Biniyam asrat getachew

Biniyam asrat getachew

Share

personal blogger ዶ/ር ቢኒያም አስራት

06/05/2022

#እድሜያቸው ከ 1-2 አመት ያሉ #ህፃናትን ምን አይነት ምግብ እንመግባቸው❓️ በቀን ስንት ጊዜ❓️
💖🔹🔹🔹🔹💖🔹🔹🔹🔹💖🔹🔹🔹🔹

👉 ህፃናት አንድ አመት ከሞላቸው በኋላ ዕድገታቸው ቀስ ብሎ ስለሚሄድ የምግብ ፍላጎታቸው በመጠኑም ቢሆን ሊቀንስ ይቺላል ይሄ ተፈጥሯዊ ነገር ነው::

👉 ሆኖም ግን በተቻለ መጠን የተለያዩ ጤናማ እና የተመጣጠኑ ምግቦችን እንዲመገቡ ማበረታታት እና አዳዲስ ጣእሞችን እንዲሞክሩ ማድረግ ያስፈልጋል::

👉 አንዳንዴ በዝህ እድሜ ያሉ ህፃናት ከራሳቸው ምግብ ይልቅ የቤተሰቡ ምግብ ሊመርጡ ይቺላሉ :: ይሄም በሳይንሱ የሚመከር የሚጠበቅ ስለሆነ የቤተሰቡን ምግብ ቀስ በቀስ ማስለመድ ተገቢ እና ተፈጥሯዊ ነው❗️

⚠️ ሆኖም የቤተሰቡን ምግብ ብቻ መስጠት ማግኘት ያለባቸውን ንጥር ነገሮች ሊያጡ ስለሚችሉ የራሳቸውን ምግቦች እና የቤተሰቡ ምግብ እያፈራረቁ መሰጠት ይቺላል::

🛑 #በቀን ስንት ጊዜ ነው መብላት ያለባቸው❓️

👉 ከ 1-2 አመት ያሉ ህፃናት በቀን 3 ቋሚ ምግቦች እና 2 እንደ መክሰስ የሚሆኑ ምግቦችን ማግኘት አለባቸው

👉 እነዝህ ከላይ ከተጠቀሱ ምግቦች በተጨማሪ የእናት ጡት ወተት እስከ 2 አመት ቢቀጥሉ የበሽታ መከላከል አቅማቸው ጠንካራ ይሆናል::

🛑 #ጥያቄ: #መጀመርያ ጡት ነው ማጥባት ያለብኝ ወይስ ምግቡን ልስጠው❓️

🛑 #መልሱ : #መጀመርያ ምግቡን በ አግባቡ ይመግቡ ቀጥሎ ደሞ ጡት ያጥቡ ወይም ወተት ይስጡ ❗️

👉 ይሄንን ማድረግ ካልተቻለ ግን የጣሳ(ፎርሙላ)ወይም የላም ወተት(የደም ማነስ ከሌለባቸው እና የጣሳ ወተት ማግኘት ካልተቻለ) መስጠት ይቻላል::

🛑 #ምን #አይነት #ምግቦች እንመግባቸው❓️

👉 በዝህ የእድሜ ክልል ያሉ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አለባቸው::

1. ከ ኃይል ሰጪ ምግቦች(carbohydrate)
🔺 ከተለያዩ የእህል ዘሮች የሚዘጋጀውን ምጥን በገንፎ መልክ ማዘጋጀት እና መመገብ
🔺 ገንፎውን ላይ እንቁላል ወተት እና ቅቤ መጨመር
🔺 የተፈጩ ድንች ካሮት ቀይ ስር ብሮኮሊ መመገብ
🔺 ቤት ዉስጥ የሚዘጋጁ እና ስኳር ያልበዛበት ጁስ
🔺 ለስላሳ መጠጦችን ጣፋጭ ምግቦች እና የታሸጉ ጁሶችን በፍፁም አያስለምዱ❗️

2. ከ ሰውነት ገንቢ(Protein)

🔹 የተቀቀለ እንቁላል
🔹 በደንብ የሰለ ስጋ (የበግ የበሬ የአሳ እና የዶሮ)
🔹 ወተት (የእናት> የ ጣሳ> የላም )
🔹 አተር ሽንበራ ባቄላ ቦሎቄ በተለያየ አዘገጃጀት ይመግቡ

⚠️ #አስተውሉ⚠️

🛑 ህፃናት የጣሳም ይሁን የላም ወተት በቀን ከ 500 ሲሲ (ከ 3 ኩባያ)በላይ መውሰድ የለባቸውም‼️ ምክንያቱም የደም ማነስ ድርቀት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሊያመጡ ይቺላሉ‼️

3. ቅባት /ዘይት
🔸 ቅቤ እና ዘይት ከተለያዩ ምግቦች ዉስጥ መጨመር
🔸 ጤናማ ያልሆኑ ክባቶች (የሚረጉ እና ከእንስሳት ስብ የሚገኙትን ) ያስወግዱ‼️
🔸 ጤናማ ቅባቶችን ከወተት እና ከአቦካዶ ማግኘት ይቻላል

🛑 🛑 #የአሳ #ዘይት መቼ ነው መጀመር ያለብን❓️

👉 የአሳ ዘይት ለአይምሮ እና ለሰውነት እድገት በጣም ጠቃሚ ነው :: ይሄ ማለት ግን ሁሉም ህፃናት የታሸገ እና የሚሸጥውን የአሳ ዘይት ግዴታ መጠቀም አለባቸው ማለት አይደልም ❗️

👉 የአሳውን ዘይት ከ አሳ ስጋ ዉስጥ ማግኘትም ይቻላል❗️ እና ለልጆዎ የአሳን ስጋ ከ 6 ወር ጀምሮ መስጠት ማለማመድ ይመከራል ::

4. ቫይታሚኖች እና ሚንራሎች(ዋና ዋናዎቹ)

✔️ ቫይታሚን ኤ: ከድንች ካሮት ብሮኮሊ ጎመን ወተት
✔️ ቫይታሚን ቢ: ከአትክልቶች ወተት እና
✔️ ቫይታሚን ሲ:ከአረንጉአዴ እና ቢጫ የጓሮ አትክልት ከተለያዩ ፍራፍሬዎች )
✔️ ቫይታሚን ዲ :ከፀሐይ እና እንስሳት ተዋፆዎች
✔️ ፎሌት : ከአቦካዶ ጎመን ምስር እና እንስሳት ተዋፆዎች
✔️ አይረን : እንስሳት ተዋፆዎች በተለይ ቀይ የበሬ ስጋ ጉበት እና ኩላሊት ስጋ

5. ፋይበር(ቃጮነት ያላቸው ምግቦች)

👉 ፋይበር እስከ መጨረሻው የማያደቅ የእፅዋት ክፍል ሲሆን ከትኛዉም አትክልት እና ፍራፍሬ ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን ዋና ጥቅሙ ድርቀትን መከላከል እና የ አንጀት ስራን ማፋጠን ነው::
👉 ካሮት ድንች ጎመን ሙዝ አቦካዶ.... ዉስጥ ይገኛል

🛑 ከ 1-2 አመት አሉ #ህፃናት በአንድ ጊዜ ምን ያህል #ምግብ ነው መመገብ ያለባቸው❓️ እምቢ ሲሉስ ምንድነው የምናረገው❓️

✍️ በዝህ እድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ ህፃናት 70 ሲሲ የሚይዝ ኩባያ ሙሉውን ወይም 3/4ኛውን እንዲወስዱ ይመከራል::
✍️ ይሄ ግን ሁሌ ይሳካል ማለት አይደልም❗️ቀስ ብለው በትዕግስት በጨዋታ ይሞክሩ ጊዜ ይስጡት::
✍️ በፍቅር እንጂ በ ማስገደድ መሆን የለበትም‼️
✍️ የህፃናት የምግብ ፍላጎት ከ ቀን ቀን ሊለያይ ይቺላል እና ብዙ መጨነቅ ተገቢ አይደልም

🛑" ግን #ልጄ #በትክክል የሚበቃውን ያህል እየተመገበ መሆኑን እና አለመሆኑን ግን በምን አውቃለሁ❓️ ጡቴስ ለልጄ በቂ መሆኑን እና አለመሆኑ በምን አውቃለሁ❓️
🛑 መልሱን በነገው ዕለተ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ እናቀርባለን:: ቴሌግራማችንን Join ያርጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔹 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil

🔷 ፌስ ቡክ: fb.me/drfasilpediatrician

✍️ አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም)

👨‍⚕️ ለልጆዎ ማንኛዉም አይነት ሕክምና ለማድረግ ወይም ክትትል ለማድረግ ከፈለጉ በእዝህ ስልክ ቁጥር ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ ::👇👇👇

☎️ +251984650912

👉 ወይም ዶ/ር ፋሲልን ለማማከር ከፈለጉ በ "Wecare ET patient" Application(መተግበሪያ) ከ google play ላይ download አርገው በመጠቀም እና ማማከር ይቺላሉ ::

🔷 መተግበርያውን ለማውረድ ከታች ያለውን link ይጫኑ👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

🛑 ስለ መተግበርያው አጠቃቀም ለመጠየቅ እና ቀጠሮ ለማስያዝ 9394 ደውለው ይጠይቁ::

የ ኩላሊት ጠጠር መንስኤ፣ ምልክቶች እና ህክምና kidney stone |NERI TENA ኔሪ ጤና| 07/09/2021

የኩላሊት ጠጠር
የጤና መረጃዎች እንዲደርስዎ
subscribe to our YouTube channel

የ ኩላሊት ጠጠር መንስኤ፣ ምልክቶች እና ህክምና kidney stone |NERI TENA ኔሪ ጤና| የ ኩላሊት ጠጠር መንስኤ፣ ምልክቶች እና ህክምና kidney stone |NERI TENA ኔሪ ጤና|ሰላም፨ የ ኔሪ ጤና ቲዩብ ቤተሰቦች ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማደርግ በየወቅቱ የሚወጡ የጤና መረጃዎችን ያግኙ.....

10 እስከ ዛሬ ሰምታችሁ ማታውቋቸው በሽታዎች AMAZING MEDICAL CONDITIONS 29/08/2021

የ YouTube ቻናሉን subscribe በማድረግ የጤና መረጃዎችን ያግኙ

10 እስከ ዛሬ ሰምታችሁ ማታውቋቸው በሽታዎች AMAZING MEDICAL CONDITIONS ሰላም፨ የ ኔሪ ጤና ቲዩብ ቤተሰቦች ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማደርግ በየወቅቱ የሚወጡ የጤና መረጃዎችን ያግኙ። ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉት።Hello family! subscribe and share our YOU TUBE channel ...

በሽታ መንስኤ እና ምልክቶቹ |stroke| ኔሪ ጤና NERI TENA TUBE 19/07/2021

Hi friends
This is my new simple educational channel
Please subscribe and share 🙏🙏🙏

በሽታ መንስኤ እና ምልክቶቹ |stroke| ኔሪ ጤና NERI TENA TUBE ሰላም፨ የ ኔሪ ጤና ቲዩብ ቤተሰቦች ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማደርግ በየወቅቱ የሚወጡ የጤና መረጃዎችን ያግኙ። ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉት።Hello family! subscribe and share our YOU TUBE channel

30/04/2021

መልካም ስቅለት

27/11/2020

Coming soon 👌👌👍
Aster Abebe
በዘመኔ አያለሁ !!❤🔊
Can't wait

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa