14/09/2024
ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!
| የልማት ተነሺ ተብሎ ሰዎች ድንገት ቤታቸው ሲፈርስ ስለገጠማቸው ጉዳት ብዙ የሚያሳዝኑ ታሪኮች ሲነገሩ ሰምቻለሁ። ነገሩ ቢያሳዝነኝም፣ የስሚ ስሚ አይቼ ሳልመረምር አስተያየት ብሰጥ ሚዛናዊ አልሆን ይሆናል፣ እሳሳት ይሆናል በሚል ከማዘን በስተቀር ምንም አላልኩም ነበር፣ አሁን ግን ለልማት ድንገት መፍረስ የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት።
የማወራው ስለአንድ ሰው ታሪክ ነው፣ ተቆጥሮ ህዝብ ስለሚባለው፣ ሀገር በማቅናት ውስጥ ማህበረሰብ በመስራት ውስጥ አስተዋጽኦ ስላለው አንድ ሰው ነው።
የህይወት ታሪኩ እንዲህ ነው ...
ገና ጎረምሳ እያለ ከተወለደበት ገጠር ወጥቶ 250 ኪሎሜትር በእግሩ ተጉዞ አዲስ አበባ ገባ። አዲስ አበባ የግለሰቦች ንግድ ቤት ተቀጥሮ ከጽዳት አንስቶ የተለያዩ ስራዎችን ሰርቶ ከራሱ አልፎ ወላጆቹን ቤተሰቡን ረድቶ፣ ትዳር መስርቶ፣ ልጆች አፍርቶ፣ የግል ንግድ ከፍቶ ሲኖር ቆይቶ የዛሬ 60 ዓመት አካባቢ ከፈረንሳይ ኢምባሲ ወረድ ብሎ ከሃይዌዩ ድልድይ ስር የግንብ ግድግዳ ላይ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” የሚለው ጽሁፍ በደማቁ በቀይ ቀለም ከተጻፈበት ፊትለፊት ወደ ቤላ በሚወስደው ቀኝ መታጠፊያ መንገድ ላይ መሬት ገዝቶ ቆንጆ ቤት ሰርቶ ኑሮውን መሰረተ።
12 ልጆችን አሳድጎ፣ አስተምሮ ለወግ ለመዓረግ አበቃ፣ የልጅ ልጅ አየ። አሁን የ 94 ዓመት አዛውንት ነው። ጠንካራ፣ ደግ፣ ሰራተኛ፣ ተጫዋች፣ ቀልድ አዋቂ፣ ሰው ሁሉ የሚወደው፣ ሰውን ሁሉ የሚወድ፣ ሃይማኖቱን አክባሪ እምነቱን አጥባቂ ነው። የግቢ አትክልት ይወዳል፣ ግቢው በወይን፣ በአቩካዶ፣ በኮክ፣ በአፕል፣ በቡና ዛፍ የተሞላ የሚያምር ግቢ ነው። የአትክልት ፍቅሩ ለራሱ ቤት ብቻም አይደለም፤ ሰፈር ውስጥ እየዞረ በሰው ቤት በዘመድ ቤትም ችግኝ ከቤቱ እየወሰደ ይተክላል።
ይህ ጠንካራ ሰው በቅርቡ በህመም አልጋ ላይ ዋለ ፥ “በቂ ኖሬያለሁ ሆስፒታል እንዳትወስዱኝ በኖርኩበት ባረጀሁበት ቤት አስከሬኔ ይውጣ” አለ። ልጆቹ ቃሉን አከበሩለት ቤቱ ውስጥ እንዳለ ሀኪም እያየው በልጆቹ፣ በልጅ ልጆቹ በቤተዘመድ በጎረቤት ተከቦ እንዲያስታመሙት አደረጉ። ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የ አዲስ ዓመት ዋዜማ በሰፈሩ አንድ ዜና ተሰማ፣ ከወረዳ የመጡ ሰዎች እየዞሩ ለልማት እየመዘገቡ ነው የሚል።
የአዲስ ዓመት በዓል ማግስት መስከረም 2 መጥተው በ20 ቀን ውስጥ ቤታችሁ ለልማት ሊፈርስ ስለሆነ ለመስከረም 3 ጠዋት ለስበሰባ ኑ የሚል መልእክት በቃል ብቻ ተነገረ። እንዲህ ያለ ዱብ እዳ ሲሰማ ለህግ ጉዳይ መዋሉ ቢቀር እንኳን ህልም ይሆን እንዴ ብሎ ድጋሚ አይቶ ለማረጋገጥ የሚያስችል ብጣቂ ወረቀት አልተሰጠም፣ ልክ እንደ ክፉ መርዶ ነጋሪ በር አንኳኩተው በቃል ትዕዛዝ ሰጥተው ሄዱ።
መስከረም 3 በስብሰባው ላይ ስልክም ሆነ ማንኛውም ድምጽ እና ምስል መቅጃ ይዞ መግባት ባልተፈቀደበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢዎቹ ቤታችሁ ለልማት ይፈርሳል የሚለው መርዶ ተነገራቸው።
ለምን?
ለጫካ ፕሮጀክት ልማት።
መቼ?
እስከ መስከረም 20።
ተሰብሳቢው ደነገጠ “ልጆቻችንን ትምህርት ቤት አስመዝገበናል፣ ዩኒፎርም አሰፍተናል፣ የደከመ ታማሚ ቤታችን ስላለ ጊዜው አይበቃንም፣ የእለት ጉርሴ ከቤት ኪራይ የማገኘው ብቻ ነው፣ ምን ልሁን? የሚሉ አዛውንቶች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ጮኸው አልቅሰው ተናገሩ። ሁለት ሳምንት አላችሁ ተባሉ።
ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል??
በየቤቱ ያለ እቅድ ፥ ያለ ኑሮ... ለቅሶ፣ ጽኑ ታማሚ፣ ሰርግ፣ አራስ፣ የደረሰች ነፍሰጡር....ቤቱ ይቁጠረው ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃ
06/12/2020
የትምህርት ፈረቃ እንደሚከተለው ነው።
በትምህርት ቤቱ
1ኛ• 12 የአስረኛ ክፍል ሴክሽኖች
2ኛ• 17 የአስራ አንደኛ ክፍል ሴክሽኖች (ስምንቱ ከ11/1 እስከ 11/8 ተፈጥሮ፣ ዘጠኙ ከ1/9 እስከ 11/17 ከማህበራዊ ሳይንስ) ናቸው።
3ኛ• 42 የአስራ ሁለተኛ ሴክሽኖች (ሐያ ሁለቱ ከ12/1 እስከ 12/22 ተፈጥሮ ሳይንስ ሲሆን ከ2/23 እስከ 12/42 ድረስ ደግሞ ማህበራዊ ሳይንስ) ናቸው።
በአጠቃላይ በትምህርት ቤቱ ሰማንያ (81) ሴክሽኖች (ከዘጠነኛ ክፍሎች ውጭ) አሉ።
ፈረቃ 1 (ሰኞ፣ ረዕቡና አርብ)
👉10ኛ ክፍል ከሴክሽን 1 እስከ 6
👉11ኛ ከሴክሽን 1 እስከ 4 (ተፈጥሮ ሳይንስ)
👉11ኛ ከሴክሽን 9 እስከ 13 (ማህበራዊ ሳይንስ)
👉12ኛ ከሴክሽን 1 እስከ 11 (ተፈጥሮ ሳይንስ)
👉 12ኛ ከሴክሽን 23 እስከ 32 (ማህበራዊ ሳይንስ) ሲሆኑ
ፈረቃ 2 (ማክሰኞ፣ ሐሙስ ቅዳሜ)
10ኛ ክፍል ከሴክሽን 7 እስከ 12
👉11ኛ ከሴክሽን 5 እስከ 8 (ተፈጥሮ ሳይንስ)
👉11ኛ ከሴክሽን 14 እስከ 17 (ማህበራዊ ሳይንስ)
👉12ኛ ከሴክሽን 12 እስከ 22 (ተፈጥሮ ሳይንስ)
👉 12ኛ ከሴክሽን 33 እስከ 42 (ማህበራዊ ሳይንስ) ይሆናል ማለት ነው።
24/11/2020
አዲስ የኮቪድ 19 መከላከልና ለተጨማሪ ውሃ አቅርቦት የተሰራው 20 የወሃ ጡት ቧንቧ ስራ ተጠናቀቀ። በቀጣይም በትምህርት ቤቱ በተለያዩ ቦታዎች ተጨማሪ የውሃ ጡት በመስራት መንግሥት ባስቀመጠው መስፈርት "አንድ የወሃ ጡት ለሃያ ተማሪ" መሰረት ተደራሽ እናደርጋለን ።
09/11/2020
This is Mrs kelemework Tiruneh secondary school official telegram address. if you want to get update and current different school's notice, exam, notes, reports, models etc please join and invite to your friend. Thank you.
Join group chat on Telegram
24/10/2020
ምናልባት የትምህርት ቤቱ ተማሪ፣ መምህር፣ ሠራተኛ ወይም አገልግሎት ፈላጊ ሆነው መጥተው፣ ወይም ወደፊት ሊመጡ ይችላሉ። ይህ ከታች የቀረበው የትምህርት ቤቱ የወይዘሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ወቅታዊና ትክክለኛ በትምህርት ቤቱ አመራሮች የሚተዳደር የማህበራዊ ድህረ ገፅ አድራሻዎች ናቸው። ተረዳድተንና ተደጋግፈን መሥራት እንድንችል እነዚህ ከታች የተዘረዘሩትን የመገናኛ ዘዴዎች ላይክና ጆይን በማድረግ አባል መሆን ቤተሰብ ይሁኑ፣ ለጓደኞቻችሁም ያጋሩ።
ቴሌግራም (private channel)
https://t.me/joinchat/AAAAAET-F0EQk-ELvuDKaQ
Or search woyzero Kelemework Tiruneh secondary school 2013
ፌስቡክ
Woyzero kelemework tiruneh secondary school 2013
Email
W/[email protected]
Join group chat on Telegram
14/06/2020
የኮሮና ስርጭት ከክልሎች አንፃር ምን ይመስላል!
ስርጭቱ በዚህ ከቀጠለ እንደ ሐገር በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ፣ ማን ይተርፋል? መንግስት ምን ማድረግ አለበት?
ካነበባችሁ በሗላ ሐሳብ ስጡበት ።
አዲስ አበባ፣
በኦሮሚያ አማራ ትግራይ ደቡብ ድሬዳዋና ሀረሪ እንዲሁም አፋር ያሉት ወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 215 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 15 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
- 3 ሰዎች ከጉጂ (የ1 ዓመት ህፃን ሴት፣ የ42 ዓመትና የ54 ዓመት ወንድ) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው።
- 2 ሰዎች ከሰበታ (የ47 ዓመት ወንድና የ32 ዓመት ሴት) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ ወንዱ ከማህበረሰቡ የተገኘ ሴቷ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላት።
- 7 ሰዎች ከቡራዩ (የዕድሜ ክልላቸው ከ21-37 ውስጥ ይገኛል) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ 3 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው፣ የተቀሩት ከማህበረሰቡ የተገኙ።
- 2 ሰዎች ከለገጣፎ (የ14 ዓመት ወንድና የ21 ዓመት ሴር )፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።
- 1 ሰው ከሱሉልታ (የ40 ዓመት ወንድ)፤
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው ምርመራ 524 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 23 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
20 ሰዎች በምዕ/ጎንደር ዞን በሚገኙ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው) ናቸው።
2 ሰዎች በጎንደር ከተማ በሚገኘው ማራኪ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል የነበሩ እንዲሁም 1 ሰው በሰ/ወሎ ዞን በሚገኘው ላልይበላ ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበረ።
በፆታ አኳያ 21 ወንድና 2 ሴት ናቸው ፤ የእድሜ ክልላቸው ከ16 እስከ 22 ዓመት ውስጥ ይገኛል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 219 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።
ከዘጠኙ መካከል 6 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 3 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።
በደቡብ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 44 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 426 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
ታማሚ 1 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ የካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።
ታማሚ 2 - የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ የካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ያለው የረዥም ርቀት አሽከርካሪ ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው ነው።
በአፋር ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 47 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 147 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።
በድሬዳዋ ከተማ አስተደር 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጧል። በቫይረሱ የተያዙት የ33 እና የ23 ዓመት ወጣቶች ናቸው። ሁለቱም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉና አንደኛው ግለሰብ ቀደም ሲል በቫይረሱ ተይዞ በህክምና ማዕከል ውስጥ ካለ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጅቡቲ ተመላሽ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓት በሐረሪ ክልል 53 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው። በቫይረሱ የተያዘው የ4 ወር ህፃን ወንድ ሲሆን የድሬ ጠያራ ወረዳ ነዋሪ ነው።
14/06/2020
ግብፅ ሆይ እኛ ኢትዬጵያዊያን አንድ እንቁላል ስምንት ብር የምንገዛ፣ ስጋ ፍርፍር አዝዘን እንጀራ ፍርፍር የምንበላ፣ ስልካችን 100% ፉል እስኪሆን ቻርጅ ለማድረግ 3 ቀን የሚፈጅብን፣ የገዛነው የኢንተርኔት ሜጋ ባይት ሳንጠቀም በደቂቃዎች የሚያልቅብን፣ የትራንስፖርት ታሪፍና ፍሰት ያጨናነቀን፣ ከኢትዬጵያዊነት ይልቅ ጎጠኝነት ገኖ ያስቸገረን ህዝቦች፣ ከሰዋዊነት ወርደን አጥንት ቆጠራ ያስቸገረን፣ የህዳሴ ግድብ አልቆ የኢትዬጵያ ሁለት ዲጂት እድገት የናፈቀን ህዝቦች፣ በአጭሩ የመረረን ሰዎች እንደሆንን እወቂ!!! ያለዛ
ግን እኛ በምንለው የማትስማሚ ከሆነ በኩርኩም ብቻ አናትሽን ብለን ወደ እስያ እንደምቀላቅልሽ እወቂ! !!!
ሰምተሻል!!!!
02/06/2020
ቀን 25 / 09 / 2012 ዓ.ም
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,932 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,344 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። የመጀመርያው የ30 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን ሁለተኛዋ የ56 ዓመት በአዲስ አበባ የተጓዳኝ ህመም ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው።በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ አራት (14) ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ አራት ሰዎች (ስድስት ከኦሮሚያ ክልል እና ስምንት ከሶማሊ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 231 ነው