እዚህ ሰፈር Gedeo
GedeoDhugatee miteefat✊👊 jabate
15/05/2026
በዲላ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ምልክት የቀደደው ግለሰብ በ2 ወር የግዳጅ ስራ ቅጣት ተቀጣ
ዲላ፡ግንቦት፣ 7/2018 ዓ.ምበዲላ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ያለበትን ወረቀት በመቅደድ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው አማኑኤል አብርሃም የተባለ ግለሰብ በ2 ወር የግዳጅ ስራ ቅጣት እንዲቀጣ የዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።
ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ገደማ በሴሳ ክፍለ ከተማ አንዲዳ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዳላቻ ቀጠና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ በችሎቱ ተብራርቷል።
የዲላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አማኑኤል አብርሃም የምርጫ ምልክት በመቅደድ የፈጸመው ድርጊት በማስረጃ በመረጋገጡ ጥፋተኛ ነው ብሎታል።
በዚህም መሰረት ግለሰቡ ለ2 ወራት የሚቆይ የግዳጅ ስራ ቅጣት እንዲቀጣ ወስኗል።
ተከሳሹ ቀደም ሲል የቀረበበትን ክስ ሐሰት ነው በማለት የክህደት ቃል ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም የዲላ ከተማ ፖሊስ ከዐቃቤ ሕግ ጋር በመተባበር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አደራጅተው በማቅረባቸው ጥፋተኝነቱ ሊረጋገጥ ችሏል።
እንደ ፍርድ ቤቱ መግለጫ ከሆነ ተከሳሹ ጥፋተኛ የተባለው በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 158 ሥር የተደነገገውን የተከለከለ ተግባር በመጣሱ ነው።
ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ቅጣቱ ተከሳሹን የሚያርምና ሌሎች መሰል ድርጊት ከመፈጸም እንዲቆጠቡ ትምህርት የሚሰጥ መሆን አለበት በማለት የ2 ወር የግዳጅ ስራ ቅጣቱን መወሰኑን አስታውቋል።
ዘገባው፦ተስፋልደት ወርቁ
ምስል፦አቤኔዘር ስዩም
05/05/2026
ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ተገለፀ
እነዚህ ካልተባረሩ የትግራይ ህዝብ ሰላም አይኖረውም ሲሉ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል ::
በትግራይ ክልል ለሦስት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የክልሉ ምክር ቤት በድጋሜ በመሰባሰብ ባካሄደው ጉባኤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡ ተዘግቧል ።
ምክር ቤቱ ወ/ሮ ኪሮስ ሓጎስን አፈ ጉባኤ፣ ወ/ሮ ምህረት በርሄን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ በመሾም ጉባኤውን አጠናቋል።
ሥልጣናቸውን በሰላም ካስረከቡ ችግር አይገጥማቸውም በሚል ከህወሓት በኩል ጫና የበረታባቸው ጀነራል ታደሰ፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከርዮት ጋር በነበራቸው ቆይታ በሰጡት ምላሽ፣ “እኔ የማስረክበው ነገር የለም ማለታቸው ይታወሳል ።
ይህ አጥፊ አካሄድ ተገቢ እንዳልሆነ እየገለጽኩ ነው። የለም በዛ መንገድ እንሄዳለን ካሉ ግን እንደፈለጉ ያድርጉ” ማለታቸው ይታወቃል::
"የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ለትግራይ ህዝብ የተስፋ ብርሃን ፈንጥቆ የነበረ ቢሆንም፣ የህወሓት አመራሮች ግን እንደገና የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ እና የስምረት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ መግለፃቸው ይታወቃል::
ጦርነት መፍትሄ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ ቀጣይ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ውድመት መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል ያሉትን መዘግባችን ይታወቃል::
ጌታቸው ረዳ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ በሰጡት አጭር ምላሽ "የሙሽሪት ጅራት የሚባለው የልጆች ጨዋታ፡ ልጆቹን ለመጨረስ የወሰኑ ደደቦች ዛሬ እየቀለዱ ደገሙት፡ እንሳቅ ወይንስ እናለቅስ?እነዚህ ካልተባረሩ የትግራይ ህዝብ ሰላም አይኖረውም ሲሉ አስቀምጧል ::
04/05/2026
👇👇👇👇
04/05/2026
ዜና ችሎት
የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከሳሽ ዐቃቤ ህግ እና በተከሳሽ በአቶ ጸጋዬ ታደሰ መካከል የነበረዉን የወንጀል ክስ መነሻነት ክስ የመስማት ሂደት ለማካሄድ ለዛሬ ቀን ቀጠሮ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል
ዲላ ሚያዝያ 26/2018 ዓ/ም ጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት
በተከሳሽ በአቶ ጸጋዬ ታደሰ ላይ ዐ,ህግ አቶ ተመስገን ዳንኤልን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉን የሚገልጽ ክስ መመስረቱ ከችሎቱ ለመረዳት ተችሏል
ከሳሽ አቃቤ ህግ እንደ ክስ አመሰራረት ያስረዱልኛል ያላቸዉን የሰዉና የሰነድ ማስረጃ እንዲቀርብ ተደርጓል ፍ/ቤቱም የቀረቡትን አራት የዐ,ህግ ማስረጃዎችን በችሎት ዉስጥ አድምጧል
የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ተከሳሹ እንዲከላከል በማለት የመከላከያ ምስክር ለመስማት ለግንቦት 05/2018 ዓ/ም ቀጠሮ መስጠቱን ከስፍራዉ የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ዘግቧል
በጉዳዩ ዙሪያ ልዩ ትኩረት በመስጠት የወንጀል ፈጻሚዎች ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ መሆኑንና ጉዳዩ የመጨረሻ ዉሳኔን ጭምር በመከታተል ለህዝባችን እናሳዉቃለን ሲሉ
የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ረ/ኢንስፔክተር ዮሐንስ በቀለ ተናግረዋል
በረ/ኢንስፔክተር ሐብታሙ ወንዶ
Miti miti man ከስልጣን የማይነሳ መስሎት ነበር መሰለኝ ሽግሽግ ስደረግ አበት ድንፋታቸው😉😂
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Efirem Alemu, Ashenaf woma, Kaleb Man
27/06/2025
እንደዚህ አይነት ቆሻሻ መንግሥት አይቸ አላውቅም
የዋጋ ግሽበትን ወደ 14 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል - ብሔራዊ ባንክ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በተገባደደው በጀት ዓመት የዋጋ ግሽበትን ወደ 14 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል አሉ።
አቶ ማሞ የብሔራዊ ባንክ የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል።
በዚህ ወቅትም ብሔራዊ ባንክ ባለፉት 11 ወራት የተገበረው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ የዋጋ ግሽበትን መቀነስ አስችሏል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም በጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ባለፉት11 ወራት ለመንግስት ይሰጥ የነበረውን የብድር ምጣኔ ወደ ዜሮ ማውረድ መቻሉን ነው ያስረዱት፡፡
ብሔራዊ ባንክ ውጤት ካስመዘገበባቸው ዘርፎች መካከል የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ÷ በዚህም በትይዩ ገበያና በባንኮች የውጭ ምንዛሪ መካከል የነበረውን ልዩነት ማጥበብ እንደተቻለ ጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም በውጭ ምንዛሪ አስተዳደር አጠቃላይ ገቢን ወደ 32 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ከፍ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡
የሀገር ውስጥ የውጭ ምንዛሪ ክምችትን ማሳደግ፣ ለግል ዘርፎች የሚቀርበውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት መጨመር፣ ዕዳ የመክፈል አቅምን የማሳደግና መሰል ትሩፋቶች መገኘታቸውንም አብራርተዋል፡፡
በሔብሮን ዋልታው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
YouTube (http://www.youtube.com/)
ሰላም guys ብዙ የዞናችን የለብነትና የብልሹ አሰራር መረጃ በውስጥ ደርሶኛል ልልቀቀው ወይ ምን ትላላችሁ 😳
06/02/2025
Darrarinxxa uwwa/የዳራሮ በዓል ስጦታ በዲላ Gift of Darraro in Gedeo zone, Dilla town❤
እዚህ ሰፈር Gedeo
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa