ወሀቢያ - እውነታና አሉባልታ

ወሀቢያ - እውነታና አሉባልታ

Share

نسف دعاوى المناوئين لدعوة الشيخ محمد بن عبد الوهاب باللغة الأمهرية الإثيوبية http://www.saaid.net/monawein/index.htm

24/09/2023

የመውሊድ በዓል በሚዛን ላይ
""""""""""""""""""""""""
ነሲሓ መጽሔት ቅጽ Vol2 ቁጥር 1

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው ፡፡ ሰላት እና ሰላም ለዐለማት እዝነት በተላኩት በነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በሰሃባዎቻቸው እና እነርሱን በመልካም በተከተሉት ሁሉ ላይ እስከ እለተ ቂያማ (ትንሳኤ) ድረስ ይውረድ፡፡
ቁርዓን እና ሐዲስን እንዲሁም ዝርዝር የሸሪዓ ህግጋትን በትክክል መረዳት ለሁሉም ሙስሊም በእጅጉ አስፈላጊ ቢሆንም ቀላል ግን አይደለም።
አላህ ለዚህ ኡማ ታላቅ ውለታ በመዋል ኡለማዎችን ሰጥቶን ያላቸውን ታላቅ ክብር ገልፆልናል፡፡ የሙስሊሞችን እምነት፣ የአምልኮ ‘ዒባዳ’ አተገባበር እና የስነምግባር እሴቶችን ማረም የዑለሞች ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ከሰሀቦችና እነሱን ከተከተሉ ታቢዒዮች መካከል ታላለቅ ዑለማዎች እና የፊቅህ ጠበብቶች ቁርዓንን በተገቢው መልኩ በመረዳት እና ዕድሜያቸውን ሙሉ በማስተማር ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል። ሰሃባዎች ከማንም በበለጠ በዕውቀት የበለፀጉ ከመሆናቸው ባሻገር የመልእክተኛውን ﷺ ንግግር እና ሱና በመተግበር ፋና ወጊዎች እንደነበሩ አያጠያይቅም።
አብደላህ ኢብን መስዑድ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና በአንድ ወቅት ስለሰሃባዎች እንዲህ ብለው ነበር፤ "ከዚህ ከነቢዩ ዑመት ከማንም በበለጠ፤ ቅን ልቦና፣ የጠለቀ እውቀት፣ የተቃና ፈለግ እና ያማረ ስብዕና ባለቤት ነበሩ። እነሱ ማለት አላህ ለነብዩ ጓደኝነት የመረጣቸው ህዝቦች ናቸው፡፡ ክብራቸውን እወቁላቸው። ፋናቸውንም ተከተሉ። እነሱ ቀጥተኛው መንገድ ላይ ነበሩ።" ኢብኑ ዐብደል በር / ጃሚዑል በያኒል ዒልም በሚባለው ኪታባቸው ቅጽ 2/946-947 ሰሃባዎች በሐቅ ላይ አንድነታቸውን ለመጠበቅ የተለያዩ ሸሪዓዊ አጀንዳዎች ላይ ይመካከሩና ይተራረሙ ነበር፡፡ ያልደረሳቸውን መረጃ ሲያገኙም ወደ ሐቅ ከመመለስ የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም። ለሐቅ ተገዢ ስለነበሩ እርምት ለሰጣቸው አካል ምስጋና እና ክብራቸው ከመጨመሩ ባሻገር በመካከላቸው የነበረው ወዳጅነት አልጎዳም። ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ብለዋል "ሰሃባዎች፣ ታቢዒዮች እና ከእነርሱ በኋላ የመጡት ዑለማዎች በመካከላቸው አለመግባባት በተፈጠረ ጊዜ የአላህን ትዕዛዝ ይከተሉ ነበር፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል «በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትሆኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡» ሱረቱ ኒሳዕ : 59 በተለያዩ የዲን አጀንዳዎች ላይ በምክክር መልክ ይወያያሉ፡፡ አልፎ አልፎ የዒልምና እና የተግባር ጉዳዮች ላይ የአቋም ልዩነት ሲኖር መዋደድን፣ መተሳሰርን እና ኢስላማዊ ወንድማማችነትን በጠበቀ ሁኔታ ይተራረማሉ።" መጅሙዑል ፈታዋ 24/172

በየዓመቱ የረቢዐል አወል ወር በገባ ቁጥር የነቢያችንን የልደት በዓል መውሊድን የማክበር ጉዳይ ሰዎችን ሲያወዛግብና መነጋገሪያ ሲሆን ይታያል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ሙእሚኖችን በመሰረታዊም ይሁን በቅርንጫፋዊ የዲን ጉዳዮች ላይ አለመግባባት ቢፈጠሩ ጉዳያቸውን ወደ ቁርዓንና ሐዲስ በመመለስ መፍትሄ እንዲፈልጉ በሚከተለው የቁርዓን አንቀጽ አዟል፡፡

فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا ٤:٥٩

«በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው» ሱረቱ ኒሳዕ : 59

ከዚህ ቁርአናዊ መመሪያ በመነሳት ለአንባቢዎቻችን ነሲሓ ይሆን ዘንድ ትክክለኛውን አቋም እናመላክታለን። አላህ ሀቁን አይተው ከሚከተሉት ሰዎች ያድርገን። ይህ በዓል በሸሪዓ መሰረት የሌለውና ሰዎች በዲን ውስጥ የጨመሩት አዲስ ነገር ከመሆኑ ባሻገር አላህና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ተግባር በቀን የተገደበ ወደ አላህ መቃረቢያ አምልኮ ማድረግ መሆኑ ዋነኞቹ የመውሊድ ችግሮች ሲሆኑ፤ በተጨማሪም ክርስቲያኖችን በመፎካከር የመጣ መሆኑ ከእነሱ ጋር መመሳሰል ነው። በተጨማሪ በዚህ በዓል ውስጥ በሸሪዓ የተወገዙ በርካታ ተግባራት ይፈፀማሉ። መውሊድ አንድን ስራ ቢድዓ የሚያሰኙ ምክንያቶች ሁሉ እንዳሉበት አያጠራጥርም። ይህም በሚከተሉት ሶስት ነጥቦች ይብራራል፤
1) አዲስ ነገር መፍጠር (ኢሕዳስ)
ካለ ሸሪዓዊ ማስረጃ፤ ማንኛውንም ቀን ወይም ወር ልዩ ሀይማኖታዊ ክንውን የሚፈፀምበት እንደሆነ በማሰብ በዋጂብነት ወይም ሱናነት ሰዎችን የምናበረታታበት ከሆነ በዲን ውስጥ አዲስ ነገር መፍጠር ነውና ሀራም ነው።

አሏህ እንዲህ ብሏል:-
أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ
«ከሀይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?» ሱረቱ ሹራ ቁጥር 21

ቡኻሪ እና ሙስሊም በዘገቡት የተረጋገጠ ሰሂህ ሐዲስ ነቢያችን ﷺ ብለዋል፤

مَنْ أحْدَثَ في أمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ

«በዲናችን ውስጥ ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ ስራው ተመላሽ ይደረግበታል» ብለዋል።

ይህ ማለት በሸሪዓ ያልተደነገገን ነገር ፈጥሮ ቢፈፅም ተቀባይነት አያገኝም ማለት ነው።

እንደሚታወቀው፤ መውሊድን ረሱል ﷺ የተከበሩት ኸሊፋዎች እና ሌሎችም ሰሀባዎች አላከበሩትም። እንደዚሁ በተከበረው ዘመን ውስጥ የኖሩት ሰሀባዎችን በመልካም ሲከተሉ የነበሩ ታቢዒዮች አልሰሩትም። እነሱ ደግሞ ከማንም በላይ የሱና አዋቂዎችና ለነቢያችን የነበራቸው ውዴታም ከማንም በላይ እንደነበር እሙን ነው። የነብዩን ፈለግ በሚገባ በመከተልም የማይታሙ እንደ ነበሩ ለማንም ግልፅ ነው። ለኛ አርአያ መሆናቸውም ተነግሮናል። ምንም ሳንጨምር መንገዳቸውን አጥብቀን እንድንይዝ የአላህ መልዕክተኛ አደራ ብለውናል፤

عَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ الْمَهْدِيِّينَ، وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الْأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ، وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ
«የእኔን እና የቅን ምትኮቼን ሱና አደራ! በጥርሶችችሁ አጥብቃችሁ ያዙ! አዳዲስ ፈጠራዎችን ተጠንቀቁ (ተከልከሉ)፣ በዲን ውስጥ የተጨመረ ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው» ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል

መውሊድ በቀደምቶቹ ዘመን እንዳልነበረ እና ኃላ የተፈጠረ (ሙህደስ) ለመሆኑ መውሊድ አክባሪዎች ሁሉ የማይክዱት እውነታ ነው። መውሊድ ማክበርን ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩት ከአራተኛው
ክ/ዘመን በኋላ እራሳቸውን ፋጢሚዮች ብለው ይጠሩ የነበሩት ኡበይዲዩች ግብፅን በ362 ዓመተ ሂጅራ የወራሩ ጊዜ ነበር።

ቀጣዩን ያንብቡ👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1336321059824881&id=1003047829818874

የመውሊድ በዓል በሚዛን ላይ
""""""""""""""""""""""""""
ነሲሓ መጽሔት ቅጽ Vol2 ቁጥር 1

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው ፡፡ ሰላት እና ሰላም ለዐለማት እዝነት በተላኩት በነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በሰሃባዎቻቸው እና እነርሱን በመልካም በተከተሉት ሁሉ ላይ እስከ እለተ ቂያማ (ትንሳኤ) ድረስ ይውረድ፡፡
ቁርዓን እና ሐዲስን እንዲሁም ዝርዝር የሸሪዓ ህግጋትን በትክክል መረዳት ለሁሉም ሙስሊም በእጅጉ አስፈላጊ ቢሆንም ቀላል ግን አይደለም።

አላህ ለዚህ ኡማ ታላቅ ውለታ በመዋል ኡለማዎችን ሰጥቶን ያላቸውን ታላቅ ክብር ገልፆልናል፡፡ የሙስሊሞችን እምነት፣ የአምልኮ ‘ዒባዳ’ አተገባበር እና የስነምግባር እሴቶችን ማረም የዑለሞች ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ከሰሀቦችና እነሱን ከተከተሉ ታቢዒዮች መካከል ታላለቅ ዑለማዎች እና የፊቅህ ጠበብቶች ቁርዓንን በተገቢው መልኩ በመረዳት እና ዕድሜያቸውን ሙሉ በማስተማር ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል። ሰሃባዎች ከማንም በበለጠ በዕውቀት የበለፀጉ ከመሆናቸው ባሻገር የመልእክተኛውን ﷺ ንግግር እና ሱና በመተግበር ፋና ወጊዎች እንደነበሩ አያጠያይቅም።

አብደላህ ኢብን መስዑድ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና በአንድ ወቅት ስለሰሃባዎች እንዲህ ብለው ነበር፤ "ከዚህ ከነቢዩ ዑመት ከማንም በበለጠ፤ ቅን ልቦና፣ የጠለቀ እውቀት፣ የተቃና ፈለግ እና ያማረ ስብዕና ባለቤት ነበሩ። እነሱ ማለት አላህ ለነብዩ ጓደኝነት የመረጣቸው ህዝቦች ናቸው፡፡ ክብራቸውን እወቁላቸው። ፋናቸውንም ተከተሉ። እነሱ ቀጥተኛው መንገድ ላይ ነበሩ።" ኢብኑ ዐብደል በር / ጃሚዑል በያኒል ዒልም በሚባለው ኪታባቸው ቅጽ 2/946-947

ሰሃባዎች በሐቅ ላይ አንድነታቸውን ለመጠበቅ የተለያዩ ሸሪዓዊ አጀንዳዎች ላይ ይመካከሩና ይተራረሙ ነበር፡፡ ያልደረሳቸውን መረጃ ሲያገኙም ወደ ሐቅ ከመመለስ የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም። ለሐቅ ተገዢ ስለነበሩ እርምት ለሰጣቸው አካል ምስጋና እና ክብራቸው ከመጨመሩ ባሻገር በመካከላቸው የነበረው ወዳጅነት አልጎዳም። ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ብለዋል "ሰሃባዎች፣ ታቢዒዮች እና ከእነርሱ በኋላ የመጡት ዑለማዎች በመካከላቸው አለመግባባት በተፈጠረ ጊዜ የአላህን ትዕዛዝ ይከተሉ ነበር፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል «በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትሆኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡» ሱረቱ ኒሳዕ : 59

በተለያዩ የዲን አጀንዳዎች ላይ በምክክር መልክ ይወያያሉ፡፡ አልፎ አልፎ የዒልምና እና የተግባር ጉዳዮች ላይ የአቋም ልዩነት ሲኖር መዋደድን፣ መተሳሰርን እና ኢስላማዊ ወንድማማችነትን በጠበቀ ሁኔታ ይተራረማሉ።" መጅሙዑል ፈታዋ 24/172

በየዓመቱ የረቢዐል አወል ወር በገባ ቁጥር የነቢያችንን የልደት በዓል መውሊድን የማክበር ጉዳይ ሰዎችን ሲያወዛግብና መነጋገሪያ ሲሆን ይታያል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ሙእሚኖችን በመሰረታዊም ይሁን በቅርንጫፋዊ የዲን ጉዳዮች ላይ አለመግባባት ቢፈጠሩ ጉዳያቸውን ወደ ቁርዓንና ሐዲስ በመመለስ መፍትሄ እንዲፈልጉ በሚከተለው የቁርዓን አንቀጽ አዟል፡፡

فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا ٤:٥٩

«በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው» ሱረቱ ኒሳዕ : 59

ከዚህ ቁርአናዊ መመሪያ በመነሳት ለአንባቢዎቻችን ነሲሓ ይሆን ዘንድ ትክክለኛውን አቋም እናመላክታለን። አላህ ሀቁን አይተው ከሚከተሉት ሰዎች ያድርገን።
ይህ በዓል በሸሪዓ መሰረት የሌለውና ሰዎች በዲን ውስጥ የጨመሩት አዲስ ነገር ከመሆኑ ባሻገር አላህና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ተግባር በቀን የተገደበ ወደ አላህ መቃረቢያ አምልኮ ማድረግ መሆኑ ዋነኞቹ የመውሊድ ችግሮች ሲሆኑ፤ በተጨማሪም ክርስቲያኖችን በመፎካከር የመጣ መሆኑ ከእነሱ ጋር መመሳሰል ነው። በተጨማሪ በዚህ በዓል ውስጥ በሸሪዓ የተወገዙ በርካታ ተግባራት ይፈፀማሉ። መውሊድ አንድን ስራ ቢድዓ የሚያሰኙ ምክንያቶች ሁሉ እንዳሉበት አያጠራጥርም። ይህም በሚከተሉት ሶስት ነጥቦች ይብራራል፤

1) አዲስ ነገር መፍጠር (ኢሕዳስ)፦
ካለ ሸሪዓዊ ማስረጃ፤ ማንኛውንም ቀን ወይም ወር ልዩ ሀይማኖታዊ ክንውን የሚፈፀምበት እንደሆነ በማሰብ በዋጂብነት ወይም ሱናነት ሰዎችን የምናበረታታበት ከሆነ በዲን ውስጥ አዲስ ነገር መፍጠር ነውና ሀራም ነው።

አላህ እንዲህ ብሏል:-

أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ
«ከሀይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?» ሱረቱ ሹራ ቁጥር 21

ቡኻሪ እና ሙስሊም በዘገቡት የተረጋገጠ ሰሂህ ሐዲስ ነቢያችን ﷺ ብለዋል፤

مَنْ أحْدَثَ في أمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ

«በዲናችን ውስጥ ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ ስራው ተመላሽ ይደረግበታል» ብለዋል።

ይህ ማለት በሸሪዓ ያልተደነገገን ነገር ፈጥሮ ቢፈፅም ተቀባይነት አያገኝም ማለት ነው።
እንደሚታወቀው፤ መውሊድን ረሱል ﷺ የተከበሩት ኸሊፋዎች እና ሌሎችም ሰሀባዎች አላከበሩትም። እንደዚሁ በተከበረው ዘመን ውስጥ የኖሩት ሰሀባዎችን በመልካም ሲከተሉ የነበሩ ታቢዒዮች አልሰሩትም። እነሱ ደግሞ ከማንም በላይ የሱና አዋቂዎችና ለነቢያችን የነበራቸው ውዴታም ከማንም በላይ እንደነበር እሙን ነው። የነብዩን ፈለግ በሚገባ በመከተልም የማይታሙ እንደ ነበሩ ለማንም ግልፅ ነው። ለኛ አርአያ መሆናቸውም ተነግሮናል። ምንም ሳንጨምር መንገዳቸውን አጥብቀን እንድንይዝ የአላህ መልዕክተኛ አደራ ብለውናል፤

عَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ الْمَهْدِيِّينَ، وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الْأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ، وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ

«የእኔን እና የቅን ምትኮቼን ሱና አደራ! በጥርሶችችሁ አጥብቃችሁ ያዙ! አዳዲስ ፈጠራዎችን ተጠንቀቁ (ተከልከሉ)፣ በዲን ውስጥ የተጨመረ ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው» ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል

መውሊድ በቀደምቶቹ ዘመን እንዳልነበረ እና ኃላ የተፈጠረ (ሙህደስ) ለመሆኑ መውሊድ አክባሪዎች ሁሉ የማይክዱት እውነታ ነው። መውሊድ ማክበርን ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩት ከአራተኛው ክ/ዘመን በኋላ እራሳቸውን ፋጢሚዮች ብለው ይጠሩ የነበሩት ኡበይዲዩች ግብፅን በ362 ዓመተ ሂጅራ የወራሩ ጊዜ ነበር።

አልሚቅሪዚይ "አልመዋኢዝ ወል-ኢዕቲባር" በተሰኘው ድርሳናቸው ቅፅ 2 ገፅ 436 ላይ እንዲህ ብለዋል፦ የፋጢሚያ (ዑበይዲዮች) ነገሥታት አመቱን ሙሉ የተለያዩ በአላት ነበሯቸው። ለምሳሌ፤ የአመቱ መግቢያ፣ የመጀመሪያው አመት፣ የዓሹራ ቀን፣ የነብዩ ﷺ መውሊድ ይገኙበታል። በተመሳሳይ መልኩ አቡ ሻማህ–አል-ባዒስ አላ ኢንካሪል-ቢደዕ ወልሀዋዲስ ገፅ 23 ላይ እንዲህ ብለዋል፤ በኛ ጊዜ ከሚፈፀሙ ተመሳሳይ መጤ (ሙህደስ) ተግባራት መካከል፤ በኢርበል ከተማ በየዓመቱ የሚፈፀመው የሰደቃ፣ የበጎ አድራጎትንና ደስታን ለመግለፅ ተውቦና ደምቆ በመዋል (የሚከበረው) የነቢዩ ﷺ የልደት ቀን አንዱ ነው።

ኢብኑ ነሓስ – ተንቢሁል ጋፊሊን ገፅ 331 ላይ እንዲሁም ኢብኑል ሀጅ – አልመድኸል ቅፅ 2 ገፅ 2 ተመሳሳይ መልዕክቶችን አስፍረዋል።
በዚሁ አጋጣሚ መውሊድን ስለጀመሩት ሰዎች ማንነት አንዳንድ ነገሮችን ማንሳት ግድ ይለናል፤ "ዑበይዲዮች" ምንም እንኳ ራሳቸውን ወደ ፋጢማ ቢያስጠጉም፤ ሸሪዓዊ ትዕዛዛት እና ክልከላዎች የራቁ ትርጉሞችን በመስጠት ስርአት አልበኝነትን የሚከተለውን የባጢኒያ አመለካከት በማራመድ፣ የዲነልኢስላም ፋና እንዲጠፋ የቻሉትን ሁሉ በማድረግና ኡለማዎችን በመጨፍጨፍ የታወቁ ነበሩ። እነዚህ ሰዎች የኩፍር ንግግሮችን በመናገራቸዉ፣ አላህንና ነብያቶችን በግልፅ በመሳደባቸዉ፣ ክልክሎችን ሀላል በማድረጋቸዉ ወዘተ... ታላላቅ የኢስላም ሊቃዉንት ከኢስላም ምንም ድርሻ እንደሌላቸዉ ተናግረዋል። ሰላሀዲን አል-አዩቢይ አላህ ይዘንለትና ቁድስን ካስለቀቀ በኋላ ሙስሊሙን ከነዚህ ሰዎች ወረራ ለማላቀቅ ዘምቶባቸው ሙስሊሙን ህብረተሰብ እፎይ አሰኝቷል። ከፊሎቹ ደግሞ መውሊድን የጀመረው በ630 ዓ.ሒ የሞተው ንጉስ መሊክ ሙዞፈር ሲሆን እሱ ደግሞ ፍትሃዊ ንጉስ ነበር ይላሉ። በዘመኑ የነበረው የታሪክ እና የጂዖግራፊ ሊቅ ያቁተል ሀመዊ ሙዘፈርን ሲገልፀው “የሰው ንብረት ይዘርፋል ግን ለድሃዎች ያበላል፣ ስራዎቹ ሁሉ ግራ የሚያጋቡ ናቸው” ይላል። መውሊድን ማንም ቢጀመረው ከብዙ ክፍለ ዘመናት በኋላ በዲን ላይ የተጨመረ ለመሆኑ ምስክር ነው።

ከላይ በተዘረዘሩት መረጃዎች መሰረት መውሊድ የዲን አካል ያልነበረ የዑበይዲዮች ወይም የኢብኑ ሙዞፈር ፈጠራ እንደሆነ ግልፅ ነው።

مَنْ أحْدَثَ في أمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ» متفق عليه

ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በዲናችን ውስጥ ከእሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ ስራው ተመላሽ ነው” ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል

2) ዒባዳን በጊዜ መለየት (ተኽሲስ)፦
ጊዜያትን ለተለያዩ ዒባዳዎች መፈፀሚያ አድርጎ የወሰነልን አላህ ነው። በሸሪዓችን ረመዳን ለፆም ዙልሒጃ ለሐጅ እንደተለዩት በጊዜ የተገደቡ ዒባዳዎችን በመወሰን በዚህ ቀን ወይም ወር ይህ ይፈፀማል የሚል ድንጋጌ ማውጣት ለማንም አይፈቀድም።

መውሊድ የሚያከብሩ ወገኖች ግን በሸሪዓችን ያልተደነገገውን የረቢዕን ወር አስራ ሁለተኛ ቀን በተለያዩ የዒባዳ ተግባራት ለማሳለፍ በአል አድርገው መርጠውታል። አቡሁረይራህ ባስተላለፉት ሐዲሥ ረሱልﷺ እንዲህ ብለዋል፤

لَا تَخْتَصُّوا لَيْلَةَ الْجُمُعَةِ بِقِيَامٍ مِنْ بَيْنِ اللَّيَالِي، وَلَا تَخُصُّوا يَوْمَ الْجُمُعَةِ بِصِيَامٍ مِنْ بَيْنِ الْأَيَّامِ، إِلَّا أَنْ يَكُونَ فِي صَوْمٍ يَصُومُهُ أَحَدُكُمْ

“የጁምዓ ሌሊትን ከሌሎች ለሊቶች በመለየት በቂያም አትለዩ። ምን አልባት ከምትፆሙት ፆም ጋር ከገጠመ እንጂ የጁምዓ ቀንን ከሌሎች ቀናት በመለየት አትፁሙ» ሙስሊም ዘግበውታል

በዚህ ሐዲሥ የነቢዩ ንግግር ተኽሲስን ያመለከታል። ከጁምዓ ጋር አያይዘው ስለ ተከለከለ ወይም ስለ ታዘዘ ነገር ሲነግሩን ችግሩ በሸሪዓ ልዩ ያልተደረገን ጊዜ በተወሰኑ ኢባዳዎች መለየት ላይ መሆኑን እንረዳለን። አንድን ጊዜ ከሌሎች ጊዜያት በፆም በሶላት አትለዩት ተብሎ መከልከሉ ለሚሰራው ስራ መበላሸት መንስኤው በሸሪዓ ያልተገደበለትን ጊዜ መገደብ (ተኽሲስ) መሆኑን ያስረግጥልናል።

3) ሙስሊም ካልሆኑ ጋር መመሳሰል (ተሸቡሕ)፦

መውሊድን ማክበር ክርስቲያኖች የእየሱስ ልደት (ገና) ብለው ከሚያከብሩት በአል ጋር በእጅጉ ተመሳሳይነት አለው።
አንዳንድ የቢድዓ ሰዎች ነቢዩን ለማላቅ በማሰብ መውሊድን ሲጀምሩት ክርስቲያኖች እንዴት "የነብያቸውን የውልደት ቀን በማውሳት ይቀድሙናል" ከሚል የፉክክር ስሜት ነው። ይህንኑ እውነታ በማረጋገጥ አሕባሽ በመባል የሚታወቀው ቡድን መስራች የሆነው ዐብዱላህ አልሐበሺ የ ‘ኢዝሀሩል አቂደቲሱኒያህ’ የድምፅ ማብራሪያ ካሴት ቁ.9 የመጀመሪያው ክፍል ላይ መውሊድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያከበረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዘፈር እንደሆነ እና አጀማመሩም ክርስቲያኖች የመሲህን ልደት ሲያከብሩ አይቶ "ሙሀመድﷺ ወደዚህ አለም ብቅ በማለታቸው አላህን ላመስግን" በማለት እንደጀመረው ተናግሯል።

ቡኻሪ ከአቢ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንደዘገቡት የአላህ መልዕክተኛﷺ እንዲህ አሉ፤
لَتَتَّبِعُنَّ سَنَنَ مَنْ قَبْلَكُمْ شِبْرًا بِشِبْرٍ، وَذِرَاعًا بِذِرَاعٍ، حَتَّى لَوْ سَلَكُوا جُحْرَ ضَبٍّ لَسَلَكْتُمُوهُ»، قُلْنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ: اليَهُودَ، وَالنَّصَارَى قَالَ:«فَمَنْ»

"ከናንተ በስተፊት የነበሩትን (ህዝቦች) ፈለግ ስንዝር በስንዝር እርምጃ በእርምጃ ትከተላላችሁ። የተሳቢ እንስሳ ጉድጓድ እንኳ ቢገቡ ትከተሏቸዋላችሁ" የአላህ መልዕክተኛﷺ ሆይ አይሁዶችንና ነሳራዎችን ነው? ተብለው ሲጠየቁ፤ «ሌላ ማንን ነው!» (እነሱን ነው እንጂ) በማለት መለሱ።

ቡኻሪ እና ሙስሊም በዘገቡት ሌላ ሐዲሥ “ሙሽሪኮችን ተፃረሯቸው” ብለዋል። ይህ ማለት በማንነታችሁ ላይ አትደራደሩ፣ በሀይማኖታዊ ጉዳዮች ሌሎችን ከመምሰል ተጠንቀቁ ነው።

በሌላ በኩል በመውሊድ በዓል ላይ በነቢያችን ﷺ ላይ ድንበር በማለፍ እና የአላህን ስልጣን በመስጠት የሚያወድሱ ግጥሞች ይነበባሉ። እርሳቸው ግን የዚህ አይነቱን ድንበር ማለፍ ከልክለዋል፤
لاَ تُطْرُونِي، كَمَا أَطْرَتْ النَّصَارَى ابْنَ مَرْيَمَ، فَإِنَّمَا أَنَا عَبْدُهُ، فَقُولُوا عَبْدُ اللَّهِ، وَرَسُولُهُ
«ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ እንዳጋነኑት እኔንም አታጋንኑኝ፤ እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ የአላህ ባሪያ እና መልዕክተኛ ብቻ በሉኝ» ሀዲሱን ቡኸሪ ዘግበውታል።

በመሆኑም መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች ሁለት የመመሳሰል (ተሸቡሕ) ጥፋቶችን ፈፅመዋል።
1ኛ:- ከኩፋሮች ጋር በበዓል መመሳሰል
2ኛ:- ድንበር ባለፈ የውዳሴ አካሄድ መመሳሰል
ሲጠቃለል፤

የመውሊድ በዓል የሸሪዓ አካል ስላልሆነ፣ ተቀባይነት የሌለው፣ መሰረታዊ የአምልኮ መርሆዎችን የሚጥስ የቢድዓ ተግባር ነው።
እርግጥ ነው የነብዩ ውዴታ ‘መሐባ’ እና እሳቸውን ማላቅ በእጅጉ የሚያስፈልገን ነገር ነው። ሆኖም ውዴታቸውን የምንገልፀው መንገዳቸውን በመከተል፣ ሱናቸውን አጥብቀን በመያዝ እና ከአዳዲስ ፈጠራዎች በመራቅ መሆን አለበት። ‘የነብዩ ውዴታ’ በሸሪዓ መሰረት ያለው፤ ብሎም የኢማን መገለጫ መሆኑ አጠያያቂ ባይሆንም፤ ከተለያዩ የቢድዓ ተግባራት ጋር ተጣምሮና በቀን ተገድቦ ከተፈፀመ ግን በቢድዓነት ይፈረጃል።

መውሊድ ቢድዓ ከመሆኑ ባሻገር በየጊዜው እንግዳ ጥፋቶች እየታከሉበት እምነትን ከሚጎዱ ብዙ ተግባራት ጋር ከሁለቱ ኢዶች እኩል ወይም ከነሱ በደመቀ ሁኔታ በይፋ በመከበር ላይ ነው። በተለይም በአንዳንድ ቦታዎች ከተራ ወንጀሎች እስከ ቀብር አምልኮ የሚደርሱ ጥፋቶች ይሰራሉ። በተለይ ደግሞ ዓዋቂ የሚባሉ ሰዎች ሲሳተፉበት የቢድዓ አራማጆችም ተራ ሙግቶችን በጥሩ ገለፃዎች ከሽነው በስፋት ሲያሰራጩ ብዙሀኑን ህዝብ መደናገር ውስጥ ይከታሉና ሐቁን መግለፅ የሁሉም አዋቂዎች ግዴታ መሆኑን እናስታውሳለን።

አላህ እውነተኛ የነብዩ ወዳጆችና ተከታዮች ያድርገን። ሀሰትን ተከትሎ መንገድ ከመሳት ይጠብቀን።

ወል ሐምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን!

http://nesiha.com/blog/Vol1/01/index.php?Article=58

09/06/2022
26/05/2021

“ይህ ነው እምነቴ”

ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐብዱልወሃብ
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
๏| ነሲሓ መጽሔት ቅጽ Vol 2 ቁጥር 1 |๏

ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሃብ ዕምነትን ከአንደበታቸው
______

ባለፉት ዓመታት መስሊሞች ሃይማኖታቸውን በነፃነት መተግበር እንዳይችሉ በሰፊው ሲነዙ ከነበሩ ማስፈራሪያዎችና አግላይ ስያሜዎች መካከል “ወሃብያ” አንዱና ዋነኛው ነበር። ስያሜው ተውሒድ እና የመልዕክተኛውን ሱንና የሚከተሉ ሙስሊሞችን ለማሸማቀቅና ለማግለል የዋለ መሣሪያ ይሆን ብዙ ተብሏል። ከዚህም አልፎ በመንግስት ደረጃ በአክራሪነት የሚያስፈርጅ ወንጀል ይሆን ዘንድ በውጭ አካላት ይዘወር የነበረው መጅሊስ እና ከሊባኖስ የመጣው የአሕባሽ አንጃ ጀሌዎች ያደረጉት ግፊት ሙስሊሙን ማሕበረሰብ እጅግ አሳዛኝ የታሪክ ጠባሳ ጥሎበት አልፏል። የተውሒድ ተጣሪዎች ላይ ወሃብያ የሚለውን ስያሜ ለመለጠፍ መነሻ ያደረጉት የተውሒድ ተጣሪና የዑማው ባለ ውለታ የሆኑትን ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐብዱልወሃብ ድርሳናት እና አስተምህሮዎች ትቀበላላችሁ የሚል ነው። ለኢስላም ብዙ ውለታ የዋሉ ታላላቅ ሊቃውንቶችን መተቸት እና በኩፍር መፈረጅ ለነሱ ቀላል መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በተለይም ባለፉት ዓመታት ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ በመንግስት ሚዲያዎችን ሳይቀር ሸይኹን እና እምነታቸውን ለማጥላላት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ማራመጃ አድርገዋቸው ከርመዋል። ከምዝበራና ብክነት የተረፈውን የሙስሊሙን ሀብት በመጠቀም በሊባኖስ ነውጥ ፈጣሪነታቸው የታወቁ የአሕባሽ አንጃ መሪዎችን በማምጣት የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጭምር ተጠቅመው ተከታታይ የስም ማጠልሸት አሉባልታዎችን ነዝተዋል። ለመሆኑ በሸይኹ ላይ ሲነዙ የነበሩ ትችቶችን በመገምገም እውነታ ነው ወይስ አሉባልታ የሚለውን ለመወሰን በጠላቶቻቸው የሚሰነዘሩባቸውን ክሶች መሰረት ከማድረግ ይልቅ የሸይኹን የራሳቸውን ንግግርና ድርሳናት ማመሳከር አጠያያቂ ያልሆነ መፍትሔ በመሆኑ ስለ ሸይኹ እምነት ከራሳቸው አንደበት ልናስነብባችሁ ወደናል፤ ፍርዱን ለአንባብያን እንተዋለን።

የአላህ እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁንና የቀሲም ህብረተሰብ በአንድ ወቅት ስለ ሸይኹ እምነት እና አካሄድ ጠይቋቸው የሚከተለውን ደብዳቤ ፅፈዋል፡-
‹‹አላህና በኔ ዘንድ ያሉት መላዕክቶቹ መስካሪዎቼ ናቸው... እናንተም ምስክሮቼ ሁኑ፤ እኔ የማምነው፤ አህለ ሱና ወልጀመዓ፣ ፊርቀቱ ናጂያ በሚያምኑበት እምነት ብቻ ነው። በቅድሚያ፤ በአላህ ማመን፣ በመላዕክቶቹ፣ በኪታቦቹ (በመፃህፍቱ)፣ በመልዕክተኞቹ፣በትንሳዔው ቀን እንዲሁም በክፉውም በደጉም ቀደር ማመን ነው እምነቴ...

በአላህ ማመን ስል፤ አላህ ስለራሱ በቁርዓንና በመልዕክተኛው ﷺ አንደበት ስለአላህ ባህሪያት የገለፀውን ሁሉ ያለምንም ትርጉም ማዛባት(ተህሪፍ) እና ትርጉም ማሳጣት(ተእጢል) ማመን ሲሆን፤ እንደ አላህ ያለ ማንም እንደሌለና አምሳያ እንደሌለው፣ ሰሚና ተመልካች አምላክ መሆኑን አምናለሁ። አላህ እራሱን የገለፀበትን ባህሪ ውድቅ አላደርግም። ንግግሩን በሌላ አልቀይርም፣ መልዕክቶቹንም አላዛባም። ስሞቹንና አንቀጾቹን አላጣምም፣ ይህን ይመስላልም አልልም። የላቀዉን አላህ ባህሪዎች ከፍጡራን ባህሪ ጋር አላመሳስልም፣ምክኒያቱም የላቀው ጌታዬ አቻም ይሁን ቢጤ የለውምና በፍጡራኑ አይገመትም።

ጥራት የተገባው አምላካችን ስለራሱም ይሁን ስለሌላው ከፍጡራኑ ይበልጥ አዋቂ፣ ንግግሮቹም የእውነቶች ሁሉ ዕውነት እና ውብ ናቸውና፤ አላህን ከፍጡራን ጋር በማመሳሰል “ተምሲል” እና ስለባህሪያቱ ምንነት ግምታቸውን በመናገር “ተክዪፍ” የታወቁት፤ የሐቅ ተጻራሪ ቡድኖች ለእርሱ ከሰጧቸው መገለጫዎች ሁሉ አላህ እራሱን አጥርቷል። እንደዚሁ ባህሪዎቹን ተቃርነው አንቀበልም፣ አናጸድቅም ያሉት “ሙዓጢላዎች” እርሱን ከሚገምቱበት ነገር ሁሉ አላህ ራሱን አጥርቷል። አላህ እንዲህ ይላል፤
﴿سُبحَٰنَ رَبِّكَ رَبِّ ٱلعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ١٨٠ وَسَلَٰمٌ عَلَى ٱلمُرسَلِينَ١٨١ وَٱلحَمدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلعَٰلَمِينَ١٨٢﴾ [الصافات: 180-182]
«የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፤ በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹን፤ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን» አልሳፋት 180-182

የቀሲም ህብረተሰብ በአንድ ወቅት ስለ ሸይኹ እምነት እና አካሄድ ጠይቋቸው የሚከተለውን ደብዳቤ ፅፈዋል፡-
ቀጥተኛውን መንገድ የሚከተሉት የስኬት ቡድኖች “አል-ፊርቀቱ ናጂያ” በአቋማቸው፤ የአላህ ተግባርን በተመለከተ፤ «የሰው ልጅ ምንም ነገር የመፈጸም ፈቃድና ችሎታ የሌለው ለድርጊቶች የተገራ ነው» በሚሉት “ጀብሪያዎች” እና «የሰው ልጅ ማንኛውንም ነገር ለመተግበር ሙሉ ፈቃድና ችሎታ አለው» በሚሉት “ቀደሪያዎች” መካከል ናቸው።

የአላህን የተስፋ ቃል (ዋዕድን) በተመለከተ፤ አቋማቸው በአጉል ተስፈኛ (ሙርጂዓዎች) እና በተስፋ ቢሶቹ (ወዒዲያዎች)መካከል ነው።

ኢማንን እና ዲንን በተመለከተ «ኢማን ተግባርን አያካትትም፤ አይቀንስም አይጨምርም፤ ወንጀልም ኢማንን አይጎዳም» በሚሉት “ጀህሚያ እና ሙርጂዓ” እንዲሁም «ተግባር ከኢማን ስለሆነ ወንጀል የፈፀመ ሁሉ ኢማኑ ተገፏል ካፊር ነው» በሚሉት “ሀሩሪያ እና ሙዕተዚላ” መካከል ናቸው፣ ሰሀቦችን በተመለከተ፤ ጥቂት የነብዩ ﷺ ቤተሰብ የሆኑ ሰሀቦችን እስከማምለክ በደረሱት “ረዋፊድ (ሺዓዎች)” እና ሰሀቦችን ካፊር ናቸው በሚል እስከመዋጋት በደረሱት አማፂያን» “ኸዋሪጆች” መካከል ናቸው፡፡

 እኔ የማምነው፤ ቁርዓን ፍጡር ሳይሆን ከአላህ የመጣ እና ወደ እርሱ የሚመለስ የእርሱ ንግግር መሆኑን ነው። አላህ በግልጽ ተናግሮታል፤ በእርሱ እና በባሮቹ መካከል አምባሳደር ወደሆኑት ታማኙ ባሪያው እና መልዕክተኛው ሙሐመድ ﷺ አውርዶታል፡፡

 አላህ የፈለገውን ሁሉ አድራጊ መሆኑን አምናለሁ፡፡ ከአላህ ፍላጎት ውጪም ተፈፃሚ የሚሆን ነገር የለም፡፡ ከእርሱ የይሁንታ ፈቃድ ውጪ የሚከሰት ነገር የለም፡፡ ከአላህ ውሳኔ የሚወጣ ፈፅሞ የለም፡፡ እርሱ ካስተናበረው ውጪም የሚከሰት ነገር የለም፡፡ ከተገደበው የአላህ ውሳኔ እና ፈቃድ የሚወጣ አይኖርም፤ በጥብቁ ሰሌዳ (ለውሀል መህፉዝ) ላይ ከተፃፈለት ውጪ ማንም አይተላለፍም፡፡

 የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከሞት በኋላ ይከሰታል፣ ይኖራል ብለው የነገሩንን ሁሉ አምንበታለሁ፡፡ የቀብር ውስጥ ፀጋንም ይሁን ቅጣትን አምንበታለሁ፡፡ ህይወት ወደየ ግለሰቡ አካል እንደምትመለስ እና የሰው ልጅ ሳይጫማ እርቃኑን ያልተገረዘ ሆኖ በትንሳዔው እለት በመሰብሰቢያው ሜዳ ለጌታው እንደሚቆም አምናለሁ፡፡ በዕለቱ ፀሐይ በጣም ትቀርባቸዋለች፣ ሚዛኖች ለምዘና ይቀመጣሉ፣ የባሮችም ተግባራት ይመዘናሉ፣ መልካም ተግባራቸው ሚዛን የደፋላቸው የሚድኑ ናቸው። ሚዛኑ የቀለለባቸው ግን ነፍሳቸውን የከሰሩ ሲሆኑ በጀሀነምም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ የባሮች ተግባር የተፃፈባቸው ድርሳናት ይዘረጋሉ፡፡ ከፊሉ በቀኝ እጁ መፀሐፉን የሚወስድ ሲሆን ከፊሉ ደግሞ በግራው የሚቀበል መሆኑን አምናለሁ፡፡

በትንሳዔው ሜዳ ላይ ለነብያችን ለሙሐመድ ﷺ ሀውድ የተሰኘ ኩሬ እንዳለ እምነቴ ነው። ውሀው ከወተት የነጣ፣ ከማር የጣፈጠ፣ መጠጫዎቹ በሰማይ ከዋክብት ቁጥር ልክ የሆኑ፣ አንዴ የተጎነጨ ሰው ከዛ በኋላ በፍፁም የማይጠማው መሆኑ እምነቴ ነው፡፡ ሰዎች በተግባራቸው መጠን በጀሀነም አፋፍ ላይ በተዘረጋው የሲራጥ ድልድይ ላይ እንደሚያልፉ አምናለሁ፡፡

 በነብዩ ﷺ አማላጅነት “ሸፋዓ” አምናለሁ፤ የመጀመሪያው አማላጅ መሆናቸውን እና እንዲያማልዱም ከሁሉም በፊት እንደሚፈቀድላቸው አምናለሁ። የእርሳቸውን ምልጃ የሚፃረር የጥመት ባለቤት የቢድዓ አራማጅ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይሁንና አማላጅነት ከአላህ ፍቃድና ውዴታ በኋላ የሚሆን ነው፡፡

وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَى - الأنبياء: 28
«ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም» አል አንቢያዕ 28

مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ - البقرة: 255
«ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?» አልበቀራ 255

وَكَمْ مِنْ مَلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِنْ بَعْدِ أَنْ يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَنْ يَشَاءُ وَيَرْضَى - النجم: 26
«በሰማያት ውስጥ ካሉ መላዕክትም ብዙዎች፤ አላህ ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም» አልነጅም 26

እርሱም ከተውሒድ ውጪ ምንም አይወድምና ለተውሒድ ባለቤቶች እንጂ ለማንም አይፈቀድም፡፡

 ሙሽሪኮች ከምልጃ ምንም ድርሻ አያገኙም፡፡ አላህም እንዳለው፡-
فَمَا تَنْفَعُهُمْ شَفَاعَةُ الشَّافِعِينَ - المدثر: 48
«የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም» ሱረቱል ሙደሲር 48
ጀነትና እሳት ፍጡራን መሆናቸውን፣በአሁኑ ሰዓትም እንዳሉ አምናለሁ።የሚጠፉና የሚወገዱ አይደሉም።

 የትንሳዔው ዕለት ባሮች በዓይናቸው ጌታቸውን እንደሚመለከቱ አምንበታለሁ፣ልክ ጨረቃ ፍንትው እና ድምቅ ባለችበት ምሽት ምንም ነገር ከእይታ እንደማይደበቅባቸው ሁሉ፤ እነርሱም በግልፅ ጌታቸውን ያያሉ፡፡

ነብያችን ሙሐመድ የነብያት እና የመልዕክተኞች መደምደሚያ መሆናቸው እምነቴ ነው፡፡ የትኛውም የአላህ ባሪያ በመልዕክታቸው ካላመነ ነብይነታቸውን ካልመሰከረ እምነቱ ትክክለኛ አይሆንም።

ከህዝባቸው መካከል በላጩ አቡበከር ሲዲቅ ናቸው፣ ከዚያም ዑመሩል ፋሩቅ፣ ከዚያም ዑስማን ዙኑረይን፣ ቀጥሎም ተወዳጁ ዐሊይ ናቸው። ከዚያም በጀነት ከተበሰሩት አስሩ ሰሀቦች የተቀሩት (ከአራቱ ኸሊፋዎች ውጪ ያሉት )፣ ከዚያም የበድር ዘማቾች፣ ቀጥሎም በይዐቱ ሪድዋን የተባለውን ቃልኪዳን በዛፍ ስር ለነብዩ የገቡት ባልደረቦች፣ ከዚያም ቀሪዎቹ ሶሀቦች ናቸው ፡፡ አላህ ሁሉንም ስራቸውን ይውደድላቸው።

 የመልዕክተኛውን ባልደረቦች እወዳቸዋለሁ፣ መልካም ዝናቸውንም አነሳለሁ፣ ተግባራቸውንም እወድላቸዋለሁ፣ ከጌታችንም ምህረትን እለምንላቸዋለሁ፤ የእነርሱን ነውር ከመጥቀስ እቆጠባለሁ፣ በመካከላቸው በተፈጠረው ጉዳይ ዙሪያም ዝምታን እመርጣለሁ፡፡ የአላህን ትዕዛዝ በመተግበር የተሰጣቸዉን ደረጃ አምኜ እቀበላለሁ። አላህ እንዲህ ይላል፤
وَالَّذِينَ جَاءُوا مِنْ بَعْدِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا اغْفِرْ لَنَا وَلِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ سَبَقُونَا بِالْإِيمَانِ وَلَا تَجْعَلْ فِي قُلُوبِنَا غِلًّا لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا إِنَّكَ رَءُوفٌ رَحِيمٌ - الحشر: 10
«እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት፤ «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምሕረት አድርግ፣ በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፤ ጌታችን ሆይ! አንተ ርኅሩህ አዛኝ ነህና» ይላሉ። ሱረቱል አል-ሐሽር 10

 የምዕመናን እናቶች (የነብዩ ባልተቤቶች) ከማንኛውም መጥፎ ነገር የፀዱ ንፁሀን መሆናቸውን አምናለሁ፤ እወዳቸዋለሁም።

 አውሊያዕ (የአላህ ወዳጆች) ከራማ እና ነገሮችን የሚለዩበት “ሙካሸፋት” እንዳላቸው እምነቴ ሲሆን፤ ይሁንና ከአላህ ሐቅ ምንም ድርሻ የላቸውም። ከአላህ በስተቀር ማንም የማይችለውን ጉዳይ ከእነርሱ አይከጀልም፡፡

 አላህና መልዕክተኛው ﷺ ከመሰክሩላቸውና ከመሰክሩባቸው ግለሰቦች ውጪ ለማንም “የጀነት ወይም የእሳት ነው” ብዬ አልመሰክርም፣ ይሁንና፤ መልካም ስራን ለሚተገብር ጀነትን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ለጥፋተኛም እሰጋለሁ። ማንኛውንም ሙስሊም ወንጀል ስለፈፀመ ካፊር አልልም፤ ከእስልምና ኬላም አላስወጣውም፤

ነብዩ ﷺ ከተላኩበት ዘመን አንስቶ፤ የዚህ ኡማህ የመጨረሻ ትዉልድ ደጃልን እስከሚጋደሉበት ወቅት ድረስ ቀጣይነት ባለው መልኩ ጂሀድ ተደንግጓል። አስፈላጊ በሆነበት ወቅት ሸሪዓዊ ህግጋቱን ጠብቆ ይፈጸማል። ጂሀድን የአምባገነኖች አድሎም ይሁን የፍትሀዊያን ፍትህ ውድቅ አያደርገዉም። ከመጥፎም ይሁን ጥሩ የሙስሊም መሪ ጋር ጂሀድ እንደተደነገገ አምናለሁ። የጀመዓ ሰላት ከእነርሱ ኋላ ተከትሎ መስገድም ይቻላል፡፡

 የሙስሊም መሪዎችን መስማት እና መታዘዝ ግዴታ መሆኑን የምቀበለው ነው፣ ጥሩዎችም ይሁኑ ክፉዎች የአላህን ተእዛዝ እንድንጥስ እስካላዘዙን ድረስ የመታዘዝ ግዴታ እንዳለብን አምናለሁ፡፡ የሙስሊሞች መሪን ተክቶ ኸሊፋ በመሆን ስልጣን የያዘ እና ሙስሊሙ ህብረተሰብ ወዶ የተቀበለውን መሪ እንዲሁም በጦር አሸንፎ ስልጣን የያዘ እና መሪ የሆነን ሰው መታዘዙ በርሱም መተዳደሩ ግዴታ ነው፡፡ እርሱ ላይ አምፆ መውጣት የተከለከለ ነው። የቢድዓ (የፈጠራና ፍልስፍና) ሰዎችን ማኩረፍና ተውበት እስኪያደርጉም እነርሱን መራቅ ይገባል እላለሁ፤ ይፋ በሚያደርጉት አቋማቸው መሰረት ውሳኔዬን አሳልፍባቸዋለሁ፣ በልባቸው የደበቁትን ግን ለአምላኬ እተወዋለሁ፣ ማንኛውም ቢድዓ ፈጠራ መሆኑንም አምናለሁ፡፡

ኢማን ወይም እምነት ማለት፤ በአንደበት መናገር (መመስከር)፣ በሰዉነት በአካላት መተግበር፣ በልቦና ማመን መሆኑን እና በመልካም ተግባር የሚጨምር በኃጢያት ደግሞ የሚቀንስ መሆኑን አምናለሁ። ኢማን ከ70 በላይ እርከኖች አሉት፤ ከፍተኛው ከአላህ ውጪ ሌላ አምላክ አለመኖሩን መመስከር ሲሆን ዝቅተኛው ደረጃ ደግሞ ከመተላለፊያ ጎዳና ላይ አስቸጋሪ ነገርን ማስወገድ ነው።

መልካምን ማዘዝ እና ከመጥፎ መከልከል ጽዱ የሆነው የሙሐመድ ﷺ ድንጋጌ ግዴታ በሚያደርገው መሰረት ሊፈጸም እንደሚገባው አምናለሁ፡፡ ይህ የምሞረከዝበት የምታገልበት እምነቴ ነው፣ እኔ ዘንድ ያለውን ድርሳኔን መልዕክቴን እንድታጠኑ የማስብላችሁ የምጓጓላችሁ ብሎም የምጨነቅላችሁ ጉዳይ ነው፡፡ አላህም በምንናገረው ላይ ተቆጣጣሪ ነውና›› ሲሉ ባጠቃላይ ህብረተሰቡ ላይ ክፍተት የተገባበትን ጉዳይ እና የራሳቸውን አቋም ገሀድ አድርገዋል፡፡ ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ኢብን ዐብዱልወሀብ በእያንዳንዱ ባነሱት ነጥብ ላይ የመጠቀ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ እያንዳንዱ ነጥብም አደናጋሪ የቢድዓ አራማጆች ሙስሊሙን ህብረተሰብ ያሳሳቱበት እና ከቅኑ መንገድ ያንሸራተቱበት ብዥታም ውስጥ የከተቱበት በፍልስፍና ያቀዣበሩበት ጉዳይ ነውና፡፡

ሙአለፋት አሽሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱልወሀብ ቅጽ 15/ገጽ 11-12

አሕመድ ሙሐመድ አቡ ፈውዛን

https://telegram.me/nesihablog

24/01/2021
14/05/2020

الوهابية ـ مصطلح أطلقه الخبثاء لتشويه صورة أهل السنة ، كيف نشأ هذا المصطلح ؟ ولماذا ؟ ومن وراءه ؟

كلام لربما غاب عن الكثير مننا وخُدِع الكثير به ....

بسم الله الرحمن الرحيم
أخوتي في الله تعلمون جيداً ، أن حركة الإصلاح الديني التي أعلنها شيخ الإسلام محمد بن عبد الوهاب ، قد قامت لتزيح عن كاهل أمة الإسلام ركاماً هائلاً من البدع والدجل والخرافة والشعوذة ، هذا الركام الذي أطفأ نور الإسلام ، وعكر صفو العقيدة ، ولوث التوحيد بالوثنية ، فأعاد إمام التوحيد الشيخ محمد بن عبد الوهاب ـ رحمه الله ـ أن يعيد للتوحيد صفاءه ، وللعمل الصالح سنته ، وقضى على كل أشكال الدجل الكهنوتي ، وحارب كل أنواع البدع في العقائد والعبادات ، وربط الناس بخالقهم ، بعدما ربطهم شيوخ التصوف والتبرك بالحجر والشجر والقبور. ومن المعلوم أن دعوة من هذا الصنف تحيي نور الإسلام بعدما أوشك على الانطفاء،من الطبيعي ألا تمر بسلام عند شيوخ التصوف والتشيع وشيوخ التقليد الأعمى الذين تضررت مصالحهم بعودة التوحيد إلى نقائه ، والإسلام إلى بهائه ، لأنهم يرتزقون على حساب تعكير صفو العقيدة ، وغياب التوحيد وتلويثه ، وإماتة السنة وإحياء البدعة .

فكاد هؤلاء الشيوخ الدجاجلة للشيخ محمد بن عبد الوهاب ، كل أنواع الكيد ، وحاربوه بكل ما أوتوا من قوة ، لأنه دمرهم اقتصادياً ، إذ سد عليهم كل أبواب النفع التي افتتحوها من خلال إحياء البدع الشركية والتعبدية ، إذ جعلوا من أنفسهم أوصياء الله على البشر ، وأنهم هم الجسر الذي يربط الناس بالله ، وهم الوسيلة بينهم وبين الله ، فتسللوا إلى جيوب الناس وأعراضهم ومن جملة كيد هؤلاء الدجاجلة لشيخ الإسلام محمد بن عبد الوهاب ما يلي :
1 ـ افتراؤهم على شيخ الإسلام بأنه يكره النبي ـ صلى الله عليه وسلم ـ
2 ـ افتراؤهم على الشيخ أنه يطعن بالأولياء ويزدريهم وينتقص منهم .
3 ـ افتراؤهم على الشيخ بأنه يطعن في كل علماء الأمة السابقين والمعاصرين بما فيهم الفقهاء الأربعة وسائر أئمة السلف .
4 ـ افتراؤهم على الشيخ بأنه يكفر كل المسلمين في عصره .
5 ـ افتراؤهم بأنه الشيخ استحدث ديناً جديداً .
6 ـ افتراؤهم بأن الشيخ أراد إحياء فكر الخوارج من خلال دينه الجديد ـ لذلك أطلقوا على اسم دعوته الإصلاحية باسم (الوهابية) مع أنه هو وأتباعه يستنكرون هذه التسمية ويضيقون ذرعاً بها .

ومن هنا حُقَّ لنا أن نسأل :
(من الذي أطلق هذه التسمية ؟ ، ولماذا ؟ ، ولماذا هذه التسمية بالذات ؟) .
أولاً : من خلال ما سبق عرفنا من الذي أطلق هذا المصطلح الذي ما أريد به إلا الكيد والخبث .
إنهم شيوخ الطرق الصوفية ، وشيوخ التقليد الأعمى ، وشيوخ الأشعرية والجهمية ، والشيعة بكل فرقها الخبيثة ، وعلى رأسها الرافضة والإسماعيلية والنصيرية والدروز . ووالدولة العثمانية ، ومحمد علي باشا (حاكم مصر) ومن ورائه شيوخ الأزهر وشيوخ التصوف .

ثانياً : الهدف من إطلاق هذا الاسم على هذه الحركة الإصلاحية هو تشويه صورتها ، وتثبيط عزم أتباعها ووهنهم ، ذلك لصرف الناس عن مجرد التعرف على حقيقتها ، وإيهام الناس أن هذا دين جديد هدام ، وتسميتهم بالوهابية هي تسمية خبيثة يراد بها أنها تنتسب لرجل مخترع ديناً جديداً ، على غرار المزدكية نسبة لمزدك ، والمانوية نسبة لماني ، والزرادشتية نسبة لزرادشت ، والبهائية نسبة للبهاء عباس ، ومن ثم يقولون للناس هذه حركة وهابية نسبة لمؤسسها محمد بن عبد الوهاب ، حتى ينفِّروا الناس منها ، وهذا ما حدث مع كثير من الناس وللأسف الشديد .

ثالثاً : أما عن الجواب لماذا هذه التسمية بالذات ؟ فأقول :
إن هذا الاسم لم يطلق بشكل عفوي أو اعتباطي ، بل أتى بعد مراجعة وتخطيط ، و إنهم لو أرادوا تسمية حركة الإصلاح على اسم من نادى بها لكان الأولى بأن تسمى على اسم شيخ الإسلام ـ رحمه الله ـ ومن المعلوم أن اسمه محمد ، وعلى هذا فكان ينبغي أن تسمى بـ (المحمدية) وليس الوهابية ، فالوهابية موافقة لاسم أبيه (عبد الوهاب) ، ومن المعلوم أن أباه لا دخل له بحركة الإصلاح ، ولا يعرف عنها شيء .
إذن لماذا اختير لفظ الوهابية بالذات ؟
والحقيقة أنه كان في القرن الثاني الهجري دولة لبعض الخوارج في شمال أفريقيا ، اسمها (الوهابية) نسبة لمؤسسها عبد الوهاب بن عبد الرحمن بن رستم ، وكانت حركة سيئة للغاية ، حاربت أهل السنة ، وأبغضت أهل السنة والشيعة معاً ، وعطلت السنة النبوية ، كما عطلت فريضة الحج ، فمقتها سائر المسلمين ، وهاجمها كثير من علماء الأندلس والمغرب وعلماء الشرق ، وألفوا في الرد عليها الكثير من الرسائل ، وكفرها سائر علماء المسلمين ، ولهم في تفيد هذه الحركة خبيثة وتكفيرها الكثير من الفتاوى التي تزخر بها كتبهم .
وبقيت هذه الدولة حوالي مئة سنة تقريباً ، فأهلكها الله تعالى على يد أهل السنة في المغرب ، وأراح الله المسلمين من خطرها .
وعندما صدح إمام التوحيد وشيخ الإسلام الإمام محمد بن عبد الوهاب ـ رحمه الله ـ بدعوته الغراء ، لتنقية العقيدة والتوحيد من الوثنية ، وتنقية العبادات من البدع ، محاولاً إرجاع إلى النبع الصافي إلى عصر النبوة ، مركزاً على أهمية التمسك بالكتاب والسنة وتقديمهما على كل قول وفعل ، محاولاً ربط الناس بخالقهم بعدما ارتبطوا بالقبور والأشجار والأحجار .
هنا وجد أهل الباطل من خلال تلاقي اسم أبيه مع مؤسس الحركة الوهابية الخارجية في القرن الثاني الهجري (عبد الوهاب بم عبد الرحمن بن رستم) ، فاستغلوا تلاقي هذه الأسماء ، ومن ثم أطلقوا على دعوة الشيخ باسم الوهابية ، بطرقة هي في غاية الخبث والدهاء ، وأتوا بكتب الفقهاء السابقين التي تزخر بالفتاوى التي تكفر الوهابية وفتحوها أمام الناس العوام ، وقالوا لهم ، حقيقة كفر الوهابية ، هذه فتاوى العالم فلان والشيخ فلان والعلامة فلان والإمام فلان كلها تكفر الوهابية فصدق الناس افتراءهم .
ومن هنا عرفنا من هم الذين أطلقوا هذا المصطلح ، وكيف ، ولماذا ؟ .
مع أنه في الحقيقة ليس في وقتنا الحالي شيء اسمه الوهابية ، بل هناك أناس لبوا دعوة إمام التوحيد محمد بن عبد الوهاب ، اسمهم الحقيقي أهل السنة والجماعة ، يصفون أنفسهم أحياناً بأنهم السائرون على نهج السلف الصالح في فهم العقيدة وآيات الصفات وفي العبادات) ويعبدون ربهم كما كان النبي ـ صلى الله عليه وسلم ـ وأصحابه الكرام يعبدون ربهم ، بلا زيادة ولا نقصان .

"منقول"

Photos 12/12/2019

!
«عقيدة فرقة الأحباش»
በሚል ርዕስ፤በተከታታይ 110 ክፍሎች በዛዱል መዓድ የትምህርት መድረክ በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ሲሰጥ የነበረው ወሳኝ የዐቂዳ ትምህርት በስፋትና፣ በመረጃ የቀረበበት ትምህርት ሲሆን ይህም ትምህርት በቅርቡ በአላህ ፈቃድ ወደ መፅሃፍ ተቀይሮ ለአንባብያን የሚደርስ መሆኑን እንገልፃለን

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🔸 ሙሉ ትምህርቱን ለማግኜት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ

🔎http://bit.ly/36rMgVn
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ክፍል (1) ፦ የአሕባሾ እምነት በሚዛን ላይ (መግቢያ)
🔎http://bit.ly/36rSJzQ

ክፍል (2) ፦ የአሕባሽ እምነት መችና በማን ተመሰረተ?
🔎http://bit.ly/38tYcb6

ክፍል (3) ፦ አብደላህ አል ሀረሪ በኢትዩጵያ ቆይታው ምን አደረገ?
🔎http://bit.ly/36nUAFx

ክፍል (4) ፦ አብደላህ አል ሀረሪ ሊባኖስን ለምን መረጠ? ወሀቢና ሱፊይ ምን ማለት ነዉ?
🔎http://bit.ly/2scyVSa

ክፍል (5) ፦ አብደላህ አል ሀረሪና መፅሀፎቹ
🔎http://bit.ly/35b3LZX

ክፍል (6) ፦ የአሕባሽ እምነት እንዴት ተመሰረተ? ለምንስ አሕባሽ ተባሉ?
🔎http://bit.ly/38sho91

ክፍል (7) ፦ አሕባሾች አለም ላይ ያላቸዉ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?
🔎http://bit.ly/2Pb7np3

ክፍል (8) ፦ የአሕባሾች ዋና አላማ ምንድን ነዉ? ከጀርባቸዉስ ማን ነዉ ያለዉ?
🔎http://bit.ly/38BGJO2

ክፍል (9) ፦ አሕባሽና አላህን ማወቅ
🔎http://bit.ly/2LGjB7e

ክፍል (10)፦ የመጀመርያው የሰዉ ልጆች ግዴታ ምንድን ነዉ?
🔎http://bit.ly/35bl50L

ክፍል (11)፦ ተዉሒድ በአሕባሾች ዘንድ
🔎http://bit.ly/2t6XCjk

ክፍል (12) ፦ እዉነት ተሒሂድን ለሶስት ከፍሎ ማየት ቢድዓ ነዉ?
🔎http://bit.ly/2rywJUQ

ክፍል (13) ፦የጀነት ቁልፍ የሆነችዋን ላኢላሀ ኢለላህ አሕባሾች ምን ብሎ ነዉ የሚተረጉሙት?
🔎 http://bit.ly/2E8GAne

ክፍል(14) ፦ ዒባዳ አሕባሾች ዘንድ ምን ማለት ነው?
🔎http://goo.gl/0KaeqN

ክፍል (15)፦ ዱዓ በኢስላምና በአሕባሾች ዘንድ ያለው ቦታ
🔎https://goo.gl/vXpYvz

ክፍል (16)፦ ቀደምት ዑለሞች ዱዓን አስመልክተው ምን አሉ? አሕባሾችስ ዱዓን ከዒባዳ ያስወጡበት ምክንያት ምንድነው?
🔎https://goo.gl/3ZPL0I

ክፍል (17) ፦ አሕባሾች የሞቱ ወሊዬችንና ሷሊሆችን መለመንና መጣራት ይቻላል ብለዉ ለሚያቀርቧቸዉ ማስረጃዎች በሚዛን ላይ
🔎https://goo.gl/o9R7mH

ክፍል (18) ፦ እዉነት አሕባሾች እንደሚሉት ወሊዮችንና ነቢያቶችን እርዳታ መጠየቅና ኢስቲዐና ማድረግ ይቻላልን?
🔎https://goo.gl/Fk9aXS

ክፍል (19)፦ አሕባሾችና ኢስቲጛሣ(ሙታንን መጣራት)"
🔎https://goo.gl/WD8Ebe

ክፍል (20) ፦ "አሕባሾች ሙታንን መጣራት (ኢስቲጛሣ) ይቻላል" ብለው ለሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች ምላሽ
🔎https://goo.gl/mZykAW

ክፍል (21)፦ "አንዳንድ ሰዎች ሙታንን ተጣርተው ያሰቡት መሳከቱ ድርጊታቸው ትክክል የመሆኑ ምልክት ነውን?"
🔎https://goo.gl/bTYv1m

ክፍል (22) ፦ አሕባሾችና በፍጡራን (በሙታን) መጠበቅ
🔎https://goo.gl/zq1UyZ

ክፍል (23)፦ በተለምዶ ከሰው ልጆች የማይጠየቅን ነገር መኽሉቅን(ፍጡርን) መጠየቅ እንዴት ይታያል?
🔎https://goo.gl/LPx2kn

ክፍል (24)፦ በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ የሽርክ ዓይነቶች የመስፋፋት መንስኤዎች (ቁ-1)
🔎https://goo.gl/smOuBJ

ክፍል (25) ፦በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ የሽርክ ዓይነቶች የመስፋፋት መንስኤዎች (ቁ-2)
🔎https://goo.gl/dtqbFL

ክፍል(26)፦ በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ የሽርክ ዓይነቶች የመስፋፋት መንስኤዎች (ቁ-3)
ወልዮች ላይ ድንበር ማለፍ
🔎https://goo.gl/UpHWNZ

ክፍል (27) ፦ በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ የሽርክ ዓይነቶች የመስፋፋት መንስኤዎች (ቁ-4)
🔎https://goo.gl/i7xcsp

ክፍል (28) ፦ የሺርክ አስከፊነትና ከአደጋው የመዳኛ መንገዶች
🔎https://goo.gl/apPAEy

ክፍል (29) ፦ አሕባሾችና የአላህ ባህሪያት
🔎https://goo.gl/Zh33Tw

ክፍል (30) ፦ እውነት የአላህ ባህሪያት 13 ብቻ ናቸውን? በዚህ ዙሪያስ ደጋግ ቀደምቶች ምን ብለዋል?
🔎 https://goo.gl/G3uuhw

ክፍል (31) ፦ የአላህ ባህሪያት ዱሮ ሆነዉ ያበቁ ናቸዉ ወይስ ...?
🔎http://bit.ly/2P9P43B

ክፍል (32) ፦ አላህ ራሱ ከፍጡራኖች ሁሉ በላይ መሆኑና የአሕባሾች አቋም
(ቁ-1)
🔎http://bit.ly/2PCBNjj

ክፍል (33) ፦ አላህ ራሱ ከፍጡራኖች ሁሉ በላይ መሆኑና የአሕባሾች አቋም
(ቁ- 2)
🔎http://bit.ly/34aEUEn

ክፍል (34)፦ አላህ የት ነው ብሎ መጠየቅ እንዴት ይታያል?
🔎http://bit.ly/2E3bv4a

ክፍል (35)፦ የአላህን እላይ መሆን የሚያሳዩ የሐዲሥ ማስረጃዎችና የቀደምት ዑለማዎች አቋም
🔎http://bit.ly/2E5hntV

ክፍል (36)፦ የአላህ ከዓርሽ በላይ መሆንና የአሕባሾች አቋም
🔎http://bit.ly/2si7ING

ክፍል (37) ፦ ኢስተዋ የሚለውን ቃል የቋንቋ ሊቃውንት ምን ብለው ተረጉሙት?
🔎http://bit.ly/2PwK8Vu

ክፍል (38)፦ አሕባሾች "ወሕይን" እየተዉ ተናጋሪውና ምንጩ የማይታወቅን "ግጥም" ማስረጃ ያደርጋሉ
🔎http://bit.ly/2YCddTs

ክፍል (39)፦ የአላህ ከአርሽ በላይ መሆን የሚያሳየዉ የኢማሙ ማሊክ ንግግርና የአሕባሾች ሽሽት

🔎http://bit.ly/2RHooJs

ክፍል (40)፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን የሚያሳዩ ጥቂት የሰሓባና የታቢዒዮች ንግግር
🔎http://bit.ly/2PMbPtN

ክፍል (41) ፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን በተመለከተ ደጋግ ቀደምቶች ምን አሉ?
🔎http://bit.ly/2PBf86F

ክፍል ( 42)፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን በተመለከተ ኢማም አቡ ሐኒፋና ኢማሙ ማሊክ ምን አሉ?
🔎http://bit.ly/2Pywz86

ክፍል (4 3)፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን በተመለከተ ኢማሙ አሽሻፊዒና ኢማሙ አሕመድ ምን አሉ?
🔎http://bit.ly/2E6yiMv

ክፍል (44) ፦ አሕባሾች የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን ለማስተባበል የሚጠቀሟቸው ቃላቶች

الله موجود بلا مكان❌
🔎http://bit.ly/2RJf07U

ክፍል አርባ (45)፦ የአላህን ከዐርሽ በላይ መሆን የተመለከተ ማጠቃለያ ትምህርት

💥ለብዥታዎች መልስ የሚሰጥበት
💥የአላህን ስምና ባህሪ በተመለከተ ጠቃሚ ምክሮች የተለገሱበት ትምህርት

🔎http://bit.ly/2YElaaN

ክፍል አርባ (46)፦የአላህ በየሌሊቱ ወደ ቅርቧ ሰማይ መውረድና የአሕባሾች አቋም
🔎http://bit.ly/2rpKoOd

ክፍል (47) ፦ አሕባሾች የአላህን ወደ ቅርቧ ሰማይ መውረድ ለማስተባበል የሚያነሷቸው ብዥታዎችና መልሶቻቸው
🔎http://bit.ly/2Pyawyg

ክፍል (48) ፦የአላህ ንግግርና የአሕባሾችአቋምን
(ቁ-1)
🔎http://bit.ly/2Ead9RM

ክፍል (49) ፦የአላህ ንግግርና የአሕባሾች አቋም
(ቁ-2)
🔎http://bit.ly/2E7xYx1

ክፍል (50) ፦"إنه لقول رسول كريم" ማለት ምን ማለት ነው?
*እውነት ቁርኣን የጂብሪል ንግግር ለመሆኑ ማስረጃ ይሆናልን?
🔎http://bit.ly/34cYQGD

ክፍል (51) ፦ የአላህ ንግግር በፊደልና በድምጽ ነው ወይስ..?
🔎http://bit.ly/38mtUXA

ክፍል (52)፦ የአላህን ፊት የሚመለከቱ ጥቅሶችና አሕባሾች
🔎http://bit.ly/34bGupp

ክፍል (53) ፦ ለአላህ እጅና እግር አለው? የአሕባሾችስ አቋም ምንድን ነው?
🔎http://bit.ly/36r2Gxm

ክፍል (54)፦ አላህ ይቆጣል ማለት አሕባሾች ዘንድ ምን ማለት ነው?
🔎http://bit.ly/36oxcaV

ክፍል (55) ፦ የሙእሚኖች ኣኺራ ላይ አላህን ማየት እና የአሕባሾች አቋም
🔎http://bit.ly/2PFlTo2

ክፍል(56):-ኢማን ማለት አሕባሾች ዘንድ ምን ማለት ነው?
🔎http://bit.ly/2PDv0Wf.

ክፍል (57) ፦ ደጋግ ቀደምቶች ዘንድ ኢማን ማለት ምን ማለት ነው?
🔎http://bit.ly/358rFVQ

ክፍል (58) ፦ ኢማንና ሰላት
🔎http://bit.ly/2LM0vfI

ክፍል (59) ፦ የኢማን መጨመርና መቀነስ አሕባሾችና አህል-አስሱና ዘንድ "ኢን'ሻ'አላህ ሙእሚን ነኝ" ማለትስ ይቻላል?
🔎http://bit.ly/2RIRGaC

ክፍል (60) ፦ አሕባሾችና ሙስሊምን ማክፈር
🔎http://bit.ly/2LJU3Wu

ክፍል (61) ፦ አሕባሾችና በቀደር ማመን እና እውነት አላህ ከሃዲያንን በክህደታቸው ላይ አግዟቸዋልን?
🔎http://bit.ly/2seSvgu

ክፍል (62)፦ የሰሓባዎች ደረጃ አሕባሾች ዘንድ
🔎http://bit.ly/2P9v7dl

ክፍል (63) ፦ ሁሉም ሰሓባዎች መወደድና መከበር እንዳለባቸው የሚያሳዩ የቁርኣና የሐዲሥ ማስረጃዎች ከቀደምት ዑለማዎች ንግግር ጋር
🔎http://bit.ly/38sPidU

ክፍል (64) ፦ የምእምናን አጎት ሙዓዊያ
(رضي الله عنهما) በአሕባሾች እይታ
🔎http://bit.ly/36qGyTA

ክፍል (65) ፦ ዐሊይና ሙዓዊያን رضي الله عنهما ምን ነበር ያጋጫቸው?
★የሌሎች ሰሓቦችስ ሚና ምን ነበር?
🔎http://bit.ly/2LL9P3u

ክፍል (66) ፦ በዐሊይና በሙዓዊያ ጉዳይ ዙሪያ የዲን ሊቃውንት ምን አሉ?
🔎http://bit.ly/2RHXkK4

ክፍል (67) ፦ ቁርኣን፣ ነቢዩ፣ (ﷺ) ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው ስለ ሙዓዊያ ምን አሉ? የሙዓዊያ ትሩፋት
🔎
http://bit.ly/2LIQdNF

ክፍል (68) ፦ የሙዓዊያ رضي الله عنهما ስነ ምግባርና ስብዕና
🔎http://bit.ly/2LLrgkt

ክፍል (69) ፦ የሰሓባዎችን رضي الله عنهم ግጭት በተመለከተ የአህል-ስሱና አቋም ምንድን ነው?
🔎http://bit.ly/2slsHPD

ክፍል (70) ፦ ቢድዓና አሕባሾች
🔎http://bit.ly/2RGLmAj

ክፍል (71) ፦ ዲን ላይ ጥሩ ቢድዓ የሚባል ነገር አለን?
🔎http://bit.ly/36mA2gP

ክፍል (72) ፦"من سن في الإسلام سنة حسنة...
የሚለው ሐዲሥ እውነት የቢድዓ ጥሩ እንዳለ ማስረጃ ነውን?
🔎http://bit.ly/2sdLNrd

ክፍል(73) ፦ የዑመር رضي الله عنه
("نعمت البدعة هذه") የሚለው ንግግራቸው እውነት የቢድዓ ጥሩ እንዳለ ማስረጃ ነውን?
🔎http://bit.ly/2rA4Sne

ክፍል (74) ፦ ኢማሙ አሽሻፊዒይ ቢድዓን በተመለከተ አቋማቸው ምን ይመስላል?
🔎http://bit.ly/2E4EO6q

ክፍል (75)፦ አሕባሾች የጥሩ ቢድዓ ምሳሌዎች ናቸው የሚሏቸው ነገሮችና መልሶቻቸው
🔎http://bit.ly/2YFfjSL

ክፍል (76)፦መውሊድና አሕባሾች
🔎http://bit.ly/2sgW1ah

ክፍል (77) ፦ የሶፊያ ጠሪቃ / መንገዶች እውነት መልካም ቢድዓ ናቸውን?
🔎http://bit.ly/2LKtT6m

ክፍል (78) ፦ "ተወሱል" ማለት ምን ማለት ነው? የአሕባሾችስ አቋም ምንድነው?
🔎http://bit.ly/38vYG08

ክፍል (79) ፦ ለአሕባሾች የተሳሳተ ተወሱልና ለደሊሎቻቸው ምላሽ
🔎http://bit.ly/2rpSnLb

ክፍል (80) ፦ አሕባሾች ለተሳሳተው ተወሱላቸው ማስረጃ የሚሏቸው 2 ነገሮች ምላሽ
🔎http://bit.ly/35cD86V

ክፍል (81)፦ ተበሩክ አሕባሾች ዘንድ እና እውነት የነቢዩ ጸጉር አሕባሾች ዘንድ አለን?
🔎http://bit.ly/2PzeE0V

ክፍል (82) ፦ የአሕባሾች በመቃብርና በሼኻቸው ተበሩክ ማድረግ
🔎http://bit.ly/2YFhNk3

ክፍል (83)፦ የአሕባሾች መቃብር ላይ ድምበር ማለፍ
🔎http://bit.ly/38sEZGL

ክፍል (84)፦ መቃብር ላይ መገምባት፣ለተበሩክ ብሎም ቀብርን መንካት በተመለከተ የዑለሞች አቋም ምን ይመስላል?
🔎http://bit.ly/2RHMnI9

ክፍል (85)፦ አሕባሾች ማንን ነው የሚከተሉት?
🔎http://bit.ly/2LGWqcM

ክፍል (86) ፦ አሕባሾች ኢብኑ ተይሚያን ለምን ይጠላሉ?
🔎http://bit.ly/2RCZr1E

ክፍል (87) ፦ ዐብደላህ አልሀረሪ የኢብኑ ተይሚያህ ታሪክ ላይ የፈጸማቸው ስህተቶች
🔎http://bit.ly/2qInilv

ክፍል (88) ፦ በኢብኑ ተይሚያህ ዘመን የነበሩ ዑለሞች ስለሳቸው ምን አሉ? ዐብደላህ አልሀረሪስ?!
🔎http://bit.ly/34d80mv

ክፍል (89)፦ እውነት ኢብኑ ተይሚየህ "አላህ አርሹ ላይ ተቀምጧል" ብለዋልን?!
🔎http://bit.ly/36sG8fo

ክፍል (90)፦ አሕባሾች ለምን በሸይኽ ሙሐመድ አብዱል-ወሃብ ላይ ይቀጥፋሉ?!
🔎http://bit.ly/346WxVq

ክፍል (91) ፦እውነት የሼኽ ሙሐመድ አብዱል-ወሃብ ወንድም የሳቸው ተቃዋሚ ነበረን?
🔎http://bit.ly/2RHChqY

ክፍል (92) ፦ ስለ ሸይኽ ሙሐመድ አብዱል-ወሃብ በዘመኑ የነበሩ ሊቃውንት ምን አሉ?
🔎http://bit.ly/2E6GlZL

ክፍል (93) ፦የአሕባሾች ቅጥፈት
🔎http://bit.ly/2RIU698

ክፍል (94) ፦የአሕባሾች ቅጥፈትና ግፍ
🔎http://bit.ly/2LM20uB

ክፍል (95) ፦አሕባሾች ወሃቢያ የሚሏቸው ሰዎች ላይ የሚዋሹበት ምክንያት ምንድነው?
🔎http://bit.ly/2rstxub

ክፍል (96)፦ ሽይኹል- ኢስላም ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ ማን ናቸው?
🔎http://bit.ly/36wpmfL

ክፍል (97)፦ የሽይኹል- ኢስላም ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ እምነት (ዐቂዳ) ምን ይመስላል?
🔎http://bit.ly/2PCIK3E

ክፍል(98) ፦ አሕባሾችን በተመለከተ የፈትዋና ኢስላማዊ ጥናቶች ቋሚ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫና ማብራሪያው
🔎http://bit.ly/2PcXtUb

ክፍል (99) ፦ አሕባሾች ለቀደምት የዲን ዑለማዎች ያላቸው አመለካከት
🔎http://bit.ly/35ejJCq

ክፍል (100)፦ አሕባሾች ለዘመናችን ታላላቅ ዑለማዎች ያላቸው አመለካከት
🔎http://bit.ly/2qJrcKX

ክፍል (101)፦ ዑለማዎችን ማጣጣል በማን ተጀመረ? ጉዳቱስ ምን ይመስላል?
🔎http://bit.ly/34botHF

ክፍል (102)፦ አሕባሾች ያመጡት የእምነት/የዐቂዳ መዘዝ
🔎http://bit.ly/34dzR5O

ክፍል (103)፦አሕባሾችና ኡማውን መከፋፈል
🔎 http://bit.ly/36rqtxe

ክፍል (104)፦የአሕባሾች ረብሻ በዓለም ዙሪያ
🔎 http://bit.ly/2LK98Y6

ክፍል (105) ፦ የተሳሳቱና ችግሮችን ያስከተሉ የአሕባሾች ፈትዋና የፊቅህ ነጥቦች
🔎http://bit.ly/2YJOTzd

ክፍል (106)፦ የተሳሳቱ ገንዘብና ኸምርን የሚመለከቱ የአሕባሾች ፈታዋ
🔎http://bit.ly/2YFrT4r

ክፍል (107) :-ከሴቶችና ከአለባበሳቸው ጋር የተያያዙ የተሳሳቱ የአሕባሾች ፈታዋ
🔎http://bit.ly/2WkQv17

ክፍል (108) ፦አሕባሾች የዑለማዎች ቅርስ ላይ ያስከተሏቸው መዘዞች
🔎http://bit.ly/2p69e4m

ክፍል (109) ፦ አሕባሾች ደዕዋ ላይ ያስከተሉት መዘዝ
🔎http://bit.ly/33Vs2Cw

ክፍል (110)፦ (የመጨረሻ ክፍል) አሕባሽ ሲጨመቅ
🔎http://bit.ly/2ሊR8lUTQ

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address


Addis Ababa