23/11/2015
በረራው ሴቶች ሁሉን ማድረግ እንደሚችሉ ያሳየንበት ነው :-ሴት አብራሪዎች
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙሉ በሙሉ በሴቶች መሪነት ወደ ባንኮክ ያደረገው በረራ ብቃታቸውን ለዓለም ህዝብ ያስመሰከሩበት ታሪካዊ አጋጣሚ መፍጠሩን የበረራው መሪዎች ገለጹ።
በአየር መንገዱ ታሪክ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተካሄደው የታይላንድ ባንኮክ ደርሶ መልሰ በረራ በሰላም ተጠናቋል።
በረራውን በዋና አብራሪነት የመሩት ካፒቴን አምሳለ ጓሉ እና ረዳት አብራሪ ሰላም ተስፋዬ ሴቶች ጠንክረው ከሰሩ ስኬታማ መሁን እንደሚችሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰው ሃይል አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ አዚዛ መሀመድ አየር መንገዱ በተለያዩ የአመራር ደረጃዎች ሴቶችን ለማብቃትና ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ የሚያስችል አሰራር እየተገበረ መሆኑን ገልፀዋል።
በታሪካዊው በረራ የተሳተፉት ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ሀገራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ስኬታማ ሴቶችን ማፍራት ችላለች እነዚህን ተምሳሌቶች ይዘን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይገባናል ብለዋል።
ለስኬቱ የማህበረሰቡ ድርሻ ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ20 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን 33 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው።
ምንጭ፡ ኢብኮ/ህዳር 12፣2008/