FDRE Education and Training Authority-ETA

FDRE Education and Training Authority-ETA Encourage and assist the growth of organizational culture in education and training institutions.
(1)

የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የኘሮግራም ፈቃድ ዕድሳት ቅድመ ሁኔታዎች -----------------------------------------------------------------------**  የፕ...
21/08/2026

የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የኘሮግራም ፈቃድ ዕድሳት ቅድመ ሁኔታዎች
-----------------------------------------------------------------------
** የፕሮግራሞቹ እድሣት /የፈቃድ እድሳት/ እንደ ፕሮግራም ቆይታው በተቋሙ ላይ በየጊዜው የሚደረግ ምርመራን መሠረት በማድረግ በየሶስት ዓመቱ የሚደረግ ሲሆን ይህንን ሳያመለክት የቀረ ማንኛውም ተቋም ፕሮግራሙ የማይታደስለት ይሆናል።

** ለተቋማት የኦዲት፣ እውቅና፣ ድጋፍና ኢንስፔክሽን ሊደረግ የሚችል ሲሆን በዚህም የተገኘው ሪፖርት መጨረሻ ላይ ለፈቃድ እድሣት በግብዓትነት የሚያገለግል ይሆናል።

** ከስልጠና ፕሮግራሙ ተመራቂዎች ውስጥ በፌደራል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ብቁ ሆነው የተገኙትንና በግልም ሆነ በቅጥር ስራ ያገኙት ሰልጣኞች ብዛት ባለፉት ሦስት ዓመታት እየጨመረ የመጣ መሆኑን ማረጋገጥ።

** በፈቃድ ተመዝግበው ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ሰልጣኞች ምዘና አፈጻጸም ከ50% በታች ያስመዘገበ ተቋም የፈቃድ እድሳት አይሰጠውም።

** የተቋሙ ራእይ፣ ተልእኮ፣ ዓላማና አሰራር ከትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት።

** የሙያ ደረጃዎችንና ስርዓተ ትምህርትን፣የአሰልጣኞችን ብቃት፣ የማሰልጠኛ እቃዎችን ፣ የስልጠና መሳሪያዎችን ፣ ቁሳቁሶችንና የመረጃ መሳሪያዎችን አስመልክቶ የተቀመጡትን ዝቅተኛ መለኪያዎች ማሟላት ይኖርበታል።

** ለስልጠና ሂደቱ ይረዳ ዘንድ እንደየሙያ ዓይነቱ ባህሪ ተቋሙ በምቹ ቦታ እና የተሟላ ማስተማሪያ ክፍሎች/ሰርቶ ማሳያ ቦታ/ /Laboratory/ /work shop/ ያሉት ስለመሆኑና በአስፈላጊው የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ስለመደራጀቱ ዝግጅቱ ሁሉ ይህን የሚያሳይ መሆን አለበት።

** የሙያ ምዘናን የማሣለፍ መጠን ስልጠና ካጠናቀቁት ውስጥ ቢያንስ 50 በመቶ የሚሆኑት የሙያ ምዘናን ማለፍ ይኖርባቸዋል።

** እየጨመረ የመጣ ወደ ስራ የተሰማሩ ምሩቃን መጠን፤

** የተሻሻለ የሙያ ደረጃን ካለ ተከትሎ የተሻሻለ ስርአተ ትምህርትና የማስተማሪያ የማሠልጠኛና የመማሪያ ማቴሪያሎች፤

** እየጨመረ የመጣ ብቃታቸው የተረጋገጠ መምህራን በደረጃና በመቶኛ፤

** ስልጠና አጠናቀው የወጡ ባለሙያዎች ያሉበትን ሁኔታ የሚያሣይ የጥናት ሪፖርት (Tracer Study) ፤

** ፈቃድ ባለው የሒሣብ ባለሙያ የተደረገ የኦዲት ሪፖርት፤

** የተከማቸና የተሸጋገረ ቴክኖሎጂ፤

** በአካባቢው ካለ ኢንዱስትሪ ጋር የተደረገ ከኘሮግራሙ ጋር ተዛማጅነት ያለው የመግባቢያ ስምምነት አተገባበር፤

** በተቋሙ ድጋፍ አማካኝነት የተደራጁ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ብዛት፤

** የጥራት አመራር ስርአት /Quality Management System/ ትግበራ የሚያሳይ መረጃ፤

** በዚህ የማረጋገጥ ሂደትም የአካባቢው የሰው ሀይል ገበያ መረጃ፣ የክትትል ሪፖርቶች፣ ጥራት ያለው የአመራር ስርአት ሪፖርትን አስመልክቶ የተሰጡ ግብረ መልሶች፣ አመላካች ጥናት ነው፡፡በተጨማሪም በዚህ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ለአካል ጉዳተኛ ሰልጣኞች ተገቢውን እድል የሰጠ ተቋም ከመደበኛው መስፈርት ተጨማሪ ነጥብ ያገኛል፡፡

** በስልጠናው የተሳተፉ አካል ጉዳተኞች ብዛትና ከስልጠና በኋላ ስላሉበት ሁኔታ የሚገልፅ የጥናት ሪፖርት (Tracer Study)

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ።

በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ 988/2016 መሠረት አጫጭር ስልጠና፤የተማሪ ቅበላ መጠን ጥያቄ፤ፕሮግራም ማስፋፊያ ጥያቄ፤ተጨማሪ ካም...
18/08/2026

በከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ 988/2016 መሠረት አጫጭር ስልጠና፤የተማሪ ቅበላ መጠን ጥያቄ፤ፕሮግራም ማስፋፊያ ጥያቄ፤ተጨማሪ ካምፓስ ጥያቄ እና ተጨማሪ ፕሮግራም ጥያቄ ማለት፡-
-------------------------------------------------------------------------
፡-

ማንኛውም ተቋም የከፍተኛ ትምህርትን ወይም የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ሊያግዝ የሚችል ተጨማሪ እውቀትንና ክህሎትን ለማስተላለፍ የሚሰጥ ማንኛውም ስልጠና ነው።

፡-

ተቋማት ባላቸው የግብዓትና የሰው ሀይልመጠን ለማስተማር የሚፈቀድ የተማሪ ቁጥር ብዛት ጥያቄ ነው።

፡-

ማንኛውም ተቋም ቀድሞ ፈቃድ ባገኘበት ፕሮግራም በተፈቀደለት የተማሪ ቁጥር ላይ ተጨማሪ ተማሪዎችን ለመቀበል በመስፈርቱ መሠረት ተጨማሪ የግብዓት እና የሰው ሃይል ተሟልቶ የሚቀርብ ጥያቄ ነው።

፡-

ማንኛውም ተቋም ቀደም ብሎ ፈቃድ ካገኘበት ካምፓስ ውጪ አዲስ ካምፓስ ለመክፈት የሚቀርብ ጥያቄ ነው።

፡-

ማንኛውም ተቋም ፈቃድ ካገኘበት ፕሮግራም ዉጪ ሌላ አዲስ ተጨማሪ ፕሮግራም ለመክፈት የሚቀርብ ጥያቄ ነው።

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።

የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የኘሮግራም ፈቃድና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መስፈተርቶች/ስታንዳርዶች/-------------------------------------------------------------...
14/08/2026

የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የኘሮግራም ፈቃድና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መስፈተርቶች/ስታንዳርዶች/
-------------------------------------------------------------------------------
** የተቋሙ አመራር እና አደረጃጀት፤
** የአስተዳደራዊ ሰነዶች፣ መመሪያዎችና ተሟልተው መያዝ ስላለባቸው ደንቦች እና ደጋፊ ሰነዶች፤
** የማሰልጠኛ ተቋማት ሕንፃዎች ከባቢያዊ ሁኔታና የቦታ ስፋት መለኪያዎች፤
** የስርዓተ ትምህርት መስፈርቶች፤
** የሰው ሀብት፤
** የመማሪያ ክፍሎች ስፋትና ተፈላጊ ቁሳቁሶች፤
** ቢሮዎችና የተቋሙ ፊዚካል ግብዓቶች፤
** የሰርቶ ማሳያ ክፍሎች ስፋት እና ግብአቶች (ላብራቶሪዎች፣ዴሞንስትሪሽን፣ወርክ ሾፖች እና ኮምፒውተር ማዕከል)፤
** ቤተመጻሕፍት ስፋትና ይዘት፤
** የተማሪ ቅበላና ሬጂስትራር ፤
** የጥራት ማረጋገጥ ስርዓት፤እና
** የጥናት እና ምርምር፤ የፕሮጀክት ኢንዳስትሪያል ኤክስቴንሽን እና የማህበረሰብ አገልግሎት ናቸው፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።

በዓለም ዓቀፍ፣ የማህበረሰብ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ 992/2016 መሠረት በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ፈ...
12/08/2026

በዓለም ዓቀፍ፣ የማህበረሰብ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ 992/2016 መሠረት በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ፈቃድ ጠያቂ ትምህርት ቤት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ ሲገኝ ባለሥልጣኑ ፈቃድ ይሰጣል
--------------------------------------------------------------------------------------------------
** ትምህርት ቤቱ ከሚቋቋምበት ሀገር ጋር የተደረገ የስምምነት ሰነድ እና የትምህርት ቤቱን ደረጃ የሚመጥን ግብአቶችን ማሟላት፤
** ለደረጃው የሚመጥን አካዳሚያዊና አስተዳደራዊ አደረጃጀትን የሚያሳይ ሰነድ፤
** የትምህርት ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ እና የመመስረቻ ሰነድ ሲቀርብ እውቅና የሚሰጥ ይሆናል።
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።

በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 ረቂቅ ማሻሻያ ላይ   የፊት ለፊት ወይም የገጽ ለገጽ የውይይት መድረክ ተካሄደ----------------------------...
07/08/2026

በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 ረቂቅ ማሻሻያ ላይ የፊት ለፊት ወይም የገጽ ለገጽ የውይይት መድረክ ተካሄደ
------------------------------------------------------------------------------------------------------

ነሀሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ረቂቅ ማሻሻያ ላይ ከትምህርት ማህበረሰብና ከባለድርሻ አካላት የፊት ለፊት ወይም የገጽ ለገጽ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የውይይት መድረኩን የመሩት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ መስፍን ባለሥልጣኑ የማሻሻያውን ረቂቅ ማስታወቂያ ፤ የአስተያየት መስጫ ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ በማዘጋጀት እና በተቋሙ የኢ-ሚይል አድራሻ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ከሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም አስተያየተቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ ሰፊጥረት መደረጉን ገልጸው ባለሥልጣኑ የተጣለበትን የትምህርትና ስልጠና ጥራት የማረጋገጥ ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶች የመቅረጽ እና አላሰራ ያሉ መመሪያዊች እንዲሻሻሉ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።

የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሞላ ጸጋዬ በበኩላቸው ባለሥልጣኑ የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ እየሰራ ያለውን ሥራ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ የባለሥልጣኑ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና አቻ ግመ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ገ/መድህን በረቂቅ ሰነዱ ላይ ያተኮረ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሀሳብ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሐሳቦች፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ፡፡

ባለሥልጣኑ በአረንጓዴ አሻራ እና በክረምት በጎ ተግባራት ድጋፍ ላይ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ተወያየ ------------------------------------------------...
04/08/2026

ባለሥልጣኑ በአረንጓዴ አሻራ እና በክረምት በጎ ተግባራት ድጋፍ ላይ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ተወያየ
--------------------------------------------------------------------------
ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ባለሥልጣኑ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በአረንጓዴ አሻራ እና በክረምት በጎ ተግባራት ድጋፍ ላይ ውይይት አካሄደ ።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው ሊሰሩ የታቀዱት የአፀደ ህጻናት እና የአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ በቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን መሆኑ ገልጸው በዚህ በጎ ተግባር የሚሳተፉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የእውቅና ሰርተፍኬት ፤የሚሰጡት ድጋፍ ከታክስ ነጻ እንዲሆን የሚያደርግ የድጋፍ ደብዳቤ ፤ከተቋማቸው ተልእኮ አንጻር የማህበረሰብ አገልግሎት እና የጥናትና ምርምር ሥራዎች ጋር በተያያዘ የላቀ አበርክቶ እንዳለው አብራርተዋል።

የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ መስፍን በበኩላቸው ለሚገነቡት የአጸደ ህጻናት እና ለአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ በአጠቃላይ በትንሹ 24 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ወጪው የህጻናቱን የደብተር፣ የእስክሪፐቶ እና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን የሚሻፍን መሆኑን ገልጸዋል ።

የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሞላ ጸጋዬ ተቋማት ፈቃድ እንዲያገኙ ማሟላት ከሚገባቸው መስፈርት አንዱ የማህበረስብ አገልግሎት በመሆኑ ተቋማቱ በተለያየ መንገድ የሚያደርጉትን የማህበሰብ አገልግሎት እንዲህ በተደራጀ መልኩ እንዲሆን ባለሥልጣኑ ከመንግስት የተረከበውን የአረንጓዴ አሻራ እና የክረምት በጎ ተግባራት ሀገራዊ ንቅናቄ ኃላፊት እንዲወጣ ለማስቻል በቦርዱ እና በተቋማቸው ስም ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለአረንጓዴ አሻራ እና ለክረምት በጎ ተግባራት የያዙት በጀት ባይኖርም ለትምህርት የሚደረግ ድጋፍ የዜግነት ግዴታ በመሆኑ በራሳቸውና በቀድሞ ተማሪዎች እንዲሁም በሌሎችም ድጋፍ የሚጠበቅባቸው ኃላፊት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ 800 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምብር የመትከል መረሀ ግብር አካሄዱ--------------------------------------------------------...
03/08/2026

የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ 800 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምብር የመትከል መረሀ ግብር አካሄዱ
----------------------------------------------------------------------

የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከተማ በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ አካባቢ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ።

በጋራ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሐሳብ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው 800 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምብር መረሀ ግብር ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት ለሀገራችን ሁለንተናዊ ልማትና ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ወሳኝ መሆኑን ፤ችግኝ መትከል ከራስ አልፎ ለቀጣይ ትውልድ የመልካም አካባቢ ውርስ ማስቀመጥ እና ከራስ አልፎ ለትውልድና ለሀገር ማሰብ የሰው ልጅ ትልቅነትን የሚያሳይ መለኪያ መሆኑን ገልጸው በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተተከሉት ችግኞች ከምግብ ምንጭነታቸው ባሻገር ለደን ልማት፣ ለአፈር ለምነት ጥበቃ እና ለአካባቢ ሥነ-ምህዳር መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ በመሆናቸውየዘርፉ አመራሮችና ሠራተኞች እነዚህን ችግኞች በመትከል አርአያነታቸውን በተግባር ማሳየታቸው የሚደነቅ እና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ነው ብለዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ፤ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ፤በኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የተቋማት ቁጥጥር ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሺሻይ አማረ እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በቦታው በመገኘት ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።


የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ::

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርበጋራ ተስፋን እንትከል!ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ምበሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጸናች ኢትዮጵያ ያላቸውን ጠንካራ አንድነት እና የጋራ ኃላፊ...
31/07/2026

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር
በጋራ ተስፋን እንትከል!
ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
በሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጸናች ኢትዮጵያ ያላቸውን ጠንካራ አንድነት እና የጋራ ኃላፊነት በሚያንጸባርቀው፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሥር ለታሪካዊው ሀገራዊ ዘመቻ በጋራ በመሰብሰብ በአንድ ቀን 800 ሚሊዮን ችግኞችን ይተክላሉ።
!

 #ማስታወቂያ !የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ብቻ ሀ፣ለ እና ሐ ተብሎ ተጨምሮ...
31/07/2026

#ማስታወቂያ
!

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ብቻ ሀ፣ለ እና ሐ ተብሎ ተጨምሮ በተዘጋጀው ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ዓርብ ነሐሴ1 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ የፊት ለፊት (የገጽ ለገጽ) የመወያያ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓትና ቦታ ተገኝተው የውይይቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።

የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች  የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን  ገመገሙ------------------------------------------------------------------...
29/07/2026

የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገሙ
------------------------------------------------------------------------------------------
ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም በባለሥልጣኑ ሊሰሩ የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን መነሻ በማድረግ በየሥራ ክፍሎቹ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እና ግምገማ ተደርጓል።

በግምገማ መድረኩ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት፤የእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ፤የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ፤የሥራ አመራር እና የአስተዳደር ዘርፎች በ12 ወራት ሊሰሯቸው የታቀዱ ዋና ዋና ግቦችን መነሻ በማድረግ በየሥራ ክፍሎቹ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት በባለሥልጣኑ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት በወ/ሮ አመለወርቅ ቀርቦ ሰፊ ውይይት እና እና ግምገማ ተደርጓል።

ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ በርካታ ውጤታማ ተግባራትን እንዳከናወነ የተገመገመ ሲሆን በተለይም በፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት ዘርፍ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ መደረጉ እና የዳግም ምዝገባ ውሳኔ የያዘ ሪፖርት ለተቋማቱ እንዲደርስ መደረጉ ፤ በክልል የሚገኙ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ፤ ለክልል መንግስታት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ፤ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እና በዳግም ምዝገባ ውሳኔ ቅሬታ ላቀረቡ ተቋማት ምላሽ መሰጠቱ፤ የጥራት ኦዲት ሥራን አስመልክቶ የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አካዳሚክ የጥራት ኦዲት የአሠራር ስርዓቶች ተዘጋጅተው እንዲጸድቁ መደረጉ፤ በአካዳሚክ የጥራት ኦዲት የአሠራር ስርዓቶች እና ስታንዳርዶች ዙሪያ ለአካዳሚክ የጥራት ኦዲተሮች ስልጠና መሰጠቱ፤ በራሳቸው ተነሳሽነት ለጠየቁ ተቋማት በተቋማዊና በፕሮግራም አካዳሚክ የጥራት ኦዲት አጠባበቅና የግል ግምገማ አዘገጃጀት ላይ ስልጠና መሰጠቱ፤የእርካታ ዳሰሳ ጥናት መካሄዱ፤በፕሮግራም የጥራት ኦዲት ስታንዳርድ መሠረት ተቋማት ግለ ግምገማ ማካሄዳቸው እና በአስር የከፍተኛ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የጥራት ኦዲት መከናወኑ ተገልጿል።

የአጠቃላይ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ ላይ የተሠሩ ሥራዎች አፈጻጸም ያደገ መሆኑ በተለይም ለዓለም አቀፍ እና ለማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች አዲስ ፈቃድና የፈቃድ እድሳት ሥራ በእቅዱ መሠረት መከናወኑ ፤ በእውቅና እና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ስለእውቅና አሰጣጥ ያለው ግንዛቤ መዳበሩ፣ የእውቅና አሰጣጥ ሥራ ዲጂታላይዝ መደረጉ ፣በርካታ ተቋማት የፕሮግራም እውቅና ይሰጠን የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው እና ለሁለት ፕሮግራሞች ሙሉ እውቅና ለአምስት ዓመት ለአስራ አንድ ፕሮግራሞች ደግሞ በቅድመ ሁኔታ ለሶስት ዓመት እውቅና መሰጠቱ፤እንዲሁም በባለሥልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ስራ ክፍል የአሰራር ስርዓቶች ከተቋሙ ዓላማና ግብ ስኬት አንጻር ተግባራዊነታቸው ላይ ክትትል መደረጉ፤ከ2014 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም የተዘጋጁ ማኑዋሎች፣ ጋይድላይኖች፤ስታንዳርዶች ፣ መመሪያዎች ደንቦች ተሰብስበው እንዲገመገሙ መደረጉ፤ የአሰራር ስርዓቶች እንዲዘጋጁ መደረጉ፤የትምህርትና ሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥና ለማጎልበት የሚያግዙ ዘጠኝ የትኩረት መስኮችና የጥናትና ምርምር እና ሀምሳ አንድ ቁልፍ የምርምር ትኩረቶች ተለይተዉ በባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ጉባኤ እንዲጸድቅ መደረጉ እና የጆርናል ኤዲቶሪያል ፖሊሲ እና የጥናትናምርምር መምሪያ ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎችን ከዩኒቨርሲቲዎችና ከምርምር ተቋማት በመጋበዝና በማሳተፍ ተዘጋጅተው ለማፅደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ዘርፍ የተቋማት የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና የኢንስፔክሽን ሥራ አፈጻጸም ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑ እንዲሁም የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ አገልግሎት አሰጣጥን መሻሻል በመቻሉ ከበርካታ የመንግስት እና የግል ተቋማት የሠራተኞቻችን የትምህርት ማስረጃ የይረጋገጥልን ጥያቄ መቅረቡ እና በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው በግል የራስን ትምህርት ማስረጃ የማረጋገጥ ፍላጎትና ተነሳሽነት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ እንዲሁም ባለሥልጣኑ ከመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ለበርካታ የትምህርት ማስረጃዎች ማረጋገጫ የሰጠና እና የአቻ ግመታ ሥራ ያከናወነ መሆኑ፤ በሥራ አመራር እና በአስተዳደር ዘርፉም የተቋሙ ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች በመደገፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሠሩ ሥራዎች ጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የባለሥልጣኑን ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ የሚያስችለው የውስጥ ጥራት ኦዲት ስራ ከኢትዮጵያ ስታንዳር ኢንስቲትዩት ጋር በጥራት አስተዳደር ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የቴክኒክ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሞ ወደ ሥራ መገባቱ እና ለማኔጅመንትና ለተቋቋመው ግብረ ሀይል የዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ለመተግበር የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱ፣የሥራ ክፍሎችን የአሰራር ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያግዙ ማንዋሎች፣የተለያዩፎርማቶች፣ፕሮሲጀሮች፣ቼክሊስቶች፣ኳሊቲኦብጀክቲቭ፣ሪስክ አይደንትፊከሽና አሰስመንት፣ፖሊሲ እና ሌሎችም ተዘጋጅተው በየሥራ ክፍሎች የተገመገሙ መሆኑ በውይይቱ እና በግምገማ መድረኩ ተብራርቷል:።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብተው በበኩላቸው መድረኩ ያለፉት ሥራዎች የተገመገሙበት ፤የቀሩ ሥራዎች የሚከናወኑበት እና ለቀጣይ በጀት ዓመት የሚሆን እቅድ የሚዘጋጅበት መሆኑን ገልጸው ባለፈው በጀት ዓመት ሁሉም የሥራ ክፍሎች ያቀደቱን ሥራ ሙሉ በሙሉ ያከናወኑበት፤ለተቋሙ ወሳኝ የሆኑ የሥራ ክፍሎችን የማጠናከር ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተከናወነበት፤ቀደም ሲል ፈቃድ

የተሰጣቸው ተቋማት ወደ ጥሩ ቁመና እንዲመጡ እና አዳዲስ ተቋማት ጤናማ ሆነው እንዲወለዱ ሰፊ ሥራ የተሠራበት መሆኑን ገልጸው በበጀት ዓመቱ የተበታተኑ ሥራዎች ወደ አንድ እንዲመጡና ተናባቢ እንዲሆኑ በተቋሙ ውስጥ በላቀ መግባባትና ቁርጠኝነት መሠራቱን ገልጸዋል ፡፡ የባለሥልጣኑን የውስጥ አሰራር ጥራት በማረጋገጥ ረገድ የዓለም አቀፍ የጥራት አመራር ስርዓት ISO9001:2015 ትግበራ መጀመሩ እና የበሰለ የጥራት ኦዲት ሪፖርት ዝግጅት መጀመሩ በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑት ዐበይት ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ተቋማት በአመሰራረታቸው፣በቆይታቸው እና በደረሱበት ደረጃ ለመለየት የሚያስችል የኦዲት፣የእውቅና አሰጣጥ እና የኢንስፔክሽን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና ባለሥልጣኑ ተዓማኒነትን፣ግልጸኝነትን እና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ ለውጥ በማምጣት ለትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መሠረት የሆነውን የለውጥ ስራ ማጠናከር በቀጣይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ገልጸዋል ፡፡

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ፡፡

Address

Addis Ababa, Sidist Kilo, Shero Meda
Addis Ababa
27424/1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FDRE Education and Training Authority-ETA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share