ቅኝት ፔጅ

ቅኝት ፔጅ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቅኝት ፔጅ, College & University, Addis Ababa.

19/02/2025

በቅዱሳት ገድላትና ድርሳናት ዙሪያ እንዲሁም በጥንተ አብሶ ዙሪያ

፩፦ እስካሁን በተመለከትኩት ገድላት አያስፈልጉም መወገድ አለባቸው የሚል ንግግርም ጽሑፍም ከኦርቶዶክሳውያን አልሰማሁም። ምክንያቱም ገድላትና ድርሳናት የወንጌል ትርጉሞች ናቸው። የቅዱሳን ሕይወት የሚታይ የሚዳሰስ የወንጌልን ቃል በተግባር የሚያሳይ ነውና።

፪፦ ነገር ግን በአንዳንድ ገድላትና ድርሳናት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ብዙ ስሕተቶች ሊገኝባቸው ይችላል። ይህ እንዳይፈጠር የሊቃውንት ጉባኤያችን ጠንክሮ ማዕከላዊ የቅዱሳት መጻሕፍት ኅትመት ቢኖረውና በዚያ ቢታተሙ መልካም ነው። ብሔርን ከብሔር የሚያጣሉ፣ ጥላቻን የሚያስተላልፉ ሐሳቦች በግል በሚታተሙት ገድላት ይስተዋላል።

፫፦ ለምሳሌ ቡና ይጠጣል ወይስ አይጠጣም የሚለው ክርክር ምንጩ ገድልና ድርሳን ነው። ለምሳሌ እኔ ከአምስት የገድላትና የድርሳናት መጻሕፍት ቡና እንደማይጠጣ የሚገልጽ አግኝቻለሁ። በተማርኩባቸው ጉባኤ ቤቶችና በየትኛውም የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት ቡና አይጠጣም የሚለው ሐሳብ ተቀባይነት የለውም። ታዲያ ጉባኤ ቤቶች ይህንን ሐሳብ ቀጥታ የመቀበል ግዴታ አለባቸውን?

፬፦ ባለፈው መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ (የጠቅላይ ቤተክህነት የትምህርትና ሥልጠና ክፍል ኃላፊ) ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በነበረው ሥልጠና እንደማሳያ ብለው ብዙ የተአምረ ማርያም ቅጅዎችን እንዳዩ ገልጸውልን ነበር። እና በአንዱ የብራና ተአምረ ማርያም ቅጂ አጼ ቴዎድሮስን እጅግ በጣም አክፋፍቶ የሚገልጽ እንዳገኙ ገልጸውልን ነበር። አስተውሉ በአንዱ ቅጂ ነው የተገኘ እንጂ በሁሉ አይደለም። ትክክልነቱ ምን ያህል ነው? የሚለው ጥናት ይጠይቃል።

፭፦ ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ ላይ ዮሐንስ አሥር ጊዜ ከተለያዩ እናቶችና አባቶች እንደተወለደ የሚገልጽ አግኝቻለሁ። ዮሐንስ መጀመሪያ የተወለደ ከአዳምና ከሔዋን ሲሆን ስሙም ያን ጊዜ "ሔና" ነበረ ይላል። ከዚያ በየዘመናቱ እየተወለደና መጨረሻ ላይ ከዘካርያስና ከኤልሳቤጥ ተወለደ ይላል። ይህ በአንድ ወቅት ደብረ ሊባኖስ ገዳም ግጭት ፈጥሮ ነበር። በወቅቱ በገዳሙ የነበሩት የንታ ብሩክ ይህ መስተካከል አለበት ሲሉ አንዳንድ ከመጻሕፍት ሩቅ የነበሩ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር ስለሌለ እንዳለ እንቀበላለን አሉ። ነገሩ ግን ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር መመርመር አለበት። ይህ በአንዳንድ የገድለ ዮሐንስ መጥምቅ ቅጂዎች አይገኝም።

፮፦ ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ላይ እስከ ዕለተ ምጽአት የጎጃም ሕዝብ ይቅር እንደማይባል ይገልጻል። በሌሎች ገድሎችና ድርሳኖች ለምሳሌ በገድለ አቡነ ሰላማ፣ በድርሳነ ኡራኤል፣ በገድለ ተከሥተ ብርሃን፣ በገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ ደግሞ እስከ ዕለተ ምጽአት ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ብለው እግዚአብሔርን የሚያመልኩና እግዚአብሔርም የሚወዳቸው በሃይማኖታቸውና በምግባራቸው የተመሰከረላቸው የጎጃም ሰዎች ናቸው ይላል። እና የትኛውን እንቀበለው? መመርመር አለበት። ራእየ ማርያም ላይ ሻን*ቅላ ለዘለዓለም እንደማይጸድቅ የሚናገር አለ። በእውነት ይህን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት የተናገረችው? ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ጋር አይጋጭም?

፯፦ እንደዚህ እርስ በእርሱ የሚጋጩ ጉዳዮች ገድላት ላይና ድርሳናት ላይ ይስተዋላሉ። ይህ በተለያየ ምክንያት ነው። አንዳንድ መምህራን ሚሲዮናውያን ኢትዮጵያውያንን ለማለያየት ያስገቧቸው ናቸው ይላሉ። ይህ ሁሉ ቢሆንም ገድላትና ድርሳናት የሚታረሙት እየታረሙ በማዕከላዊነት በጠቅላይ ቤተክህነት ቢታተሙ እነዚህን ችግሮች መቅረፍ ይቻላል።

፰፦ በጥንተ አብሶ ዙሪያ ለምሳሌ ማኅበረ ቅዱሳን ባሳተመው ሊቀ ጉባኤ

Photos from ቅኝት ፔጅ's post 30/01/2023

ጴንጤ ለኦርቶዶክስ ሲጨነቅ😂😂😂
ይሄን ሰሞን በየ ሚዲያው ላይ ጴንጤዎች ሲጨንቃቸው ሲጠባቸው እንቅልፍ አጥተው ሲፖስቱ ያድራሉ
።ምነው ተጨነቁ አስርገው ያስገቡት መናፍቃን አለ ማለት ነው አይመስልም??

Photos from ቅኝት ፔጅ's post 30/01/2023

በኮንሶ ዞን በጥር ወር ብቻ 967 ነፍሳት በኮንሰኛ ቋንቋ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አምነው መጠመቃቸው የወረዳ ቤተክህነት አሳውቋል
***

ቅድስት ቤተክርስቲያንን የአከባቢ ቋንቋን ለስርዓቷ ብቻ ሳይሆን ነፍስ ማደኛ ጥሩ የእግዚአብሔር ዕቃ ይሆን ዘንድ ሁሉ እየተጠቀመች ነው።

የአከባቢ ቋንቋ የአገልግሎት መጠን ዘመኑን በዋጀ መልኩ ባይሰፋም በእዚህ ምክንያት ወቀስ ልጀምር ካልክ ግን ከእራስህ ጀምር።

እግዚአብሔር ይመስገን !!

29/01/2023

የቤተ ክርስተ
ቲያን ጉዳይ በእጅጉ አሳሰበኝ

27/01/2023

ወደ አቶ አካለ ወልድ
ወደ አቶ አራርሳ
ወደ አቶ አሰፋ

ወርደዋል

Photos from ቅኝት ፔጅ's post 26/01/2023

ዮናታን እና ይህንን ድፍረት እንድታደርጉ ያደረጉ ፓለቲከኞችከውግዘት እስራታችሁ ይፈቷችሁ ዘንድ ይቻላቸዋልን??
አሁንም አልረፈደም ተመለሱ ክብር የሰጠቻችሁን ቤተ ክርስቲያንን ክብር ስጡ ለሕዝቡና ለራሳችሁ ስትሉ እራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ ለምትመሩት ምሳሌ ሁኑ ተመለሱ

Photos from ቅኝት ፔጅ's post 25/01/2023

ሰበር ዜና
ጥር 14 ቀን 2015 ዓ᎐ም በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የተመራው "የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት" ሕገ ቤተ ክርስቲያን የጣሰ በመሆኑ ከሕገ ወጥ ቡድኑ መውጣታቸውን መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ገለጹ።
አባ ጸጋ ዘአብ "አቡነ ኤጲፋንዮስ" በሚል በምሁር ኢየሱስ ገዳም "የበላይ ሓላፊ ጳጳስ" በሚል ተሹመው የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ምሽት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ "ያሳደገችኝን ቤተ ክርስቲያንን የከፈለ አባቶችንና ምእመናንን ያሳዘነ ድርጊት በመሆኑ የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸውን አሳውቀዋል።
ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር) በእንባ የይቅርታ ደብዳቤያቸውን አስገብተዋል።

Photos from ቅኝት ፔጅ's post 25/01/2023

የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም መከናወን ጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በማያውቀውና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ባልጠበቀ መንገድ የተሰጠውን ሕገ ወጥ "ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት" በማስመልከት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በአስተላለፉት ጥሪ ለሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ረቡዕ ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የመክፈቻ ጸሎት ማድረግ ተጀምሯል፡፡

የጸሎት መርሐ ግብሩ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት በመከናወን ላይ ነው፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን!

ሼር አድርጉት

25/01/2023

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ውጪ የሚደረግን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደማይቀበል የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአቋም መግለጫው አስታውቋል።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የአቋም መግለጫ
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ
ልዩ ጽሕፈት ቤት፣
ካይሮ፡ 24 ጃንዋሪ 2023 ዓ/ም (ጥር 16 ቀን 2015 ዓ/ም)
የአቋም መግለጫ
የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አቡነ ሳዊሮስ በተባሉ ጳጳስ የተፈጠረውን ቤተ ክርስቲያንን የመክፈልና ራሳቸውን በኢትዮጵያ የኦሮሞ ክልል ፓትርያርክ አድርገው የመሠየም ተግባር ሙሉ ለሙሉ የማይቀበለው ፍጹም ሕግን የጣሰ መሆኑና እና በእሳቸው መሪነት ተሾሙ የተባሉ 26 ጳጳሳት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሕግ የጣሱ እንዲሁም መሠረት ያለውን እና ቋሚ የሆነን ከጥንት ጀምሮ በትውልዱ ሁሉ ሲተላለፍ ከመጣውን ከኦርቶደክስ ቀኖና እና መመሪያ ሕገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ዕውቅና ውጭ የሚደረግን ሢመት ዕውቅና አትሰጥም አትቀበልም።

ከዚህ በተጨማሪ ኮሚቴው (የውጭ ጉዳይ) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ወዳጅነት እና አጋርነት እየገለጽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፤ ሜትሮፖሊታን የሆናቸሁ ሁላችሁ ጥንታዊነት እና በታሪክ የበለጸገች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ትሥሥር በፍቅርና በሰላም ሁናችሁ እንድትጠብቁ በጥብቅ አደራ እንላለን፡፡

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ

አባ ቶማስ የቂሊያ ሜትፖሊታን እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa