የላካው ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች page

የላካው ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች page

Share

Ethiopia Orthodox litrcher

18/06/2026

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለሊቀ መልእክት ለ
ቅዱስ ሚካኤል በዓል
ኑ ሰኔ 12 እለተ ዓርብ በላካ ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን

Photos from የላካው ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች page's post 04/06/2026

ት ሐጌ 1:4 በእውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን ????????

1 :8፤ ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ት.ሐጌቤቱንም ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
በጋሞና አከባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በቦንኬ ወረዳ የበዛ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በ1824 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን 194 ዓመት ያስቆጠረ ዕድሜ ጠገብ ቤተ ክርስቲያን ነው ።
ይህ ህንፃ ቤተክርስቲያን በዉስጡ በርካታ ክፍሎችን የያዘና ያካተተ ሲሆን ለህንፃ ቤተክርስቲያኒቱ የተለያየ የቁሳቁስና ገንዘብ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ የቤተክርስቲያኒቱ የንግድ ባንክ አካውንት 👉( 1000262155092) ( በዛ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ኮሚቴ Beza kidus M/s/g/h/a komite ) !!!
በተጨማሪ 👉0953771028 ;0920464380; 0943962423; 0919703837;0949596675
በመደወል ድጋፍ እንዲታደርጉ እናሳስባለን።
ያስጀመረን የአባቶቻችን አምላክ ያስጨርሰናል ።
🙏♥⛪

ዲያቆን መሰለ ብሩ ___አርባምንጭ
27/09/2018 ዓ፡ም
𝑭𝒐𝒍𝒍𝒐𝒘𝒆𝒓𝒔.

29/05/2026

የሰኔ ጾም (ጾመ ሐዋርያት)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ (የግዴታ) ጾሞች አንዱ ነው። ይህ ጾም በየዓመቱ የጰራቅሊጦስ (የመንፈስ ቅዱስ መውረድ) በዓል በዋለ ማግስት በሰኞ ቀን ይገባና ሐምሌ ፭ (5) ቀን በቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት ቀን ይፈታል።

የዚህን ጾም መንፈሳዊ ምስጢር፣ ለምን እንደምንጾም እና እነማን መጾም እንዳለባቸው በአመክንዮ እና በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት እንደሚከተለው በዝርዝር እንመልከት፦

1. የሰኔ ጾም (ጾመ ሐዋርያት) ለምን እንጾማለን?

እኛ ክርስቲያኖች ይህንን ጾም የምንጾምበት ሦስት ዋና ዋና መንፈሳዊና ታሪካዊ ምክንያቶች አሉን፦

ሀ) የሐዋርያትን አርአያነት ለመከተል

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ሳለ አይሁድ “ደቀ መዛሙርትህ ለምን አይጾሙም?” ብለው በጠየቁት ጊዜ፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጾሙ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያን ጊዜም ይጾማሉ” (ማቴ 9፥15) ብሎ ትንቢት ተናግሮ ነበር።

ጌታችን አርጎ፣ በ፶ኛው (50ኛው) ቀን መንፈስ ቅዱስ በነደደ እሳት አምሳል በሐዋርያት ላይ ከወረደላቸው በኋላ፣ ሐዋርያት ወንጌልን ዓለምን ዞረው ከመስበካቸው በፊት አስቀድመው በጾምና በጸሎት ራሳቸውን አዘጋጅተዋል። እኛም የሐዋርያትን ፍልስፍና እና ፈለግ በመከተል፣ መንፈሳዊ ኃይልን ለማግኘት እንጾማለን።

ለ) ለአገልግሎትና ለስብከተ ወንጌል ስኬት

ሐዋርያት በጾም ውስጥ ሆነው ሳለ መንፈስ ቅዱስ መመሪያ ይሰጣቸው ነበር። ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ 13፥2-3 ላይ እንዲህ ተጽፏል፦ “እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጾሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። በዚያን ጊዜም ከጾሙና ከጸለዩ እጃቸውንም ከጫኑባቸው በኋላ ሰደዷቸው።” ይህ የሚያሳየው ጾም መለኮታዊ ጥሪን ለመስማትና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲከናወን ታላቅ መሣሪያ መሆኑን ነው። እኛም ዛሬ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲሰፋ፣ ወንጌል እንዲጸና በዚህ ጾም እንማጸናለን።

ሐ) በረከትንና ሰላምን ለማግኘት

ሰኔ ወር የክረምት መጀመሪያ፣ ገበሬው ዘር የሚዘራበትና አገር ወደ አዲስ የምርት ወቅት የምትሸጋገርበት ጊዜ ነው። ስለዚህ ሕዝቡ በሥጋውም ሆነ በነፍሱ እግዚአብሔር የሰላምና የበረከት ክረምት እንዲሰጠው፣ ምድር ፍሬዋን እንድትሰጥ በዚህ ጾም ወደ ፈጣሪው ይጮኻል።

2. እነማን ናቸው መጾም ያለባቸው?

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት፣ ይህ ጾም የአዋጅ (የጋራ) ጾም በመሆኑ፦

እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሁሉ መጾም አለበት፦ ጾሙ “የመነኮሳት ወይም የካህናት ብቻ” ሳይሆን የጠቅላላው ምእመናን ጾም ነው። ሕፃናት የጾም ዕድሜያቸው ከደረሰ (ከ7 ዓመታቸው) ጀምሮ፣ ወጣቶች፣ አባቶችና እናቶች በሙሉ የመጾም ግዴታ አለባቸው።
ልዩ ሁኔታዎች (ሕጋዊ ፈቃዶች)፦ እንደማንኛውም ጾም ሁሉ፣ በጣም በጽኑ የታመሙ ሰዎች፣ ነፍሰ ጡር እናቶች እና የሚያጠቡ እናቶች ከነፍስ አባታቸው ጋር በመመካከር በጾሙ ሥርዓት ላይ ቀኖናዊ ማቃለያ ሊደረግላቸው ይችላል። ከዚህ ውጭ ግን ጤነኛ የሆነ ክርስቲያን ሁሉ ሊጾመው ይገባል።

3. የመንፈሳዊ አመክንዮ ሚዛን (Theological Logic)

አንዳንዶች “ይህ ጾም የሐዋርያት ከሆነ እኛ ለምን እንጾማለን?” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።

የአባቶች ትምህርት አመክንዮ፦ እኛ የሐዋርያት ልጆች ነን፤ ቤተ ክርስቲያናችንም "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኵላዊትና ሐዋርያዊት" (Apostolic) ተብላ በነገረ ሃይማኖት ትታወቃለች። አባቶች የጾሙትን ልጆች የመጾማቸው ምስጢር የሃይማኖት አንድነትንና ውርስን ያሳያል። አባቶቻችን ሐዋርያት አለምን በወንጌል ብርሃን የረቱት በጾምና በጸሎት ከሆነ፣ እኛም ሰይጣንንና የዚህን ዓለም ፈተና ማሸነፍ የምንችለው የነሱን ጋሻ (ጾምን) ስንታጠቅ ብቻ ነው።

ማጠቃለያ

በአጭሩ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን እንዲሠራ፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ስኬት እና የሐዋርያትን በረከት ለመካፈል የምንጾመው ታላቅ የጸጋ ወቅት ነው። ዘንድሮም ጾሙን በሰላም አስጀምሮ በበረከት ለማጠናቀቅ እግዚአብሔር አምላክ መንፈሳዊውን ብርታት ይስጠን።

Photos from የላካው ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች page's post 25/05/2026

እንኳን ደስ አለክ

ውድ ወንድማችን የላካ ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ፍሬ የሆነው አሁን የአንጋፋው የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ መምህር ደቭ (Dave)ሁለተኛ ዲግሪውን ተመርቋል::

ክርስቲያን በሁለቱም በኩለ የተሳለ መሆን እንዳለበት እናምናለን!
እንኳን ደስ አለ በሉት

Photos from የላካው ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች page's post 19/05/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
የተወደዳችሁ የክርስቶስ ልጆች አንደምን ቆያችሁ?
ከስር በፎቶ የሚትመለከቱት በጋሞና አካባቢ ሀገረስብከት በዳራማሎ ወረዳ የዳራ ድሜ አድሱ የመዳንአለም ቤተክርስቲያን ስሆን ቁጥራቸወ ጥቅት የሆኑ ግን በእምነታቸው ጠንካራ የሆኑ ምዕመናን ብርቱ ጥረት በማድረግ ለዚህ አድርሰዋል። የሚገርማችሁ ምዕመናንን ሙሉ አርሶአደሮች ስሆኑ በቁጥራቸው 40 የሚሆኑ ናቸው። አጠቃላይ ከ350000 በር በላይ በማውጣት ለሚናየው ደረጃ አድርሰዋል።ስለዚህ ወድ ኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላችሁ የመዳንአለም ልጆች ቀሪ ስራዎች ተጠናቀው መሉ አገልግሎት እንድጀምር እርዳታችው ያስፈልገናል።ይህን የሚታነቡ በገንዘብ፣በሀሳብ እና በጉልበት መርዳት የሚትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር
1000699369447(ዳራ ቦላ መዳንአለም ቤተክርስቲያን )
ስልክ ቁጥር 0925548339 ወይም 0927110019
ነው። እንድሁም share በማድረግ ሌሎችም የበረከቱ ተካፋይ እንድታደርጉ በመዳንአለም ስም እንጠይቃለን።

Photos from የላካው ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች page's post 13/05/2026
13/05/2026

እሰቲ ዛረ ወጣ ያለ ነገር
መልሳችሁን በcomment አስቀምጡ

22 ሚሊዮን ሎቶሪ አሸንፈሃል፤ የ102 ዓመት ሴት አያትህም ለቀዶ ጥገና 21.5 ሚሊዮን ያስፈልጋታል። ትከፍላለህ?🤔😂

12/05/2026

ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን ፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን ። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

05/05/2026

መራራ እውነት ስለሚጠላ እንጅ እሸቱ የተናገረው ስርዓተ ቤተክርስቲያን ነው ኃጢአተኛ መሆን እና ኃጢአትን በአደባባይ መስበክ ትልቅ ልዩነት አለው መረን የለቀቀ ነውርን ጌጥ ያደረገ ከባህል ከወግ ከእሴት ያፈነገጠ ትውልድ የምትቀርጽን ሴት ለቤተክርስቲያን ምልክት ልትሆን አትችልም ማለት ትክክል ነው ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የሚባል ነገር አለ ያን ወደ ጎን ትታ ምግባር አልባ ትውልድን በንግግሯ የምትቀርጽ ለገዳማት ማስታወቂያ ልትሰራ አይገባም ማለት መራራ እውነት ነው

Photos from የላካው ኢየሱስ ወቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች page's post 05/05/2026

ከኮንሶ ምድር የተገኘ፣ እንደ ሰይፍ በሁለት በኩል የተሳለ አገልጋይ

በኮንሶ ዞን ወረዳዎች ቤተ ክህነት፣ የጋሞሌ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ-ክርስቲያን ዕጩ የሰበካ ሰብሳቢና አገልጋይ ቄስ፣ እንዲሁም በካራት ከተማ ቀበሌ 01 ሊቀ-መንበር የሆኑት ቀሲስ ግሩም ኡርማሌ፣ በArba Minch University የሁለተኛ ዲግሪ (Master’s) ጥናታዊ ጽሁፍ፦

“Challenges of Physical Education on Teaching Performance: The Case of Selected Secondary Schools in Konso Zone”

በሚል ርዕስ በስኬት አጠናቀው ተመርቀዋል።
ቀሲስ ግሩም ኡርማሌ ለዚህ የታላቅ ስኬት እንኳን ደስ አሎት፤

እግዚአብሔር በቀጣይ አገልግሎትዎ ይባርክዎ።

🎓 Congratulations! 🎉

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa