19/09/2025
Begena & kerar for sale
Feel Ethiopia’s Sound
Begena (በገና) – The sacred “Harp of King David.”
10 strings (usually 6 played)
Deep, meditative tones with a calming buzz
Traditionally used for prayer & reflection
Krar / Kerar (ክራር) – Ethiopia’s beloved lyre.
5–6 strings, tuned to a pentatonic scale
Bright, rhythmic, and expressive
Perfect for love songs, storytelling & celebration
🎼 Both are handmade with traditional materials, carrying Ethiopia’s rich spiritual and musical heritage.
📍 Visit us in person: [Lideta Fizak Building & Bisrategebriel in front of Laphto Mall]
🌍 Shop online: ermiasbegena.com
26/06/2025
ኤማን የበገና ማሰልጠኛ እና ማምረቻ ተቋም ከኒውማ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር የበገና ትምህርት እና የበገና ሕክምና (ቴራፒ) ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
ሰኔ 16/2017 ዓ.ም
የመግባቢያ ስምምነቱን የኤማን በገና ማሰልጠኛ እና ማምረቻ ተቋም ባለቤት እና ሥራአስኪያጅ መ/ር ኤርሚያስ ኃይላይ እና የኒውማ ኢትዮጵያ በጎ አድርጎት ድርጅት መስራች እና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዘክርስቶስ ጸጋዬ ተፈራርመዋል።
የስምምነቱ ዓላማ ለኒውማ ኢትዮጵያ በጎ አድርጎት ድርጅት ሰራተኞች እና ሕሙማን የበገና ትምህረት እና የበገና ሕክምና (ቴራፒ) አገልግሎት ለመስጠት እና የጋራ ግንኙነትንና መግባባትን ማዳበርና አብሮ ለመስራት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
#በገና #ኤርምያስበገና
ethiopia.rehab_center
04/06/2025
ኑ አዲሱን የኤማን በገና ቁጥር 2 ሱቅ መከፈቱን አብረን እንመርቅ
ሰዓት ከጠዋቱ 4:00 እሰከ
ማታ 2:30
ቀን ከግንቦት 28/2017
እሰከ ግንቦት 30/2017
ከአንድ ወዳጅዎ ጋር በመሆን እንዲገኙልን
ግብዣችን ነው!
ቦታ:ብሥራተ ገብርኤል ከላፍቶ ሞል ፊት ለፊት ሁለተኛ ፎቅ
ኤማን በገና
በገናን ከነ ግርማው
ስልክ ቁጥር 0911525282
20/05/2025
ኤማን የበገና ማሰልጠኛ እና ማምረቻ ተቋም ወ/ሪት አክሊል መኮንን አምባሳደር አድርጎ ሾመ
ኤማን በገና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ ዓመት የአርክቴክታል ኢንጂነሪንግ ተማሪ እና ሞዴል የሆነችውን ወ/ አክሊል መኮንንን በዛሬው ዕለት የክብር አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
ወ/ አክሊል መኮንን የኤማን በገና የክብር አምባሳደር በመሆን መንፈሳዊ እና አዕምሯዊ ጠቀሜታው ልዩ የሆነውን የበገና እና የመንፈሳዊ ዜማ መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማሰልጠኛ ተቋም ለሀገራችን ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ በዛሬው ዕለት በክብር አምባሳደር ሆናለች።
የኤማን በገና መስራችና ባለቤት መ/ር ኤርሚያስ ኃይላይ በዕለቱ እንደገለጹት ኤማን በገና የተለያዩ በገናዎችን እና የዜማ መሳሪያዎችን ማምረቻ እና ማስለጠኛ ተቋሙ ላለፉት አራት አመታት በአካል እና በኦንላይን የተለያዩ የዜማ መሰሪያዎችን ሲያሰለጥን መቆየቱን እና በቅርቡ ብሥራተ ገብርኤል አካባቢ ቁጥር ሁለት የንዋያተ ቅድሳት መሻጫ ሱቅ መክፈታቸውን ገልጸዋል።
#ኤርምያስበገና #በገነኞች #በገና
13/05/2025
ተመስገን
ከብዙ ልፋት በኋላ
የቤተክርቲያናችንን ንዋየተ ቅድሳት እና የዜማ መሳሪያዎች የምታገኙበትን ቁጥር ፪ የኤማን ንዋየተ ቅድሳት መሸጫ ሱቃችንን በብሥራተ ገብርኤል ከላፍቶ ሞል ፊት ለፊት ከፍተናል !
ከግንቦት 28—30/2017
ለምርቃቱ እንገናኝ🙏
📸
#ኤርምያስበገና #በገና
07/08/2024
👇🏾👇🏾👇🏾
https://yt.psee.ly/6ahfup
🔊🔊🔊+++በገና+++🔊🔊🔊
"በገና" የበገና ቀጥተኛ ትርጉሙ መዝሙር ሲሆን.
በገና፡- በገነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ማለትም ደረደረ መታ፡ነዘረ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በገና ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር... ማለት ነው።መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሠረት በማድረግ ይተረጎማል፡፡ ለምሳሌ፦
"አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግናለሁ" መዝ.42/43:4
"ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት" መዝ.48:5
"እግዚኣብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት አሥር አውታር ባለው በበገና ዘምሩለት" መዝ.32/33:2
በገነኛው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ በገናን ሲተረጉም መዝሙር፣ምስጋና... በማለት ሲገልጽ እናገኘዋለንና።
በገና የሚያገለግለው ለመንፈሳዊ ትሩፋት ማለትም ለምስጋናና ለልመና ብቻ ነው፡፡በመሆኑም ተመርጦ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ይውላል።
ከዚህ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ ለማኅበራዊ እሴት፣ ለሃገር ክብር፣ ለሉዓላዊነት...በገና ይደረደራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማስረጃችን በአፄቴዎድሮስ ጊዜ የተደረደረውና እስከ አሁን ድረስ የበገና መማርያ የሆነው የበገና አገልግሎት ነው።ከዚህ ውጭ በገና ለዓለማዊ ፍላጐት ማስፈጸሚያ ማለትም፡- ለዳንስና ለዳንኪራ ለዘፈንና ለጭፈራ ለዝናና ለጉራ ለቀልድና ለፉከራ... ወዘተ ፈጽሞ አገልግሎት አይሰጥም፡፡
የበገና ዜማ ልብን የሚነካ፤ ከፈጣሪ ጋር ለመገናኘት እራስንም ለማግኘት ጥቅም ላይ የሚዉል ምስጋና ማቅረብያ የዜማ መሳርያ ነዉ። የሰዉን ልጅ ስሜት የመግዛት ከፍተኛ ሃይል እንዳለዉ የሚነገርለት የበገና ድርድር በተለይ በጾም ወራት በብዛት
ይደመጣል።በብዛት ተባለ እንጂ ዓመት እስከ ዓመት የሚመሰገንበት ነው።
በገና በገዳማዉያንም ዘንድ የተወደደና የተከበረ ሲሆን። ግን ኋላ ኋላ የመጥፋት አዝማምያ ገጥሞት እንደነበርና አሁን ደግሞ ዳግም ለትንሳኤ በቅቶአል በገና። «በአገራችን አጼ ቴዎድሮስ በገና በመደርደራቸዉም ይታወቃሉ፤ዕቴጌ ጣይቱ እንዲሁ በገና ደርዳሪ ናቸው» በጾም ወቅትም ወደራስ የመመለሻም ግዜ ስለሆነ በገና በሰፊው ይደመጣል።
በበገና
እግዚአብሔር፦ ይመሰገንበታል፣ ይቀደስበታል፣ ይለመንበታል... "
ሕሙማን፦ ይፍወሱበታል፡፡
ሕዙናን፡- ይጽናኑበታል፡፡
አማኞች፡- ይመከሩበታል፡፡
የሀገር ክብር ይገለጽበታል።
የዚህ ታሪካዊና ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጣዕም ለሥርዓተ አምልኮ፣ ለልመናና ለምስጋና ተጠቅመን በሕይወታችን በንስሐ መርተን ፍጻሜአችን ያማረ የተስተካከለ እንዲሆንልን አምላከ ዳዊት እግዚአብሔር ይርዳን።
15/01/2024
በገና አስተሳሰር
የበገና አስተሳሰር በገና ትምህርት ክፍል 13 Begena lesson part 13
ልበ_አምላክ_ቅዱስ_ዳዊት 🤲 ፦ በገናን እየደረደረና መዝሙር እየዘመረ ድውይን ህሙምን መፈወስና የመንፈስን ጭንቀት ማስወገድ።በዚህ በተሰጠው ሀብተ ፈውስ በገና በመምታትና ....
24/12/2023
የvocal ዋና ዋና ጥቅሞች
1.ድምፅን ለመግራት
3.major ለማወቅ
4.ዜማን እና ቅኝቶችን በደንብ ለይቶ ለማወቅ
5.ለትንፋሽ አወጣጥ እና ሌሎችም መሰረታዊ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን በይበልጥ ደግሞ በገና ክራር መሰንቆ ዋሽንት የመሳሰሉት መሳሪያዎችን ለምትለማመዱ ተማሪዎች እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው
የቮካል ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን
08/12/2023
ከኀዘን ለመጽናናት
👉በገና በተለያየ ምክንያት ከሚደርስ ኀዘን ለመጽናናት ወይንም ለማጽናናት አገልግሎት ላይ ይውላል። ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ ከተጠቀሰበት የዩባል ልጆች ዓላማ ጋር የሚገናኝ ነው። የዩባል ልጆች ዓላማ በዘራቸው ከሆነው የእርስ በርስ መገዳደል ታሪክ ኀዘን መጽናናት ነው።
✅በዚህም በገና ቃለ ማኅዘኒ ተብሏል።
•••
⚜ይሄው ፈለግ በመዝሙረ ዳዊት እንደምንረዳው በአሳዛኝ ወቅቶች ሁሉ የበገና አገልግሎት የማይቋረጥ መሆኑን ነው።በኢትዮጵያውያን ዘንድም እንዲሁ በተለይ በጾምና በጸሎት፣ በጽሞና፣ በንስሐ እና ሰዎች በሞት በሚለዩበትም ጊዜ በገና ለመጽናናት አገልግሎት ሲውል ይታያል።
🔰ትንቢት ለመናገር
👉ቅዱስ ዳዊት የተናገራቸው ቃለ ትንቢቶች በሙሉ በበገና እየደረደረ ነው፡፡
📖"ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስሱ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል"
🔰ከመናፍስት ሥቃይ ለመዳን
📖"እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፡፡ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር" (፩ኛሳሙ.፲፮፡፳፫) እንዲል፡፡
🔰የሀገር ሉዓላዊነትን ለመግለጽ
👉በገና የሃገር ሉዓላዊነት የሚያወሱ መዝሙሮችን ለመዘመር ይረዳል። "ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ"... የሚለው መዝሙር ለዚህ አገልግሎቱ ተጠቃሽ መዝሙር ነው።
🔰ነፍስን ያለ ጣር ከሥጋ ለመለየት
👉በገና ጻረ ሞት ወይም ስቃይ ሳይኖር ነፍስን ከስጋ የመለየት ሃብት እንዳለው ሐምሌ የሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር ያስረዳል።
•••
ስለ አባ ኪሮስ የተጻፈና ምእመናን ስለ እመቤታችን መዝሙር በሚዘምሩበት ወቅት እግዚአብሔር እልፍ አእላፍ መላእክት፣ነቢያትን ሐዋርያትን እንጦንስና መቃርስን ይዞ እንደ ወረደ ያን ጊዜም ቅዱስ ዳዊት በአካለ ነፍስ አብሮ እንደተገኘ ያስረዳሉ።
•••
ቅዱስ ዳዊት ጻድቁ አባታችን “በማንኛው አውታር፣ በማንኛው ዜማ፣ በማንኛውስ ወገን በመጀመሪያው ነውን? በሁለተኛ ነውን? ወይስ በሶስተኛ ልዘምርልህ?” ባላቸው ጊዜ “የዐሥሩን አውታር በየወገናቸው ዜማቸውን ልሰማ እወዳለሁ” አሉት፡፡ ያን ጊዜም ዳዊት በገናውን አዘጋጅቶ እየደረደረ “ፈጽመን ደስ እንሰኝባት ዘንድ አግዚአብሔር የሠራት ቀን ናት እግዚአብሔርን በመፍራት በሕጉ የሚኖሩ ብጹዓን ናቸው” እያለ ዘመረ፡፡ ዳግመኛም “ጎረመስኩ ነገር ግን የሚጣል ጻድቅ አላየሁም” ብሎ ሲጮህ የአባ ኪሮስ ነፍስ ከሥጋ ተለየች ይላል። ዳግመኛ የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው እያለ በልብሱ ዘርፍ እንኳ አውታር እየመታ ይደረድር ነበረ፡፡"(ገድለ አቡነ ኪሮስ)
•••
በተመሳሳይ ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በበገና ጣዕመ ዝማሬ ነፍሷ ከሥጋዋ በሚለይበት ወቅት ጻእረ ሞት ወይም ያያት ስቃይ ሳይኖራት በበገና ጣዕመ ዝማሬ አማካኝነት ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየ”።
"ዳዊት በበገና ዕዝራ በመሰንቆ እያጫወቷት፣
ሳታውቀው አለፈች ያን መልአከ ሞት።"
የሚለው በክብረ በዓል የሚዘመረው መዝሙር እውነታውን ያስረዳናል። ከዚህ በተጨማሪም፣ በብዙዎቹ ቅዱሳን እረፍት ጊዜ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ለመቀበል ሲመጣ ቅዱስ ዳዊትም እንደሚገኝ በርካታ ገድላት እና ድርሳናት ይናገራሉ።
#በገና
07/12/2023
ማስተማሪያ ክፍሎቻችን
ለመመዝገብ 0946411882
0777144114