የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያም እና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያም እና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያም እና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት እንኳን ወደ ደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅ/ማርያም እና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራ እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ መጣችሁ!!!

አዲስ ለተመደቡት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ አቀባበል ተደረገላቸው።በመርሐ ግብሩ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ...
14/08/2026

አዲስ ለተመደቡት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ አቀባበል ተደረገላቸው።

በመርሐ ግብሩ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክልት ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ሰላም ዶ/ር አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሐላፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የሀገረ ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት/Addis Ababa Diocese Media Service

11/08/2026

ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን! አገልግሎቱ ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ሼር እና ላይክ ማድረግ እንዳትረሱ! እንዲሁ...

09/08/2026

Enjoy the videos and music that you love, upload original content and share it all with friends, family and the world on YouTube.

09/08/2026

Enjoy the videos and music that you love, upload original content and share it all with friends, family and the world on YouTube.

09/08/2026

ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን! አገልግሎቱ ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ሼር እና ላይክ ማድረግ እንዳትረሱ! እንዲሁ...

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ...
06/08/2026

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ!

የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤
ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡

ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው!

ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤

የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል
ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣

ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣

በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤
የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡

ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤

በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣

እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤

ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤

05/08/2026
የክረምት ልዩ ስልጠና☞  የመክፈቻ ፕሮግራም ሐምሌ  11  ቀን 2018 ዓ·ም☞ ስልጠናው ሐምሌ 18 ይጀመራል በሣምንት 2 ቀን☎ ለመመዝገብ  +251900481488                  ...
18/07/2026

የክረምት ልዩ ስልጠና
☞ የመክፈቻ ፕሮግራም ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ·ም
☞ ስልጠናው ሐምሌ 18 ይጀመራል በሣምንት 2 ቀን
☎ ለመመዝገብ +251900481488
+251912024845

🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓" በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው"ያዕ.1:17  ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለተመረቃችሁ የእ/ብ/ሰ/ት/ቤት አባላት ለበዛዊት ወርቁ ፣ ለቴዎድሮስ አበራ...
18/07/2026

🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
" በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው"ያዕ.1:17

ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለተመረቃችሁ የእ/ብ/ሰ/ት/ቤት አባላት ለበዛዊት ወርቁ ፣ ለቴዎድሮስ አበራ እና የትምወርቅ መለሰ እንኳን ደስ አላችሁ!
እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት በተማራችሁት ለራሳችሁ ለማኅበረሰቡና ለሀገር የሚጠቅም መልካም ትሩፋት በትጋትና በታማኝነት ለማበርከት ትፋጠኑ ዘንድ አደራ ትላችኋለች።

መልካም የሥራና የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ!
🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓

Address

Addisabeba
Addis Ababa
090989

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያም እና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያም እና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት:

Shortcuts

Share