20/12/2025
Ethiopia Education and Training Tribune
About creating a plat form of all concerned to share and discuss issues related to Ethiopia all levels of education quality,equity, efficiency, and access
The page named tribune because it is a platform (opportunity to speak or express opinions) to bring changes on the nations future, in putting together optimistic ideas for improvement of quality, efficient, equitable and accessible education to citizens at any circumstances and levels. The page will browse and share education related pages posts. And expected form members to do the same. The sky is the limit to cover issues regarding education and training. thank you!
20/12/2025
20/12/2025
20/12/2025
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1325184269647637&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
08/11/2025
በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በማስፈን ለተማሪዎች ውጤትና ሥነ-ምግባር መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገለጸ።
---------------------------- // -----------------------------
(ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም) ትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ አግባብነት ካላቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩን የከፈቱት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል የተዘጋጀው ረቂቅ ደንቡ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በማስፈን ለተማሪዎች ውጤትና ሥነ-ምግባር መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።
የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያውኩ ጉዳዮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ በመምጣታቸው ይህንን ለማስተካከል ረቂቅ ደንቡ መዘጋጀቱን ጠቅሰው ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ ዜጋ ማፍራት የደንቡ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ለተግባራዊነቱ ከሚመለከታቸው ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶና ተናቦ መሥራት እንደሚጠበቅ ሚኒስትር ደኤታዋ አሳስበዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ እቶ ኡመር ኢማም በበኩላቸው ረቂቅ ደንቡን ለማዳበር በርካታ የውይይት መድረኮች ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተካሄዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በየመድረኮቹ የሚነሱ ሀሳቦች በግብዓትነት ተወስደው ከተካተቱበት በኋላ ረቂቅ ደንቡ ሲጽድቅ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ይደረጋልም ነው ያሉት።
የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባለፈው ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ መውጣቱንና ይህም ደንብ አዋጁን ለማስፈጸም እየወጡ ካሉ የህግ ማዕቀፎች መካከል አንዱ መሆኑንም በመድረኩ ተጠቅሷል።
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
Ministry of Education Ethiopia This is FDRE Ministry of Education Official Face Book Page.We are promoting Educational Achievement & Attainment.
02/10/2025
ተጨማሪ መረጃዎች በ2017 ትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና ላይ ተሰጠ፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተፈታኞችን ውጤት የገለጸ ሲሆን ተፈታኞች በተገለጸው ውጤታቸው እና ተያያዥ መረጃዎች ላይ ቅሬታቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ አቅርበዋል፡፡ የቅሬታ አቅራቢዎች ብዛት በከፍተኛ ደረጃ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ የመጠ ሲሆን በ2017 ላይ በየይነ መረብ በተፈተኑ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ የፊዝክስ ውጤት ወደ መቶኛ ያልተቀየረላቸው እንዲሁም ወደ መቶኛ ስቀየር በነጥብ ቤት የነበሩ ቁጥሮች ያልተደመረላቸው ተማሪዎች ተስተካክሎላቸዋል፡፡
በተጨማሪም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ በተወሰነው መሠረት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም በአጠቃላይ 3,350 ተጨማሪ ተማሪዎች ዝቅተኛውን የማለፊያ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡
በዚሁ መሠረት የ2017 ትምህርት ዘመን ላይ 50 ከመቶና በላይ ያመጡ አጠቃላይ ተፈታኞች 52,279 ሆነው የተመዘገቡ ሲሆን በአጠቃላይ በመቶኛ ስገለጽ ወደ 8.9 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በዓመቱ በየትምህርት መስኩ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተፈታኞች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
መስከረም 2018 ዓ/ም
09/09/2025
09/09/2025
https://www.facebook.com/share/p/1CWTnKSCt5/
የተማሪ ጥሪ ማስታወቂያ
********************
ለደባርቅ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች እና ሁለተኛ ዓመት 2ኛ ሴሚስቴር ተማሪዎች በሙሉ!
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ተማሪዎች እና ከጤና ሳይንስ ውጭ ለሆናችሁ ሁለተኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስቴር አጠናቀቃችሁ ለእረፍት የወጣችሁ ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመመዝገቢያ ቀን መስከረም 12-13/2018 ዓ.ም እና በቅጣት ምዝገባ መስከረም 14/2018 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 14/2018 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
መጠኑ 3በ4 የሆነ 3 ጉርድ ፎቶግራፍ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ለወጪ መጋራት ስለሚያስፈልግ እንድታዘጋጁ ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ዘግይቶም ሆነ ቀድሞ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ከላይ ከጠቀስናቸው ውጭ ያላችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች በሙሉ በቅርብ በሌላ የጥሪ ማስታወቂያ እስከምንገልፅ ድረስ በትግስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት!!
08/09/2025
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Addiss Ababa
Addis Ababa
32742