31/05/2021
Being wise in your business life it's essential. Learn from the experiences of other big entrepreneurs.
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mube Tech, Computer training school, Addis Ababa.
At mubeatech, we offer high quality software products, Enterprize standard software project consultancy and Computer Network configuration and installation service.
31/05/2021
Being wise in your business life it's essential. Learn from the experiences of other big entrepreneurs.
29/05/2021
22/12/2020
This is Elon musk👇. What do we learn from
11/08/2020
እስካሁን የታወቁት የኮቪድ 19 ምልክቶች ምንድን ናቸው?
ብዙዎቹ የአለም አቀፍ የጤና ኤክስፐርቶች የኮሮናቫይረስ ከተነሳበት የመጀመሪያ ወራት አንስቶ ቫይረሱ በሰዎች ላይ የሚኖረውን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የበሽታው ምልክቶች በየጊዜው ሊቀያየሩ እንደሚችሉ ሲገልፁ ነበር፡፡ የአለም አቀፍ የጤና ድርጀት ወረርሽኙ በተከሰተበት የመጀመሪያ ወራት ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በመጀመሪያዎቹ አጭር ቀናት የደረቅ ሳል እና ትኩሳት ምልክቶች እንደሚያሳዩ ሲገልፅ የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ በበሽታው ዙሪያ እየታወቁ የመጡ ጉዳዮችና የሚወጡ ጥናቶች እንዳሳዩት ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶች እንደሚኖሩ እና ስለቫይረሱ ባህሪ ብዙ የማይታወቁ ጉዳዮች መኖራቸውን ነው፡፡
የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል እንዲሁ በይፋዊ ድረ-ገፁ በሚያወጣቸው የጤና መመሪዎች በኮቪድ 19 ዙሪያ ቀድመው ከሚታወቁት የትኩሳት፣ ደረቅ ሳል እና የትንፋሽ መቆራራጥ ምልክቶች በተጨማሪ ሌሎች ተያያዥ የበሽታው ምልከቶች በስፋት ሊኖሩ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ ሲገልፅ ቆይቷል፡፡ ተቋሙ በመመሪያው ይፋ ሲያደርጋቸው ከቆዩት ከእነዚህ የኮቪድ 19 ተያያዥ ምልክቶች መካከል አንዳንዶቹ ቀድመው በተለያዩ የጤና ኤክስፐርቶች ሲጠቆሙ የነበሩ ቢኆንም ብዙዎቹ ግን በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ ምልክቶች ናቸው፡፡
አሁን ላይ ብዙዎቹ የጤና ኤክስፐርቶች እና ባለስልጣነት እንደሚጠቁሙት በኮቪድ 19 ዙሪያ ቀድመው ከሚታወቁት የትኩሳት፣ ደረቅ ሳል እና የትንፋሽ መቆራራጥ ምልክቶች በተጨማሪ ሰዎች ሊያጤኗቸው የሚገቡ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ከእነዚህ የህመም ምልክቶች መካከል
* ከፍተኛ የድካም ስሜት (Fatigue)
* የጡንቻ ወይም የአካል ህመም (Muscle or body aches)
* የጉሮሮ ህመም (Sore throat)
* የአፍንጫ መታፈን (congested nose)
* ከአፍንጫ የሚወጣ ፍሳሽ መብዛት (runny nose)
* ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ (Nausea or vomiting)
* ራስ ምታት
* ከቅዝቃዜ ጋር የተያያዘ ተደጋጋሚ የሰውነት ማንቀጥቀጥ፣
* ተቅማጥ እና ብርድ ዋናዎቹ ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪም ሽታንና ጣዕም የመለየት ችግርም በመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ ሊታዩ የሚችሉ የበሽታው ቀላል ምልክቶች እንደሆኑ ይገለፃል፡፡
እነዚህ ምልክቶች በሁሉም ሰው ላይ የመታየት እድላቸው ሙሉ ለሙሉ የተረጋገጠ ባይሆንም ከበሽታው ቀላል ምልክቶች መካከል በዋናነት የሚመደቡ በመሆናቸው እና በተለያየ መልኩ ሰዎች ላይ የመታየት እድል ስለሚኖራቸው በጥንቃቄ ማየቱ አስፈላጊ ነው፡፡
የኮሮናቫይረስ አዲስ ወረርሽኝ ከመሆኑ እንፃር እና በበሽታው ላይ የሚደረጉ ተጨማሪ ጥናቶች ገና በሂደት ላይ በመሆናቸው እነዚህ የተጠቀሱት ተያያዥ ምልክቶች አካታች ወይም (inclusive) ናቸው ማለት ባይቻልም እንደሰዎቹ የእድሜ ሁኔታ እና ሌሎች መመዘኛዎች ተመስረቶ ቫይረሱ በያዘው ሰው ላይ አብዛኛውን ጊዜ ከ5 እስከ 6 ቀናት አለፍ ካለ ደግሞ በቀጣዮቹ 14 ቀናት የመታየት እድል አላቸው፡፡ ይህ ሁኔታ በተለይም ከወጣቶች እና ታደጊዎች ጋር በተያያዘ አብዛኞቹ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቀድመው ሲጠቀሱ የነበሩ የህመም ስሜቶች ሳይሰማቸው እና ምልክቶች ሳይታይባቸው ቀናትን ሊያሰቆጥሩ በመቻላቸው ሁኔታውን ከዚህ ጉዳዩ ጋር ይበልጥ ተያያዥ እንደሚያደርገው የጤና ባለሙያዎች እምነት ነው፡፡
ይህ በተለይም አብዛኞቹ የተጠቀሱት የበሽታው ምልክቶች ቀላል ከሚባሉት መካከል የሚመደቡ በመሆናቸው በዙሪያችን ካሉ የጤና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር መወሰድ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን ለመውሰድ እንድንችል እና አደጋውንም በቀላሉ ለመከላከል እንዲያስችለን ትልቅ በር የሚከፍት ነው፡፡ ምናልባት በዚህ ሁኔታ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባን እና ሌሎች አፋጣኝ እርምጃዎች መውሰድ የሚያስፈልገን በአተነፋፋስ ላይ ችግር ካለ፣ በደረት አካባቢ ፅኑ የሚባል ህመምና ግፊት ካለ፣ በከንፈርና ፊት ላይ የቀለም ለውጥ ካስተዋልን እንዲሁም ከመኝታ ለመነሳት ስንቸግር ወይም ግራ የመጋባት ስሜት ሲኖረን በአቅራቢያ ላሉ የጤና ተቋማት በማሳወቅ አፋጣኝ የህክምና እርዳታዎችን ማግኘት ይገባናል፡፡
ምንጭ፡ WHO እና CDC guidelines
Via Technology and Innovation Institute, Ethiopia
02/05/2020
Support your loved ones, during -19 pandemic
02/05/2020
Ways to cope with stress