የሀበሻልጆች

የሀበሻልጆች

Share

ትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም

30/12/2023

🗣️የፉልሀም አሠልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ከነገው የፉልሃም እና አርሰናል ጨዋታ በፊት ይህንን ተናግረዋል

🗣 " አርሰናል ምንም ጥርጥር የለውም በሊጉ ጥሩ ብቃት ላይ ነው ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም ነገ በሜዳችን የምንገጥመው የሊጉን ምርጥ ቡድን ነው።"

🗣"ቡድኑ የሜዳ ላይ እንቅሥቃሴያቸው እጅግ የሚያሥገርም ነው የፊት መሥመራቸው ኳሡን የሚቆጣጠሩበት እንዲሁም የኋላ መሥመር ላይ የተደራጀ መከላከል ድንቅ ብቃት አላቸው ለየትኛውም ቡድን ምቾት የማይሠጥ ኳሥን እንደፈለጉ የሚቆጣጠሩ እና አጥቂዎቻቸው ለተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች ምቾት የማይሠጥ ከፍተኛ የማጥቃት በሀሪ የተላበሰ ቡድን ነው።"

🗣 " አርሠናል በሁሉም መሥፈርት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ቡድን ነው ማለት።"

🗣 "የሚጫወቱበት መንገድ ተጋጣሚ ቡድንን ወደ ኋላ የመግፋት አቅም አላቸው። እናም እነሱን ተጭኖ ለመጫወት ለማጥቃት እና ለመጫን በጣም ከባድ ነው ምክንያቱም እነሡ የሚጫወቱበት መንገድ ተጋጣሚን በመጫን እና ኳሥ በመቆጣጠር የሚጫወቱ በመሆኑ እነሡን ተጭነን ለመግጠም ከእነሡ ጋር በዚህ መንገድ ለመጋፈጥ አስቸጋሪ ቡድን ናቸው።"

🗣" ተመልከት የዚንቼንኮን ፖዚሽናል ቦታ ዚንቼንኮ ምንም እንኳን በተመለላሽ ቦታ ላይ የሚሠለፍ ቢሆንም ወደ መሀል ሜዳ እየተሳበ በመሃል ክፍሉ ላይ ከአንድ ተጨማሪ ሃይል ይፈጥራል ለመሀል ክፍላቸውም ጥራትን ይሰጣቸዋል።"

🗣 " ቡድናቸው ውሥጥ ለተቃራኒ ቡድን አሥቸጋሪ ፈጣን ተጫዋቾች አሏቸው እንደ ማርቲኔሊ ሳካ Ødegaard እና Havertz የመሳሰሉ ድንቅ ብቃት የላቸው ተጫዋቾች ሁሌም ለተጋጣሚ ቡድን አስጊ ናቸው።"

🗣 " አርሠናል እጅግ የላቀ ብቃት ባላቸው ተጫዋቾች የተዋቀረ እጅግ ጥራት ያላቸውን ተጫዋቾች የያዘ ቡድን ነው እነሡ በዚህ ሀገር ውስጥ የሚገኝ የትኛውም ደረጃ ላይ የሚገኝ ቡድን በሚገባ ማሸነፍ ይችላሉ በዚህ ሊግ የሚገኝ የትኛውም ቡድን መግጥም የማይፈልገው ቡድን አርሠናል ነው ብል ምንም ማጋናነን አይሆንብኝም እነሱን ለማቆም እንደ ቡድን በደንብ መደራጀት ከመጀመሪያ እሥከ ጨዋታው ፍጻሜ ትኩረት ሳይለይህ እንደ ቡድን አንድ ላይ እነሡን መጣበቅ አለብን እኑሡ እኛን በመጫንና እኛን በቅጽበት ጫና ውስጥ እንድንገባ ኳሥ እንድንይዝ አይፈቅዱልንም ነገር ግን ኳሱን ሥናገኝ እኛም በተደራጀ ጨዋታ የምናገኛቸውን እድሎች በመጠቀም ራሳችንን መግለጽ ያለብን እና እንደ አርሠናል ካለ ከፍተኛ ብቃት ይዞ ከሚገኝ ቡድን ጋር ተጋፍጠህ ለማሸነፍ ቁርጠኛ መሆን አለብህ ለዚህ ደሞ ዝግጁ ነን።"

🔜በማለት የፉልሃሙ አለቃ ማርኮ ሲልቫ ከጫወታው በፊት ተናግረዋል🖐

30/12/2023

ሩሲያ እና ቻይና ዶላርን ሙሉ ለሙሉ ከንግድ ስረዓታቸው አስወጡ
****************************
የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካሂል ሚሹስቲን በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረጉ የንግድ ልወውጦች በሙሉ በሩብል እና በዩዋን እየተደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ የተባለው ጠቅላይ ሚንስትሩ ከቻይናው አቻቸው ሊ ኪያንግ ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ በሰጡት መግለጫ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካሂል ሚሹስቲን የሩሲያ እና ቻይና መሪዎች መደበኛ ስብሰባን በቤጂንግ እየተካፈሉ ይገኛሉ።

ባለፈው ግንቦት ወር በሻንጋይ በተካሄደው የጋራ የንግድ ፎረም ከሁለቱም ሀገራት ከ1ሺህ 500 በላይ ስራ ፈጣሪዎች መሳተፋቸውን በማስታወስ የንግድ ግንኙነቱ መጠናከሩንም ጠቅሰዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ።

በሩሲያ እና በቻይና ገበያዎች ለንግድ ድርጅቶች ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠርን እንገኛለን ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።

የቻይናው አቻቸው ሊ ኪያንግ በበኩላቸው በሞስኮ እና ቤጂንግ መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠሉን ብሎም ዓለምአቀፍ ተፅእኖውም እየጨመረ መምጣቱን እንደጠቆሙ አርቲ ዘግቧል።

በጦርነቱ ምክንያት የተጣሉ ማዕቀቦች ሞስኮን ከምዕራቡ የፋይናንስ ሥርዓት ገሸሽ ካደረጋት በኋላ ሩሲያ እና የንግድ አጋሮቿ በጋራ ንግድ የሚጠቀሟቸውን ምንዛሬዎች መቀየር ጀምረዋል።

30/12/2023

በአሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ እና ሜሪላንድ ፡ ተንቀሳቃሽ ኮፊ ትራኮችን በመጠቀም የቡና ንግድ ስራ ላይ ለተሰማራው AweCherry Coffee የሚከተለዉን የኢኮሜርስ ዌብሳይት ለመስራት እድሉ ስላገኘን ደስ ብሎናል። ➥ https://awecherrycoffee.com/

ማንኛዉም ድረገጽ፣ የሞባይል መተግበርያ እና ሲስተሞች ለማሰራት ከፈለጉ በሚከተለው የቴሌግራም አድራሻችን ያነጋግሩን። ➥ https://t.me/Ezedin_Kamil

Photos from DireTube's post 30/12/2023
30/12/2023

አየር መንገዶች በ737 ማክስ አውሮፕላን የበረራ መቆጣጠሪያ ስርዓት ውስጥ ሊላላ የሚችል ብሎን ላይ ፍተሻ እንዲያደርጉ በቦይንግ ማሳሰቢያ ተሰጠ።
የአሜሪካው ግዙፍ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ አወዛጋቢ ሆኖ የቆየውን አውሮፕላኑን የተመለከተ ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው በበረራ መቆጣጠሪያ ስርዓት ውስጥ አንድ ብሎን ያለማቀፊያ ከተገኘ በኋላ ነው።
ቦይንግ የሚላላ ብሎን ተገኝቶበታል ያለው አውሮፕላን 737 ማክስ አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዢያ ባጋጠመ አደጋ ምክንያት ከበረራ የታገደው አውሮፕላን ነው።
ኩባንያው ለጥንቃቄ ሲባል 737 ማክስ አውሮፕላን ባለቤት የሆኑ አየር መንገዶች በአውሮፕላኑ ላይ ፍተሻ አድርገው ውጤቱን እንዲያሳውቁኝ እፈልጋለሁ ብሏል።
ቦይንግ ሰራሹ 737 ማክስ አውሮፕላን ከበረራ መቆጣጠሪያ ችግር ጋር በተያያዘ የኢንዶኔዢያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገዶች አውሮፕላኖች ከተከሰከሱ በኋላ አውሮፕላኑ በመላው ዓለም ከበረራ ታግዶ ቆይቷል።
>>> https://bbc.in/3GZ5UMD

30/12/2023

ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ “የዘር ማጥፋት ድርጊቶች እየፈጸመች ነው” ስትል በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ መሰረተች።

የተከፈተው መዝገብ እስራኤል በዘር ማጥፋት ኮንቬንሽን ስር የተቀመጡትን ጥሳለች በሚል መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ችሎት አረጋግጧል።

እስራኤል ይህንን ውንጀላ “መሰረተ ቢስ” በማለት አጥብቃ ተቃውማለች።

የእስራኤል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር “እስራኤል ደቡብ አፍሪካ ስሟን በደም ልታጠለሸው የምታደርገውን ጥረት አጥብቃ ታወግዛለች” ሲል ተናግሯል።

https://bbc.in/3THS0Gz

30/12/2023
Photos from Babul Keyer NGO's post 29/12/2023
29/12/2023

የሰሜን ኮሪያው መሪ ጦራቸው ወታደራዊ ዝግጅቱን እንዲያፋጥን አዘዙ

የፒዮንግያንግ የጦር መሳሪያ አምራች ኩባንያዎች እና የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ሴክተሩም ጭምር ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርግ ነው ያሳሰቡት።

ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ዝግጅቷን ከማፋጠን ባሻገር ከ”ጸረ ኢምፔሪያሊስት ነጻ” ሀገራት ጋር ትብብሯን እንደምታጠናክር ነው ኪም ጆንግ ኡን የተናገሩት።

ተጨማሪ ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/kim-orders-military-accelerate-war-preparations

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


ካራቆሬ
Addis Ababa