DemxComputer

DemxComputer

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from DemxComputer, Education, Addis Ababa.

07/02/2024

Microsoft Excel for Beginner (ኤክሴል ለጀማሪዎች)

✅ ወርክቡክ (Workbook) ማዘጋጀት
---------------------------------
🔵 ኤክሴል ወርክቡክን እንደ አንድ መረጃ መያዣ ቋት ወይም እንደ መጽሃፍ ማየት እንችላለን፡፡ ይህ መጽሀፍ በውስጡ ብዙ ገጾች ይኖሩታል፡፡ ገጾቹን በወርክ ሽት ልንመስላቸው እንችላለን፡፡ እያንዳንዱ ወርክ ሽት የተለያየ መረጃን ይይዛል፡፡ ባጠቃላይ የወርክ ሽት ጥቅም በአንድ ቦታ ግን በተለያየ ገጽ የተለያየ መረጃ የምናስቀምጥበት ክፍል ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ገጾች (መረጃዎች) በአንድ ላይ እንደ መጸሀፍ የሚይዝልን ደግሞ ወርክቡክ እንለዋለን፡፡

🟤 ማይክሮሶፍት ኤክሴልን ለመጀመሪያ ግዜ ስንከፍት የተለያዩ እይታዎችን የያዘ አንድ መስኮት ይከፈትልናል። ሁልግዜም አዲስ የኤክሴል ወርክቡክ ለመክፈት Blank Workbook የሚለውን እንጫናለን። ለመጀመሪያ ግዜ በምንፈጥረው ወርክቡክ ውስጥ አንድ ወርክሽት ብቻ ይኖረናል። ይህም ማለት አንድ ገጽ ብቻ ያለው መጽሃፍ ይኖረናል እንደማለት ነው። አንድ ግዜ ወርክቡክ ከከፈትን በኋላ የፈለግነውን ያህል ወርክሽቶችን መጨመር እንችላለን።

✅ሴል (Cell)
========
ሴል ማለት በአንድ ወርክሽት ውስጥ የሚገኝ መረጃ የምናስቀምጥበት አራት መዓዘን ቦታ ነው፡፡ በውስጡም ጽሁፍ ቁጥር ወይም ፎርሙላ ሊቀመጥበት ይችላል፡፡ ይህ ቦታ በቁጥር (Number) እና በፊደል (Letter) ጥምረት የተገኘ ነው፡፡ ቁጥሩ ከተርታ (Row) የሚነሳ ሲሆን ፊደሉ ደግሞ ከቋሚ ረድፍ (Columns) ይነሳል፡፡ እነዚህ ሁለት መስመሮች ሲገናኙ አንድ ሴል ይፈጥራሉ፡፡

ለምሳሌ ፡- የመጀመሪያው ሴል ከላይ በ A ትክክል የተቀመጠ ሲሆን ከጎን ደግሞ በ 1 ትክክል ተቀምቷል፡፡ ስለዚህም ይህ ሴል ስሙ A1 ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ በኤክሴል መጨረሻ ላይ የሚገኘው ሴል ስም XFD1048576 ይሆናል፡፡
✅ ወርክሽት (Worksheet)
===============
ኤክሴል ወርክሽት ማለት በአንድ ስፕሪድሽት ላይ የሚገኙ የብዙ አራት መአዘን ሴሎች ስብስብ ነው፡፡ ይህ ስብስብ በአግድም አምድ (Columns) እና በቋሚ ረድፍ (Row) ድርድር ውጤት ነው፡፡ በዚህ ድርድር ላይ 1,048,576 አምድ (Columns) እና 16,384 ረድፍ (Row) ይገኛል፡፡ በጠቅላለውም 17,179,869,184 ሴሎች በአንድ ገጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ ስፕሪድ ሽት (ወርክሽት) ላይ የሚገኙ ረድፍ (Row) ከአንድ ጀምሮ ወደ ታች እስከ 1,048,576 የሚቆጥር ሲሆን አምድ (Columns) ደግሞ ከ A ጀምሮ ወደ ጎን እስከ XFD ይሄዳል፡፡
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሙሉ ትምህርቱን በሚከተሉት አማራጮች መከታተል እና ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ!

📌 Facebook = DemxComputer
📌 Instagram = Instagram.com/DemxComputer
📌 Tiktok = Tiktok.com/
📌 Telegram = t.me/DemxComputer
📌 Youtube = Youtube.com/

30/09/2023

Excel ከጀማሪ ወደ አስተማሪ በቅርብ ቀን . . .

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa