሰማያዊ በኾኑ ጸጋዎች የተሸለመች ናት"
▬▬▬የሚላኑ ቅዱስ አምብሮስ
🙏እንኳን ለኅዳር ጽዮን ዓመታዊ የእመቤታችን ክብረ በዓል አደረሰን!
30/11/2023
✞እንኳን አደረሳችሁ!✞
"መዝሙር ፻፴፯:፩"
፩. በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤
ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።
፪. በአኻያ ዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።
፫. የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም። የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።
፬. የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?
፭. ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ።
፮. ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።
፯. አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ። እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።
፰. አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።
፱. ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም!
28/11/2023
"ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ? አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።"
(ሰቆ. ኤርምያስ 5፥20-21)
26/11/2023
ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ዘማሪ መሆን እንደምትፈልግ ገለፀች፣ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር በነበራት ቆይታ ዘማሪ ለመሆን እንደምትፀልይ ተናግራለች። «እግዚዓብሔርን አምነዋለሁ እሱ ደጅ ቆሜ እንደማገለግለው፣ እሱን ለማድረግ እኔ ሰው ነኝ በስጋ ነው የምኖረው፣ ወደ መንፈሳዊ የሚያደርገኝ ፈጣሪ ስለሆነ ፀልያለሁ፣ እሱን ለማገልገል ያብቃኝ፣ ዘማሪ ሆኜ በሰይፉ ሾው ላይ ለመቅረብ ያብቃኝ!» ብላለች።
26/11/2023
ሰንበት ••ክቡር ነው
ሰንበት•ቅዱስ ነው ሰንበት የእግዚአብሔር ነው።
ሰንበት •• እሁድ ነው
ከሰንበት በረከት ረድኤት ይክፈለን።🙏❤
23/11/2023
የምሕላና የጸሎት መርሐ ግብርን በተመለከተ
ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ ማሳሰቢያ።
+++++++++++++++++++++++++++++++++
ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ከኅዳር 15 አስከ21 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሔደው የምህላና የጸሎት መርሐ ግብር ከላይ በተጠቀሱት ሰባት ቀናት ከማለዳው 12:00 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 1:00 ሰዓት በምሽት መርሐ ግብር ደግሞ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ የሚከናወን ሲሆን ሕዝበ ክርስቲያኑ በየ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ በመገኘት በመርሐ ግብሩ ላይ እንዲሳተፍ እየገለጸ አጠቃላይ መርሐ ግብሩ ቀደም ሲል በተሰጠው መግለጫ መሰረት የሚፈጸም መሆኑን ያስታውቃል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት
23/11/2023
አባ ሕርያቆስ ፀጋዬ (ቆሞስ) የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪ ሆነው ተመደቡ።
ገዳሙን ሲያስተዳድሩ የነበሩት አባ ጽጌሥላሴ መዝገቡ (ቆሞስ) ለህክምና ወደ አሜሪካ ከሄዱ ከሰባት ወራት በላይ ቢሆንም ከህመማቸው አገግመው መመለስ ስላልቻሉ በምትካቸው ቆሞስ አባ ሕርያቆስ ፀጋዬ ከኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአስተዳዳሪነት ተመድበዋል።
ደብሩ ከሰባት ወራት በላይ ያለ አስተዳዳሪ በመቆየቱ አባ ጽጌሥላሴ ህክምናቸውን በሀገር ቤት እየተከታተሉ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ በብፁዓን አባቶች ቢጠየቁም በሀገረ አሜሪካ የጀመሩት ህክምና በሂደት ላይ ያለ ቀጠሯቸውም ገና በመሆኑ መምጣት እንደማይችሉ በማሳወቃቸው በምትካቸው አስተዳዳሪ መመደቡን ሀገረ ስብከቱ አስታወቋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ወልድያ መንበረ ንግሥት ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበሩት ቆሞስ አባ ሕርያቆስ ፀጋዬ ኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም ከማኅበረ ካህናቱና ምዕመናን ጋር ተዋውቀው ሥራ መጀመራቸውን ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዘገባ ያሳያል።
22/11/2023
🌹 #እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ📌
✅ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ ካ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው። ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥ «አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት መካከል) አንተን የሚመስል ማነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነው?» ብሏል። ዘጸ ፲፭፥፲፩። ቅዱስ ዳዊትም፦ «አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። መዝ ፹፭፥፰።
heran ሔራን