04/01/2026
Derartu tulu Former Student.
school preparatory
04/01/2026
አንዲት የጽዳት ሰራተኛ አንድ ቦርሳ ይዛ ወደ አለቃዋ ቢሮ ገባችና "ጌታዬ፣ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ እያጸዳሁ ሳለ ይህንን ቦርሳ አገኘሁት" አለች።
አለቃውም "እሺ፣ እዚህ አስቀምጪው" አለ።
ሰራተኛዋም በመቀጠል "ቦርሳው በከፊል ክፍት ስለነበር፣ 3,000 ዶላር አየሁ። አንዳንድ ዕቃዎችም ወድቀው ስለነበር በጥንቃቄ መልሼ አስቀምጬዋለሁ" አለች::
አለቃው አመስግኖ አሰናበታት:: ወዲያውም ትልቅ ደንበኛቸው ለሆነውና ለቦርሳው ባለቤት ለሚስተር ዊልሰን ደውሎ "ሄሎ፣ ቦርሳዎን እኛ ጋር ረስተውት ሄደዋል" አላቸው::
ሚስተር ዊልሰንም፣ "ኦ! እግዚአብሔር ይመስገን! የት ጣልኩት ብዬ ተጨንቄ ነበር። ውስጥ 5,000 ዶላር አለበት" አሉ።
ስልኩ ሲዘጋ አለቃው ግራ ተጋባ። የጽዳት ሰራተኛዋ ያለችው 3,000 ነው፤ ባለቤቱ ግን 5,000 ነው ያለው።
ጸሃፊዋ ጣልቃ ገባችና "ጌታዬ፣ የጎደለውን 2,000 ዶላር በእርግጠኝነት እሷ ነች የወሰደችው" አለች::
አለቃውም "ለምን እንደዚያ አሰብሽ?" ሲል ጠየቃት።
"ምክንያቱም እሷ የሁለት ልጆች እናት የሆነች፣ ያለ ባል የምትኖር ችግረኛ ናት። ባለፈው ሳምንት ደሞዝ እንዲጨመርላት ስትለምን አይቻታለሁ። እንዳይገርምህ ጌታዬ፣ እንዲህ አይነት ሰዎች በጣም አጭበርባሪ ናቸው፤ እመነኝ እሷ ናት የሰረቀችው" አለች።
ከስራ በኃላ ወደ ቤት ሲሄዱ፣ አለቃው የጽዳት ሰራተኛዋን ጠጋ ብሎ "እሜቴ፣ በኑሮ እየተቸገርሽ ነው?" ሲል ጠየቃት።
"አዎ ጌታዬ፣ ትንሽ ከበድ ብሎኛል። ልጄ ሆስፒታል ታማብኝ ለህክምናዋ 2,000 ዶላር አስፈልጎኛል" አለች።
ወዲው ጸሃፊዋ ጮኸች! "አየህ ጌታዬ! ልክ የጎደለው ገንዘብ መጠን ነው! እሷ ሌባ ናት!" አለች::
የጽዳት ሰራተኛዋም ደነገጠች:: መልሳም "ሌባ? ኧረ እኔ ምንም አልሰረቅኩም፤ ለምን ትዋሺለሽ?" አለች።
አለቃውም "በቃ ይበቃል፣ ሂጂ" ብሎ ተሰናበታት።
በሚቀጥለው ቀን ሚስተር ዊልሰን ቦርሳቸውን ሊቀበሉ መጡ። ቦርሳውን ሲከፍቱ ግን 3,000 ዶላር ብቻ አገኙ።
አለቃውና ፀሐፊዋም ምን ይፈጠር ይሆን ብለው ይጠብቁ ጀመር::
ነገር ግን ሚስተር ዊልሰን አልተቆጡም፣ እንዲያውም ተገረሙና "ኦ! ይቅርታ በጣም ትላንትና ረስቼው ነበር። ለካ 2,000 ዶላሩን ለጓደኛዬ ለመስጠት ቀንሼ ነበር። ቦርሳው ውስጥ ትቼ የሄድኩት 3,000 ዶላር ብቻ ነው። ስለ ስህተቴ ይቅርታ" አሉ።
በዚህ ጊዜ ጸሃፊዋ በአፍረት ደርቃ ቀረች። በስህተት ጽዳት ሰራተኛዋን በመወንጀሏ ምክንያት::
አለቃው ግን ፈገግ አለና የጽዳት ሰራተኛዋን አስጠራት። ለደንበኛው እያሳየ፣ "ቦርሳዎን ያገኘችው ይህች ሴት ናት። ምንም እንኳን የራሷ ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ቢኖርባትም፣ እምነቷን ጠብቃ ቦርሳውን መልሳለች። ከዛሬ ጀምሮ እሷ አዲሷ ምክትል ረዳቴ ናት። ደሞዟም ይጨምራል፣ የልጇም ህክምና ይሸፈናል" አለ።
-------------- ------------- -------------
በችግር ውስጥም ሆኖ ታማኝ መሆን ትልቅ ዋጋ ያስገኛል።
ሰውን በሁኔታው አይተን መፍረድ ስህተት ነው።
እውነት ትዘገይ ይሆናል እንጂ፣ የልፋት እና የታማኝነት ዋጋ መከፈሉ አይቀርም።
ታማኝነት መሸለም አለበት ብላችሁ ካመናችሁ፣ እስቲ የልብ ምልክት (❤️) ኮሜንት ላይ አስቀምጡ።
🛑ላይክ ሼርና ፎሎ ማድረግ እንዳይረሳ!!!
30/12/2025
Who wll win today ?
03/12/2024
ታላቅ_መንፈሳዊ_የንግስ በዓል ጥሪ
የፊታችን ታሕሳስ 19-04-2017 ዓ/ም በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በገላን ክ/ከተማ ልዩ ስሙ ደ/ቅ/ደ/መ/የዋሻው ቅዱስ ገብርኤል ቤተ_ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት የሚከበረዉን የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን አመታዊ በዓለ ንግስ ምክንያት በማድረግ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን የበዓሉ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን እንዲሁም በመገንባት ላይ ያለውን ዘመናዊ ሕንፃ ቤተ_ክርስቲያን ከ90% በላይ ስራዉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪዉን 10% ለማጠናቀቅ
የደብሩ ሕንፃ አሰሪኮሚቴ እና የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በጋራ በመሆን በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ስም የበኩላችሁን አስተዋፅዎ እድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን
ሕንፃ አሰሪኮሚቴ የባንክ ሒሳብ ቁጥር
CBE 1000180789689
የቴሌግራም ገጽ የሲዳ አዋሽ የዋሻው ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ አሰሪኮሚቴ/https://t.me/+ql-2ojBKasJmZGJk ሼር 1 ሰዉ ለ19 ሰዉ.
11/09/2024
11/09/2024
zerihun a on TikTok .a6 1013 Followers, 3 Following, 8 Likes - Watch awesome short videos created by zerihun a
08/09/2024
TikTok · zedo Check out zedo’s video.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa