Let us congratulate our beloved brothers Tatek from GCS 🏆
German Church School -GCS Alumuni
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from German Church School -GCS Alumuni, School, Addis Ababa.
the aim of the alumini is continuing our friendship after graduation or living the shool,giving guide for the new students(freshman),healping graduate students how to apply for jobs,life experiance sharing , helping GCS students .... so many reasions
‘’ ሀምሳ ሎሚ ላንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ’’
ሰላም ውድ የGCS ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? በቅድሚያ እስካሁን ላደረጋችሁት፣ ወደፊትም ለምታደርጉት መልካም መረባረብ ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
እንደወትሮ ሁሉ በአንድነት የምንተጋገዝበት አንድ ጉዳይ ገጥሞናል፤ ይኸውም የቀድሞ የጀርመን ት/ቤት ተማሪ የነበረችው እማዋይሽ አሳሳኸኝ የመኖሪያ ቤቷ ፈርሶባት ሁለት ልጆቿን ይዛ በጣም በችግር ላይ ትገኛለች፡፡ከቤቷ መፍረስ ባሻገር ቤቱ የተገዛበትን እዳ ከፍላ ባለመጨረሷ ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት ውስጥ ገብታለች፡፡
እኛ ቤተሰቦቿ የቻልነውን ያህል ብንተጋገዝ የእህታችንን ጭንቀት ከመቀነስ ባሻገር የሁለት ልጆቿን የነገ ተስፋን ልንታደግ ስለምንችል የቻልነውን ያህል እንርዳት ስል በGCS ቤተሰብ ስም እጠይቃለሁ፡፡
እማዋይሽ አሳሳኸኝ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አካውንት ቁጥር 1000218291779
0910296518
06/11/2022
ብርሃን ቲቪ እናመሰግናለን 🙏
የጀርመን ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ ክብረ በዓል አከበረ። BTV | ብርሃን ቴሌቪዥን | German Church School | ብርሃን ቴሌቪዥን የተለያዬ ሀገራዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና ዲፕሎማሲያዊ መረጃዎችን በዜና፣ በትንታኔ፣ በፕሮግራም መልክ ለአድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል፡፡ በብርሃን ቴሌ....
06/11/2022
መምህር ታዬ ልመነው ይባላሉ፡፡ በመምህራን ማሰልጠኛ ገብተው ከውጡ በኃላ ከ40 ዓመት በላይ በመምህርነት ትውልድን በማፍራት ለሀገራቸው ከፍተኛ ውለታ ውለዋል፡፡
ክፈለሀገር ለሶስት ዓመት ከሰሩ በኃላ ጃል ሜዳ (6 ኪሎ) በሚገኘው በጀርመን ቤተክርሲቲያን ትምህርት ቤት ለረጅም ጊዜ ማለትም ከ35 ዓመት በላይ አስተምረዋል፡፡ በ2015 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ጡረታ ወተዋል፡፡
ቢሆንም ግን አሁንም ትምህርት ቤት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ይገኛሉ፡፡ ምክንያቱም ከልጆች ጋር መዋል እድሜን ያድሳል ብለው ሲለሚያምኑ፡፡
> ብለው በድፍረት ይናገራሉ፡፡ መምህርነት ለእሳቸው የተሰጡበት የተፈጠሩበት ሙያ ነው፡፡ > ብለውም ይመሰክሩለታል፡፡
የህግ ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ ተመርቀውማል፡፡ በቢዝነስ ትምህርትም ተመርቀዋል፡፡ ግን ከመምህርነት በላይ ለእሳቸው ምንም ስራ የለም፡፡ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ እንዲሁም በመንግስት ዓይን ውስጥም ገብተው ስልጣን የማግኘትም እድል ተፈጥሮ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በዚሁ ሙያ እንዳሉ ጡረታቸውን አስከብረዋል፡፡
ከልምዳቸው በመነሳት ያስተማሩበትን ጊዜ በሁለት ይከፍሉታል፡፡
በጉርምስና ጊዜ ነገሮችን ማለፍ አትፈልግም፡፡ ፈጣን መልስ ለመስጠት ትሞክራልህ ፡፡ ያኔ ነገር ሊበላሽ ይችላል፡፡ ሁለተኛው ከጉርምስና መልስ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሁሉን ነገር በሰከነ መንፈስ የምታይበት የስራ ዘምን ነው፡፡ ብዙ ነገር ሊያናድድህ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ በትግስት ታልፈዋለህ፡፡
> ብለውም ይጠይቃሉ፡፡ > ሲሉም ይሞግታሉ፡፡
መምህርነት ስለሚወዱት ዘመናቸውን በመምህርነት ጨረሱት ፡፡ በዚህ ሙያ ዶክተሮችን ፣ ኢንጂነሮችን ፣ መምህራንን ፣ የህግ ሙያዎች ... ወዘተ አፍርተውበታል፡፡ የሰው ሃብታም ነኝ ብለው ይናግራሉ፡፡ ይኮራሉ፡፡
መምህርነት የሙያዎች ሁሉ አባት ፡፡
05/11/2022
እንኩዋን ለGCS 50 ኛ አመት በአል አደረሳችሁ !
በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው የቀድሞ ትምህርት ቤታችን 50ኛ ዓመት ክብረ በዐል #2 ቀን ብቻ ቀረው፡፡
ኹላችሁም የቀድሞ የGCS ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ (ጥቅምት 26) ከ 7:30 ጀምሮ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኀል፡፡ የምትችሉ ደግሞ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እንድትገኙና በጠዋቱም ፕሮግራም እንድትሳተፉ ተጋብዛችኀል፡፡
🎊🎉🎊🎉🎊🎉🎊🎉
Save the date !
23/05/2021
ትምህርት ቤታችን የsolar energy ተጠቃሚ ሆነ እኛም በእለቱ በመገኘች አስመርቀናል !
ትምህርት ቤታችን የsolar energy ተጠቃሚ ሆነ እኛም በእለቱ በመገኘች አስመርቀናል !
06/01/2020
መልካም የልደት በዓል ይሁንልን አልሚንና አበባን ከመምህር አበባ ገፅ የወሰድኩት ፎቶ ነው ለመምህሮቻችሁ መልካም ምኞት መግለጥ ይቻላል !
ሰኔ 28 የወላጆች ቀን ሊከበር ነው በጀርመን ት/ቤት
የተከበራችሁ የቀድሞ GCS ተማሪዎች ባላችሁበት እንደተለመደው የአመቱ የትምህርት መዝጊያ ሰኔ 28 ስለሆነ ሁላችሁም ትምህርት ቤታችሁ በመምጣት ከአስተማሪዎቻችሁ ጋር አክብሩ !
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Website
Address
Addis Ababa
184050