Sharp Swords

Sharp Swords Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sharp Swords, Tutor/Teacher, Addis Ababa.

ይህ በብዕር ጫፍ የተከተበ አግራሞት፣ በቃላት ስዕል የተሳለ የነፍስ መስታወት ነው። "አግራሞቴን በብዕር" ስንል መገረማችን ስለ ዱንያ ውበት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በመከራ ውስጥ ስላለው ጥንካሬ፣ በውድቀት ውስጥ ስላለው ተስፋና በዝምታ ውስጥ ስላለው ታላቅ ድምፅ እንጂ። ይህ ጽሑፍ የቆሰሉ ልቦችን የሚጠግን፣ የሰነበቱ ተስፋዎችን የሚያድስና ለነገው ማንነታችን የብርሃን ፋኖስ የሚሆን የቃላት ሰይፍ ነው። 🔰 The Sharp Swords // سيوف حادة // ስለታማ ሰይፎች

🎯 My Goal is to make people realize their dreams by Developing their Natural Experiences‼️

⭕️

Reminder:
⚙️ The ideas that I will raise are taken from the teachings of Islam❗️

By Reshad Ibnu Muzemil
▬▬▬▬▬▬▬▬🔗 🔗 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🎯 አላማዬ ሰዎችን የተፈጥሮ ልምዳቸውን በማዳበር ህልማቸውን እንዲያውቁ ማድረግ ነው‼️

⭕️ ማሳሰቢያ:
⚙️ የማነሳቸው ሀሳቦች ከእስልምና አስተምህሮት የተቀዱ ናቸው❗️

በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

t.me/Sharp_Swords

YouTube.com/

01/07/2026

🏁 መንገዳችን ለነገያችን (ሙጎ) | Our Path, Our Future (Mugo)

❝ዳገቱ የጥንካሬያችን መለኪያ ሳይሆን የጋራ ርህራሄያችን መፈተኛ ነው! ❞

♦️ የችግሩ አሳሳቢነት
በስልጤ ዞን ሙጎ አካባቢ (ወሸርሚኔ-ዶዮ-ዪቃር) የሚገኘው ዳገት ተራ መንገድ አይደለም፤ የአረጋውያን ትንፋሽ የሚቆራረጥበት፣ የደረሶች ጉልበት የሚዝልበትና የማህበረሰቡ የኢኮኖሚ ሰንሰለት የሚበጠስበት ፈተና እንጂ።
◆ እናቶች በገበያ ቀን የሚደርስባቸው ድካም፣
◆ ደረሶች ለኢልም ብርሃን ሲሉ የሚወጡት አድካሚ ዳገት፣
◆ የታመሙ ሰዎች ወደ ህክምና ለመድረስ የሚገጥማቸው መከራ አሁን ያበቃ ዘንድ እናንተ ተጠርታችኋል።

📖 የአላህ ቃል (ሱረቱ አል-በቀራህ፡ 261)
❝እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ምሳሌያቸው እንደ አንዲት ቅንጣት ሰባት ዘንቦችን እንዳበቀለች፣ በእያንዳንዱም ዘንብ ውስጥ መቶ ቅንጣቶች እንዳሉበት ናት። አላህም ለሚሻው ሰው (ምንዳውን) ይደራርባል።❞

📜 የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሂህ ሀዲስ
“የአደም ልጅ ሲሞት ከሦስት ነገሮች በስተቀር ሥራው ሁሉ ይቋረጣል፤ እነርሱም፡- ቋሚ ምጽዋት (ሰደቀተል ጃሪያህ)፣ ሰዎች የሚጠቀሙበት ዕውቀት ወይም ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ናቸው።”

➊ ለምን ትሳተፋላችሁ?
ይህ ፕሮጀክት በወረዳው እውቅና ያገኘ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በቁርጠኝነት የጀመረውና በግልፅነት የሚመራ ነው። እናንተ ዛሬ የምታወጡት ድጋፍ፦
✅ የአንድን አዛውንት ዱዓ ያተርፍላችኋል።
✅ የአንድን ደረሳ የኢልም መንገድ ያቀልላችኋል።
✅ እናንተ በሌላችሁበት ቀን እንኳን ዘላለማዊ አጅር (Reward) ሆኖ ይጠብቃችኋል።

➋ የኸይር ጥሪ
ይህ ጥሪ ለሙጎ ተወላጅ ብቻ ሳይሆን፣ "ለወገኔ ምን ላድርግ?" ለሚል ኸይር ፈላጊ ሙስሊም በሙሉ ነው።

📢 ልዩ ማሳሰቢያ፦ በግሩፓችን ላይ ወንድሞቻችሁንና ጓደኞቻችሁን Add በማድረግ እና ይህን መልዕክት Forward በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።
ለመሳተፍና መረጃ ለማግኘት፦

🔗 የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/MugoPath

👥 የቴሌግራም ግሩፕ (Add ያድርጉ): https://t.me/MugoPathGroup

ነገን በብርሃን ለመቀበል፣ ዛሬ በኸይር እንዝራ!
​"ከሁሉ የተሻለው ስራ በጥቂቱም ቢሆን ዘውታሪ የሆነው ነው!" እንደተባለው፤ ዛሬ ካለን ላይ የምናበረክታት ጥቂት ብር ለነገው ዘላቂ ቤታችን (ለኺራችን) የምናስቀምጠው ታላቅ ስንቅ ናት።
​መንገዳችንን ዛሬ በችሮታ ካቀናን፣ ነገ በጨለማው ቀን ብርሃን ይሆንልናል። አቅማችን የፈቀደውን ያህል በመለገስ የዚህ በረከት ተካፋይ እንሁን!

​🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) አካውንት፦
📌 1000774905611

የአካውንት ስም: BEHRE AND TEMAM AND MEHAMEDNUR

👆የካውንቱ ለዚህ መንገድ ብዙ መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ በሶስት ወንድሞች ስም ተከፍቷል።

​📞 ለበለጠ መረጃ፦ +251910083272

👆ይህንን ድንቅ ሀሳብ (ኸይር ስራ) የጀመረው፣ እያስተባበረ ያለና ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ ያለ ወንድም ስልክ ነው።

📱 የእኔ ስልክ (ረሻድ)፦ +251919728324

✅ ​አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!

🔶 የምትችሉትን ያህል አስገቡ፣ ደረሰኙን በዚህ የቴሌግራም አካውንት ላኩልኝ። ለማስተባበር ይሆነናል! አላህ መልካም ምንዳን ይክፈላችሁ!!

👇👇👇👇👇👇👇

የወንድሞች አሳሳቢ መልዕክት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በሙሉ!

🔶 ይታይ፣ ይደመጥ‼️

🏁 መንገዳችን ለነገያችን (ሙጎ) | Our Path, Our Future (Mugo)❝ዳገቱ የጥንካሬያችን መለኪያ ሳይሆን የጋራ ርህራሄያችን መፈተኛ ነው! ❞♦️ የችግሩ አሳሳቢነትበስልጤ ዞን ሙጎ...
25/06/2026

🏁 መንገዳችን ለነገያችን (ሙጎ) | Our Path, Our Future (Mugo)

❝ዳገቱ የጥንካሬያችን መለኪያ ሳይሆን የጋራ ርህራሄያችን መፈተኛ ነው! ❞

♦️ የችግሩ አሳሳቢነት
በስልጤ ዞን ሙጎ አካባቢ (ወሸርሚኔ-ዶዮ-ዪቃር) የሚገኘው ዳገት ተራ መንገድ አይደለም፤ የአረጋውያን ትንፋሽ የሚቆራረጥበት፣ የደረሶች ጉልበት የሚዝልበትና የማህበረሰቡ የኢኮኖሚ ሰንሰለት የሚበጠስበት ፈተና እንጂ።
◆ እናቶች በገበያ ቀን የሚደርስባቸው ድካም፣
◆ ደረሶች ለኢልም ብርሃን ሲሉ የሚወጡት አድካሚ ዳገት፣
◆ የታመሙ ሰዎች ወደ ህክምና ለመድረስ የሚገጥማቸው መከራ አሁን ያበቃ ዘንድ እናንተ ተጠርታችኋል።

📖 የአላህ ቃል (ሱረቱ አል-በቀራህ፡ 261)
❝እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ምሳሌያቸው እንደ አንዲት ቅንጣት ሰባት ዘንቦችን እንዳበቀለች፣ በእያንዳንዱም ዘንብ ውስጥ መቶ ቅንጣቶች እንዳሉበት ናት። አላህም ለሚሻው ሰው (ምንዳውን) ይደራርባል።❞

📜 የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሂህ ሀዲስ
“የአደም ልጅ ሲሞት ከሦስት ነገሮች በስተቀር ሥራው ሁሉ ይቋረጣል፤ እነርሱም፡- ቋሚ ምጽዋት (ሰደቀተል ጃሪያህ)፣ ሰዎች የሚጠቀሙበት ዕውቀት ወይም ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ናቸው።”

➊ ለምን ትሳተፋላችሁ?
ይህ ፕሮጀክት በወረዳው እውቅና ያገኘ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በቁርጠኝነት የጀመረውና በግልፅነት የሚመራ ነው። እናንተ ዛሬ የምታወጡት ድጋፍ፦
✅ የአንድን አዛውንት ዱዓ ያተርፍላችኋል።
✅ የአንድን ደረሳ የኢልም መንገድ ያቀልላችኋል።
✅ እናንተ በሌላችሁበት ቀን እንኳን ዘላለማዊ አጅር (Reward) ሆኖ ይጠብቃችኋል።

➋ የኸይር ጥሪ
ይህ ጥሪ ለሙጎ ተወላጅ ብቻ ሳይሆን፣ "ለወገኔ ምን ላድርግ?" ለሚል ኸይር ፈላጊ ሙስሊም በሙሉ ነው።

📢 ልዩ ማሳሰቢያ፦ በግሩፓችን ላይ ወንድሞቻችሁንና ጓደኞቻችሁን Add በማድረግ እና ይህን መልዕክት Forward በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።
ለመሳተፍና መረጃ ለማግኘት፦

🔗 የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/MugoPath

👥 የቴሌግራም ግሩፕ (Add ያድርጉ): https://t.me/MugoPathGroup

ነገን በብርሃን ለመቀበል፣ ዛሬ በኸይር እንዝራ!
​"ከሁሉ የተሻለው ስራ በጥቂቱም ቢሆን ዘውታሪ የሆነው ነው!" እንደተባለው፤ ዛሬ ካለን ላይ የምናበረክታት ጥቂት ብር ለነገው ዘላቂ ቤታችን (ለኺራችን) የምናስቀምጠው ታላቅ ስንቅ ናት።
​መንገዳችንን ዛሬ በችሮታ ካቀናን፣ ነገ በጨለማው ቀን ብርሃን ይሆንልናል። አቅማችን የፈቀደውን ያህል በመለገስ የዚህ በረከት ተካፋይ እንሁን!

​🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) አካውንት፦
📌 1000774905611

የአካውንት ስም: BEHRE AND TEMAM AND MEHAMEDNUR

👆የካውንቱ ለዚህ መንገድ ብዙ መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ በሶስት ወንድሞች ስም ተከፍቷል።

​📞 ለበለጠ መረጃ፦ +251910083272

👆ይህንን ድንቅ ሀሳብ (ኸይር ስራ) የጀመረው፣ እያስተባበረ ያለና ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ ያለ ወንድም ስልክ ነው።

📱 የእኔ ስልክ (ረሻድ)፦ +251919728324

✅ ​አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!

🔶 የምትችሉትን ያህል አስገቡ፣ ደረሰኙን በዚህ የቴሌግራም አካውንት ላኩልኝ። ለማስተባበር ይሆነናል! አላህ መልካም ምንዳን ይክፈላችሁ!!

ወላጅ እናቱን የሚኒስትሪ ፈተናው ቀን በሞት ያጣው ተማሪ ኻሊድ የባንክ አካውንት ይፋ ሆኗል።ተማሪ ኻሊድን መርዳት የምትፈልጉ የሲንቄ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ አካውንት ተከፍቷል። ተማሪ ኻሊድ...
20/06/2026

ወላጅ እናቱን የሚኒስትሪ ፈተናው ቀን በሞት ያጣው ተማሪ ኻሊድ የባንክ አካውንት ይፋ ሆኗል።

ተማሪ ኻሊድን መርዳት የምትፈልጉ የሲንቄ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ አካውንት ተከፍቷል። ተማሪ ኻሊድ እድሜው 18 ስላልሞላውና ዘመድም ስለሌለው፤ ብቻውን ገንዘብ አውጥቶ መጠቀም ስለማይችል፣ አካውንቱ በአካባቢው መስጅድ ኡስታዝ፣ ከሀገር ሽማግሌ እና ከራሱ ጋር በጋራ በመሆን አካውንት ተከፍቶለታል።

①) ስንቄ ባንክ
11 14385901915

②) አዋሽ ባንክ
013201115433100

🚢 መግቢያ፡ የታላቅነት ጥሪ (The Grand Intro)​በመላው የሕይወት ውቅያኖስ ላይ የምትጓዙ፣ የነገን ብሩህ ተስፋ የምትናፍቁና የአላህን እገዛ አቅጣጫ መጠቆሚያ (Compass) አድርጋች...
18/06/2026

🚢 መግቢያ፡ የታላቅነት ጥሪ (The Grand Intro)

​በመላው የሕይወት ውቅያኖስ ላይ የምትጓዙ፣ የነገን ብሩህ ተስፋ የምትናፍቁና የአላህን እገዛ አቅጣጫ መጠቆሚያ (Compass) አድርጋችሁ ወደ ስኬት የምትገሰግሱ ውድ ወንድም እና እህቶቼ!
​ይህ አሁን የምታነቡት መልዕክት ተራ የቃላት ድርድር ወይም የሰነፍ መዝናኛ አይደለም። ይልቁንም በውስጣችሁ የተዳፈነውን ትልቅነት የሚቀሰቅስ፣ ልክ እንደ ተሳለ ሰይፍ የተሳሳቱ የሕይወት አመለካከቶችን ቆራርጦ የሚጥል፣ እንደ ሚሳዔልም ትክክለኛውን የስኬት ግብ ላይ ሄዶ የሚመታ የንቃት ጥሪ ነው። የዛለውን ልብ እያረሰ፣ እንደ ቀዝቃዛ ውሃ ጥማችሁን እየቆረጠ ወደ ቀጥተኛውና ወደ በላጩ የስኬት ጎዳና ይመራችኋል — በአላህ (ሱ.ወ) ፍቃድና እገዛ!
​ሕይወት ሰፊና ማዕበል የበዛባት ውቅያኖስ ናት። ታላቁ ዓሊም ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) ይህንን የሕይወት ጉዞ ሲገልጹት እንዲህ ይላሉ፦

​"ዱንያ ልክ እንደ ማዕበለኛ ውቅያኖስ ናት፤ አኺራ ደግሞ የባህሩ ዳርቻ (ወደብ) ናት፤ መርከቧ ደግሞ ተቅዋ (አላህን መፍራት) ናት፤ የሰው ልጆች ደግሞ በዚች ባህር ላይ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው።"

​በዚህ ውቅያኖስ ላይ የምንጓዝበትን የጀልባና የመርከብ ምስጢር በጥልቀት እንድንመረምርና ራሳችንን እንድንፈትሽ ይሄው በታላቅ ትሕትና የውስጤን እውነት አጋራችኋለሁ። ዓላማችን መማማር፣ መታረምና ወደ ላቀው ደረጃ አብሮ መገስገስ ብቻ ነው!

​ክፍል 1፡ "ትልቅ መርከብ" እየቆረጡ "ትንንሽ ጀልባ" ከመስራት...

​አላህ (ሱ.ወ) እያንዳንዱን የሰው ልጅ ሲፈጥረው ትልቅ እምቅ አቅም (Potential)፣ ታላቅ ክብርና ሰፊ ራዕይ ሰጥቶታል። ይህ በውስጣችን ያለው ታላቅ አቅም፣ ትክክለኛው የኢማን መስመር፣ የረጅም ጊዜ ራዕይና የጋራ ጥንካሬ "ትልቁ መርከብ" ይባላል።
​ነገር ግን ዛሬ ላይ ብዙዎቻችን የምንሰራው ትልቅ አስከፊ ስህተት አለ። እሱም ምንድን ነው? ያንን አላህ የሰጠንን ታላቅ ራዕይ፣ የረጅም ጊዜ ግብና የጋራ ጥንካሬ በስሜታዊነት፣ በትዕግስት ማጣትና በጊዜያዊ ጥቅሞች ስም እየቆራረጥን "ትንንሽ ጀልባዎችን" ለመስራት እንፈጥናለን።

​በትምህርታችንና በሙያችን የመጨረሻው የላቀ ደረጃ ላይ ደርሰን ለኡማው ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር ሲገባን፣ ጥቂት እርምጃዎችን ብቻ ተጉዘን በትንሹ (በጊዜያዊ ጥቅም) ረክተን እንቆማለን።

​ትልቅና ዘላቂ የሆኑ የዱንያና የአኺራ ስኬቶችን (መርከቦችን) ትተን፣ ለጊዜያዊ ስሜት ማርኪያና ለአጭር ጊዜ ዝና (ጀልባዎች) ስንል ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንንና እምነታችንን እንሰዋለን።

​ይህ በትዕግስት ማጣትና በጥበብ ጉድለት መርከብን ሰባብሮ ጀልባ መስራት የብልሆች መንገድ አይደለም። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

​"በዱንያ ላይ ያለች አንዲት ጀነት አለች፤ እሷን ያልገባባት ሰው የአኺራዋን ጀነት አይገባም። እሷም አላህን ማወቅ፣ እርሱን መውደድና በመገዛት ውስጥ የምትገኝ የልብ እርካታ ናት።"

​ታዲያ ይህንን ታላቅ የልብ ስኬት (መርከብ) ለትንሽ ዱንያዊ ስሜትና ጭንቀት ብሎ እየቆራረጡ ማጥፋት ኪሳራ አይደለምን?

​ክፍል 2፡ "ትንሿን ጀልባ" ሰብስቦ "ትልቁን መርከብ" መጠገን ይበልጣል!!

​ይህቺ ዐረፍተ-ነገር የእውነተኛ ንቃትና የለውጥ ቁልፍ ናት! የእስልምናችንም አስተምህሮ (ሱና) የሚያስተምረን ይህንን ታላቅ ጥበብ ነው። የነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወትና ሰሐባዎች የገነቡት ታሪክ የሚያሳየን የተበታተኑ አነስተኛ አቅሞችን፣ ትንንሽ በጎ ተግባራትንና የተሰባበሩ ተስፋዎችን በአንድ ላይ ሰብስቦ ታላቅ ስልጠናና ስኬት መገንባትን ነው።

​ሀብትንና አቅምን መሰብሰብ፦ በየቦታው የምናባክነውን ጥቃቅን ሰከንዶች፣ ሳንቲሞችና ጉልበቶች በአንድ ላይ ስንሰበስባቸው ትልቅ ተቋም፣ ትልቅ የፈጠራ ስራና ትልቅ ስኬት መፍጠር እንችላለን።

​በተውባ (በመፀፀት) መርከብን መጠገን፦ ስህተቶቻችንን፣ ድክመቶቻችንንና የወደቅንባቸውን ስብራቶች አይተን ተስፋ መቁረጥ የለብንም። ማዕበል መርከባችንን ሊያናውጠው ወይም ሊቀደው ይችላል። ያቺን ያለችንን ትንሿን አቅም (ትንሿን ጀልባ) ይዘን፣ በተውባና በኢስቲግፋር የተበላሸውን ማንነታችንንና የላቀውን ግባችንን (ትልቁን መርከብ) ለመጠገን መነሳት ይበልጣል።

​በትናንሽና በተበታተኑ ጊዜያዊ ስኬቶች ከመኩራትና ከመረካት ይልቅ፣ ሁሉንም አቅጫጫዎች አቀናጅቶ ወደ ትልቁና ወደ እውነተኛው የስኬት ወደብ መጓዝ ጥበብ ነው።

​ክፍል 3፡ ለታላላቅ ህልሞች መዘጋጀትና ማህበረሰብን መታደግ

​እውነተኛ ሙስሊም ህልሙና አላማው በራሱ የግል ህይወት ቅጥር ግቢ ውስጥ ብቻ አይታጠርም። "ትልቁን መርከብ መጠገን" ስንል አላማችን ታላቅ ህልሞችን ሰንቆ፣ ለዛ ታላቅ ህልም በፅናት ታግሎ የሙስሊሙን ማህበረሰብ (ኡማውን) መርዳትና መታደግ ጭምር ነው።
​ዛሬ ማህበረሰባችን በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚና በስነ-ምግባር ዘርፍ ትላልቅ መርከቦችን የሚጠግኑ፣ ማዕበሉን ተቋቁመው ህዝባቸውን የሚመሩ ብቁ መሪዎችንና ባለሙያዎችን ይፈልጋል። እኛ በግል ጥቅማችን ጀልባ ላይ ብቻ ተሳፍረን ማህበረሰባችንን ማዕበል ሲያናውጠው እያየን ዝም ልንል አይገባም!
​ህልምህን ከፍ አድርግ! በትምህርትህ፣ በስራህና በፈጠራህ የምታደርገው ጥረት ሁሉ የመጨረሻ ግቡ ማህበረሰብህን የምትጠቅምበት፣ የተቸገሩትን የምትደግፍበት፣ የወደቁትን የምታነሳበት ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር ሊሆን ይገባል። ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት፦ "ከሰዎች ሁሉ በላጩ ሰዎችን ይበልጥ የሚጠቅመው ነው።" ታዲያ ለኡማው ከሚተርፍ ትልቅ መርከብ በላይ ምን ጥገና ያስፈልገናል?

​ክፍል 4፡ በአላህ እገዛ የሚመራ የስኬት ቀመር

​ይህ ለውጥና ስኬት እንዲሳካ ግን የምንከተላቸው ሸሪዓዊና ሱናዊ እሴቶች አሉ፦

​ኢኽላስና ኒያ (ንፁህ ዓላማ)፦ የምንሰራው እያንዳንዱ ስራ መጀመሪያ ለአላህ ብለን፣ በመቀጠልም ለራሳችንና ለወገኖቻችን የተሻለ ነገርን ለማበርከት መሆን አለበት። ኩራትና እኔ ብቻ ልታይ የሚል ስሜት በረካን ያጠፋሉ።

​ተውኩል (በአላህ መተማመን)፦ ሰበቦችን በሙሉ እናደርሳለን፤ ትንሿንም ጀልባ ሰብስበን መርከቡን ለመጠገን እንጥራለን፤ ነገር ግን ውጤቱን ለአላህ እንተዋለን። እርሱ ካልረዳን በስተቀር በገዛ አቅማችን ብቻ የትም እንደማንደርስ በትሕትና እናምናለን።

​ትዕግስትና ፅናት (ሶብር)፦ መርከብ መጠገንና ለማህበረሰብ የሚተርፍ ስራ መስራት ጊዜና ድካም ይጠይቃል። በአንድ ጀምበር የሚገነባ ታላቅነት የለም። በመንገዳችን ላይ የሚገጥሙንን ፈተናዎች በአላህ ፍቃድ እያለፍን ወደፊት መጓዝ ይኖርብናል።

​🏁 ማጠቃለያ፡ የውሳኔው ሰዓት አሁን ነው!

​ውድ ወንድሜ! ውድ እህቴ! ዛሬ ላይ ቆም ብለህ ራስህን ጠይቅ፦ በሕይወትህ እያደረግክ ያለኸው ምንድን ነው? አላህ የሰጠህን ሰፊ ዕድሜ፣ እውቀትና ወጣትነት እየቆራረጥክ ለጥቃቅንና ለአላፊ ነገሮች እየገበርክ ነው (መርከብ እየቆረጥክ ጀልባ እየሰራህ ነው)? ወይስ ያለህን ጥቃቅን አቅም በሙሉ አቀናጅተህ ነገ በአላህ ፊት የምትድንበትን፣ ለዚህችም ዓለምና ለኡማው የሚተርፍ ታላቅ ስራ እየገነባህ ነው (ጀልባዋን ሰብስበህ መርከቧን እየጠገንክ ነው)?
​ምርጫው የኛው ነው! ዛሬውኑ ካለንበት የቸልተኝነትና የጥቃቅን ነገሮች ባርነት እንውጣ። የተበታተነውን አቅማችንን እንሰብስብ፤ የተሰበረውን ማንነታችንን በእምነትና በዕውቀት እንጠግን። አላህ በሰጠን ሙሉ ፀጋ ተጠቅመን በስኬት ማዕበል ላይ በፅናት የምትጓዝ ታላቅ መርከብ እንገንባ።
​አላህ ሁላችንንም ሰምተውና አንብበው ከሚጠቀሙት፣ ሕይወታቸውን በአግባቡ አስተካክለው በዱንያም በአኺራም ስኬታማ ከሚሆኑት ባሮቹ ያድርገን። አሚን! 🤲

​✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

📚 ​📚 ርዕስ: የድል ዋዜማ ማሳሰቢያ፦ የመጨረሻ ጥሪ ለወደፊቱ የሀገር ብርሃኖች!​ለንጋቱ ፀሐዮች፣ ለውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈታኝ አበቦቻችን በሙሉ፤​የፊታችን ሰኞ ሰኔ 8 (ለ6ኛ ክፍል...
12/06/2026

📚 ​📚 ርዕስ: የድል ዋዜማ ማሳሰቢያ፦ የመጨረሻ ጥሪ ለወደፊቱ የሀገር ብርሃኖች!

​ለንጋቱ ፀሐዮች፣ ለውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈታኝ አበቦቻችን በሙሉ፤
​የፊታችን ሰኞ ሰኔ 8 (ለ6ኛ ክፍል) እና ሰኔ 11 (ለ8ኛ ክፍል) የምትወስዱት የከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ደርሷል። ይህ ዕለት የድካማችሁ ዋጋ የሚከፈልበት፣ የተስፋችሁ ማማ የሚቆምበት ወርቃማ ቀን ነው። አሁን መደናገጥና ፍርሃትን አውርዳችሁ፣ ሙሉ እምነታችሁን በአላህ ላይ ጥላችሁ፣ በፈገግታና በውስጥ ሰላም ወደ ፈተናው አዳራሽ የምትገቡበት ጊዜ ነው።
​የአንድ ዓመት ሙሉ ልፋታችሁ ፍሬ እንዲያፈራ፣ በአላህ ፈቃድና እገዛ የሚከተሉትን ወሳኝና ጥብቅ መመሪያዎች በንቃት ተግብሩ፡

​❶. የፈተናው ዋዜማ እና የጠዋት ዝግጅት
​የመግቢያ ካርድ እና ቁሳቁስ፡ የመግቢያ ካርዳችሁን (Admission Card)፣ HB ወይም 2B እርሳስ፣ ጥሩ ላጲስ እና መቅረጫ በዋዜማው ምሽት አዘጋጅታችሁ አስቀምጡ።
​እረፍትና አመጋገብ፡ በፈተናው ዋዜማ በቂ እንቅልፍ ተኙ። ጠዋት ላይ ቀለል ያለ ቁርስ፣ ከሰዓት ደግሞ ቀለል ያለ ምሳ ተመገቡ፤ በቂ ውሃም መጠጣታችሁን አትርሱ።
​በሰዓቱ መገኘት፡ ሳይጣደፉና ሳይደናገጡ፣ አእምሮአችሁ እንዲረጋጋ ከፈተናው መጀመሪያ 30 ደቂቃ ቀድማችሁ በጣቢያው ተገኝታችሁ ተረጋጉ።

​❷. የኦፕቲካል (OMR) መልስ መስጫ ወረቀት ጥንቃቄ (እጅግ ወሳኝ!)
​የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ፡ የፈተና ወረቀት እንደደረሳችሁ ከAdmission Card ላይ አይታችሁ ስማችሁን፣ የትምህርት ቤቱን ስም፣ ክፍለከተማ እና ወረዳ በትክክል ፃፉ እንዲሁም የመለያ ቁጥራችሁን (Registration Number) እና የትምህርት አይነት መለያ ኮዱን (Subject Code) በየሳጥኑ በትክክል ፃፉ።
​ሳጥኖችን ማጥቆር፡ ከፃፋችሁት ቁጥር ትይዩ ያለውን አራት ማዕዘን ቅንፍ [ ] በእርሳስ ብቻ በጥንቃቄ አጥቁሩ።
​ምርጫ መቀየር ሲፈልጉ፡ መጀመሪያ ያጠቆራችሁትን ቦታ በላጲስ ምንም አይነት የእርሳስ ዱካ ሳይቀር በደንብ አጥፉት።
​የወረቀቱ ደህንነት፡ ወረቀቱ ላይ ምንም አይነት ትርፍ ጭረት፣ ስዕል ወይም ነጥብ አታድርጉ፤ ማዕዘኖቹን አታጥፉ። ማሽኑ (OMR) እንዳያነበው ሊያደርግ ስለሚችል በከፍተኛ ንፅህና ያዙት።
​እገዛ መጠየቅ፡ በአጋጣሚ ወረቀቱ ቢቀደድ ወይም ቢበላሽባችሁ፣ ምንም ሳትደነግጡ እጅ በማውጣት ፈታኙን መምህር በአክብሮት ጠይቁ።

​❸. ከፈተና በኋላ...
​ፈተናው እንደተጠናቀቀ "ምን አገኘሁ? ስንት ጥያቄ ተሳሳትኩ?" በማለት ጥያቄዎችን ከጓደኞቻችሁ ጋር አትወያዩ። ይህ ጭንቀትን ስለሚጨምር ለቀጣዩ ፈተና አእምሮአችሁን ያደክማል። ከአላህ እገዛ ቀጥሎ የተረጋጋ አእምሮ ለቀጣዩ ፈተና ትልቅ ስኬት ነው።
​ውድ ተማሪዎቻችን፤ እኛ በበኩላችን ሙሉ እምነት ጥለንባችኋል። እናንተ ሰበቡን (ምክንያቱን) በሚገባ አድርሳችኋል፤ ቀሪውን ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ሁሉንም ነገር ማድረግ በሚችለው በፈጣሪያችሁ በአላህ ላይ ጥሉት (ተወኩል አድርጉ)። ጥረታችሁን አምኖ በአላህ ላይ የተደገፈ ተማሪ መቼም አይወድቅም። ከፊት ለፊታችሁ ድልና ስኬት ይጠብቃችኋል!

═══════════════
የግጥም ግብዣ፦

​ንፁዎችን አደራ
በተወኩል ልመሳጠር - ከጌታዬ ጋራ
መጥፎን አርቅላቸው - ከሚቀማመጡበት ስፍራ
ወዳጅ አበርክትላቸው - አላህን የሚፈራ፤
ሰውን የሚያከብር - የማያውቅ ጎራ፤
ህይወቷቸው ይመር - ኑሮአቸውም ይብራ፤
በተውሒድ ይሞላ - የህይወታቸው ጎተራ፤
በአላህ ይጠበቁ - ከመጥፎ አሻራ
እባክህ የአላህ - ተማሪዎችን አደራ፤
እባክህ የአላህ - ንፁዎችን አደራ።

✨━━━━━━━━━━━━✨
​🤲 አጭር ዱዓ ለአንፀባራቂ ኮከቦቻችን ⭐
​ያ አላህ! አንተ እውቀትን ሰጪ፣ ልብን ከፋች እና ጥበብን መጋቢ አምላክ ነህ። እነዚህን ውድ ልጆቻችንን በፈተና ወንበር ላይ በሚቀመጡበት ወቅት ልባቸውን አስፋላቸው፤ ያጠኑትን ወደ አእምሯቸው መልስላቸው፤ ያልገባቸውን አብራራላቸው። በፈተና ወቅት የሚመጣን ጭንቀት እና መደናገር አንሳላቸው፤ ብዕሮቻቸውን ወደ ትክክለኛው መልስ አቅናላቸው። በጥረታቸው ብቻ ሳይሆን በአንተ ሰፊ እዝነት፣ ልፋታቸውን አሳምረህ አስደሳች እና ያማረ ውጤት ወፍቃቸው። አሚን! ያ ረበል ዓለሚን! 🤲

═══════════════
​✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

🎯 የክብር ዘመቻው የመጨረሻው 10 ሜትር፦ ከጭንቀት ወደ ንግስና!​ለንጋቱ ፀሐዮች፣ ለ2018 ዓ.ል የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ! 🎓✨​🔶 ክፍል ❶፦ መ...
03/06/2026

🎯 የክብር ዘመቻው የመጨረሻው 10 ሜትር፦ ከጭንቀት ወደ ንግስና!

​ለንጋቱ ፀሐዮች፣ ለ2018 ዓ.ል የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ! 🎓✨

​🔶 ክፍል ❶፦ መግቢያ፦ ለውድድር ሳይሆን ለታሪክ የተፈጠራችሁ የነገው አበቦች!
​ይህ ታላቅ ዕለት የውድድር መድረክ ሳይሆን፣ እናንተ ለታሪክ የተፈጠራችሁ ድንቅ ትውልድ መሆናችሁን ለዓለም የምታበስሩበት የክብር መጀመሪያ ነው! ዛሬ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ል ላይ ቆመን ወደፊት ስንመለከት፣ ወደዚያ ታላቅ የድል አደባባይ ለመድረስ የቀሩን ቀናት ከ10 አይበልጡም። የ6ኛ ክፍል ሰኔ 8፣ 9 እና 10፤ የ8ኛ ክፍል ደግሞ ሰኔ 11 እና 12 የውሳኔ ቀናቶቻችሁ ናቸው። ይህ የሚኒስትሪ ፈተና እናንተን ለመመዘን ወይም ለማስፈራራት የሚመጣ ጠላት ሳይሆን፣ ለአመታት በክፍል ውስጥ ያፈሰሳችሁትን የትጋት ላብ፣ ያደራችሁበትን የሌሊት ጥረት እና የወላጆቻችሁን ተስፋ በታላቅ ውጤት የምታክሱበት፣ የታላቁ ስኬታችሁ ባለቤት የምትሆኑበት ወርቃማ አጋጣሚ ነው።
​ከፊት ለፊታችሁ የሚጠብቃችሁ ፈተና ፍርሃትን ሳይሆን ስኬትን የሰነቀ፣ የትላንት ጥረታችሁ ዛሬ አብቦ ነገ ፍሬ የሚያፈራበት የከፍታ ማማ ነው። እናንተ የምድር ጨው፣ የሀገር ኩራት እና የነገዋ ማራኪ ማለዳ ናችሁ! ይህ መመሪያ ለእናንተ የተዘጋጀ የመጨረሻው ስልታዊ የድል ጎዳና ነው፤ እንደ ሰይፍ የሳለ፣ በአላህ ፍቃድ እንደ ሚሳኤል ያለ ስህተት ግቡን የሚመታ። ይህንን የመጨረሻ 10 ሜትር በልበ-ሙሉነት፣ በፈገግታ እና በድል አድራጊነት እንዴት እንደምትሻገሩት እነሆ በተግባር የተፈተኑ መመሪያዎች።

​📚 ክፍል ❷፦ የቀሩትን 10 ቀናት "መጨቅለቅ" (The Ultimate Crunch Time)
​ጊዜው የሰከንድ ሳንቲሞች የሚቆጠሩበት ወርቃማ ወቅት ነው። አሁን አዲስ መጽሐፍ የምታገላብጡበት ሳይሆን፣ የነበራችሁን እውቀት የምታጠቁሩበት ጊዜ ነው።
​◆ የጊዜ አጠቃቀም (Time Compression): የቀሩትን ቀናት በሰዓታት ከፋፍሏቸው። በእያንዳንዱ ሰዓት ላይ ምን እንደምታነቡ ግልጽ እቅድ ይኑራችሁ።
​◆ የአንበሳው ድርሻ ለዋናው ርዕስ: ከፍተኛ ማርክ ሊያስገኙ የሚችሉ ዋና ዋና አርዕስቶችን ለይታችሁ አጥኑ።
​◆ ትኩረትን ሰብሰብ ማድረግ: ማህበራዊ ሚዲያ እና ትኩረት የሚሰርቁ ነገሮችን ለነዚህ 10 ቀናት በቁልፍ አስቀምጧቸው። ታላቁ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን እንደተናገረው፦
​"በጣም ብልህ ስለሆንኩ ሳይሆን፣ ከችግሮች ጋር ረዘም ላለ ጊዜ አብሬ ስለማቆይ ነው!"
አሁን ካጠኑት ርዕስ ጋር ብቻ አብሮ የመቆያ ጊዜ ነው።

​🔄 ክፍል ❸፦ የክለሳ ጥበብ እና የሞዴል ፈተናዎች ስልታዊ ውጊያ
​ማንበብ ብቻውን አይበቃም፤ ያነበቡትን ማስታወስና ለፈተናው ማዋቀር የድል ቁልፍ ነው።
​✅ በማጠቃለያ መክለስ (Active Recall): የያዛችኋቸውን አጫጭር ማስታወሻዎች (Summary Notes) ብቻ በዓይን እያነበቡ በፍጥነት መሮጥ።
​✅ የሞዴል ጥያቄዎች ጋጋታ: ላለፉት ጥቂት ወራት የተሰጡ የሞዴል ፈተናዎችን እና ያለፉት ዓመታት የሚኒስትሪ ጥያቄዎችን ሰዓት እያዩ መስራት። ይህ ፈተናው ላይ የሚመጣውን ድባብ በጭንቅላታችሁ ውስጥ አስቀድሞ ይቀርጻል።
​✅ ስህተትን ማረሚያ ደብተር: በሞዴል ጥያቄዎች ላይ የተሳሳታችሁትን ነጥብ ደግማችሁ እዩት። ስህተት አሁን ሲታረም ለፈተናው ዕለት ትልቅ ስጦታ ይሆናል።

​🧠 ክፍል ❹፦ በራስ መተማመን እና በአላህ መመካት (Effort + Trust)
​በራስ መተማመን የሚመጣው ካለምክንያት አይደለም። ለአመታት ካፈሰሳችሁት ላብ፣ ካደራችሁበት ሌሊት እና ካደረጋችሁት ከፍተኛ ጥረት የሚቀዳ ነው።
​🔶 ከትጋት በኋላ መመካት፦ ሙሉ አቅማችሁን አውጥታችሁ ካጠናችሁ፣ ከለፋችሁና ከደከማችሁ በኋላ፣ በራሳችሁ ጥረት ላይ ሙሉ እምነት ይኑራችሁ።
​🔶 ቀሪውን ለባለቤቱ መስጠት፦ ሰበቡን (ምክንያቱን) በሚገባ ካደረሳችሁ በኋላ፣ ቀሪውን ነገር ሙሉ በሙሉ በአላህ ላይ ጣሉት (ተወኩል አድርጉ)። ጥረታችሁን አምኖ ፈጣሪ ላይ የተደገፈ ተማሪ መቼም አይወድቅም። ያኔ ፍርሃት ቦታውን ለውስጥ ሰላም ይለቃል።

​🛡️ ክፍል ❺፦ የጭንቀትና የውጥረት ሚሳኤል መከላከያ (Psychological Armor)
​ፈተናው ሲቃረብ የልብ ትርታ መጨመርና "ሁሉንም ነገር የረሳሁት መሰለኝ" የሚል ስሜት መፈጠሩ ተፈጥሯዊ ነው። ይህ የውሸት ስሜት ነው። ጭንቅላታችሁ መረጃዎችን እያደራጀ መሆኑን ማሳያ እንጂ የመርሳት ምልክት አይደለም።
​♦️ አዎንታዊ ንግግር (Positive Self-Talk): "እችላለሁ! ተዘጋጅቻለሁ! የለፋሁበትን ውጤት አገኛለሁ!" እያላችሁ ለራሳችሁ ንገሩ።
​♦️ የኢማሙ አሕመድ ድንቅ ምክር: ታላቁ ሊቅ ኢማሙ አሕመድ የተረጋጋ አእምሮ ስላለው ስኬት ሲናገሩ፦
​❝በጎ ነገርን አስብ፤ ሁልጊዜም በበጎ ነገር ላይ ትሆናለህ።❞
ጭንቀትን በአዎንታዊ አስተሳሰብ አሸንፉት።
​♦️ ከአሉታዊ ሰዎች መራቅ: "ፈተናው ይከብዳል" የሚሉ፣ ፍርሃትን የሚዘሩ ጓደኞችን ለነዚህ ቀናት በሩቁ በሏቸው። አሁን የሚጠቅማችሁ ብርታትና ተስፋ ብቻ ነው።

​🕋 ክፍል ❻፦ የሰበብ ማድረስ ትርጉም (የአላህ ቃል ማጠናከሪያ)
​ሙስሊም ተማሪዎችም ሆናችሁ የሌላ እምነት ተከታዮች፣ የሰው ልጅ ግዴታ መጣርና መጣር ብቻ ነው። ውጤቱን የሚወስነው ግን ፈጣሪ ነው። አላህ በቁርዓኑ እንዲህ ይላል፦
❝​...በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፤ አላህ ትዕዛዙን አድራሽ ነው...❞ (ሱረቱ አጥ-ጠላቅ፡ 3)

​እናንተ ሰበቡን አድርሱ፤ ቀሪውን ለፈጣሪ ተዉት፣ ፍጹም ሰላምና መረጋጋት ያቅፋችኋል።

​🤲 ክፍል ❼፦ የዒባዳ፣ የዱዓ እና የወላጆች ምርቃን ኃይል
​እውቀት የፈጣሪ ስጦታ ነው፤ ያንን ስጦታ ደግሞ በዱዓ እና በጸሎት እንለምነዋለን። የወላጆቻችሁ ምርቃን ደግሞ የተዘጋውን በር ሁሉ የመክፈት ምስጢራዊ ኃይል አለው።
​◆ በዒባዳ መበርታት: ፈርደ ሰላቶቻችሁን በወቅቱ ስገዱ፤ በሱጁድ ላይ እውቀትንና መረጋጋትን ለምኑ።
​◆ የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰልም) መመሪያ: የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፦
​❝ለአንተ የሚጠቅምህን ነገር ላይ ጉጉ ሁን (ትጋ)፤ በአላህም ታገዝ፤ አትስነፍም!❞ (ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2664)

​◆ የወላጆች ዱዓ: ዛሬውኑ ወደ ውድ ወላጆቻችሁ ሂዱና ዱዓና ምርቃታቸውን ለምኑ። የወላጆች ዱዓ በቀጥታ ተቀባይነት አለው፤ መንገድን ያቀናል፣ አእምሮን ይከፍታል።

​💤 ክፍል ❽፦ በቂ እረፍት እና የእንቅልፍ ወሳኝነት (The Brain Recharge)
​ብዙ ተማሪዎች የሚሳሳቱበት ትልቁ ስህተት ሌሊቱን ሙሉ ባለመተኛት አእምሯቸውን ማድከማቸው ነው። የተዳከመ አእምሮ ፈተና ላይ መረጃዎችን ማውጣት አይችልም።
​✅ ከ6-8 ሰዓት እንቅልፍ: በእነዚህ 10 ቀናት ውስጥ በተለይም በፈተናው ዋዜማ በቂ እንቅልፍ መተኛት ግዴታ ነው።
​✅ የአንጎል ሳይንስ: እንቅልፍ ስትተኙ ያጠናችሁት ነገር ከአጭር ጊዜ ማህደረ-ትውስታ ወደ ረጅም ጊዜ ማህደረ-ትውስታ ይሸጋገራል።
​✅ የኢብኑ ተይሚያህ ድንቅ ጥቅስ: ታላቁ ሊቅ ኢብኑ ተይሚያህ ስለ ነፍስና አካል እረፍት ሲናገሩ፦
​"ነፍስ እረፍት ስታገኝ ትበረታለች፤ ስትደክም ግን ትጠፋለች።"
አካላችሁንና አእምሯችሁን በቂ እረፍት በመስጠት አድሱት።

​📝 ክፍል ➒፦ የፈተና ዕለት ተግባራዊ ስነ-ስርዓት (Exam Day Readiness)
​♦️ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት፦ የእርሳስ፣ የላጲስ፣ የመቅረጫ እና የመግቢያ ካርዳችሁን (Admission Card) በዋዜማው ምሽት አዘጋጅታችሁ አስቀምጡ።

​♦️ አመጋገብና ውሃ፦ በፈተናው ጥዋት ቀለል ያለ ቁርስ መመገብን አትርሱ። አእምሯችሁ ንቁ እንዲሆን በቂ ውሃ ጠጡ።

​♦️ የሰዓት እና የፈተና አያያዝ ስልት፦ ፈተናው ሲጀምር መጀመሪያ የምታውቋቸውን ጥያቄዎች በፍጥነት በመስራት በራስ መተማመናችሁን አሳድጉ። በአንድ አስቸጋሪ ጥያቄ ላይ ከሁለት ደቂቃ በላይ በማባከን ሰዓታችሁን አትጨርሱ። የከበዳችሁን ጥያቄ ምልክት አድርጋችሁ አልፉት፤ ሁሉንም ከሰራችሁ በኋላ ወደ እሱ ትመለሳላችሁ።
​♦️ በሰዓቱ መገኘት፦ ጥዋት ሳይደናገጡና ሳይጣደፉ በሰዓቱ (ከተቻለ 30 ደቂቃ ቀድሞ) በመፈተኛ ጣቢያ መገኘት አእምሮ ሰላም እንዲሆን ያደርጋል።

​🏅 ክፍል ➓፦ መዝጊያ፦ ወደ ድል አደባባይ ሂዱ!
​ውድ አበቦቻችን! ይህ ምናልባትም ከፈተናው በፊት የምንለዋወጠው የመጨረሻው ትልቅ መልዕክታችን ሊሆን ይችላል። እኛ በበኩላችን ሙሉ እምነት ጥለንባችኋል። እናንተ የታሪካችን አዲስ ምዕራፎች ናችሁ።
​ሰኔ 8 (ለ6ኛ ክፍል) እና ሰኔ 11 (ለ8ኛ ክፍል) ወደ ፈተና ክፍሉ ስትገቡ፣ ትከሻችሁን ቀና አድርጋችሁ፣ ፈገግ ብላችሁ፣ በፈጣሪ ስም ተማምናችሁ ግቡ። ይህንን ያህል የለፋችሁለት ስኬት በእጃችሁ ላይ ይወድቃል።
​የስኬት ቃል ኪዳን፦ "ያለፈውን ጊዜ በሚገባ ተጠቅሜያለሁ፤ አሁንም ያለኝን ጊዜ እጠቀማለሁ። ፈጣሪዬን አምኜ የላቀ ውጤት አመጣለሁ!"
​መልካም የፈተና እና የድል ቀናት ይሁኑላችሁ! እናንተ የነገዎቹ አሸናፊዎች ናችሁ! 🏆 ያ አላህ ተፈታኝ ተማሪዎቻችንን በድል አጅባቸው! አሚን።

🤲 ​ያ አላህ! ያ ረብ! 🤲
​እነዚህ የነገው ንጋት ብሩህ ፀሐዮች የሆኑት ውድ ተማሪዎቻችን ላለፉት ዓመታት የለፉበትን ድካም ከንቱ አታድርግባቸው። በፍርሃት ፈንታ ፍጹም መረጋጋትን በልባቸው ውስጥ አስፍር።
​ያ አላህ! በፈተናው ዕለት አእምሯቸውን አብራው፤ ማህደረ-ትውስታቸውን ክፈትላቸው። ያጠኑትን ነገር ሁሉ በፈተናው ወረቀት ላይ በትክክለኛው ሰዓት እንዲያስታውሱት ቀናውን መንገድ ምራቸው። ብዕሮቻቸውን ወደ ትክክለኛው መልስ አቅናላቸው።
​ፈጣሪ ሆይ! ከፈተናው አዳራሽ በታላቅ ድልና በፈገግታ እንዲወጡ አድርጋቸው። የወላጆቻቸውን ልብ በደስታ አርስ፤ የትምህርት ቤታቸውን እና የአስተማሪዎቻቸውን ድካም በላቀ ውጤት አጅበው። የወደፊት ጉዟቸውን የከፍታና የብርሃን ማማ አድርገው!
​አሚን! ያ ረበል ዓለሚን! 🤲

══════════════
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ለ2018 ዓ.ል የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ! 🎓✨​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ እና የ8ኛ ክፍል የመካከ...
21/05/2026

ለ2018 ዓ.ል የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ! 🎓✨

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበትን ጊዜ በይፋ አሳውቋል።
​ትምህርት የማህበረሰባችን የውበት እና የእድገት መሰረት ነው። ውድ ተማሪዎቻችን ያካበቱትን እውቀት የሚያሳዩበት እና ወደ ላቀ የህይወት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት የፈተና ቀናት እንደሚከተለው ተወስነዋል፦

​📌 የፈተና ቀናት፦
📚 ​የ6ኛ ክፍል ፈተና፦ ሰኔ 8፣ 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ል የሚሰጥ ሲሆን

📚 ​የ8ኛ ክፍል ፈተና፦ ሰኔ 11 እና 12 ቀን 2018 ዓ.ል ይሰጣል!

​📊 የዘንድሮው ዝግጅት በቁጥር፦
​6ኛ ክፍል፦ 84,882 ተማሪዎች በ199 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።
​8ኛ ክፍል፦ 86,808 ተማሪዎች በ201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

​💡 ለወላጆች እና ለተማሪዎች፦
​ለተማሪዎች፦ እውቀት መፈለግ እና መትጋት ትልቅ ክብር አለው። አላህን በመፍራት፣ በዱዓ፣ በራስ መተማመን እና በጽናት ተዘጋጁ። ድል የናንተ ነው! 📚🤲
​ለወላጆችና፦ ልጆቻችን የነገ ተስፋዎቻችን ናቸው። በዚህ የፈተና ወቅት ተገቢውን የሞራል እና የሀሳብ ድጋፍ በማድረግ፣ አእምሯቸው በሰላም እንዲፈተን የበኩላችንን እንወጣ። ፈጣሪ ጥረታቸውን ይባርክ! 🤝❤️

​ለሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎቻችን መልካምና የተሳካ የፈተና ወቅት ይሁንላችሁ! ✅

═══════════════
◆ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!!
✅ ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦች፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦች!

ወደ ስኬት ማማ የሚወስደው ወርቃማው ድልድይ!​(የሞዴል ፈተና ሚስጥር)​════════════════​አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!​📚 ውድ የዕውቀት ፈላጊዎች፣ የነገ ሀገር ተስፋዎች...
18/05/2026

ወደ ስኬት ማማ የሚወስደው ወርቃማው ድልድይ!

​(የሞዴል ፈተና ሚስጥር)
​════════════════
​አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!

​📚 ውድ የዕውቀት ፈላጊዎች፣ የነገ ሀገር ተስፋዎችና የዚህ ዘመን የለውጥ ፀሐዮች!
​ይህ መልዕክት ለዛሬ ወይም ለነገ ብቻ ሳይሆን፣ አላህ በሰጠን የዕውቀት ጎዳና ላይ እስካለን ድረስ ዘወትር የሚሰራ እውነተኛ የህይወት ስንቅ ነው። ልባችሁን ሰፋ አድርጋችሁ፣ በአላህ ፈቃድ ሕይወትን የሚያናውጸውን ይህንን ውብ ሀሳብ አጣጥሙት፤ አላህም ማስተዋሉንና ማስተርጎሙን ይክፈትላችሁ። 🤲

​1. ራስን የመመልከቻው "እውነተኛው መስታወት"
ብዙዎቻችን የምንሰናከለው ባለማወቃችን ሳይሆን፣ "አውቃለሁ" በሚል ስሜት ውስጥ ስለሚዘናጋን ነው። ሞዴል ፈተና ማለት የውሸት ካባችንን አውልቆ፣ ትክክለኛውን የእውቀት ደረጃችንን የሚያሳይ ጥርት ያለ መስታወት ነው።

​የድክመት ካርታ፦ ሞዴል ፈተና የትኛው የእውቀት ክምችትህ ላይ ክፍተት እንዳለ የሚጠቁም ጠቋሚ መሳሪያ (Compass) ነው። ክፍተቱ ሳይንስ ላይ ነው? ወይስ ቋንቋ ላይ? ዋናው ፈተና መጥቶ ሳይነግርህ በፊት በሞዴል ፈተና እራስን መገምገም ትልቁ ጥበብ ነው።

​2. የስነ-ልቦናው "ሰላምና እርጋታ" (Peace of Mind)
ፈተና ማለት እውቀት ብቻ አይደለም፤ የስነ-ልቦና ዝግጅትም ጭምር ነው። ብዙ ተማሪዎች ጎበዝ ቢሆኑም፣ የፈተና ክፍል ሲገቡ ግን ይርበተበታሉ።

​ድንጋጤን ማራቅ፦ ሞዴል ፈተናን በተደጋጋሚ መውሰድ አዕምሮን ከ"አዲስ ነገር" ድንጋጤ ያላቅቀዋል። ልክ ዋናተኛ ውሃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን እንደሚያላምደው፣ እናንተም የፈተና ወረቀት ሲሰጣችሁ ልባችሁ በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ እንዲመታ ያደርጋል።

​3. ጊዜን የመግራት ብልሃት ሰዓቱ ሲሮጥ ማየት ያስጨንቃል።
ሞዴል ፈተና ግን ከሰዓቱ ጋር አብሮ መጓዝን ያስተምረናል። አንድን ጥያቄ ለመመለስ ስንት ደቂቃ እንደሚያስፈልግህ በደመ-ነፍስ እንድታውቅ ያደርግሃል።

​ጊዜ እንደ ወርቅ ነው፦ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ይባክናል። ጊዜን መግደል አንችልም፤ በአግባቡ ካልያዝነው ግን እሱው ጥሎን ይበርራል። ሞዴል ፈተና ይህንን ውድ ጊዜ እንዴት በብልሃት እንደምትጠቀሙበት መንገዱን ያሳያችኋል።

​4. አዕምሮን ማጎልበትና ማነቃቃት
አንድ ስፖርተኛ ለውድድር ከመቅረቡ በፊት ሰውነቱን ያሟሙቃል። ለምን? ብቁ ለመሆን! የኛም አዕምሮ ዝግጅት ያስፈልገዋል።

​የማስታወስ አቅም፦ ሞዴል ፈተና ስትሰሩ፣ አዕምሮአችሁ በመጋዘኑ ውስጥ ያስቀመጠውን መረጃ በፍጥነት ፈልጎ የማውጣት ልምምድ ያደርጋል። መጽሐፍን ዝም ብሎ ደጋግሞ ከማንበብ ይልቅ፣ እራስን መፈተን የማስታወስ ችሎታንና የመረዳት አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

​5. ከስህተት የመማር "ወርቃማው ሚስጥር"
ፈተናውን መውሰድ ብቻውን ሙሉ አይሆንም፤ ትልቁ ትምህርት የሚገኘው ከፈተናው በኋላ ነው።

​ስህተትን ማረም፦ በሞዴል ፈተና ላይ መሳሳት ወንጀል አይደለም፤ ስህተትን አለማረም ግን ዋናው ፈተና ላይ ዋጋ ያስከፍላል። ፈተናውን ከጨረሳችሁ በኋላ የተሳሳታችሁትን ጥያቄዎች ለምን እንደተሳሳታችሁ መለስ ብሎ መመርመርና መምህራንን መጠየቅ ለስኬት ዋነኛው ቁልፍ ነው።

​6. በራስ መተማመን እና የድል መንፈስ
አንድን ተራራ ከመውጣትህ በፊት፣ የመንገዱን ካርታ የሚያውቅ ሰው ልበ-ሙሉነቱ ልዩ ነው።

​የአሸናፊነት ስሜት፦ በአላህ እገዛ በሞዴል ፈተና ጥሩ ውጤት ስታመጡ፣ ውስጣችሁ "እችለዋለሁ!" የሚል ኃይለኛ ተነሳሽነት ይገነባል። ይህ ስሜት በዋናው ፈተና ቀን እንደ ጋሻ ሆኖ ከጭንቀት ይጠብቃችኋል።

​መረጋጋት (ሰኪና)፦ በደንብ የተዘጋጀ ተማሪ አይጣደፍም። እርጋታው እራሱ ለሌሎች ተማሪዎች ያስቀናል። ይህ እርጋታ የሚመጣው ከቅድመ-ዝግጅት ነው።

​🔥 የልብ መልዕክት

​ሞዴል ፈተናን እንደ "ሸክም" አትዩት። እንደ "ወርቃማ እድል" ቁጠሩት። ዛሬ ላይ ተሳሳቱ፣ ዛሬ ላይ ተደናገጡ፣ ዛሬ ላይ ጊዜ ይለቅባችሁ። ምክንያቱም ዛሬ በአላህ ፈቃድ ማረም ይቻላል! በዋናው ፈተና ቀን ግን ስህተትን ማረም አይቻልም፤ የሚቻለው ውጤትን መቀበል ብቻ ነው።
​ይህንን እድል ተጠቅማችሁ፣ እራሳችሁን አብቅታችሁ፣ ድክመታችሁን አርማችሁ ለድል ብቁ እንድትሆኑ አደራ። ትምህርት የኢባዳ (የአምልኮ) አካል ነው፤ ጠንክሮ መማር ደግሞ "ኢህሳን" (ምርጥ ስራ) ነው። ስኬታችንም ሆነ ጥረታችን ሙሉ የሚሆነው በአላህ እገዛና ቸርነት ብቻ መሆኑን አንዘንጋ።

​🤲 ዱዓ

​ያ የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ሆይ! ይህንን ለወገኖቻቸው፣ ለሀገራቸውና ለራሳቸው ብለው ሌት ተቀን የሚደክሙ ተማሪዎችን ልፋት አንተ ባርክላቸው።
​ጌታዬ ሆይ! በፈተና ሰዓት የመረጋጋትን መንፈስ አውርድላቸው። የረሱትን አስታውሳቸው፣ የከበዳቸውን አቅልላቸው። እውቀታቸው በወረቀት ላይ ብቻ ሳይሆን በህይወታቸውም ላይ ብርሃን ሆኖ እንዲፈነጥቅ አድርግላቸው።
​ለወላጆቻቸው የዓይን ማረፊያ፣ ለሀገራቸው የጀርባ አጥንት፣ ለዲናቸውም ጋሻና መከታ አድርገህ ያማረ ውጤትን ወፍቃቸው። አሚን! 🤲

​📖 ማጠቃለያ (መለኮታዊ ቃል)

​ንግግሬን የምዘጋው ሁሉን በሚያውቀውና ስኬትን ሁሉ በእጁ በያዘው ጌታችን በአላህ ቃል ነው። የሰው ልጅ የሚለፋው ለራሱ ነው፤ ውጤቱንም የሚያገኘው በአላህ ፍቃድ እንደ ልፋቱ ልክ ነው።

​"ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጂ ሌላ የለውም። ሥራውም ወደ ፊት (በቂያማ ቀን) በእርግጥ ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ዋጋ ይመነዳል።"
(ሱረቱ አን-ነጅም፡ 39-41)

​በልበ ሙሉነትና በአላህ ተስፋ ተዘጋጁ! የስኬት ማማ በጌታችን እገዛ እጃችሁ ላይ ነው!

✨━━━━━━━━━━━━✨
🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

📚 ርዕስ: ከፈተና በፊትና በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮችውድ የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ተማሪዎች፤ የፊታችን ግንቦት 10 እስከ 12/2018 ዓ.ል ለምትወስዱት የሞዴል ፈተና እንዲሁም ለ...
14/05/2026

📚 ርዕስ: ከፈተና በፊትና በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች

ውድ የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ተማሪዎች፤ የፊታችን ግንቦት 10 እስከ 12/2018 ዓ.ል ለምትወስዱት የሞዴል ፈተና እንዲሁም ለቀጣዩ የሚኒስትሪ ፈተና እንዲሁም ለ12ኛ ክፍሎች ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ (Entrance) ፈተና ስንቅ ይሆን ዘንድ፣ ይህንን አጭር እና ጠቃሚ ምክር በጥንቃቄ አንብቡት።
የፈተና ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ እና ተፈጥሯዊ ነገር ነው። ይህንን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት።

1. ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገቡን ወርቃማ ዘዴዎች
♦️አመለካከትን ማስተካከል፡ ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። መሳሳትን አትፍሩ፤ ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጁ መሆን የብልህ ተማሪ መገለጫ ነው።
♦️የጋራ ጥናት፡ ከጓደኞቻችን ወይም ከወላጆቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ ትልቅ ጥቅም አለው። ይህ ዘዴ የማስታወስ ብቃታችንን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያደርጋል።
♦️በቂ እረፍት እና እንቅልፍ፡ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ጭንቀትን ይቀንስልናል፤ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።

💡የሳይንቲስቶች እይታ፡ "እንቅልፍ የተማርነውን አዲስ እውቀት ወደ ዘላቂ ማህደረ-ትውስታ (Long-term memory) የምናሸጋግርበት ወርቃማ ድልድይ ነው።" ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ማግኘት ያጠናነውን እንዳንረሳ ያደርገናል።

2. በፈተና ወቅት መከተል ያለብን ጥበቦች
♦️ቅድመ ዝግጅት፡ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት አለብን።
♦️ድንገተኛ ጭንቀትን ማሸነፍ፡ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይኖርብናል። ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ወሳኝ ነው።

📖 ነቢዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ከባድ ሀላፊነት ሲገጥማቸው አላህን እንዲህ ብለው ተማጸኑ፦ ❝ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፤ ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ።❞ (ሱረቱ ጣሀ፡ 25-26)። እናንተም በፈተና ወንበር ላይ ስትቀመጡ ይህንን በማሰብ አላህ ነገራችሁን እንዲያገራላችሁ ጠይቁ።

♦️ራስን ማረጋጋት፡ "እኔ የምችለውን አድርጌያለሁ (ሰበብ አድርሼያለሁ)፣ የቀረውን ለአላህ ሰጥቼዋለሁ!" በማለት የማረጋጊያ ቃላትን ለራሳችሁ ንገሩ።
♦️የጥያቄ አያያዝ ስልት፡ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግምት መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይገባናል። በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን መጨነቅ የለብንም።
🔴 መሰረዝና መደለዝን መቀነስ፡ ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ሌላ መልስ እንድንሰጥ ስለሚያረግ፣ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ አለብን።

3. ከፈተና በኋላ...
አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት መገመት አይገባንም።
ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን፣ ከዚህ ይልቅ እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ይመከራል። አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን አለብን።

⭐💫 ማጠቃለያ
ሁሌም ልናስታውሰው የሚገባን ትልቁ እውነት፡- ፈተና ማለት ለጀነት ማለፊያ ትኬት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን ነው። ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ውጭ እንደማይሆን ማመን አለብን። ከኛ የሚጠበቀው የአቅማችንን ያህል ማድረግ፣ ሌላውን ለአላህ መተው ነው። አላህ በናንተው ጥረት ብቻ ሳይሆን በሱ እዝነት መልካም የሆነ ውጤትን ይሰጣችኋል።

🤲 ዱዓ
ያ አላህ! አንተ እውቀትን ሰጪ፣ ልብን ከፋች አምላክ ነህና ለእነዚህ ልጆች ልባቸውን አስፋላቸው። ያጠኑትን ወደ አእምሮአቸው መልስላቸው፤ ያልገባቸውን አብራራላቸው። በፈተና ወቅት የሚመጣን ጭንቀት እና መደናገር አንሳላቸው። በጥረታቸው ብቻ ሳይሆን በአንተ ሰፊ እዝነት፣ ልፋታቸውን አሳምረህ አስደሳች እና ያማረ ውጤት ወፍቃቸው። ያረብ... ቀጣዩን የህይወት ዘመናቸውንም በስኬት፣ በኢማን እና በጥበብ የተሞላ አድርግላቸው! አሚን! 🤲

═══════════════
◆ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!!
✅ ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦች፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦች!
✨━━━━━━━━━━━━✨
🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sharp Swords posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Sharp Swords:

Shortcuts

Share