አርያም ሚዲያ
ማንኛውንም ዓይነት ሀሳብ አስተያየት በ+251941413461 በቴሌግራም በዋትስ አፕ በኢሞ ሊልኩልን ይችላሉ፡፡
©አርያም ሚዲያ - Aryam Media
25/11/2025
በእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተደረገው የሰበካ ጉባኤ "ምርጫ " ምእመናንንና አገልጋዮችን ያላካተተ ሕገወጥ መሆኑን ምእመናን ገለጹ !
ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በዛሬው ዕለት ኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ሕገ ወጥ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ምእመናንን እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ አገልጋዮችን ማሳዘኑ ተገልጿል።
ቅሬታውን ያቀረቡልን ምእመናን ከዚህ በፊት የቆዩት የሰበካ ጉባኤ አባላት ከቃለ ዓዋዲው ባፈነገጠ መልኩ ከ 9 ዓመታት በላይ የቆዩ ሲሆን በተደረጉ ተቃውሞዎች ከበላይ አካላት በተላለፈ ትዕዛዝ መሠረት ምርጫው ለመካሄድ ችሏል ብለዋል።
አክለውም የምርጫ ሂደቱ ሕግን ያልተከተለ በቂ የምርጫ ቅስቀሳ ጊዜ ፣ የምዝገባ ጊዜ ሳይሰ'ጥ እንዲሁም ለምዝገባ በተሰጡት ቀናት የምዝገባ ቢሮው ዝግ ሆኖ ምእመናን መጉላላታቸው ፤ ይልቁንም የምርጫ ካርድ ቤት ለቤት ሲታደል ነበር ብለዋል።
በአካባቢው ተመዝግበው የአባልነት አስተዋጽኦ እያደረጉ ከሚገኙ ከ5,000 በላይ አባወራ እና እማወራ ከ150 ያልበለጡ ምእመናን ብቻ የተሳተፉበት የሕግ መሠረት የሌለው ምርጫ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ደብሩ ላይ ደመወዝ ከሚከፈላቸው አገልጋዮች ሌላ አገልጋይ አናውቅም ፤ በምርጫው ሂደት ላይ መሳተፍ አትችሉም ተብለናል ያሉት ደግሞ በአካባቢው ላይ በትሩፋት የሚያገለግሉ ዲያቆናት ናቸው።
በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከተው የበላይ አካል የሰበካ ጉባኤው ምርጫ ቤት ለቤት በመጠቋቆም የተሠራ መሆኑን ተገንዝቦ አስፈላጊውን እርምት እንዲወስድ እንጠይቃለን ሲሉ ለሚዲያችን ቅሬታቸውን አቅርበዋል።በጉዳዩ ላይ የአራዳና ጉለሌ ክፍለከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ምንጭ: ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMC
25/11/2025
ውድ የአርያም ሚዲያ ቤተሰቦች ትክክለኛው የአርያም ሚዲያ ፌስቡክ ገጽ ይህ ሲሆን ነገር ግን በእኛ ስም እና ሎጎ @አርያም ሚዲያ ማዕከል በሚል የሀሰት ገጽ ከፍቶ የሚንቀሳቀስ ሰው በመኖሩ እና የተለያዩ ጽሑፎችን በእኛ ስም እየጻፈ ስለሆነ እና በውስጥ መስመር የተለያዩ መልዕክቶች እየደረሱን ስለሆነ ትክክለኛው የአርያም ሚዲያ ገጽ ይህ መሆኑን እንድታውቁ እና ያኛው የእኛ ገጽ እንዳልሆነ እንድትረዱ በትህትና እንጠይቃለን።
አርያም ሚዲያ
የመስቀል ደመራ በዓል 2018 ከመስቀል አደባባይ
እስከ መጨረሻው አድምጡት ታተርፋላችሁ አባ ሕርያቆስ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
እጅግ አፅናኝ ትምህርት በአባ ዮሴፍ ሙሉውን አርያም ሚዲያ ላይ ያገኙታል 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
እጅግ አፅናኝ ዝማሬ ዘማሪ አቤል መክብብ ሙሉውን አርያም ሚዲያ ላይ ያገኙታል 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Address
Addis Ababa
1000