Henok beyene

Henok beyene

Share

Debre Berihan university

27/11/2025

+ የካህን ጡረታ የለውም +

ከልጅነታችን ጀምሮ በቤተ መቅደስ ያሳደጉን ድንቅ ድንቅ አባቶች ዛሬ ትዝ አሉኝ፡፡ ግርማ ሞገሳቸው ቅኔ ማሕሌቱን የሚሞላ ፣ መንበሩን ለማየት እስኪያስቸግር ድረስ ማዕጠንታቸው ደመና የሚሠራ ፣ ኪዳን ሲያደርሱ ፍርሃታቸው ፍርሃት የሚያጋባ ፣ እግዚኦታቸው ልብ የሚሰነጥቅ ፣ ዳዊታቸው አጋንንት የሚያርድ አባቶቼን ዛሬ አሰብኳቸው፡፡

ክህነት ማላገጫ በሆነበት በዚህ ዘመን ላይ ሆኜ ፣ የቅትለተ ዘካርያስን ዋዜማ እያየሁ አደግድገው ግብረ ሕማማት አንብበው የሚሰግዱትን ፣ የክት ልብሳቸው መቀደሻ የሆነላቸውን ፣ ሰዓታት ቆመው ፣ ማሕሌት ቆመው ፣ ዞረው አጥነው ፣ ክርስትና አንሥተው ፣ ፍትሐት ፈትተው ፣ በሽተኛ ጠይቀው ፣ የተጣላ አስታርቀው ፣ ሌሊቱን ቆመው አድረው ቀኑን ክርትት ሲሉ የሚውሉትን አባቶች ዛሬ አሰብኳቸው፡፡

አባ መቃርስ ስለ አባ ጳውሊ ሊተርክ ሲጀምር ‘መነኩሴ አይደለሁም ፤ መነኩሴ ግን አይቼ አውቃለሁ’ ብሎ ነበር፡፡ እኔም ዛሬ ልበል ‘አባት አይደለሁም አባቶችን ግን አይቼ አውቃለው’

መስቀላቸው በትልቅ ሰበን የተሸፈነች ፣ ሲያሳልሙ በውድ መዓዛ የሚያውድ መስቀል ያላቸው ፣ ጥምጥማቸው የደመና ክምር የመሰለ ፣ ጥና ይዘው ሲዞሩ መሬት የሚረግጡ የማይመስሉ ፣ መንበሩ ፊት ሲቆሙ የሚብረከረኩ ፣ ሥርዓት የሚጠነቅቁ ፣ እንደ ፀሐይ የሚያንጸባርቁ ፣ ጭራቸው ከሽበታቸው ጋር ቀለሙ አንድ የሆነ አባቶቼ አስቤ ትካዜ ውስጥ ገባሁ፡፡

ከቤተ እግዚአብሔር ውጪ መሔጃ የላቸውም ፤ ተረኛ ባይሆኑም ከመቅደሱ አይለዩም፡፡ ዕረፍት ቢሠጣቸው ከደጁ ርቀው ዕረፍት የላቸውም፡፡ የመጣ የሔደው የሚያዝዛቸው ፣ ብዙ እንዳላገለገሉ ሁሉ አጎንብሰው የሚታዘዙ የቤተ መቅደሱ አእማድ ካህናትን አሰብኳቸው፡፡

ቄስ ሀብቱ ዛሬ ትዝ አሉኝ፡፡ ጥምጥም ተሳክቶላቸው አያውቅም፡፡ የሚጠመጥሙት ደግሞ ቢጫ ጥምጥም ነበር፡፡ አጠማጠሙ ግን አይሆንላቸውም፡፡ ልጆች ነበርንና ስናያቸው ፈገግ እንላለን፡፡ ቅዳሴ ይወዳሉ፡፡ ሰሞነኛ ሆነውም ሳይሆኑም ለራሳቸውም ለሌላውም እሺ ብለው ይቀድሳሉ፡፡ ዛሬ ግን ያነሣኋቸው የንስሐ ልጆቻቸው ትዝ ብለውኝ ነው፡፡

የቄስ ሀብቱ የንስሐ ልጅ ለመሆን ፈልገህ ሔደህ ብትጠይቃቸው እሺ አይሉህም፡፡ እርሳቸው የሚቀበሉት የንስሐ ልጅ እስረኛ የሆነ ብቻ ነው፡፡ የትኛውም ወህኒ ቤት ያሉ እስረኞች የእርሳቸው ልጆች ናቸው፡፡ ለዕድሜ ልክ ወይም ለብዙ ዓመታት የታሰሩ አለዚያም ፍርድ የሚጠባበቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የቄስ ሀብቱ ልጆች ናቸው፡፡

ወህኒ ቤቶች ለእርሳቸው ወለል ብለው ይከፈታሉ፡፡ ጥበቃዎች በአክብሮት ያስገቧቸዋል፡፡ እየዞሩ እስረኞቹን አሳልመው ፣ ጸሎት አድርገው ፣ ንስሐ የሚገባ ካለ ሰምተው ፣ ጸሎተ ንስሐ ደግመው ይወጣሉ፡፡ ሥራቸው ወህኒ ቤት ብቻ አያበቃም፡፡ የእስረኞቹን ቤተሰቦች ደግሞ ዞረው ይጠይቃሉ፡፡ መልእክት ያደርሳሉ፡፡ የታመመ ቤተሰብ ካለ ይጠይቃሉ፡፡ የሞተ ካለ እስረኛውን ወክለው ቀብሩን ያስፈጽማሉ፡፡ እስረኛውም ባለበት መርዶ መስማት ካለበት ያረዳሉ፡፡ ያጽናናሉ፡፡

ሦስተኛው ሥራቸው ደግሞ ቢጫ የክላሰር ሽፋን ያላት መዝገባቸው ናት፡፡ በዚያ መዝገብ ላይ የእስረኞቹ የፍርድ ቤት ቀጠሮ አለ፡፡ ቀኑ ሲደርስ ባለ ቢጫ ጥምጥሙ ቄስ ሀብቱ እስረኛውን ተከትለው ችሎት ላይ ይታደማሉ፡፡ ሙሉ ቀን ከወህኒ ቤት ፍርድ ቤት ፤ ከፍርድ ቤት የእስረኛ ቤተሰብ ጋር ሲንከራተቱ ይውሉና ማታ ሰዓታት ይቆማሉ፡፡ ጠዋት ቅዳሴ ይቀድሳሉ፡፡ እኛ ደግሞ ተስተካክላ ያልተጠመጠመች ጥምጥማቸውን እያየን እንሳሳቃለን፡፡ ቄስ ሀብቱ ያረፉ ቀን ቀብራቸው ላይ ሁሉም ሰው የሚያለቅሰው ‘አባቴ አባቴ’ እያለ ነበር፡፡ የሥጋ ልጆቻቸውን ለይቶ ማወቅ አይቻልም ነበር፡፡

ዛሬ ወርቆቹ ጸሎተኛ አባቶች ትዝ አሉኝ፡፡ ‘ተዘከር’ ሲሉ ምነው ሞቼ በተጠራሁ የሚያሰኙት ምስኪን ካህናት ፣ ከቤተ መቅደስ ውጪ ሕይወት የሌላቸው እነዚያ የመቅደስ መብራቶች ትዝ አሉኝ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ገባን ብለን ስንነግራቸው የወለዱት ልጅ ያህል የፈነደቁ ፣ በሰበብ በአስባቡ ‘ክህነትህን ይባርክ’ ብለው ያሳደጉን አባቶችን አሰብኳቸው፡፡ ትንሽ ሳንቲም ማግኘት ስንጀምር ምን ላድርግልዎ ስንላቸው ጥያቄያቸው ከመስቀልና ከዳዊት ከፍ ቢል ከካባ የማያልፈውን አባቶች ዛሬ አሰብኳቸው፡፡

መጋቤ ሃይማኖት ገብረ ማርያም የመጽሐፍ መምህር ናቸው፡፡ ቤተልሔም ገብቶ እርሳቸውን ሳያገኝ የሚወጣ የለም፡፡ ጸሎት አያስታጉሉም፡፡ ጸሎት ሲጨርሱ ስንክሳር ያነባሉ፡፡ ከዚያ ትርጓሜ ወንጌል ያነባሉ፡፡ አንድ ጊዜ መጽሐፈ ሄኖክ ትርጓሜ ሲታተም ደስ ላሰኛቸው ብዬ ገዛሁላቸው፡፡ ስሠጣቸው ደስ ይላቸዋል ብዬ ነበር፡፡ ክው አሉ፡፡ ‘መጽሐፈ ሄኖክ ተተረጎመ?’ አሉኝ፡፡ አዎ አልኩኝ፡፡ ‘ዓለም ሊያልፍ ነው ማለት ነው’ አሉና ተከዙ፡፡ በጊዜው በጣም አሳቀኝ፡፡ ለምን እንኳን ብዬ አልጠየቅኳቸውም፡፡

በኋላ ግን መጽሐፈ ሄኖክ እና የዮሐንስ ራእይ ያላቸውን ትሥሥር ፣ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን የዮሐንስ ራእይ ከመጽሐፈ ሄኖክ የተቀዳ ነው እስከማለት ያስደፈራቸውን የነገረ ምጽአት እውነታዎች ሳይ የየኔታ ገብረ ማርያም ድንጋጤ ተራ ነገር እንዳልሆነ እየገባኝ መጣ፡፡

መምህር ገብረ ማርያም ስብከተ ወንጌል ላይ ያገለግሉ ነበር፡፡ በኋላ ሹማምንት ሲቀያየሩ ከስብከተ ወንጌል መደበኛ ሥራ አገዷቸው፡፡ ማስተማር ሕይወታቸው ስለሆነ ቅዳሜ ቅዳሜ አድንኑ ከተባለ በኋላ ሕዝብ እስኪበተን ድረስ ያስተምሩ ነበር፡፡ ከመቅደሱ መለየት አይፈልጉም ነበር፡፡ ድንገት አንዱ መጥቶ እንዳያስተምሩ አገዳቸው፡፡ አዝነው ከቤት ታመው ቆዩ፡፡ ወር ሳይሞላ ዐረፉ፡፡

ይህ የብዙ አረጋውያን ካህናት ታሪክ ነው፡፡ በዕድሜ ብዛት ቢደክሙ ዕረፍት እንዲያደርጉ ተፈቅዶ እስኪያልፉ ድረስ ቤተ ክርስቲያን ልትጦራቸው ይገባል:: ከዚያ ውጪ ግን ካህን በጡረታ ተገለለ የሚባል ነገር የለም:: የካህን ጡረታ የለውም፡፡ የማያንቀሳቅስ ደዌ ካልያዛቸውና የአልጋ ቁራኛ ካልሆኑ በቀር ካህን አረጀ ተብሎ ከመቅደሱ ሊገለል አይገባም፡፡

ሕይወቱን ሙሉ በእግዚአብሔር ቤት የደከመ ካህን እንዴት በመጨረሻ ዓመታቱ እንደማይጠቅም ይተዋል? ንዋያተ ቅድሳት ቢሰበሩ አክብራ የምታስቀምጥ ቤተ ክርስቲያን የከበረው ካህንዋን ተሰበረ ብላ ልትጥል ትችላለችን? ከመንግሥት ሥራ በጡረታ የተገለሉ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣሉ:: ከቤተ ክርስቲያን ጡረታ ውጡ የተባሉ አባቶች ወዴት ሊሔዱ ይችላሉ? እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ "እግዚኦ ኀበ መኑ ነሐውር:: እንዘ ቃለ ሕይወት ዘለዓለም ብከ" "ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሔዳለን? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ" ይሉ የለምን? (ዮሐ. 6:65)

ካህንና ወይን አንድ ናቸው፡፡ ዕድሜው ሲጨምር ብስለቱ ፣ እርጋታው ፣ ጥበቡና መንፈሳዊነቱ ይጨምራል፡፡ እንዴት ሰባ ዓመት የቆየ ወይን እንደ ውኃ ይደፋል? ሲቀድስ ፣ ሲያወድስ ፣ ሰዓታት ማሕሌት ሲቆም ፣ ክርስትና ሲያነሣ ፣ ፍትሐት ሲፈታ ፣ ዳዊት ሲደግም የኖረ ካህን እንዴት አረጀ ይባላል? ለመቅደሱ ግርማ ሞገስ ፣ ለደጀ ሰላሙ አክሊል የሆነ አረጋዊ ከተገኘ ካባ እንጂ ጡረታ እንዴት ይገባዋል?
ቅዱስ ጳውሎስ "ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝ" እንዳለ ካህናትም ኃይላቸው እንደ ንስር የሚታደሰው ሲደክሙና ሲያረጁ ነው::

የጸሎት ጡረታ ፣ የአገልግሎት ዕረፍት የለም፡፡ ሕይወታቸው ቤተ ክርስቲያን ናትና ‘ይበቃችኋል አትምጡ’ ሲባሉ የመኖር ትርጉም ጠፍቶባቸው ወዲያውኑ ይሞታሉ፡፡ ይህ ደግሞ ብዙ መርገም ያመጣል፡፡ በየአድባራቱ ያሉ አረጋውያን ካህናት የደብሩ እጅግ ውድ ቅርስ ናቸው፡፡ የታሪክ መዝገቦች ፣ የጸሎት ምዕራጎች ፣ የስብሐተ እግዚአብሔር መሰላሎች ናቸው፡፡ እነዚህ አረጋውያን ካህናት የቀረቻቸውን ጥቂት ዕድሜ ደሞዛቸው ሳይጓደል ፣ ጥቅማቸው ሳይነካ እንደተከበሩ እየባረኩ እየጸለዩ ዳዊት እየደገሙ ቢቆዩ ለቤተ ክርስቲያን ክብር ናቸው፡፡ ጉልበት ስመን ፣ መርቀውን ቢሔዱ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ የሽበት ዘውድ ለደፉ አረጋውያን ካህናት ካልሆነ ለማን ይሆናል?

እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ ያልተቋረጠ ጸሎታቸው እንዳያልፈን ፤ መርቀውን እንዲሔዱ ፣ እንደ ይስሐቅ በረከታቸውን ፣ እንደ ያዕቆብ የእጅ መስቀላቸውን ፣ እንደ ኤልያስ መጎናጸፊያቸውን እንዲሠጡን ልንሻማ ይገባናል፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 2018 ዓ.ም.

27/02/2023

ሰበር ዜና!!!

ቴዲ አፍሮ 1,000.000.00 ብር ለቦረና



ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ለቦረና ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ የሚውል 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር ለግሷል።

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ የዘንድሮን የዓድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ በድርቅ ሳቢያ አስቸኳይ እርዳታ ለሚፈልገው የቦረና ሕዝባችን የ1ሚልየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

በዳግማዊ አፄ ምኒልክ መሪነት መላው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ዓድዋ ላይ ወራሪን ድባቅ በመምታቱ በዓለም የነጻነት መድብል ውስጥ ኢትዮጵያ የታሪክ ማማ ላይ መስፈር ችላለች። 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በምናከብርበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያዊያን ኹሉ በትብብር እና በአንድነት በመቆም የአያቶቻችንን አደራ መጠበቅ ይገባናል።

በዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል እንደ ወትሮው ኹሉ የአፍሪካ የነጻነት ፈር ቀዳጅ የጥቁር ሕዝብ ኹሉ ኩራት በሆኑት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ አደባባይ ላይ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ እንደሚያከብር በመተማመን ሕዝባችን በዓሉን በታልቅ ክብር ሲዘክር የዓድዋ ጀግኖችን አንድነት በመውረስ በድርቅ ሳቢያ ለችግር የተጋረጠውን የቦረና ሕዝባችን በአስቸኳይ እንዲታደግ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ለዚህ ዘመቻ የመጀመሪያውን 1,000,000.00 (አንድ ሚልየን) ብር በመለገስ ፈር ቀዳጅ በመኾኑ የተሰማንን ኩራት እና ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን።

በዝርዝር እንመለስበታለን።
Via - ያሬድ ሹመቴ



የማይበላሹ ደረቅ ምግቦችን በመያዝ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ልገሳዎቻችሁን ይዛችሁልን ኑ!!!







Photos from Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)'s post 01/02/2023
29/01/2023
29/01/2023

[ጥር ፳፩ የእመቤታችን ዕረፍትና የሊቃውንት ውዳሴ]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደገለጹልን የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር፤ በቤተ ዮሐንስ 15 ዓመት ከቆየች በኋላ፤ ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት።

💥 ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፤ ያን ጊዜ የአምላክ እናት ፊት ተሰብስበው ከእጆቿ በረከትን አገኙ፡፡

💥 ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ጌታም ተገልጾ "ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳን “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ በማለት ተናገረ።

💥 ከዚያም ጌታ እናቱን "የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ፤ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በነበልባላማ ሰይፋቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡

💥 የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ አላት፡፡

💥 ይኽን ከልጇ በሰማች ጊዜ ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ።

♥❖♥ ቅዱስ ያሬድም በመጽሐፈ ድጓው ላይ፡-
“ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና (ለማርያም)
ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና
ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና”

(በማርያም ዕረፍት ጊዜ ወልድ ከልዕልና ወረደ፤ የንግሥና (የክብር) መጐናጸፊያን በዚያን ጊዜ ሸፈናት) በማለት የዕረፍቷን ነገር አስተምሯል፡፡

♥❖♥ የመልክአ ማርያምም ጸሐፊ በአድናቆት፦
“ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ ጻዕር ወጻማ
ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ”

(ከሃሊ (ማእምር፣ ጠቢብ) በሚኾን ልጅሽ ቀኝ ዘወትር ለመቀመጥ ያለ ድካምና ያለ ጣር ለኾነ የነፍስሽ መለየት ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፨

💥 ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፤ የከበረ ሥጋዋም የጠራና መዐዛው ድንቅ ነበር።

♥❖♥ የመልክአ ማርያም ደራሲው ሊቁ፦
“ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ
ዘተመሰለ ባሕርየ"

(ዕንቊን ለተመሰለ የጠራ የሥጋሽ በድን ሰላም እላለኊ) በማለት ያመሰግናል።

💥 ከዚያም ቅዱሳን ሐዋርያት በዚያ አስደናቂ መጎናጸፊያ በክቡራን ሽቱዎች የከበረ ሥጋዋን አጅ እየነሡ ገንዘዋታል።

💥 ሊቁም በመልክአ ማርያም ላይ፦
“ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ
በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕጹብ"

(የዋጋው ስሌት እጅግ ውድ በኾነ ያማረ ሽቱ ርግቦች በተባሉ በሐዋርያት እጅ ለተደረገ የሥጋሽ አገናነዝ ሰላምታ ይገባል) በማለት ያመሰግናል።

♥❖♥ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡-

♥ “ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”

(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)፨

♥ “በደመና ተጋቢኦሙ ሐዋርያት ለድንግል ንጽሕት
ገነዝዋ በክብር ወበስብሐት
ለቀበላሃ ወረዱ ኀይላት
ወቀበርዋ ውስተ ገነት”

(ሐዋርያት በደመና ተሰብስበው ንጽሕት ድንግልን በክብር በምስጋና ገነዟት፤ ለአቀባበሏ ኀይላት ወረዱ፤ በገነት ውስጥም ቀበሯት)፨

♥ “ተጋቢኦሙ ሐዋርያት እምኲለሄ
በደመናት ዘምሉእ ሡራኄ
ገነዙ በክብር ወበስባሔ
ሥጋ ድንግል ዘይምዕዝ እምርሔ”

(ብርሃንን የተመላ በኾነ በደመናት ሐዋርያት ከአራቱ ማእዝን ተሰብስበው ልብን ከሚመስጥ ሽቱ ይልቅ የሚሸትት የድንግልን ሥጋ በክብርና በምስጋና ገነዙ)፨

♥ “ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ
ሐዋርያት ሥርግዋን በዕበይ
ገነዝዋ ለድንግል በብዙኅ ግናይ
ዳዊት ዘመራ በመሓልይ”

(በገናንነት የተጌጡ ሐዋርያት በሰማይ ደመና ተሰብስበው ድንግልን በብዙ ምስጋና ገነዟት፤ ዳዊትም በምስጋና አመሰገናት)፨

♥ “ተጋቢኦሙ አርድዕተ ወልዳ
በደመና ብርሃን ጸዐዳ
ገነዝዋ በስብሐት ለጽርሕ ሳይዳ”

(ጸዐዳ በኾነ በብርሃን ደመና የልጇ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበው፤ ውቢቱ አዳራሽን በምስጋና ገነዟት)፨

♥“ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት
ብፁዓን ሐዋርያት
ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ
በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ”

(ንኡዳን ክቡራን ሐዋርያት ቅድስት የምትኾን የጌታ እናቱን ለመገነዝ በቅጽበት ተሰበሰቡ፤ ወደ ርሷ ገብተው በሰላምታ ርሷን እጅ ነሧት፤ ሥጋዋንም በምስጋና ገነዙ) በማለት ሊቁ ማሕሌታይ በሐዋርያት እጅ የተደረገ የሥጋዋን ግንዘት አምልቶ አስፍቶ ጽፏል፡፡

♥ ከዚያም ወዲያውኑ የድንግልን የከበረ አካል ወደ ላይ በማንሣት ቅዱስ ጴጥሮስ ራሷን፣ ቅዱስ ዮሐንስ እግሮቿን ተሸክመው የተቀሩት ሐዋርያት በእጆቻቸው የዕጣን ማዕጠንት ይዘው በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡

♥ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ" በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡

♥ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡

♥ ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡

♥ ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ እነሱም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ሱባኤ ነሐሴ 1 ዠመሩ ነሐሴ 14 ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀብረዋት በተወደደች ዕለት ነሐሴ 16 በልጃ ሥልጣን ተነሥታ ዐርጋለች።

[ቅዱሳን ሐዋርያት በዕረፍትሽ ሰዓት በክቡራት እጆችሽ እንደተባረኩ በዓለ ዕረፍትሽን በስምሽ በተሠየመች ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበን የምናከብር ልጆችሽን ባርኪን]
[ወጸሐፈ በእንተ ዕረፍታ ለድንግል ገብራ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፤ አመ ፳ወ፩ ለጥር በተዝካረ በዓላ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል በክልኤ ማርያም ወላዲተ አምላክ ትንብልናሃ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን ]

❤ የመስቀል ሥር ስጦታችሁን እናታችሁ ቅድስት ድንግል ማርያምን የአደራ ልጆቿ ምእመናን በረከቷን ትሳተፉ ዘንድ በአስተያየት መስጫው ላይ አወድሷት።

28/01/2023

#. እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምሥጢርሽ ዕልፍ ነው!!

28/01/2023

#በሠላም ወደ አዲስ አበባ ገብተናል! - ቀሲስ ታጋይ
* መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ተለቅቀዋል

| "አሁን ማምሻውን በሠላም አዲስአበባ ገብተናል። ተጨንቃችሁ ለጻፋችሁ ምን ተፈጠረ ተብላችሁ ላሰባችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

ብጹእ አባታችን አቡነ እስጢፋኖስም በሠላም ወደ አዲስ አበባ ማረፊያቸው ገብተዋል ።

በጅማ ያላችሁ ምእመናንን ፍጹም መረጋጋት አለባችሁ። መልእክቴ ነው።"

ቀሲስ ታጋይ ታደለ
(የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ)

***

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ተለቅቀዋል።

***

የቤተ ክርስቲያኗ ምርቃት ወደ ሌላ ቀን መዘዋወሩንም የደብሩ አስተዳዳሪና አሠሪ ኮሚቴው ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይፋ አድርገዋል።

በነገው ዕለት የአስተርዕዮ ማርያም በዓለ ንግሥ በመቃኞ ቤቷ ተከብሮ ይውላል።


ለኃይማኖት መሞት መስዋዕትነት ነው!!

Photos from FastMereja.com's post 11/07/2022
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Africa Avenue
Addis Ababa

Opening Hours

09:00 - 17:00