Ethiopian Educational Television

Ethiopian Educational Television

Share

ITECKETEMA Welcome To ITec Ketema YouTube channel. We Are Here to Deliver Technology tips tutorials and more fun videos to You.

12/07/2021

የከፍተኛ ትምህርት ምርምር እና ቴክኖሎጂ ትሥሥር ኮንቬንሽን የመክፈቻ ስነ ስርዐት እየተካሄደ ነው።

ለአራት ቀናት የሚቆየው ኮንቬንሽኑ፤ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲዎች መሪዎች በተገኙበት የመክፈቻ ስነስርዐቱ እየተደረገ ይገኛል።

ከመክፈቻ ስነ ስርዐቱ አስቀድሞ፤ የከፍተኛ ትምህርት፣ የምርምር እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አውደ ርዕይን ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጎብኝተዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው መድረኩ፤ የፈጠራና ምርምር ስራዎችን ለማበረታታት እና ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል።

ዩኒቨርስቲዎች፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ባለሃብቶች እና ፖሊሲ አውጪዎች በጉባኤው እየሳተፉ ይገኛሉ።

ጉባኤው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በጋራ የተዘጋጀ ነው።
https://t.me/EthiopianEducationalTelevision

Photos from Ethiopian Educational Television's post 09/07/2021

#ሰበዝ የተሰኘ መጽሔት ይፋ ሆነ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀና በዓመት ሁለት ጊዜ የምትታተም ‹‹ሰበዝ›› የተሰኘች በአካዳሚያዊ፣ በማህበራዊ፣ በባህላዊ፣ በኪነ-ጥበባዊና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የምታደርግ መጽሔት የምረቃ ስነ-ስርዓት ዛሬ ሀምሌ 2/2013 ዓ/ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ አልሙኒዬም ህንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡

በዚህ ስነ-ስርዓት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የአስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሰረት ካሴ፣ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አገኘሁ ተስፋ፣ መምህራንና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡ የመረጃው ምንጭ ፦ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት https://t.me/EthiopianEducationalTelevision

09/07/2021

81-year-old Mano sat for a test at the age of 81 the 8th grade exam in ETHIPOPIA

እዚሁ በኢትዮጵያ ነዉ❗️

አንድ አዛዉንት በ81 ዓመታቸው ለፈተና ተቀመጡ

በርካታ ልጆችን አስተምረው ለወግ ማዕረግ ያበቁት የ81 አመቱ አዛውንት አቶ ማኖ ማገሶ በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ የ8ኛ ክፍል ፈተና ወስደዋል።

አቶ ማኖ ማገሶ የ5 ወንዶች እና 6 ሴቶች በአጠቃላይ የ11 ልጆች አባተ ናቸው።

ታዲያ ዛሬም አልረፈደም ብለው ፈተናውን ወስደዋል።

https://t.me/EthiopianEducationalTelevision

Photos from Ethiopian Educational Television's post 08/07/2021



ሀገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ምገባ ፖሊሲና ስትራቴጂን የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

የምገባ ስነ-ስርአቱ ብቁ እና ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሏል።

እንደ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ገለጻ ፖሊሲ እና ስትራቴጂው ሲተገበር በሃገሪቱ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የቅድመ መደበኛ እንዲሁም የአንደኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። https://t.me/EthiopianEducationalTelevision

06/07/2021

በሚቀጥለው 1 ወር ውስጥ በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተገለፀ፡፡

በሐምሌ ወር ምዕራብ ጅማ፣ ኢሊባቡር፣ የጋምቤላ ክልል፣ መካከለኛውና የምሥራቅ አካባቢዎች የዝናቡ ስርጭት እየተስፋፋ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም ተናግረዋል።

የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ባለፉት ወራት ዝናብ አለማግኘት ጋር ተያይዞ በሚቀጥለው ወር በስፋት ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን የተገኘውን እርጥበት ተጠቅመው በአግባቡ ስራቸውን ማከናወን አለባቸው ብለዋል፡፡

በተጨማሪ በሰሜን ምዕራብ፣ የምዕራብና መካከለኛው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ኅብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠቁመዋል፡፡

ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ ቅስፈታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል ያሉት ዳይሬክተሩ በእነዚህ ቦታዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
https://t.me/EthiopianEducationalTelevision

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች 15 የአቅመ ደካሞች ቤት በማደስ ስራ በትምህርት ዘርፉ የሚካሄደውን የክረምት የበጎ አድራጎት መርሀ-ግብርን በይፋ አስጀምረ 06/07/2021

https://youtu.be/biajKBK5FCM?t=3

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች 15 የአቅመ ደካሞች ቤት በማደስ ስራ በትምህርት ዘርፉ የሚካሄደውን የክረምት የበጎ አድራጎት መርሀ-ግብርን በይፋ አስጀምረ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የኢትዬጵያዊነት መገለጫ የሆነው የመተጋገዝ እና የመደጋገፍ ባህልን መሰረት በማድረግ...

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Mexico Square
Addis Ababa
3025