ስንቱን አየሁ

ስንቱን አየሁ አማራው ተራራው ተገፍቶ የማይወድቀው💪

21/02/2026

የአማራ ህዝብ ሰው ሰራሽ ረሃብ ተፈጥሮበታል። የአለም ህዝብ ሊያውቀው የሚገባ ሃቅ ነው

ውድ የስጦታው ቤተሰቦች አማራውያን ይሄኛው የፌስቡክ አካውንት ማሰጠንቀቂያ ስላመጣብኝ አዲስ የተከፈተ ተለዋጭ አካውንት እንድትጠቀሙ አሳስባለሁ። አዲሱን አካውን እየገባችሁ ፎሎው አርጉትhttp...
21/02/2026

ውድ የስጦታው ቤተሰቦች አማራውያን ይሄኛው የፌስቡክ አካውንት ማሰጠንቀቂያ ስላመጣብኝ አዲስ የተከፈተ ተለዋጭ አካውንት እንድትጠቀሙ አሳስባለሁ። አዲሱን አካውን እየገባችሁ ፎሎው አርጉት

https://www.facebook.com/share/173wvxQ9om/?mibextid=wwXIfr

አማራው ተራራው ተገፍቶ የማይወድቀው💪

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ ይፋት አውራጃ በሚገኘው በዘንቦ ቀበሌ የአርሶ አደሩ ቤት እየወደመ ነው ።" የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት በመተቀናጀ መልኩ በንጹሃን አርሶ አደሮች ላይ ጭፍጨፋና የንብረት ው...
21/02/2026

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ ይፋት አውራጃ በሚገኘው በዘንቦ ቀበሌ የአርሶ አደሩ ቤት እየወደመ ነው ።" የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት በመተቀናጀ መልኩ በንጹሃን አርሶ አደሮች ላይ ጭፍጨፋና የንብረት ውድመት እየፈጸመ ይገኛል።

ይህ የተቀናጀ ጥቃት አላማው የአማራን አርሶ አደር ከመሬቱ ማፈናቀልና ንብረቱን በማውደም ለችጋርና ለስደት አሳልፎ መስጠት ነው። ንጹሃን አርሶ አደሮች በማንነታቸው ብቻ እየተፈናቀሉና ንብረታቸው እየወደመ ባለበት በዚህ ሰዓት፣ ዝምታን መምረጥ ለጥፋቱ ተባባሪ መሆን ነው። እውነትን የምትወዱና ለፍትህ የምትቆሙ ወገኖች ሁሉ ይህንን በይፋት አውራጃ እየተፈጸመ ያለ ሰቆቃ ለዓለም እንድታሳውቁ ጥሪ እናቀርባለን።

20/02/2026

ለአፍሪካውያን የተላለፈ መልእክት ነው። በሁሉም ሚዲያ ሸር አርጉት።

25/12/2025

‼️
ይህ መልክት ለፋኖ አባላት ወንድሞቸ ነው።
ከጠላት ጋር ልትፋለሙ በተቃረባችሁ ጊዜ እንኳን ለናንተ የማይጠቅም እንዲህ አይነት ድርጊት ባታደርጉ እላለሁ። ጠላት በተጠጋህ ሰአት አድፍጠህ እንቅስቃሴ ሳታረግ መምታት እንጂ ያለብህ እንዲህ ወሬ ስታወራ ልትበላ ትችላለህ። ጓደኞችህንም ታጋልጣለህ። እባካችሁ የፋኖ አባላት እና አመራሮች ጥንቃቄ ይደረግ በቲክቶክ ዙሪያ‼️
ጠላት ተጨማሪ ድሮን በያቅጣጫው እያሰማራ በሚገኝበት በዚህ ወቅት መሰል ድርጊቶች ለጠላት ተጋላጭ ያደርጋሉና ነገሩን በቀላሉ ባታዩት እላለሁ።

ድል ለተጨቆነው ሰፊው የአማራ ህዝብ💪💪
ድል ለፋኖ💪💪
አዲስ ትውልድ‼️
አዲስ አስተሳሰብ‼️
አዲስ ተስፋ‼️

የጥንቃቄ መልዕክት !ትላንት ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE) የተነሳችና 7Q-ASU የምዝገባ ቁጥር ያላት ግዙፍ የጭነት አውሮፕላን (Ilyushin Il-76TD) መድረሻዋን ደብቃ በባህር ...
25/12/2025

የጥንቃቄ መልዕክት !

ትላንት ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE) የተነሳችና 7Q-ASU የምዝገባ ቁጥር ያላት ግዙፍ የጭነት አውሮፕላን (Ilyushin Il-76TD) መድረሻዋን ደብቃ በባህር ዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ማረፏ የተረጋገጠ ሲሆን አዳዲስ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችንም እንዳራገፈች አረጋግጠናል።

አገዛዙ ከኤምሬትስ ያስገባቸውን እነዚህ አዳዲስ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች (Su***de Drones) በክልሉ ለመሞከር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አውቀናል። ባለሙያዎችም አረቦች መሆናቸውን አረጋግጠናል።

ስለሆነም የፋኖ የማዘዣ ጣቢያዎችና የሰራዊት ስብስቦች ከአየር ላይ ጥቃት ራሳቸውን እንዲከላከሉ፣ የተበታተነ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉና የድሮን እንቅስቃሴዎችን በንቃት እንዲከታተሉ ቢደረግ ጥሩ ነው።

በአካባቢያችሁ የሚታዩ አዳዲስ የድሮን አይነቶችንም ሆነ ያልተለመዱ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን መረጃ በመለዋወጥ ለተጋድሎው ደህንነት የበኩላችሁን ተወጡ።

ቅናት አይሉት ምቀኝነት ሆኖባችሁ 24 : ሰአት ከመንግስት ጎን ተሰልፋችሁ በምታደርሱት መረጃ መከላከያ ገብቶ ቦታዉን ከወንድሞቻችን ቀምቷል።  በራሳችን ባንዳዎች መሆኑ እንዳይረሳ 👈 ለጊዜው ...
25/12/2025

ቅናት አይሉት ምቀኝነት ሆኖባችሁ 24 : ሰአት ከመንግስት ጎን ተሰልፋችሁ በምታደርሱት መረጃ መከላከያ ገብቶ ቦታዉን ከወንድሞቻችን ቀምቷል።
በራሳችን ባንዳዎች መሆኑ እንዳይረሳ 👈
ለጊዜው ይህ ቦታ በወራሪው ሰራዊት እጅ ቢወድቅም ይህን መሰል ስራ የሰሩ ጀግኖች በተለይ የአካባቢው የፋኖ አመራሮች እና የፋኖ ሰራዊት በትውልዱ ትልቅ ቦታ አላችሁ።

በምዕራብ ጎጃም ጃቢ ጠህና ወረዳ ከመሬት በታች 11 ክፍሎች ያሉት የኮንክሪት ምሽግ ነው ተብሏል። ምሽጉም በዋናነት የቁስለኛ ማከሚያ ሁኖ ሲያገለግል እንደቆየ ተገልጿል።

ለትግሉ የሚከፈል መስዋዕትነት እና ቀጣይ ምን መስራት እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያውቅ መሪ እና ሰራዊት ስለሆናችሁ ቁመን አጨብጭበናል።👏👏👏

ለጊዜው ለፎቶ የተቆጣጠረው ቢመስልም ቀጣይ የእኛ ነው!!

24/12/2025

ወልቃይትን ሰጪና ነሺ የሆነ ፋኖ የለም። ወልቃይት የግለሰብ ወይም የቡድን ጉዳይ ሳይሆን ወልቃይት የአማራ ሕዝብ ጉዳይ ነው ሲል አርበኛ አስረስ ተናገረ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ከኢትዮ ኒውስ ጋር ቆይታ አድርጓል።

አርበኛ አስረስ በነበረው ቆይታ፡ አገዛዙ ትጥቅ ላስፈታ ብሎ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪዎችን እንዲሁም ዘመናዊ የሠለጠኑ ወታደሮችን ከጥቅም ውጭ አድርገናቸዋል። አገዛዙ ደመሰስናቸው አጠፋናቸው በሦስት ወራት እና በሁለት ወራት ውስጥ እናጠፋቸዋለን እየተባለ የነበረ ቢሆንም አልተሳካም፡ በዚህ ሂደት ለውጭ ሀገራትም ጭምር አሸንፋለሁ ብሎ ተስፋ እየሰጠ የነበረበት ክሥተት ነበር ብሏል።

አሁን አለሁ ለማለትና ተስፋ ለመስጠት የማታለል ሥራ እየሠራ ነው። ይኸን ሲያደርግም መንገድ እየዘጋ ዝርፊያና ግድያ እየፈጸመ ነው። አዳራሽ ውስጥ ሰላም ይሰብካል ከውጭ ዘግናኝ ነገር ይፈጽማል። ሕዝቡ ከብልጽግና ምንም ተስፋ አያደርግም ፍላጎቱ ፋኖ ጦርነቱን አሸንፎ እንዲመራ ነው።
አርበኛ አስረስ ብልጽግና በየከተማው ሕዝብ እያወያየ ነው ግን ፋኖ የት ነው ለሚለው ጥያቄ ሲያብራራ፡ ፋኖ በየትኛውም ቦታ አለ ሕዝብ እያስተዳደረ ነው። ግን አገዛዙ ሪሶርሱን ለመጠቀም እየሞከረ ለአጭር ሰዓት እየሰበሰበ ነው።
መንግሥት የለም። መንግሥት አለ የሚባለው መዋቅሩን በትክክል ተግባራዊ ሲያደርግ ነው። አለን ለማለት ከተማ ላይ ይገኛሉ እንጂ የተለየ ነገር የለም። ከአዳራሻቸው ራቅ ብለው ተንቀሳቅሰው መሥራት አይችሉም። መንግሥት የሚባለው ሚዲያና ሌላ ሪሶርስ ስላለው እያስተዳደርሁ ነው ብሎ ይናገራል። እኛ ከባሕር ዳር ጎንደር፣ ከባሕር ዳር ደብረ ማርቆስ በአንድ ትዕዛዝ መንገድ እየዘጋን ነው። እናም ብልጽግና በዘመቻ ነው ስብሰባዎችን እያደረገ ያለው። በዘመቻና በስብሰባ መንግሥት መሆን አይቻልም። ከዚህ በፊትም እነ አበባው ታደሰና የክልሉ ካድሬዎች በኮምፖልቻና በሌሎች ከቶሞች ስብሰባ ሲያደርጉ ነበር ግን የተለየ ለውጥ የለም ነው ያለው አርበኛ አስረስ።

መንግሥት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴና ዘመቻ ሁሉን አቀፍ በመሆኑ በሕዝባችን ላይ ከባድ ጫና ስለተፈጠረ በሕዝቡና በአገዛዛዙ ዘንድ ከፍተኛ አለመተማመን ተፈጥሯል። በእያንዳንዱ ገጠርና ከተማ ያለን ሕዝብ ብንጠይቀው መንግሥት ይጨፈጭፈኛል ብሎ ነው የሚያስበውና ባለፉት ዓመታት የተሠራው ግፍ በሕዝቡ ላይ ከባድ ተጽኖ አሳድሯል። ሆኖም አገዛዙ ሠራዊት ስላለው የቴክኖሎጂ ብልጫ ስላለው ከተማ ላይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል። ነገር ግን በእኛ ላይ የሚያመጣው አንዳች ተጽኖ የለም። በሚዲያ መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። ከዚህ በፊት ሲያደርጋቸው የነበሩትን ነው እየፈጸመ ያለው ብሏል።

አርበኛው ቀጥሎም፡ መዋቅሩ ፈርሷል ስንል ፕሮፓጋንዳ እየሠራን አይደለም። ሕዝብን በአዳራሽ ሰብስቦ ሽማግሌዎችንና ሌሎች ተሰብሳቢዎችን ፋኖን ለምኑልኝ አስታርቁኝ ማለቱኮ አንዱ የውድቀቱ ማሳያ ነው። በብልጽግና መዋቅር በኩል የአማራን ሕዝብ የሚወክል አካል የለም። ብአዴንም ፈርሷል። ለዚያም ነው በመከላከያ ክልሉ እየተመራ ያለው። እናም በአዳራሽ ውስጥ የሚደረገውም ሐሜት ነው እንጂ ሐሳብ ላይ አያተኩሩም። ለዚያም ነው ጠቅላይ ሚንስትሩም ጩኸት ነው እያለ ሐሳባችንን ሲያጣጥል የነበረው። አክቲቪስታቸውም ካድሪያቸውም ወታደራቸውም ቋንቋቸው አንድ ነው የተሻለ ሐሳብ የለም። ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ሲሄድም በደፈጣ ውጊያ ዋጋ ከፍሎ ነው።

አርበኛ አስረስ ስለ ፋኖ ሥነ ምግባር ሲናገር፡ ከዚህ በፊት እንዳልሁት የፋኖ ስብስብ የመላእክት ስብስብ አይደለም፣ ከተለያየ ቦታ የመጣ ነው፣ አዲስ ኃይል ነው፣ የማኅበራዊ ንቅናቄ ውጤት የሆነ መሪና ሠራዊት ነው ያለንና ችግር ሊፈጠር ይችላል። በትግል ሂደት ውስጥ ሊከሠት የሚችል ነው። ሠራዊቱን እያሠለጥን ነው እየፐወዝነው ነው። አሳሳቢው ይኸ ሳይሆን የአገዛዙ የጅምላ ደፈራና ዝርፊያ እንዲሁም ግድያ ነው። ግን አገዛዙ ፈጥሮም ሆኖ ያየውን ትንሽ ስሕተት ያጮኸዋል። ዓላማውም ፋኖ የፖለቲካ ዓላማ እንደሌለው ለማስመሰል ነው ነው ያለው።
ዐቅም ካለው ማስተካከልና ማሸነፍ ይችል ነበር፣ ግን ምርጫው መጮህ ብቻ ነው ምክንያቱም ማድረግ ስለማይችል። ሌላም ግድያውን ማቆም የማይችለው እንደ ጦር ስልት ስለወሰደው ነው መንገድ ዘግቶ የሚገድለው የሚዘርፈው።

የእኛ ትልቁ ክፍተታችን የፋኖ አንድነት አለመኖር ነው። በዚህ ጉዳይ ማስተባበል አያስፈልግም። ትግሉ ስለትና ጠንካራ አንድነትና መሪ ይፈልጋል። ባለፉት ጊዜያት የነበሩት የሕዝባዊ ትግልና የመዋቅር መፍረስ ዘመቻ ውጤታማ ትግል ነበር። አሁን ግን አንድነት ባለማምጣቱ እንደ አንድ ችግር ሊወሰድ የሚገባና ሁሉም አመራር ሓላፊነት ሊወስድ ይገባል። በሁሉም ቀጠና ያለ አመራር ደፍሮ ለአንድነቱ ታሪካዊ ውሳኔ ሊወስን ይገባል ብሏል አርበኛ አስረስ።

አርበኛው ስለ ወሰንና ስለ ባንዳዎች ሲናገር፡ ብልጽግና ከኢሕአዴግ ከወረሳቸው ልምዶች አንዱ ጉዳዮችን ከሻብያና ከወየኔ ጋር ማገናኘት ነው። እናም አሁን ፋኖ ወልቃይትን ለህውሓት ይሰጣል ህውሓት ደግሞ አራት ኪሎን ለፋኖ ይሰጣል የሚለው የባንዳዎች ንግግር ከንቱ ወሬ ነው። ህውሓት ምን በወጣው ነው አራት ኪሎን ከተቆጣጠረ በኋላ ለፋኖ የሚሰጠው? አሁን እያየነው ያለ ነገር የባንዳዎች የወሬ ወይም የፕሮፓጋንዳ ፉክክር የገጠሙ ዐቢይን ለማስደሰት ነው። ዐቢይንና የብልጽግናን መዋቅር ለማስደሰት የሚደረግ ነው።
አሁን እጅ ሰጡ የተባሉት ግለሰቦች እንደማይጠቅሙ ያወቅናቸውና የጣልናቸው ገና ድሮ ነው። አመራር ነን ብለው የቆዩት የፋኖ አንድነት ስላልመጣ ነው። አሁን ወጥተው ቢናገሩም ምንም የሚያውቁት ምሥጢር የለም። የከዱ ባንዳዎች ቢገረፉም የሚናገሩት የኮር ሊደር ሺፕ ንግግር፣ ምሥጢርና ምክክር የለም። የአርቲስቶችን ድራማ ነው የሚያወሩት። ሌላው ወልቃይትን ሰጪና ነሺ የሆነ ፋኖ የለም። የግለሰብ ወይም የቡድን ጉዳይ ሳይሆን ወልቃይት የአማራ ሕዝብ ጉዳይ ነው። እንደዚህ የሚናገሩት የአማራን ሕዝብ ስለናቁት ነው ሲል ነው የገለጸው።

አርበኛ አስረስ ስለ ዐቢይ ዲፕሎማሲ ሲናገር፣ ዐቢይ ጭራሽ የዲፕሎማሲን አካሄድ አያውቅም። አይዲዎሎጂ የለውም። በዚህ ዘመን ዲፕሎማሲ ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው። አማራጭ ገበያዎችን ማጥናትና ትኩረት ማግኘት ያስፈልጋል። ከዚህ በፊት የደህንነት ጉዳዮችን ስትሸጥ የነበረች ሀገር ናት። ልምድ ያላት የዲፕሎማሲ ሀገር የነበረች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትትና ተመድን እንዲመሠረት ያደረገች አባልም የነበረች ናት።
ዐቢይ አሕመድ ከሕንድ መሪ ጋር ፎቶ መነሳቱ ለዝናው እንጂ ለሀገሪቱ ምንም አይጠቅምም። ሕንድ ምን ትሰጣለች ኢትዮጵያ ምን ትቀበላለች የሚለውን ማየት ግድ ይላል።
በፊት ከቱርክ ጋር ከቴክስታይልና ከባቡር ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበር አሁን ግን ግንኙነቱ በድሮን ጉዳይ ነው። የትም ሀገር ሂዶ በጦር መሣሪያ ዘሪያ ግንኙነት ነው እያደረገ ያለው። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ ስለሆነች ምንም የምትሰጠው ነገር የለም። በመጨረሻም የፋኖ ተጋድሎን ሰላምንና ሕልውናን የሚፈልግ ሰው ሁሉ መደገፍ አለበት። ሁሉም የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት ሲል ተናግሯል አርበኛ አስረስ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ስንቱን አየሁ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share