Medical Education

Medical Education

Share

@medicaleducation

Photos from Medical Education's post 07/06/2020

30/09/2012
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት፤ ሞት፤ያገገሙት በሀገር አቀፍ ደረጃና በክልል ደረጃ
ድሬደዋ
ሀረር ክልል
ደቡብ ክልል
ኦሮሚያ ክልል
ትግራይ ክልል

Photos from Medical Education's post 31/05/2020
31/05/2020

23/09/2012
ኮሮና ቫይረስ በሃረሪ ክልል

Photos from Medical Education's post 31/05/2020

23/09/12
Gabaasa COVID19 Oromiyaa
COVID19 መግለጫ በኦሮሚያ ክልል

Photos from Medical Education's post 31/05/2020

Report #82 23/09/12
የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ በኢትዮጵያ
status update on

ዜና እረፍት
በኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሦስት(3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞቱ

31/05/2020

በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ሕሙማንን ለሚያክሙ 1 ሺህ 750 የጤና ባለሞያዎች የሚያገለግሉ ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጅተዋል።
---------------------
በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ሕሙማንን እያገለገሉ ለሚገኙ 1 ሺህ 750 የጤና ባለሙያዎች ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች መዘጋጀታቸውን ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደስ ገልጸዋል።

ኮቪድ-19ን ለመከላከል ለሚሠሩ የጤና ባለሞያዎች እና ሌሎች ሠራተኞች የሚውሉ የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁሶችንም ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የኮቪድ ሕሙማንን የሚያክሙ የጤና ባለሞያዎች ራሳቸውን ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳያደርጉ የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁስ በማቅረብ ረገድ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በሁሉም ክልሎች ጊዜያዊ መኖሪያዎችን ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። የጤና ባለሞያዎች ባልታወቀ ሁኔታ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሚሆኑበት ሁኔታ ቢፈጠር ተለይተው የሚቆዩበት እና በበሽታው ቢያዙ የሚታከሙበት ቦታ መዘጋጀቱንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል። በተለይም በአዲስ አበባ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ተከትሎ ለጤና ባለሞያዎቹ እነዚህ ቦታዎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የጤና ባለሞያዎቹ መቼ እና በምን መልኩ ወደ ለይቶ ማቆያ መግባት እንዳለባቸው የሚያመላክቱ መመሪያዎች ከጤና ባለሞያዎች እና ከዘርፉ ማኅበራት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ለጤና ባለሞያዎች እና ሠራተኞች የሚቀርቡ የኢንፌክሽን ቁሳቁስ እና አልባሳት በግዥ፣ በዕርዳታ እና በማምረት የማሟላት ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ለጤና ባለሞያዎች የሚቀርቡ ደረጃቸውን የጠበቁ 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሕክምና የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች መከፋፈላቸውንም አብራርተዋል። በመጪዎቹ ሳምንታትም በልገሳ እና በግዥ 25 ሚሊዮን የፊት ጭምብሎች ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለሕክምና ባለሞያዎች እንደሚሰራጩም አመልክተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የፊት ጭምብሎች እጥረት ስላለ የጤና ባለሞያዎች ይህን ከግምት በማስገባት በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።

Source Ministry of Health,Ethiopia

30/05/2020

SNNPR

Photos from Medical Education's post 30/05/2020

22/09/2012
Gabaasa COVID19 Oromiyaa

Report of COVID 19 In Oromia region

30/05/2020

አይደናገጡ ግን በእጅጉ ይጠንቀቁ!
ሳል፣ ትኩሳት እንዲሁም ለመተንፈስ መቸገር የኮቪድ-19 ምልክቶች ቢሆኑም አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ ቫይረሱ ሊኖርባቸውና ወደ ሌሎች ሰዎች ቫይረሱን (ኮሮና ቫይረስ) ሊያስተላልፉ ስለሚችሉ ምልክቶች ቢታዩም ባይታሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ከማድረግ አይቆጠቡ።

እራሴን ከቫይረሱ እንዴት ነው መጠበቅ የምችለው ?

¤ እጅዎን ቫይረሱን ሊገድሉ በሚችሉ ሳሙናዎች ይታጠቡ።

¤በሁሉም ቦታ አካላዊ ርቀትዎን ይጠብቁ።

¤በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን ሊነኩ ስለሚችሉ ፤ በእጅዎ ዓይን ፣ አፍ እና አፍንጫዎን ከመነካከት ይቆጠቡ።

¤ወደ የሚያስነጥሱ፣ የሚያስሉ እና ትኩሳት ወዳለባቸው ሰዎች አይጠጉ።

¤ቢያንስ የ2 ሜትር እርቀት ይፍጠሩ።

¤ሲያስሉና ሲያስነጥሱ አፍና አፍንጫዎን ይሸፍኑ ከዚያም እጅዎን ይታጠቡ።

¤ይህን ማድረግዎ በቫይረሱ ተይዘው ከሆነ የማሰራጨት ዕድልዎን ያጠባሉ።

¤አስገዳጅ ጉዳይ ከሌሎት ከቤትዎ አይውጡ። ከቤትዎ የሚወጡበት አስገዳጅ ጉዳዮች ሲኖር

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንዳይዘነጉ።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa