የቅዱሳን ታሪክ

የቅዱሳን ታሪክ

Share

✞✞✞በአምላክ ቸርነት በእመብርሃን ፍቃድ ስለ ቅዱሳን ገድል

12/08/2023

ነሐሴ 7 ጽንሰታ ለማርያም

" አሁንም የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማህበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት? ከይሁዳ ወገን ለኾነችው ንጽሕት ርግብ መፀነስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ የጾታዊ ተዋሕዷቸው ቀን ይኽቺ እንዴት ያለች የተመረጠች ቀን ናት፤ ለንጉሥ ማደሪያ አዳራሽ መመሥረት የተደረገባት የደስታ ቀን እንዴት ያላች ቀን ናት "
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/መጽሐፈ አርጋኖን

ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው።

ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና ። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር ። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ።

የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች።

በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ፀንሳለች።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

09/12/2022

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን !
ወር በገባ ፩~1 የሐዋርያዊ የቅዱስ በርተሎሜዎስ ወርኀዊ መታሰቢያው ነው ።
>>ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ> ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው። {ማቴ. ፲÷፫} ነገር ግን ዜና ሕይወቱ በስፋት ሲተረክ አንሰማም ቅዱሱ ሐዋርያ እንደ ሌሎቹ ወንድሞቹ ዓለምን በወንጌል ትምሕርት አብርቷል።
>> በትውፊት ትምሕርት መሠረት "በርተሎሜዎስ" የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታችን ሲሆን ትርጉሙም 'ተክሎችን የሚያጠጣ' ማለት ነው።
>> ከሐዋርያትም ጌታ አስቀድሞ የስም ቅያሪ ያደረገለት ለእርሱ እንደ ሆነ ይታመናል። በርተሎሜዎስ የግብርና ሥራውን ትቶ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ከዋለበት እየዋለ ካደረበትም እያደረ ምሥጢረ ወንጌልን ተምሯል።
>> ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላም ከሐዋርያት ጋር ዓለምን በዕጣ ተካፍሏል ሃገረ ስብከቱም 'እልዋህ' እና 'አርማንያ' ናቸው የአርማንያ መንበርም የእርሱ ነው:: ቅዱሱ ገድሉ እንደሚለው አሕዛብን በስብከቱና በሚያስደነግጡ ተአምራቱ አሳምኗል::
>> ከቅዱስ ዼጥሮስ ከቅዱስ እንድርያስ ከክርስቶፎሮስና ከሌሎቹም ሰባክያን ጋር ዓለምን ዙሯል። ሙታንን አስነስቶ ድውያንን ፈውሶ አጋንንትን አውጥቶ ብዙወችን ወደ ሕይወት መልሷል። የደረቁ እንጨቶችም በእጁ ላይ እንዳሉ ለምልመው አብበው ያፈሩ ነበር።
>> ቅዱስ በርተሎሜዎስ እያስተማረ ወደ ኢትዮዽያም ደርሶ እንደ ነበር ይነገራል በመጨረሻም 'ለሚስቶቻችን ንጽሕናን አስተምረሃል' በሚል ተከሶ ንጉሥ አግሪዻ በሰቅ (ጸጉር) ጠቅልሎ አሸዋ ሞልቶ ባሕር ውስጥ ጥሎታል። በዚያውም ዐርፏል።
ቸሩ አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት ያሳትፈን እኛንም በፀሎታቸው አስቦ ይማረን አሜን ፫

19/09/2022

ራስህን "ነቢይ ነኝ " ብለህ ከመሾምህ በፊት ነቢዩ ኢሳይያስ እኛ አሁን እየታነፅንበት ላለው ወንጌል በመጋዝ ሁለት ቦታ ተሰንጥቆ መሞቱን ታውቃለህ?
ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለህ ከመሾምህ በፊት ለዚህ የወንጌል እውነት ሐዋርያው ዮሐንስ በሚፈላ ዘይት በርሜል ውስጥ ተዘፍዝፎ መሞቱን ፡ እንዲሁም ሐዋርያው ጴጥሮስ"እንደ ጌታዬ በቁሜ አልሰቀልም" ብሎ ወደታች ተዘቅዝቆ በመስቀል መሞቱን ታውቃለህን!?
የጥንቱ ሐዋርያት ዘመናዊ ውድ መኪና የመንዳት፡ዘመናዊ ቪላ የመስራት ፡የቱርክ ሱፍና የፈረንሳይ ሽቶ የመቀባት አባዜና ጥማት አልነበረባቸውም።
የጥንቱ ሐዋርያው በጥቁር ገበያ በተጭበረበረ ዶላር ዩሮና ፓውንድ ፡ ከድሆች መቀነት በተዘረፈ ብር ቢሊይነር የመሆን ሕልም አልነበራቸውም።
የጥንቱ ሐዋርያት ዘይት ውኃ ጨርቅ ሶፍት ጨርቃ ጨርቅ ሸጠው ባለጠጋ የመሆን ህልም አልነበራቸውም። ትልልቅ የተንጣለለ አዳራሸ አልገነቡም ፡የተሸቃቀጠ ወንጌል ሰብከው ዝናን አላካበቱም። ሐሰትን ከእውነት ቀላቅለው እንደ ሸቀጥ ለገበያ አላቃረቡም!!

03/04/2021

በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሃድ አምላክ አሜን

+++ማህበራችን ማህበረ ሥላሴ(ዘከታ) እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶሰ አብይ ፆም በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያለ

ታላቅ የበረከት መንፈሳዊ ጉዞ ወደ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ደብረ ብስሪት አንድነት ገዳም ++

🕯✝️የጉዞ ቀን+++ /03/08/2013

🕯✝️የጉዞ ሁኔታ+++ ደርሶ መልስ

🕯✝️የጉዞ ዋጋ +++350 ምግብንና መስተንግዶን ጨምሮ

🕯✝️አዘጋጅ +++ማህበረ ሥላሴ (ዘከታ)

🕯✝️የመንገድ ሁኔታ+++ የእግር መንገድ የለዉም

🕯✝️መነሻ ቦታ ከታ,አስኮ,ፒያሳ, መገናኛ, አባ ኪሮስ

🕯✝️ተጨማሪ የምንጎበኘዉ ገዳም ደይ ጊዩርጊስ
ወደ ቦታው ሲመጡ ብዙ አስደናቂ ተአምሪትን ይመለከታሉ ለምሣሌ ፃዲቁ አቡነ ተክለሐይማኖትን ለመከተል የተነሱ ዲንጋዩች እንዲሁም ለመሄድ ብለዉ በፃዲቁ ግዝት ያሉ አና ሌሎችም ለጥያቄዋች መሉ መልስ ካሻዎ ከእኛ ጋር አብረዉ ይጓዙ

🕯✝️ከቦታዉ የሚገኙ በረከቶች, ፀበል የፃዲቁ የመቃብር አፈር , የፃዲቁ ፂም ,ዛቤጣ,የአመት ቡኮ ይህንን ሁሉ በማህበሪችን ሲጓዙ ያገኛሉ።

🕯✝️አስተባባሪ እንዳለ ግርማ 0923608584

🕯✝️ተጨማራ ስልኮች0920025513,0922495039

21/03/2021

በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሃድ አምላክ አሜን

+++ማህበራችን ማህበረ ሥላሴ(ዘከታ) እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶሰ አብይ ፆም በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያለ

ታላቅ የበረከት መንፈሳዊ ጉዞ ወደ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ደብረ ብስሪት አንድነት ገዳም ++

🕯✝️የጉዞ ቀን+++ 19/07/2013

🕯✝️የጉዞ ሁኔታ+++ ደርሶ መልስ

🕯✝️የጉዞ ዋጋ +++350 ምግብንና መስተንግዶን ጨምሮ

🕯✝️አዘጋጅ +++ማህበረ ሥላሴ (ዘከታ)

🕯✝️የመንገድ ሁኔታ+++ የእግር መንገድ የለዉም

🕯✝️መነሻ ቦታ ከታ,አስኮ,ፒያሳ, መገናኛ, አባ ኪሮስ

🕯✝️ተጨማሪ የምንጎበኘዉ ገዳም ደይ ጊዩርጊስ

🕯✝️ከቦታዉ የሚገኙ በረከቶች የፃዲቁ የመቃብር አፈር , የፃዲቁ ፂም ,ዛቤጣ,የአመት ቡኮ ይህንን ሁሉ በማህበሪችን ሲጓዙ ያገኛሉ።

🕯✝️አስተባባሪ እንዳለ ግርማ 0923608584

🕯✝️ተጨማራ ስልኮች0920025513,0922495039

26/12/2020
10/09/2020

enkwan adersachu wendem ehetocha addisu amet yesselam yetena yehunelen 2013 weda neseha yemenemelesebet amet yaderegelen amen

Photos from የቅዱሳን ታሪክ's post 08/11/2019

- ጥቅምት 28
አቡነ ይምዓታ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በፎቶው የምታዩት አስደናቂ ፎቶም በትግራይ ውስጥ ከሚገኙት ሺህ ዘመናት ካለፏቸው ጥንታውያን ገዳማት አንዱ የሆነው የአቡነ ይምዓታ ገዳም ነው! እንደሚታወቀው ዘጠኙ ቅዱሳን ሁሉም የነገሥታትና የመኳንንት ልጆች ናቸው፡፡ በራእይም ተገልጦላቸው ወደ ሀገራችንን መጥተው፣ ከሕዝቡ ጋር ዘርና ነገድ፣ ቋንቋና ቀለም ሳይለያቸው በክርስቶስ አንድ ሆነው ለ12 ዓመታትም በፍጹም አንድነት አብረው ከተቀመጡ በኋላ ‹‹እርስ በራሳችን እየተያየን ብንኖር ተድላ ደስታ ይሆንብናልና ተለያይተን እንቀመጥ›› ብለው ተማከረው በተለያየ በዓት አባ ሊቃኖስ በደብረ ቁናጽል፣ አባ ጰንጠሌዎንም በእርሱ ትይዩ በሆነ ቦታ፣ አባ ገሪማ በደብረ መደራ፣ አባ ጽሕማ በደብረ ጸድያ፣ አባ ይምአታ በደብረ ገረዓልታ፣ አባ አፍጼ በደብረ ይሐ፣ አባ አሌፍ በደብረ አኅድአ መኖር ጀመሩ፡፡ አባ አረጋዊ ደግሞ በጣም ርቀው በመሄድ በደብረ ዳሞ በዋሻና በፍርኩታ ውስጥ በተራራም ላይ መኖር ጀመሩ፡፡ አቡነ ይምዓታ ከአክሱም ተነስተው በየመንገዱ ወንጌልን እየሰበኩና ከእመቤታችን ፍቅር የተነሳ "ቅዳሴ ማርያም" እየጸለዩ ሲሄፉ "አብ ጎሕ ወልድ ጎሕ መንፈስ ቅዱስ ጎሕ" እያሉ ሳሉ፤ አሁን ገዳማቸው ከሚገኝበት "ጎሕ" የሚባልበት ቦታ ላይ ደረሱና "ይኩን ስምኪ መካነ ጎሕ" ብለው ሰየሟት! በትሕርምትና በብሕትውናም በገዳማቸው ኖረው ጥቅምት 28 ዕረፍታቸው ሆኗል! የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ የተከናወነላቸው ሲሆን እጅግ አስደናቂው ቤተ መቅደሳቸው ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጭፍ ላይ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ነው፡፡
***
የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስገራሚው ቤተ መቅደሳቸው ትግራይ ገርዓልታ ልዩ ስሙ ‹‹ጎሕ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጭፍ ላይ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ያለበት የተራራው ርዝመት ብቻውን 300 ሜትር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ በጭንቅና በፍርሃት ሆኖ ተራራውን እንደዝንጀሮ በእጅ እየቧጠጡ መውጣት ይጠይቃል፡፡ የአካባቢው ካህናት ደግሞ እግራችሁን እየደገፉና መረገጫ ቦታው ላይ እያሳረፉ ካልሆነ በቀር ለመውጣት የሚከብድ ተአምራዊ ገዳም ነእ፡፡ ለእጅና ለእግር ማሳረፊያ ትንንሽ ቀዳዳዎችን ብቻ በመጠቀም ነው ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ የሚቻለው፡፡ በታላቅ ጭንቅና በፍርሃት ሆነው በአካባቢው ካህናት እየታገዙ እንደምንም ብለው ጫፍ ላይ ከደረሱ በኋላ ቁልቁል መመልከት ከአባ ይምዓታ ጋር የነበረ ጌታ አሁንም እየረዳን እንዳለ ይረዱበታል!
***
ቤተ መቅደሱ እጅግ የሚደንቀው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ ብቻ አይደለም! ውስጡ ያሉት የግድግዳ ላይ ሥዕሎችም በ15ኛው መ/ክ/ዘመን የተሣሉ እጅግ ድንቅና ጥንታዊ ናቸው፡፡ገድለ አቡነ አረጋዊ ስለዚሁ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስደናቂ ቤተ መቅደስ ‹‹በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ ነው የተከናወነው፡፡ ይልቁንም ቁመቱና ርዝመቱ ከታላላቅ ገደል እጅግ በጣም የሚበልጥ የድንጋይ ዓምድ ከወንዝ ማዶ ዘንበል ብሎ መጥቶ ሥጋቸውን በክብር ተቀብሎ በተራራው ጫፍ ላይ እስከዛሬም ድረስ ፈጽሞ ሳይነቃነቅና ሳይናወፅ ቀጥ ብሎ ቆሞ ይገኛል›› በማለት ይገልጸዋል፡፡
እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዘንድሮው በ2012 ወደ አክሱም ጽዮን የምትመጡ ኢትዮጵያውያን ይህንን ታላቁን የአቡነ ይምዓታ ቤተ መቅደስ ሳትሳለሙ እንዳትመለሱ፡፡ የአቡነ ይምዓታና የ9ቱ ቅዱሳን ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡

02/11/2019

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሃድ አምላክ አሜን
ወንድም እህቶቼ ትውልድ እንዳያስተዉል አዚም ያረገበት ማን ነዉ የእናቴ ልጅ እራስህን አዘጋጅ ለመልካም ምግባራት ታትር አባት ልጅህን ጠብቅ እናት የልጆችሽን አካሄዶች እይ ኀላ ጥርስ ማፋጨት እንዳይሆን ዋ የናቴ ልጅ ዘመኑ አለቀ ቢበዛ 80 ቢያንስ 60 አለህ ያንተ የመጠርያ ጊዜህ መች ይሆን ንስሃ ግባ ራስህን ለቅድስ ቁርባን አዘጋጅ ዋዋዋዋዋ የእናቴ ልጅ እኔ ያለኝን ተናገርኩ

02/11/2019

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
👉 “ንእምሮሙ አበዊነ ቅዱሳን ወመካኒሆሙ ይቄዲሶ ለሰብእ - ቅዱሳን አባቶቻችንን እና በቃል ኪዳናቸው ሰውን የሚቀድሱ ክቡራት ቦታቸውን እንወቅ”

👉 በማድረግ መሄድ የሚፈልጉና እግዚአብሔር የፈቀደላቸውን የተዋህዶ ልጆች የበረከቱ ተሳታፊ እናድርግ

★ ከ160 በላይ ገዳማትና አድባራትን የሚሳለሙበት ልዩና የማይቀርበት የ18 ቀናት ታሪካዊ የንግሥ ጉዞ ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት

♡†♡ አክሱም ጽዮን ማርያም ♡†♡

★ የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆች እንኳን አደረሳችሁ። ባለፈው ዓመት ከኅዳር 13 - ታኅሣሥ 3 ድረስ በነበረን የ21 ቀናት የአክሱም ጽዮን ማርያም ታሪካዊ የንግሥ ጉዞ በርካታ የኤርትራ ገዳማትን ጨምሮ ከ170 በላይ ገዳማትና አድባራትን ተሳልመን እና ብዙ ታሪካዊ ቦታዎችን ጎብኝተን በሰላም ተመልሰን ነበር። በዘንድሮው ዓመት ደግሞ ከኅዳር 13 - ታኅሣሥ 2 ድረስ ለ20 ቀናት በሚኖረን የአክሱም ጽዮን ማርያም ልዩና ታሪካዊ የንግሥ ጉዞ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ከ160 በላይ ገዳማትና አድባራትን ተሳልመንና በርካታ ታሪካዊ ቦታዎችን ጎብኝተን እንመለሳለን።
👉

†★† በዚህ ጉዟችን ውስጥ፦

👉 በገመድ የሚወጡ 4 ገዳማትን

👉 በመሠላል የሚወጡ ከ3 በላይ ገዳማትን

👉 ሴቶች ጭምር የሚገቡባቸው በመሰላልና በገመድ የሚወጡ ጥንታዊ የዋሻ ገዳማትን

👉 ከጥፍራችን ወይም ከጸጉራችን በገዳማቸው ቀብረን በከበረው ቃል ኪዳናቸው መልአከ ሞትን የማያሳዩና 12000 ቅዱሳን መላእክት ከገነት አፈር አምጥተው የመሰረቱትን ንዑድ ክቡር መካነ ቅዱሳን

👉 የ፱ቱ ቅዱሳን የሁሉንም ገዳማቸውን

👉 እፁብ ድንቅ ብለው ተደምመው የማይጨርሱት አስደናቂ የሆኑ ታሪካዊና እጅግ በጣም ጥንታዊ ገዳማትን

👉 ከክርስቶስ ልደት በፊት በገቢረ ተአምር የተሳለች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "ምስለ ፍቁር ወልዳ" ስእለ አድኅኖ ያለበት፣ ለ3000 ዓመታት ዕድሜ ባለው ሕንጻ ውስጥ ከ2000 ዓመታት በላይ የቆዩ አፅሞች ሳይፈርሱና ሳይበሰብሱበት እንዲሁም ነጋሪቶችና ደወል ያሉበትና በጅራፍ የሚከፈት በር ያለው አስደናቂ ገዳምን

👉 ማታ ማታ ፍልፍል ቤተ መቅደሱ ግድግዳው የሚያበራበት ጥንታዊ ገዳምን

👉 የእንስሳት ተዋጽዖ የበላ ከሳምንት በፊት ገዳማቸውን መርገጥ የማይችልበት አስገራሚ ገዳማችንን

👉 በቃልኪዳኑ ከክፉ አደጋ፣ ከመርዘኛ ተናዳፊ እንስሳት፣ ከበራሪ ጥይትና ከዘራፊ ወንበዴ የሚጠብቅ የቆዳ እምነት የሚሰጥበት ደብረ ዓባይ ዋልድባ ገዳምን

👉 መድኃኔዓለም ክርስቶስ በኪደተ እግሩ የባረከውንና ተራራውን በበትሩ ሸንቁሮ የመጀመሪያውን ተአምር በዋልድባ ለሰወራቸው ቅዱሳን ያሳየበትን ሰቋር ዋልድባን

👉 በታላቁ ዋልድባ ገዳም ውስጥ የእናቶች መነኮሳይያት ጸሎተ በዓት መገኛ የሆነውን ዳልሻህ ዋልድባን

👉 ከኢትዮጵያዊው ጻድቅ ከአ/ተ/ሃይማኖት ቀጥለው የተነሱና የ፯ቱ ከዋክብት አበው መምህር የሆኑት አንበሳን እንደ አህያ 7 ዓመት የገዙት የወላዴ እላፍ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደብረ በንኮልን

👉 በቃለ ግዝታቸው ጽንስ በማኅፀን 22 ዓመት ያቆዩ በእምነት ያልመጣውን ጸበላቸው ገፍትሮ የሚያስወጣ በስዕለት ለብዙዎች አማልደው ልጅ የሚያሰጡ የታላቁ ጻድቅ የአቡነ አላኒቆስን ማይበራዝዮ ገዳምን

👉 የዓሣ ነባሪ ቅርጽ ያለውና የሙታን አጽም ከ1 ዓመት በኋላ የሚሰወርበትን ድንቅ ገዳምን

👉 ሰማእታት በኣላዊያን ነገሥታት በግፍ ተሰይፈው ስለክርስትናቸው ሰማእትነት በተቀበሉጊዜ በወንዝ ላይ እንደ ጎርፍ የፈሰሰው ደማቸው እስከ ዕለተ ምጽዓት ለሕዝብ ሁሉ ምስክር ሆኖ የሚታይበትን ገዳም

👉 በ4ኛው መ.ክ.ዘ. የተመሰረቱና ከ1600 ዓመታት በላይ የቆዩ ጥንታዊና የቅዱሳን መካናተ ጸሎታት

👉 አምላከ ቅዱሳን በማይጠፋ ቃል ኪዳኑ ያከበራቸው፣ በረከት የሚታፈስባቸውና ዲውያንን የሚፈውስ ተአምረኛ እምነትና ጠበል ያላቸው በርካታ ገዳማትን

👉 በአስደናቂ ኪነሕንፃ የታነፁና እጅግ በጣም ታሪካዊ የሆኑ ጥንታዊያን ገዳማትን

👉 እንዲሁም በርካታ ታሪካዊ ቦታዎች ተካተውበታል።

†★† መነሻ ኅዳር 13 ከሌሊቱ 11፡00 መመለሻ ታኅሣሥ 2
★ የጉዞ ዋጋ የአደር መርከብ ትራንስፖርትና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 2700 ብር
አዘጋጅ፦ ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

★ ቁልቢ ቅ/ገብርኤል እና ቅ/ላሊበላ ምዝገባ ጀመረናል
★👉 ትኬቱን በአቅራቢዎ ያገኛሉ፡፡ 👈★

21/09/2019

+☦️+
ብትወስደን ፡ ምናለ!!!
+☦️+
🍀
ወይ ሰው!!!
በፈጣሪው አምሳል በክብር ተፈጠረ
ነጻነት በማለት ትእዛዛቱን ሻረ
ጸጋውን ጣለና ራሱን "አከበረ"
ሥጋው እያሞቀ ነፍሱን አሳረረ
በራልኝ እያለ ቤቱን አቃጣለ
በሥጋው "ለማትረፍ" በነፍሱ ከሰረ
ለኃጢአት ተፈቶ ለጽድቅ ታሰረ
ከበረቱ ወጥቶ ሜዳ ላይ አደረ
🍀
ጌታ ፡ ሆይ!!!
ታሪክ የዘገበው ትናንት የነበረ
ኃጢአቱ ክህደቱ ዛሬም ከቀጠለ
እጅግ እየከፋም ሰው ከኮበለለ
ስለ እኛ መሞትህ ታድያ ወዴት አለ?
እናምናለን ቃልህን እንዳልተቀየረ
ልብህ እንደሚኖር እኛን እንዳፈቀረ
🍀
ነገር ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ!!!
ሰው ባልገባው መጠን ቤትህን ደፈረ
በልቡ እንዳታድር አንተን አባረረ
ሰው የሰይጣን ሆነ ያንተ መሆን ቀረ
ክፋትን ያደርጋል ቀን እየቆጠረ
አስፈጻሚ ሆኖ በሰይጣን ተቀጠረ
በራሱ እንዳይበቃ ሌሎችን አስከተለ
ሞቱን እንዲሞቱ ኵፉኛ አቆሰለ
🍀
ከትናንት ተነስተን ዛሬ ይህ መሰለ
የክህደት እድገቱ እንዲህ ከቀጠለ
የሰው ሕይወት ወርዶ ካሽቆለቆለ
በማያውቀው ነገ እየተታለለ
የሞተለትን ጌታ ዳግም ከገደለ
የኖረባትን ቤት በእሳት ካቃጠለ
እናቱን በድፍረት ጮሆ ካቃለለ
ከዚህ በላይ መሞት ከቶ ወዴት አለ?
🍀
ተጠንቀቁ ያልከው ለካ ይህ ነበረ
ሰው በቆይታው ልክ በደል ከጨመረ
ቍጥር ብቻ እያየ ዕድሜው ካሳጠረ
ኃጢአት ጫፍ ደረሰ ምን አለ የቀረ?
🍀
በአንጻሩ ፡ ደግሞ!!!
ቃልህ የጠበቀ ጸንቶ የተጋደለ
ጠቢብ ለሕይወቱ ጸጋ የታደለ
ባንተ ሕያው ሊሆን በዓለም ተገደለ
ስለ ስምህ ሞተና በሰማይ ከበረ
🍀
እባክህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ!!!
ለደቂቃም ፡ ቢሆን
ልባችን በፍርሃት አንተን አምኖ ሳለ
አፋችን በጸሎት አባት ሆይ እያለ
ቃልኪዳኗን አምኖ ድንግል ሆይ እያለ
ሥጋህና ደምህ ተቀብለን ሳለ
ብትወስደን ምናለ?

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa