ጓደኞቼ መፃሕፍት ናቸው

ጓደኞቼ መፃሕፍት ናቸው

Share

ታላቅ ለመሆን እንጣር ።

05/01/2022

ኑ እናንብብ …

01/02/2021

💊💊💊 የትውልድ ክኒን ! 💉💉 💉
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ትውልድን የሚያክሙ ሀኪሞች፣ትውልድን የሚቀርፁ መምህር ፣ ትውልድን የሚያነቁ ሰባኪያን ፣ ትውልድን በጥበባቸው የሚያጠቡሳይሆን ንቃተ ህሊናን የሚፈጥሩ የጥበብ ሰዎች ፣ በታሪክ ፣ በትልም ፣ በመቼት ……… በሰወኛ ፣ በእንቶኔ ፣ በአየዋ ፣ በአልጎሪ …… በስህላዊ እና በምናባዊ ድርሰት የሚደርሱ ደራሲያን እነዚህ ሁሉ በሙሉ ለሀገራችን ያስፈልጓታል !!! ትውልድ የማያውቀው ማንነት ተጭኖበት እኩሌታው በቅንጦት የተቀደደ ልብስ ይለብሳል ግማሹ እርቃኑን ይባዝናል ሌላኘው ደግሞ በሽሻ ፣ በጫት እና በሲጋራ ሳንበውን አጠልሽቶ ጥርሱን አበልዞ አሸሸ ገዳሜ ይላል ። እና እሳማ ሀገሬን የሚያዋልዳት ለፍትህ የቆመ የፍትህ ሰዎች ፣ ገለልተኛ ተቋም ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የወጣቶች ማህበር ያስፈልጋታል ።

👆💐💛💐💚💜💛💐💚💐💛

28/11/2020

አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር ሁላችንም አላፊነት አለብን በሉ ሰብሰብ እንበል እስቴ ።

21/11/2020

የኢትዮጵያ የዘመናዊ ፕሮጀከት ጠንሳሽ ማናቼው ??
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
17 ኛው ክ/ዘ በዘርያዕቆብ የተጀመረው የኢትዮጵያ ፍልስፍና እርስ በእርስ የተቆላለፈ ሁለት ዓላማዎች አሉት ። አንደኛው ለዕድገት እንቅፋት የሆኑ ባህሎችን ልምዶችን እና አስተሳሰቦችን መተቸት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኢትዮጵያን የማዘመን ሓሳብ ነው። ምንም እንኳን የዘመናዊነት ሀሳብ የተጀመረው በአውሮፓ ቢሆንም ዘመናዊነትን ከአውሮፓውያን ጋርብቻ ማስተካከል ግን ስህተት ነው ። ምክንያቱም የስልጣኔ መንፈስ የሰው ልጅ መንፈስ ብልሃት እና ዕውቀት ወዳለበት ይነፍሳል የስልጣኔ ሐብታት ከሰው የህሌና ጥረት የሚገኙ ስለሆነ በየትም ቢወለዱ ዘመዳሞች ናቸው እና ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

26/04/2020

ማንበብ ማንነታችን የምንፈትሽበት እና የወደፊት አቅጣጫችን መስመር የምናስዝበት ጉልህ መነፀር ነው ። share በማድረግ ይተባበሩኝ። በቅርብ ቀን ጠቃሚ ሃሳቦች እያነሳን እንማማራለን።

14/04/2020

ማንበባችን ነገ ለምንደርስበት ቦታ የተቀመጠ የማይናድመሰረት ነው !!!

10/04/2020

" ንጉሥ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት " የተባለው ለምንድነው ???
።።።።።።።።።።።።።።።።
ንጉሥ የፈረደበት ማለት ንጉሥ ከእግዚአብሔር በተቀበለው እደራሴነቱ የፈረደበት ይቀጣል ለአገልግሎቱ የመረጠው ተከብሮ ተሹሞ እና ተሸልሞበተድላ እና በደስታ በህይወት ይኖራል ።
ንጉሥ ይሙት በቃ ብሎ የፈረደበት ሳይውል ሳያድር ወዲያው የሞት ፍርድ ይፈረድበታል የንጉሥ ቃል ይግባኝ የሌለው ማንም የማያሻሽለው የፀናሕግነው ። ምክንያቱም የንጉሥ በላይ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ እና አምላክም በንጉሡ መንፈስ አድሮ ስለሚናገር እንኳን እንኳን በምድር በሰማየሰማያት የፀደቀ ለመሆን ስለሚችል ነው ።

መርከብ የተሰበረበት ማለት መርከብ በባህር ላይእየተንሳፈፈ በሰባቱ አህጉር የሚገኙትን የዓለም ፍጥረቶችን ከቦታ ወደ ቦታ የሚያዘዋውሩ ታላቁ ህንፃ ነው ። ምንም እንኳን የውቅያኖስ ውሃ መርከቡንከነምንገደኞች እንዳያሰጥም አስፀላጊውን ጥንቃቄ ቢደረግም በእግዚአብሔር ቁጣ ምክንያት ማዕበል ቢነሳ እና ቢገለብጠው በውስጡ የሚገኙትን የምንገደኞች ህይወት የሚያድን
አንዳች መጠጊያ አይገኝም ወደ ላይ ቢያንጋጥጡ ሰማዩን ወደታች ቢመለከቱ ተቀባዩን ጥልቅ ባሕር ከማየት በስተቀር ከቶ ምንም የሚያድን ነገር አይገኝም ።

04/03/2020

ንባብ ፦ ማለት ማንበልበል ወይም ማነብነብ ሳይሆን ፍሬ ሃሳቡንቆፍሮ እና ጨምቆ ማውጣት መቻልነው።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Abeba
Addis Ababa