Zidaan mammadsali

Zidaan mammadsali

Share

www

26/08/2025

Maashaa Allah
Godina Jimmaa Bakka bu'uudhaan Mana maree dhimmoota Islaamummaa Oromiyaa irratti kan hirmaatanu ..

Sheyk Naziif Muusaa.Ulamah irraa
Naazimuu Huseen. Hayyuu irraa

10/07/2025

ምርጦቹን ምረጡ!
💥💥💥💥💥💥
በአሕመዲን ጀበል
💢💢💢💢

በቅርቡ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ምርጫ ሊደረግ በሂደት ላይ እንገኛለን።ሕዝባዊ ምርጫ በማድረግ መሪዎችን መምረጥ እጅግ አስፈላጊ መብት ነው። በነጻነትና በሰላማዊ መንገድ መምረጥን መለማመድ ያለበት ተግባር ነው። አሁን የሚመረጡትም ሆኑ የትኛውም አካል፥ ማንም ይሁን ማን የሆነ ጉባኤ አልያም ስብሰባ በማድረግ ከአሁን በኋላ ምርጫ አያስፈልግም ቢል መደመጥ ያለበት አይመስለኝም። ሕዝባዊ ምርጫ ቀርቶ በቡድን ምደባ፥ በድልድል አልያም በአንጃ ተመራርጦ ወደ መጅሊስ መግባትም የሕዝቡን መሪዉን የመምረጥ መብትን የሚነጥቅ በመሆኑ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም።

በጥቂትም ቢሆን አንዳንዶች «ማንን እንምረጥ?» እያሉ ይመክራሉ። ሌሎች ደግሞ የኔን ፎቶግራፍ ጨምሮ የተለያዩ ሰዎችን ምስል በመለጠፍ ሰው እንዲመርጥ ለመቀስቀስ ሲሞክሩ አያለሁ።

በግሌ በመጅሊስ ጉዳይ በመራጭም፥ በተመራጭም ሆነ በአስመራጭም የመሰማራት ፍላጎቱና ዝግጁነቱ እንደሌለኝ ቀደም ብዬ ጠቅሻለሁ። በመሆኑም እርሱ አለ በሚል መጠበቅ እንደማይገባ ደግሜ ለማሳወቅ እፈልጋለሁ። አላህ ካላ በቀጣይ ወዳቆምኩት የጽሑፍ ሥራዎች መመለስና በሌላ መልኩ ሚና እንዲኖረኝ እፈልጋለሁና።

በግሌ እገሌን መረጡ ወይም አትምረጡ የሚል መልዕክት የለኝም። ሆኖም ማንን እንምረጥ? ምን ዓይነት ሰው እንምረጥ? በሚል እየተመካከራችሁ ላላችሁ ወገኖች ምክር ለመለገስ ፈለግኩ። ብእሬንም አነሳሁ።እነሆ።

ከኔ ሀሳብ በፊት ግን የሚመርጡት ሰው ምን እንዲያደርግልዎ ነው መምረጥ የፈለጉት? የሚለውን በጥሞና ማሰብ ያስፈልጋል። ተመራጩ እንዲሰራልዎ የሚፈልጉት የሥራ ዘርፍ፥ እንዲወጣልዎ የሚፈልጉት ሚናን በሚገባ ሳይለዩ ስለ ግለሰቦች ማሰብ ለየትኛው የሥራ ዘርፍ ሠራተኛ እንደሚቀጥሩ ሳያውቁና ሳይወስኑ ማስታወቂያ በማውጣት ለመቅጠር እንደመሞከር ነው። ከሰውየው በፊት የሥራ ዘርፉና የሥራ መደቡ ተለይቶ መታወቅ አለበት።ይህ ሲሆን ሊሚፈለገው የሥራ ዘርፍ የሚፈለገውን ሰው የማግኘት እድሉ ይሰፋል።

የሥራ ዘርፍና ሚና ክፍፍል ጉዳይ በኢስላም
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁

ሙስሊሞች በዲናዊና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ እንደ እውቀትና ብቃት አቅማቸው፥ ዝንባሌና ዝግጁነታቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ኢስላም ይፈልጋል።ሁሉም ሰው በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍና መደብ ላይ ሊሆን እንደማይችልም እሙን ነው። ከፊሉ መሪ ሲሆን ከፊሉ መምህር ነው። ከፊሉ ታጋይ ሲሆን ከፊሉ ነጋዴ ነው። እንዲህ እያለ ሁሉም የየራሱን የሥራ ዘርፍ ይዞ አስተዋጽኦ እያበረከተ ሕይወቱን ይመራል። አንዱ ለሌላው እያገለገለ በጋራ መኖር የተፈጥሮ ሕግ ነው።

እንደ ቁርኣን ገለጻ ሌላው ቀርቶ ትልቅ ምንዳና ደረጃ በሚያስገኘው ለዲን የመታገል ዘርፍ እንኳ እጅግ አደገኛና የሁሉንም ሚና የሚጠይቅ ጉዳይ ካልተከሰተ በቀር በቀጥታ የትግል ዘርፍ ሁሉም ሙስሊም ሊሠማራ አይገባም። ለዚህም ነው ኢስላም ሙስሊሞች ሥራና ሚና መከፋፈል እንዳለባቸው የሚያስተምረው።ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ዘመን ሁሉም ሙስሊም ወደ ትግል (ጂ@ሓ@ድ) ሊሄድ (ሊወጣ) ሲነሳ ይህ መሆን እንደሌለበት አላህ(ሱወ) በመግለጽ የሥራ ክፍፍል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሷል። ቁርኣን እንዲህ ይላል፦

( وما كان المؤمنون لينفروا كافة فلولا نفر من كل فرقة منهم طائفة ليتفقهوا في الدين ولينذروا قومهم إذا رجعوا إليهم لعلهم يحذرون ( 122 )

«ምእመናንም(ከነቢዩ ጋር ካልሆነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም። ከእነሱ ዉስጥ ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም። (ሌሎቹ) ሃይማኖትን እንዲማሩና ወገኖቻቸው ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገስጹዋቸው ዘንድ (ለምን አይቀሩም)።»(ቁርኣን ሱራህ አል-ተውባህ፡122)

በዚህ የቁርኣን አንቀጽ ሦስት የዲን ኪድማ (ግልጋሎት) ዘርፎች ተጠቅሰዋል። አንደኛው ለዲን ሲሉ ዘምቶ መታገል፥ ሁለተኛው ዲንን ማስተማር ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ ወደ አላህ መንገድ ዳዕዋ ማድረግ ናቸው።በዚህ የቁርኣን ጥቅስ ዉስጥ ለዲን ተማሪዎችና አስተማሪዎች የተጠቀሰው ዘርፋቸው ዲንን መማር፥ ማስተማርና ዳዕዋ ማድረግ ናቸው። ዲን ተማሪዎችና አስተማሪዎች ዓሊሞች ስለሆኑ ለሁሉም ዘርፍ ብቁ ናቸው የሚል ሀሳብ አልተጠቀሰም።

እንዲያውም የሚገርመው ለዲን ትግል የወጡት ሲመለሱ ዲን የተማሩት ዳዕዋ በማድረግ ሊያስጠነቅቋቸው እንደሚገባ ተጠቅሷል።ይህ የሚያሳየን የዲን ዘመቻ ትግሉን መርቶ የሄደው ግለሰብና ተመርተው የተሳተፉት ሰዎች ዳዕዋ ለነርሱ እንደሚገባና ዳኢዎቹም ዓሊሞች መሆናቸው ፍንጭ ተሰጥቷል።

የሥራ ዘርፍና የሥራ መደብ ጉዳይ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

ሙስሊሞች ያላቸው ብቃትና ችሎታን አውጥተው ኢስላምን፥ ሕዝበ ሙስሊሙንና ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ በማድረግ ረገድ እንደ የአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) በጥበብ የተጠቀመ የለም። ሰሀቦች «መልካም ሥራ ምንድነው?» ብለው ሲጠይቋቸው ለተመሳሳይ ጥያቄ እንደ ጠያቂዎቹ ሁኔታ የተለያዩ ምላሾችን ሰጥተዋል። ለዲን የመታገል አቅምና ብቃት ላለው በአላህ መንገድ መታገል፥ ተግባቢ ሰው ሲሆን የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅና ሰዎችን ማቀራረብ፥ ቁርኣን የተማረ ከሆነ ቁርኣን ማስተማር፥ የገንዘብ አቅም ካለው በአላህ መንገድ ገንዘብን መለገስ፥ ለአንዳንዱ ሰዎችን ምግብ ማብላት፥ ለሌላው ደግሞ ወላጆችን መንከባከብ፥ ለጠያቂ ሴት ደግሞ ተቀባይነት ያለው ሐጅ ማድረግ፥ ወዘተ እያሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

የአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) የሰሃቦቻቸውን ዝንባሌ፥ብቃትና አቅምን በሚገባ በመረዳት እያንዳንዱ ሰሃባ ብቁ በሆነበት ዘርፍ ላለው ብቃት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ይህም እነዚያ ግለሰቦች የአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) ብቃታቸውን በተረዱበት መስክ እንዲቀጥሉ ለማነሳሳትና ሌሎችም የነርሱን ዘርፍና መደብ እንዲያውቁ ለማነሳሳት ነበር።ይህ የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) የሥራ ዘርፍና መደብ ክፍፍል እስከ ንዑስ ዘርፍ(sub specialization) ድረስ ዘልቆ የገባ ነበር። የዲን እውቀት በሚባለው ዘርፍ ራሱ በድፍኑ ዓሊም(ሊቅ) ብለው ከመመስከር ይልቅ በዲን ዘርፍ ራሱ የሰሃባ ዓሊሞች በየትኛው ዘርፍ ብቃት እንዳላቸው የመመስከር ነበር።

በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ያክል ነቢዩ ሙሐመድ(ሰዐወ) የሥራ ዘርፍና የሥራ መደብን በአግባቡ ለይተው እንደተጠቀሙ በሚገባ እንድንረዳ ዘንድ ምሳሌዎችን አንመልከት።

ሀ) የቁርኣን እውቀት ዘርፍ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የቁርኣን ዘርፍ ራሱ በተለያዩ ንዑስ ዘርፎች ተከፋፍሎ እናገኘዋለን። ከነዚህ መካካል ጥቂቶቹን እንመልከት፦

1) የቁርኣን ትርጉም(ተፍሲር) ዘርፍ
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
አብደላህ ኢብኑ አባስ፦ በቁርዓን ተፍሲር፤ አላህ ሆይ የቁርኣንን ታዕዊል አስተምረው ብለው ዱዓ ያደረጉለት።የቁርኣን ፈሳሪ(ቡካሪ የዘገቡት)

2) ቁርኣን በተጅዊድ የመቅራት ዘርፍ
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

አብደላህ ኢብኑ መስዑድ፦ አላህ ቁርኣንን ባወረደው መልኩ መቅራት የፈለገ እንደ ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ይቅራ።»(ሙስነድ አህመድ፥ ኢብኑ ማጃህ)

3) ቁርኣንን ባመረ ዜማና ቅለጼ መቅራት
🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄
«ከኔ ሕዝብ ዉስጥ ቁርኣንን ከሌሎች የበለጠ አሳምሮ የሚቀራው ዑበይ ኢብኑ ካዕብ ነው።»(ቡካሪ)፤ እና አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪ(ረዐ)፦ ያመረ ቁርዓን የመቅራት ችሎታ፤ «ከዳውድ ቤተሰብ መዛሚር መካከል ተሰጥቶሃል።» (ቡካሪና ሙስሊም የዘገቡት)

4) የቁርኣን(ወህይ) ጸሐፊ ዘርፍ
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
ዘይድ ኢብኑ ሳቢት፦ የቁርኣን ወህይ ጸሐፊ፤ የአይሁድ ቋንቋን ነቢዩ(ሰዐወ) ተማር ብለውት በ17 ቀናት የተማረ አስተርጓሚያቸው ነበር።

5) ሀላልና ሀራምን የማወቅ ዘርፍ
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል፦ ሀላልና ሀራምን በማወቅ ከነቢዩ(ሰዐወ) ዑማ በላጭ ነው። (ቲርሚዚ የዘገቡት ሀዲስ)

ለ) በነቢዩ(ሰዐወ) ሱና ዘርፍ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

1) ብዙ ሀዲስ በማስተላለፍ ዘርፍ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
አቡሁረይራ ፦ ከነቢዩ(ሰዐወ) ጋር 3 ዓመት ብቻ ቢቆይም ከርሳቸው በርካታ ሀዲስ በማስተላለፍ 1ኛ የሆነ ሰሃባ ነው። 5374 ሀዲሶችን አስተላልፏል።

2) ሐዲስን በተግባር በመኖር ዘርፍ
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር(ረዐ) ፦ የነቢዩን ሱና በመከተል የሚያክለው የለም»(ዓኢሻ ቢንት አቢበከር)

ሐ) የትግል ዘርፍ
🍀🍀🍀🍀🍀
1) የጦር መሪነት ዘርፍ
🔮🔮🔮🔮🔮🔮🔮
ካሊድ ኢብኑ ወሊድ፦ «ካሊድ ኢብኑ ወሊድ የተመዘዘ የአላህ ሰይፍ ነው።»(ሰሂህ አልቡካሪ)

2) የመረጃ ስብሰባ ዘርፍ
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሁዘይፈ ኢብኑ አል የማኒ፦ የነቢዩ ሚስጢር ጠባቂ። የሙናፊቆች ዝርዝር የተሰጠው፥ መረጃ የማሰባሰብ የደህንነት ሥራ የተሰጠው፥ ወደፊት ሙስሊሞች ላይ የሚከሰቱ ፊትናዎች የተነገረው ሰሃባ።

3) የጠላትን አንድነት በመታተን ለሕዝበ ሙስሊሙ ስጋትና አደጋ እንዳይሆኑ በማድረግ ዘርፍ፦ ኑዐይም ኢብኑ መስዑድ፦ ጠላትን ከፋፍሎ ማዳከም ሚና።

4) በጀግንነት ዘርፍ
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁

ጠልሃ ኢብኑ ዑበይዱላህ፦ ጀግንነትና መስዋዕትነት፦ በምድር ላይ የሚራመድ ሸሂድ ማየት የፈለገ ጠልሃን ይመልከት።»(ሃኪም፥ ሙስነድ አህመድ)

5) በፕሮፓጋንዳ ዘርፍ
🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ገጣሚው ሀሳን ኢብኑ ሳቢት

6) በሕዝብዊ መድረኮች ተናግሮ በማሳመንና በመከራከር ዘርፍ
🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮
ሳቢት ኢብኑ ቀይስ ኢበኑ ሸማስ፦ የነቢዩ ተናጋሪ(ከጢብ ረሱለላህ)፤- በሕዝባዊ መድረክ ላይ ባለው የመናገር፥ የመከራከርና የማሳመን ንግግር ችሎታው የተነሳ ነቢዩን
(ሰዐወ) ተክቶ የሚናገር ነበር።የተለያዩ ልዑካን ሲመጡ በመዲና እንዲናገር ነቢዩ(ሰዐወ) መርጠው እንዲናገርና መልዕክት እንዲያስተላልፍ ያደርጉት ነበር።

7) ትግልን በገንዘብ በመደገፍ ዘርፍ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ዑስማን ኢብኑ አፋን፦ በገንዘቡ ዲኑንና ዑማውን የካደመ። ከአሁን በኋላ ምንም ክፉ ነገር ቢሰራ አይጎዳውም የተባለ።

8) ለዲን በመቆርቆር ዘርፍ
🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀
የኢስላምና ሙስሊሞች ጠላት በሆኑት አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በመጎትጎት ዘርፍ ዑመር ኢብኑ አልከጣብ ጉልህ ሚና ነበረው።

9) የኢስላምን ባንዲራና እርማ የመሸከም ዘርፍ
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈
አሊ ኢብኑ አቡጣሊብ።

10) የጠላትን ቋንቋ ማወቅና መተርጎም
🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆

ዘይድ ኢብኑ ሳቢት የጠላትን የአይሁድን ቋንቋን እንዲማር ነቢዩ(ሰዐወ) መድበውት ተምሮ የነርሱን ንግግር መከታተልና የመተርጎም ሚና ነበረው።

11) የቆሰሉ ታጋዮች የማከምና የማገዝ ዘርፍ
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈
ዓኢሻ ቢንት አቡበከርና ዑሙ ሱለይም።

ሐ) በዓለም ዓቀፍና የሀገር ዉስጥ አምባሳደርነት ዘርፍ
📡📡📡📡📡📡📡📡📡📡📡📡📡📡📡

የአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) ለዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች የሚልኳቸው የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ፥ ስለዓለም ዓቀፍ ሀገራት ግንዛቤ የነበራቸው አምባሰደሮች ነበሯቸው። ለምሳሌም፦

1) ሐጢብ ኢብኑ አቢበልታ- ወደ ግብጽ መሪ የተላከ አምባሳደር።

2) አብደላህ ኢብኑ ሑዛፋ፦ ወደ ፐርሺያ መሪ የተላከ አምባሳደር።

3) ዓምር ኢብኑ ዑመያ አል-ዷሚሪ፦ ወደ ሀበሻ መሪ ነጃሺ የተላከ አምባሳደር።

4) ደህያ ኢበጁ ከሊፋህ አል-ከልቢ፦ ወደ ቤዛንታይን መሪ የተላከ አምባሳደር።

5) የሀገር ዉስጥ መልዕክት የማድረስ ዘርፍ፦ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር፦ የመጀመሪያው የኢስላም አምባሳደር።

መ) በላቀ ሥነምግባር ዘርፍ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

1) በእውነተኝነትና በጽኑ እምነት ዘርፍ፦ አቡበከር አል-ሲዲቅ፤ ፍጹም ኢማን፥ እውነተኝነትና ጽናት ያለው። ለዚህም ነበር

16/09/2022
Photos from Zidaan mammadsali's post 15/09/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ 12ኛው ዓለም አቀፍ ኢስላማዊ ፋይናንስ አዋርድ (GIFA) ተሸላሚ ሆኑ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

ሀሩን ሚዲያ፥ መስከረም 4/2015
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ 12ኛው ዓለም አቀፍ ኢስላማዊ ፋይናንስ ሽልማት (GIFA) ተሸላሚ መሆናቸውን ተቋሙ ይፋ አድርጓል። አለም አቀፉ ኢስላማዊ ፋይናንስ ሽልማት በኢኮኖሚ መስክ የፋይናንስ አካታችነት እንዲኖር እና የፋይናንስ ሥርዓቱ ላይ ለሠሯቸው የሪፎርም ሥራዎች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን በተለያየ ዘርፍ ለሚገኙ አካላት እውቅናውን ይሰጣል።
.
በዚህ አመት የሚካሔደው 12ኛው ግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንሺያል አዋርድ (GIFA) እና ግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንስ ሰሚት (GIFS) 2022 በጅቡቲ በሚገኘው በኪምፒንስኪ ቤተ መንግስት ይካሄዳሉ። የዘንድሮው ዝግጅት በጅቡቲ መንግስት ጥያቄ መሠረት በጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ለመገኘት ወደ አዘጋጇ ሀገር ጅቡቲ አቅንተዋል።
..
ከ5 አህጉራት እና ከ15 በላይ ሀገራት የተውጣጡ በኢንደስትሪው ዘርፍ እና በገበያ እንቅስቃሴ በኩል ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ኢስላማዊ የባንክ እና ፋይናንስ ስርአትን ለማስተዋወቅ ላደረጉት ጥረት እውቅና እና ሽልማት ያገኛሉ። ግሎባል ኢስላሚክ ፋይናንሺያል አዋርድ (GIFA) በየመስካቸው የላቀ ስኬት ላሳዩ መንግስታት፣ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና የሚሰጥ ተቋም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ጅቡቲ ከተማ የደረሱ ሲሆን፣ ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
.
© ሀሩን ሚዲያ
___________
በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia
በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j

haadhamilkii326 on TikTok 04/09/2022

haadhamilkii326 on TikTok 55 Followers, 394 Following, 19 Likes - Watch awesome short videos created by haadhamilkii326

Photos from Sabboonaa Laayin Koonistiraakshinii fi riilisteetii damee Sigimoo's post 07/02/2021
10/01/2021

አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከአገር መከላከያ ሠራዊቱን በማስከዳት ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩና በጦርነቱ ከሠራዊቱ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና የግል ጥበቃዎቻቸው ላይ እርምጃ መወሰዱንም የመከላከያ ሠራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።

ብርጋዴል ጄኔራሉ ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል የፍተሻ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም ተገልጿል። ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ እንደገለፁት የቀድምው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የጁንታው ሲቪል አመራሮች እንዲሁም ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ አመራሮችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-

1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረና አሁን የጁንታው ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረ

2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበረና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ጁንታውን የተቀላቀለ

3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች

4ኛ - ሁለት መስመራዊ መኮንኖች

5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ጁንታው የተቀላቀለ ናቸው።

በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ገልፀዋል።

እነዚህም

1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ

2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ

3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ

4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ

5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ

6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ

7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሁለት ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ መሆናቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ለኢዜአ ገልፀዋል።

10/01/2021

Muddamatu gargar diiga
""""""""""""""""""*"""""""""""""""""""
Har'a lafti qotamee
Har'uma hin faca'u
Ammuma sanyiin faca'ee
Daraaree firii hin ta'u
Yookiin Asheetiin gogee
Daakamee irbaataa hinta'u.

Har'uma nyaanna jedhe
Kan qarriffaa qaratee
Nu ijaaruu fakkeesse
Kan nu diiguuf karoorfate
Galmi keenya dheeratus
Imalli keenya yoom gufate?

Duruu tokkummaa keenya
Muddamat gargar diiga
Namuu waan fedhe dubbachuuf
Guuttatee qaba mirgaa
Kan kaayyoof galma qabu
Milkaa'uuf buusa dhiiga

Kan karoorsine dhugoomsuuf
Jabaanne waliin fiigna
Obsaamaan wal ijaareeti
Tulluu hiyyummaa diigna!!!

Haasawa daayireektara ol aanaa dhaabbaticha Obbo Tofik Kedir keessaa kan qindeeffamedha!!!

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Addis Ababa