22/08/2026
ያልሞከርነው አዲሱ መንገድ
ሀገራዊ ምክክሩ በስኬት በመጠናቀቁ የተሰማኝን ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ:: ሀገራችን ኢትዮጵያ ያልሞከረችው የነበረው ይህ አዲሱ መንገድ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት እና መሻት በማቀራረብ ደረጃ የተገኘበት ውጤት አመርቂ የሚባል ነው::
እጅግ ተራርቀው የነበሩ ሀሳቦች ተቀራርቦ በመድረኩ ላይ መመካከር በመቻሉ በአብዛኛው የውይይቱ አጀንዳዎች ላይ ጥቅል መግባባት ላይ መደረስ መቻሉ ለሀገራችን አዲስ ተስፋ እና ስኬት ነው::
ይህ የምክክር መድረክ ብዙ የተለፋበት የሁሉንም ኢትዮጵያዊ መሰረታዊ የልዩነት ነጥቦች እና ጥያቄዎች ወደ ምክክር ጠረቤዛ ማምጣት የቻለ ነበር::
ይህ የምክክር መድረክ በጥላቻ እና በመገዳደል እንዲሁም በመራራቅ ሊፈቱ የማይችሉ ጉዳዮችን በመወያየት እና በመቀራረብ መፍታት እንደሚቻል ያሳየ ነው::
ይህ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁ ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ ከስኬትም በላይ ሀገራችንን በአዲስ ጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት እድል የፈጠረ ነው::
በጉባኤው ከስምምነት ላይ የተደረሱባቸው ነጥቦች ወደ ተግባር ወርደው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በብሄር፣ በሀይማኖት እና በዘር አንዱ ከአንዱ ሳይበላለጥ በፍትህ እና በእኩልነት የምንኖርባትን ኢትዮጵያ እውን ትሆን ዘንድ መስራት ያስፈልጋል::
ይህ የምክክር ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ
ኢትዮጵያ አሸንፋለች!