26/07/2025
Meleket School/መለከት ት/ቤት, Addis Ababa
We, in Meleket School, create a favorable learning environment that provides a life-changing educational experience for all students.
26/07/2025
26/07/2025
ከምርቃት ስነስርዓት በከፊል
እንኳን ደስ አለን!
ሁሉም የ6ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን(100%) በአመርቂ ውጤት ማለፋቸውን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነዉ!
ልጆቻችን በስነምግባር ታንፃችሁ በውጤት እንደምታኮሩን ብናዉቅም ዛሬ ግን በተግባር አረጋግጠናል።
ውድ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ወላጆች ልፋታቹሁ ዋጋ አፍርቷል እና እንኳን ደስ ያላችሁ።
ለፈተና ዝግጅት ይረዳ ዘንድ በትምህርት ቤታችን ተገኝተው ተማሪዎችን ያበረታቱልን ዶ/ር እስማኤል አሊ እንዲሁም ከፈተና መልስ ተማሪዎች ዘና እንዲሉ አብረውን የነበሩት ማስተር አቤል አሰፋንም እጅግ በጣም እናመሰግናለን።
18/05/2025
https://www.facebook.com/100083113333529/posts/685074000939705/?mibextid=Nif5oz
"ዲላ ዩኒቨርሲቲ እያለቀስኩ ገብቼ እየሳኩ የወጣሁበት ግቢ ነው"
ቅድስት ዮሐንስ (ዶ/ር)
የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንት
ዶ/ር ቅድስት ከ1996 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂዎች አንዷ ናቸው። በአሁኑ ሰዓት የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ሁነው በማገልገል ላይ ያሉ ሲሆን በተካሄደው የቀድሞ ምሩቃን ፎረም ምስረታ ጉባዔም የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ፎረም ሰብሳቢ ሁነው ተመርጠዋል።
ዶ/ር ቅድስት በተማሪነት ዘመናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ሲመጡ የተሰማቸው ስሜት ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲወጡ ከነበራቸው ስሜት ጋር ፈጽሞ የተለያየ እንደነበር ሲገልጹልን "ዲላ ዩኒቨርሲቲ እያለቀስኩ ገብቼ እየሳኩ የወጣሁበት ግቢ ነው" በማለት ያስታውሱናል።
የ12ኛ ክፍል አጠናቅቄ ወደ ዲላ እስክመጣ ድረስ ለመማር እመኝ የነበረው የህግ ትምህርት፤ ያ ካልሆነም ኢኮኖሚክስ ማጥናት ምኞቴ ነበር ይላሉ።
ሆኖም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ወጥቶ በጋዜጣ ሲመለከቱ ካሰቡት ጋር የተለያየና ዲላ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መሆኑን ይረዳሉ። በወቅቱ የፈለጉት የትምህርት አለማግኘታቸው ብቻ ሳይሆን ዲላ የሚለውን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰሙት አስታውሰው ነገሮች ባላሰቡት መንገድ እንደሆኑባቸው በመረዳት ሐዘን እንደተሰማቸውና እንዳስለቀሳቸው ይገልጻሉ።
ባለታሪካችን በጊዜ ሂደት የመምህርነት ሙያ ክብርን በሚገባ እየተረዱ መጥተው መምህራንን ምሳሌነት በውሰድ ትምህርታቸውን በትጋት ተከታትለው በማጠናቀቅ እስከአሁን ድረስ እየኖሩበት ላለው የመምህርነት ሙያ ዲላ ዩኒቨርሲቲ መሰረት እንደሆናቸው ይናገራሉ። ለዚህ ደግሞ የቀድሞ መምህራኖች ሙያን እንዲወዱ ስላደረጓቸው ምስጋናቸውንና አክብሮታቸውን አልነፈጉም።
ዶ/ር ቅድስት በ1993 ዓ/ም ወደ ዲላ መምህራንና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአሁኑ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመምጣት ለ4 አመታት የከፍተኛ ትምህርታቸውን ከታተሉ በኋላ በ1996 ዓ.ም ሲመረቁ ከጓደኞቻቸው ጋር የነበራቸው ቅርርብ፣ የተቋሙ ሰራተኞች እና የአከባቢው ማህበረሰብ ፍቅርና ርህራሄ እንደማይረሳቸው አጫውተውናል።
"ዛሬ ድረስ ስለራሴ ሳስብ ቀድሞ የሚታየኝ እና ማንነቴን የሰራኝ ብዬ የማስበው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ነው" ሲሉ የሚገልጹት ዶ/ር ቅድስት፤ "የነበረኝ የዩኒቨርሲቲ ቆይታ 4 አመት ይሁን እንጂ በሕይወቴ ላይ ያመጣው ተጽዕኖ ግን ከዩኒቨርሲቲ ወጥቼ ከኖርኳቸው ይልቅ ጎልተው የሚታወሱ ናቸው" ይላሉ።
ከዓመታት በኃላ የቀድሞ ምሩቃን ፎርም ምስረታ ሲያካሂድ ከ21 ዓመታት ቆይታ በኃላ ዳግም ወደ ቤታቸው (ዲላ ዩኒቨርሲቲ) የመምጣት አጋጣሚውን ሲያገኙ በቃላት የማይገለጽ ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ዶ/ር ቅድስት ይናገራሉ።
የአልሙናይ ፎረም ምስረታ ለተቋማት ምን ያክል ትኩረት የሚሰጠውና አስፈላጊ መሆኑን በነበራቸው ልምድና ተሞክሮ እንደተረዱ የሚገልጹት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ፎረም ሰብሳቢ፤ በተለይ በውጪው ዓለም ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረሞችን ተጠቅመው ትላልቅ ስራዎችን ሰርተው ሲያዩ እኔስ ላስተማረኝ ዩኒቨርሲቲ በምን በኩል አስተዋጽኦ ማበርከት እችላለሁ እያልኩ ሳስብ በነበረበት ወቅት የፎረሙ ሰብሳቢ ሆኜ መመረጤ የብዙ ጊዜ ህልሜን እውን ለማድረግ ዕድል እንዳገኘሁ ተሰምቶኛል በማለት ይናገራሉ።
በተሰጣቸው ኃላፊነት ከሌሎች የፎረሙ ሃላፊዎችና አባላት ጋር በመሆን ፍሬአማ ስራ በመስራት ዩኒቨርሲቲውን በመደገፍ የበኩላቸውን አሻራ ለማኖር እንደሚሰሩ ገልጸውልናል።
*****//*****
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]
27/10/2023
28/09/2023
https://youtu.be/pCN8Vb2aaP4?si=OSIQ6wBdNgOyYTYb
በ ዞማ ሙዚየም የነበረን ልዬ የመስቀል በዐል ዝግጅት | የበዓል ዝግጅቶች | ሀገሬ ቴቪ በ ዞማ ሙዚየም የነበረን ልዬ የመስቀል በዐል ዝግጅትበማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን ፌስቡክ: http://FACEBOOK.COM/HAGERIE TV ትዊተር: https://TWITTER.COM/HAGERIET ኢንስታግራም: http://INSTAGRAM.COM/...
11/08/2023
Meleket Multiple Intelligence Inspired School is a progressive educational institution that values and nurtures the diverse strengths and interests of its students. It aims to provide a well-rounded education that prepares students for lifelong success and personal fulfilment.
ስገራሚው የሰው ልጆች እምቅ ችሎታ | መልክአ ሕይወት | ሀገሬ ቴቪ በኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ መምህርት ከሆነችው ዶክተር ቅድስት ዮሐንስ ጋር የነበረን ቆይታበማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙንፌስቡክ: http://FACEBOOK.COM/HAGERIE TVትዊተር: https://TWITTER.COM/HAGERIETኢን....
23/07/2023
የ2015 ተመራቂዎች
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Https://goo. Gl/maps/15FnDE4PUKudydcR 7
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 16:00 |
| Tuesday | 08:00 - 16:00 |
| Wednesday | 08:00 - 16:00 |
| Thursday | 08:00 - 16:00 |
| Friday | 08:00 - 16:00 |
| Saturday | 08:00 - 12:30 |